ሰኪነቱል ሩህ🖤
486 subscribers
42 photos
3 videos
1 link
መልካም የሆነ ማንፀባረቅን ከዉስጥ የሚዘልቅ ንፅፅርን እንዲሁም እርጋታን የሚሰጥ ፅሁፍን በአንድ ላይ ተሰናድቶ የሚቀርብበት channal🙌
Download Telegram
መንገድህን ስጀምር በያዝከዉ ነገር አትመካ (ማለቂያ አለዉና)
የትም ስትሄድ በእግሮችህ ወደ ቦታዉ ማድረስ እርግጠኛ አትሁን (እንቅፋት ያጋጥማልና)
ታክሲ ዉስጥ ስትገባ መድረስህን በብሮችህ አትተማመን (ተቀዳጅ ወረቀት ነዉና)
ጠዎት መንቃትህ ቀኑን ለመዎልህ ዎስትና የለዉም
በሚሰበር በሚጠፋ ነገር ላይ ምርኩዝህን አታስደገፍ


ይልቁንም


በስንዝር ስትቀርበዉ በክንድ በሚቀርብህ ተጠበቅ
ተደላድለህ ተደገፍበት
ተሸሸግ እሱ ከምርጥ ምሽጎች የተሻለ ምሽግ ነዉና
🙏8🔥2👏1
ሰኪነቱል ሩህ🖤 pinned «መንገድህን ስጀምር በያዝከዉ ነገር አትመካ (ማለቂያ አለዉና) የትም ስትሄድ በእግሮችህ ወደ ቦታዉ ማድረስ እርግጠኛ አትሁን (እንቅፋት ያጋጥማልና) ታክሲ ዉስጥ ስትገባ መድረስህን በብሮችህ አትተማመን (ተቀዳጅ ወረቀት ነዉና) ጠዎት መንቃትህ ቀኑን ለመዎልህ ዎስትና የለዉም በሚሰበር በሚጠፋ ነገር ላይ ምርኩዝህን አታስደገፍ ይልቁንም በስንዝር ስትቀርበዉ በክንድ በሚቀርብህ ተጠበቅ ተደላድለህ…»
''የነገ ሟች የዛሬን ሟች ይቀብራል''

እንዳንዘናጋ ያ አህባብ🙌
👌7🔥1
ጨለማ ባይኖር ኖሮ ጨረቃን እንደማናያት ሁሉ ችግሮች ባይኖሩ የፈጣሪን ፀጋ ባልተረዳን ነበር።
ከ እያንዳንዱ ስብራት ጀርባ ትልቅ ብስራት አለ አብሽሩ ትንሽ ብቻ ሰብሩ ትንሽሽሽ🤏

ان مع العسر يسرا
👌6🤝4
ያ አላህ ከጭንቀት ነፃ የሆነ አእምሮ ፣ ከሐዘን ነፃ የሆነ ልብ እና ከበሽታ ነፃ የሆነ አካል ስጠን።  

امين يا رب 🤲
🙏8🥰3
ከችግሮችህ ይልቅ በረከቶችህን መቁጠር ስትጀምር ህይወት ከምትገምተው በላይ ቆንጆ ሆና ታገኛለህ። ህይወትህ ላይ ሰላምን የ ቀልብ ሰኪናን እና እርጋታን ታገኛለህ።ለተሰጠን ኒዕማዎች አላህን እናመስግን 🤌

لإن شكرتم لأزيدنكم
🥰8👏4
በነገራችን ላይ ለኸይር ነዉ ብሎ ማለፍ የጥንካሬ መመዘኛ አይደለም
ማልቀስና ማዘንም የድክመት መሳርያ አይደለም

ለኸይር ነዉ ስንል ያጣነዉ ሁሉ መልካም ነዉ ማለትም አይደለም
ይልቁንም

በማጣት ዉስጥ የመጣዉን ሀዘን በማጣትነቱ መቀበልና
ነገ በማግኘት ለመሾም መጠባበቅ ነዉ
👏7👌1
ዱንያ ላይ አስደሳቹ ነገር የዱአን ፍሬ በጣፋጭ ዉጤት ማየት ሲሆን
መጥፎ ዉጤቷን መቅመስ ደግሞ የዱንያ ፈተናዎ ናት


ብዙ ልሸልም ስትፈልግ ትንሽ ትነጥቅሃለች
ስጦታዎ ደግሞ ሰብር ናት


አዉቀሃት ከተጠቀምክባት ብዙ ትቸርሃለች
ሳታዉቃት ስትጠቀምባት በራስህ ገመድ ጠልፋ ትጥልሃለች


አህ ዱንያ😫
🔥8❤‍🔥4
ሰኪነቱል ሩህ🖤 pinned «ዱንያ ላይ አስደሳቹ ነገር የዱአን ፍሬ በጣፋጭ ዉጤት ማየት ሲሆን መጥፎ ዉጤቷን መቅመስ ደግሞ የዱንያ ፈተናዎ ናት ብዙ ልሸልም ስትፈልግ ትንሽ ትነጥቅሃለች ስጦታዎ ደግሞ ሰብር ናት አዉቀሃት ከተጠቀምክባት ብዙ ትቸርሃለች ሳታዉቃት ስትጠቀምባት በራስህ ገመድ ጠልፋ ትጥልሃለች አህ ዱንያ😫»
ኢማን በልብ ነዉ ጅልባብ ኒቃብ በደረበ አይደለም የምትሉ ሰዎች ግን

ልብ ኢማን ስትላበስ ለመሰተር መጓጓቷን አታዉቁም¿

ጌታዎን ለመታዘዝ መሽቀዳደም መጀመሯን ልብ አትሉም¿

በነገሮች ላይ ሃያእ ማድረጓ ግልፅ አልሆነላቹም¿


ልብ በኢማን ስትከማች አካልን ሰትራ ንግግሯን በኢህሳን ታቀናጃለች
መሸፈንን ተቆራኝታ ለነፍሷ ምህረትን
ለአካሏ ዉበትን ታላብሳለች
ኢማን መሰረቷ ልብ ላይ ቢሆንም ተግባሯ ግን ዉጫዊዉ ገፅታ ላይ ትንፀባርቃለች

በሱ ስትመረጥ ብቻ የሚሰጥ ዉብ ኒእማ የልብ ኢማን ናት🤌
💯10🥰3👏1
ሰኪነቱል ሩህ🖤 pinned «ኢማን በልብ ነዉ ጅልባብ ኒቃብ በደረበ አይደለም የምትሉ ሰዎች ግን ልብ ኢማን ስትላበስ ለመሰተር መጓጓቷን አታዉቁም¿ ጌታዎን ለመታዘዝ መሽቀዳደም መጀመሯን ልብ አትሉም¿ በነገሮች ላይ ሃያእ ማድረጓ ግልፅ አልሆነላቹም¿ ልብ በኢማን ስትከማች አካልን ሰትራ ንግግሯን በኢህሳን ታቀናጃለች መሸፈንን ተቆራኝታ ለነፍሷ ምህረትን ለአካሏ ዉበትን ታላብሳለች ኢማን መሰረቷ ልብ ላይ ቢሆንም ተግባሯ ግን…»
በሁለት ረከዓ ሰላትና ዱኣ ለሚስተካከል ነገር ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት እምብዛም ስሜት አይሰጠኝም🙌

ጭንቀት ከሌለ የምቾትን ጥፍጥና አናዉቀዉም
ፈተና ከሌለ ጥናት የለማ ካልተፈተንክ ትዘናጋለህ ትሸሻለህ
አልተሳካም ?
አልሆነም?
ብዙ ይርቃል?
እሰየዉ

የሚሰጠዉ ለማን ነዉ ባጣህ ቁጥር ካልጠየቀዉ
አል አዚም ነዉ ትልቁ ሀጃህን ጠይቀዉ ደግሞም አል ሙጂብ ነዉ እና ......እናማ
በቃ ጨቅጭቀዉ

ኸላስ!!!
🔥9🫡3🥰1
ሰኪነቱል ሩህ🖤 pinned «በሁለት ረከዓ ሰላትና ዱኣ ለሚስተካከል ነገር ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት እምብዛም ስሜት አይሰጠኝም🙌 ጭንቀት ከሌለ የምቾትን ጥፍጥና አናዉቀዉም ፈተና ከሌለ ጥናት የለማ ካልተፈተንክ ትዘናጋለህ ትሸሻለህ አልተሳካም ? አልሆነም? ብዙ ይርቃል? እሰየዉ የሚሰጠዉ ለማን ነዉ ባጣህ ቁጥር ካልጠየቀዉ አል አዚም ነዉ ትልቁ ሀጃህን ጠይቀዉ ደግሞም አል ሙጂብ ነዉ እና ......እናማ በቃ ጨቅጭቀዉ …»
ሀቢቢ ስራህ ብቻ ነው ሚከተልህ!

ፀሀዩ ሳይበረታ ቶሎ ቀብረነው እንመለስ እንደሚባል አትርሳ!🥀

©
🙏6👏2💯1
መነሻ ከ (0 )የሆነዉ በምክንያት ነዉ
መዳረሻዉም ያልታወቀዉ በምክንያት ነዉ
ብቻ መጀመር ነዉ እንጂ መጨረሱን ለጀሊሉ ተዉለት
ሰበብ ማድረሱን እንጂ ስለ ዉጤቱ አትጨነቁለት
አላህ አለ ብሎ ማመን በራሱ ተስፋ ነዉ
ልንወድቅ ተንገዳግደን ስንቆም ያለዉ የልብ ምት ፍርሃት አሁን ለማጣት ከምንፈራዉ ነገር ተመሳሳይ ነዉ
ልንወድቅ እንችል ነበርኮ ግን ቆመናል

ስለዚህ ባንገዳገደን ቁጥር
ልባችን አትሸበር🫶
🔥7👌1
የቻናላችን ቁጥር ማነስም ሆነ መብዛት እምብዛም አያስጨንቀንም
ይልቁንም የምንከትባቸዉ ነገሮች ከቻናላችን ቤተሰቦች ጋር ማዎኸድ ነዉ ዎናዉ አላማችን
በብዙ መስዎትነት እና ጥረት ስለምናቀርብላቹ ምላሻቹን መጠባበቅ ያስደስተናል

እና አለን በሉን🙂
👏10
ሰኪነቱል ሩህ🖤 pinned «የቻናላችን ቁጥር ማነስም ሆነ መብዛት እምብዛም አያስጨንቀንም ይልቁንም የምንከትባቸዉ ነገሮች ከቻናላችን ቤተሰቦች ጋር ማዎኸድ ነዉ ዎናዉ አላማችን በብዙ መስዎትነት እና ጥረት ስለምናቀርብላቹ ምላሻቹን መጠባበቅ ያስደስተናል እና አለን በሉን🙂»
መርሳት ፀጋ ነዉ?

አስቡት እስኪ ከተወለዳችሁ ጀምሮ ያስቀየማችሁን ቃል ፣ሃዘናችሁን፣ተስፋ መቁረጣችሁን፣ እንባና ለቅሷችሁን፣የጎዷችሁን ሰዎች፣ያጋጠማችሁን አደጋ፣ የምትወዷቸዉ ሲለያችሁ ያለዉ ስሜት፣ከአላህ ደጃፍ የራቃችሁበትን፣አላህን በማመፅ የተሰማራቹበትን፣እዝነቱን በመርሳት ማርታን ያራቃችሁበትን፣ብቻ በአጠቃላይ ክፉ፣መጥፎ ጊዚያቶችን መርሳት ባንችል መንፈሳችን ተሰብሮ፣ክዉ ብለን በቅጽበት አንሞትም ነበር?!
ስለዚህ
መርሳት ፀጋ ነዉ



መዎሸትስ ፀጋ ይመስላቹሃል?
💯7🔥5
ሰኪነቱል ሩህ🖤 pinned «መርሳት ፀጋ ነዉ? አስቡት እስኪ ከተወለዳችሁ ጀምሮ ያስቀየማችሁን ቃል ፣ሃዘናችሁን፣ተስፋ መቁረጣችሁን፣ እንባና ለቅሷችሁን፣የጎዷችሁን ሰዎች፣ያጋጠማችሁን አደጋ፣ የምትወዷቸዉ ሲለያችሁ ያለዉ ስሜት፣ከአላህ ደጃፍ የራቃችሁበትን፣አላህን በማመፅ የተሰማራቹበትን፣እዝነቱን በመርሳት ማርታን ያራቃችሁበትን፣ብቻ በአጠቃላይ ክፉ፣መጥፎ ጊዚያቶችን መርሳት ባንችል መንፈሳችን ተሰብሮ፣ክዉ ብለን በቅጽበት አንሞትም ነበር?!…»
ግንባርህን መሬት ላይ አድርገህ ተናንሰህ ልዕቅናዉን የምታዉጅለት ጌታህ ዛሬ ባይሆን እንኳን በእርግጠኝነት ነገ ቀና ያደርግሃል

እንታገስ🙌
🔥9👏1
ስትሰበር ብቻ ወደሱ አትሽሽ
ሲከፋህ ብቻ ወደሱ አትቅረብ
ከሱ ጋር ያለህን መስመር በጥቅም ላይ አትገንባዉ
የሚያስፈልግህን ብቻ አትጠይቀዉ
ሳጠይቀዉ ስለሰጠኽ ነገርም አመስግነዉ
ጌታዬ ብቻ አትበለዉ ባርያዉ መሆንህንም ንገረዉ
ትንሽ ነገር አትለምነዉ እሱ ትልቅ ጌታ ነዉና
ለወንጀሎችህ ምክንያት አደርድር
ወደ እስቲግፋር በጊዜ አፈትልክ


አል -ሙጂብ
🤝5🫡4