ኤፌሶን~፩
650 subscribers
75 photos
1 video
23 links
Download Telegram
ታሕሳስ ፲፯ /17/


በዚች ቀን የቅዱስ ሉቃስ ዘዓምድ የሥጋው ፍልሰት ሆነ።

እርሱም ከፋርስ አገር ነው በመጀመሪያ በመቶ ጭፍራ ላይ መኰንን ሁኖ ተሹሞ ነበር ከዚህም በኋላ ሹመቱን ትቶ የምንኵስና ልብስን ለበሰ። በአንድ ገዳም ውስጥ ገብቶ በብዙ መጋደል ጀመረ በዚያም ቅስና ተሾመ። ከዚህም በኋላ ከዓምድ ላይ ወጥቶ በላዩ ሦስት ዓመት ቆመ በስሙም መልአክ ጠርቶት ከአንድ ገዳም አደረሰው።

ከዚህም በኋላ የማይናገር ሆነ ከሰው ጋር ከቶ እንዳይናገር ከአፉ ውስጥ ደንጊያ ጐረሰ ዳግመኛም ወደ ቊስጥንጥንያ አገር ዳርቻ ይሔድ ዘንድ መልአክ አዘዘው። ለእርሷም አቅራቢያ ወደ ሆነች ወደ አንዲት ቦታ ሔደ ከምሰሶ ላይም ወጥቶ ታላቅ ተጋድሎን እየተጋደለ በላዩ አርባ አምስት ዓመት ኖረ እግዚአብሔርም የመፈወስን ሀብት ሰጠው አስደናቂዎች ተአምራትን በማድረግ ወደርሱ የሚመጡትን ብዙዎች በሽተኞችን ፈወሳቸው።

እግዚአብሔርም ከዚህ ዓለም ድካም ሊአሳርፈው በፈቀደ ጊዜ በዚህ ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን አረፈ የሚያገለግለውም ረድ ለጳጳሳት አለቆችና ለካህናት አለቆች ስለ ዕረፍቱ ነገራቸው እነርሱም መስቀሎችን፣ ጽንሐዎችን፣ መብራቶችን ከመያዝ ጋር በዚያን ጊዜ ተነሥተው ወደ መኖሪያው ሔዱ በላዩም ጸልየው ተሸክመው ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ ወሰዱት።

በአረፈ በሦስተኛው ቀን ታኅሣሥ ዐሥራ ሰባት በዚች ቀን አደረሱት ወደ ቤተ መቅደስም አስገብተው የከበረ ሥጋው በአለበት እንደ ሚገባ ጸሎትን ፈጸሙ። ከእርሱም ተባረኩ የተሰበሰቡትም ሁሉ ተባረኩ ከዚህም በኋላ ከእርሱ አስቀድሞ የቅዱሳን ሥጋቸው ወዳለበት ሣጥን ውስጥ ጨመሩት።

የቅዱሳን በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦  መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
*🗝በልብ የተሸሸገ አፍ🔑 *
                📖🔔📖🔔📖

የለፍላፊ ከንፈር የማይመለከተውን ይናገራል ፤ የጠቢባን ቃል ግን በሚዛን የተመዘነች ናት። አላዋቂዎች ልባቸው በአፋቸው ነው ፤ የአዋቂዎች አፍ ግን በልባቸው ነው። ኃጢአተኛ ሰው ሰይጣንን ቢረግመው ራሱን መርገሙ ነው።
ሐሜተኛ ሰው ሰውነቱን ያረክሳል ፤ ባደረበትም ቦታ ራሱን ያስጠላል።
   🔔 📘📖🔔📖🔔📖📔

          📌(መ.ሲራክ 21፥25-28)
1
ታሕሳስ ፳፩ /21/

በዚችም ቀን የስሙ ትርጓሜ የመረጋጋት ልጅ የሆነ ቅዱስ ሐዋርያ በርናባስ በሰማዕትነት አረፈ።

ይህም ቅዱስ ሐዋርያ ከሌዊ ነገድ የሆነ ሀገሩ ቆጵሮስ ነው የቀድሞ ስሙ ዮሴፍ ነው ክብር ይግባውና ጌታችን ከመከራው በፊት ይሰብኩ ዘንድ ከላካቸው ከሰባ ሁለት አርድእት ጋር መረጠው ስሙንም በርናባስ ብሎ ጠራው።

በባለ ሃምሳ ጊዜ እርሱም ከሐዋርያት ጋር የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ተቀብሎ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አስተማረ ። የእርሻ ቦታ ነበረውና ሽጦ ዋጋውን አምጥቶ ከሐዋርያት እግር በታች አኖረው።

ቅዱስ ጳውሎስም በጌታችን አምኖ ወደ ሐዋርያት በመጣ ጊዜ ክብር ይግባውና ለክርስቶስ እርሱ ደቀ መዝሙሩ እንደሆነ ሐዋርያት አላመኑትም ነበር። ይህ በርናባስ ጌታችን በመንገድ እንደ ተገለጸለትና እንደአነጋገረው እርሱም በጌታ ኢየሱስ ስም በደማስቆ እንደ አስተማረ ነገራቸው።

ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔርን ሥራ ሲሠሩ ሲጾሙ ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ ሳውልንና በርናባስን እኔ እነርሱን ለመረጥኩለት ሥራ ለዩልኝ አላቸው። ከዚህም በኋላ ጹመው ጸልየው እጆቻቸውን በራሳቸው ላይ ጭነው ሾሟቸው።

በቆጵሮስ አገር የሚኖሩ አይሁድም ቀኑበት በመኳንንቱም ዘንድ ወንጅለው እጅግ ብዙ  ስቃይን አሰቃዮት በመጨረሻም ከእሳት ጨመሩት ምስክርነቱንም ፈጸመ ማርቆስም ከርሱ ጋር አለ ግን እግዚአብሔር ጠብቆ አተረፈው። እርሱም ቅዱስ በርናባስን ከእሳት ውስጥ አወጣው ሥጋውንም እሳት ከቶ አልነካውም በአማሩ ልብሶችም ገነዘውና ተሸክሞ ወስዶ ከቆጵሮስ ከተማ ውጭ በዋሻ ውስጥ አኖረው።

የቅዱሳን በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦  መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
ታሕሳስ ፳፪ /22/


በዚች ቀን የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ የገብርኤል የበዓሉ መታሰቢያ ዳናህ በሚባል አገርም ቤተ ክርስቲያኑ የተሠራችበት ተአምራትም ያሳየበትና በዚች ቀን ቤተ ክርስቲያኒቱ የከበረችበት ነው የዚያች ሀገር ኤጲስቆጶስ አርኬላዎስም ምስክር የሆነበት ነው።

ይህም መልአክ ስለ ወልደ እግዚአብሔር ሰው መሆን ምሥጢር የታመነ ሆኖ ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተላከ የደስታ መገኛ ደስ ይበልሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው አንቺም ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ አላት።

ስለ መጥምቁ ዮሐንስ መወለድም ካህኑን ዘካርያስን ያበሠረው እርሱ ነው ይህ መልአክ እጅግ የከበረ የተመረጠ ገናና የሆነ ነውና ስለ እኛ ወደ እግዚአብሔር ይማልድ ዘንድ ልባችንን አንጽተን ወደዚህ የከበረ መልአክ እየለመንን መታሰቢያውን ልናደርግ ይገባናል።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ መልአክ አማላጅነት ይማረን በረከቱ ረድኤቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦  መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለልበ_አምላክ_ለእሴይ_ልጅ ለእስራኤል ንጉሥ ለነቢዩ #ለቅዱስ_ዳዊት_ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል፣ ለከበረ ተጋዳይ አባት ለገዳማዊ #ለአባ_ጢሞቴዎስ_ዕረፍት በዓል፣ ለቅዱሳን #ለአባ_ሳሙኤል_ለአባ ስምዖን_ለአባ ገብርኤል ለዕረፍታቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_ከይስሐቅ_ከአባ_አሞን#ከአባ_አቦሊ_ከመቃርስ_ከአይተለአትካ_ከፊልጦስ_ከመርቆሬዎስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
🔥1
ታሕሳስ ፳፫ /23/

በዚችም ቀን የእሴይ ልጅ ንጉሥ ዳዊት አረፈ።

ንጉሥ ዳዊት ቤተልሔም የሆነች ከይሁዳ ነገድ ነው። ሳሙኤልም በእግዚአብሔርን ትእዛዝ ዳዊትን ከእረኝነት አስጠርቶ ቅብዐ መንግስትን ቀብቶ አነገሰው። ከፍልስጤማውያንም ጋራ ሰልፍ በሆነ ጊዜ ብርቱ ሰው ስሙ ጎልያድ የሚባል ከጌት ሰዎች የተወለደ ቁመቱ ስድስት ክንድ ከስንዝር የሆነ ከኢሎፍላውያን ሰፈር ወጣ።

በዚያም ወራት ዳዊት ወንድሞቹን ሊጐበኝ ወጣ ጎልያድንም በአየው ጊዜ አምላካዊ ቅናትን ቀና ሳኦልንም እንዲህ አለው እኔ ሔጄ ይህን ያልተገረዘ ቈላፍ ገድዬ ዛሬ ከእስራኤል ሽሙጥን አርቃለሁ አለው። ሕያው የሚሆን የእግዚአብሔርን አርበኞች ይገዳደር ዘንድ ይህ ቈላፍ ምን ቁም ነገር ነው ከድብ አፍና ከአንበሳ አፍ ያዳነኝ እርሱ እግዚአብሔር ከዚህ ካልተገረዘ ኢሎፍላዊ እጅ ያድነኛል።ሳኦልም ሒድ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሁን አለው።

ዳዊትም ዛሬ የእስራኤልን አርበኞች የተገዳደርክ አንተን ዛሬ እግዚአብሔር በእጄ ይጥልሃል እገድልህምአለሁ ራስህንም እቆርጣለሁ አለው። ዳዊትም አንዲት ደንጊያ አውጥቶ ወነጨፋት ያንንም ኢሎፍላዊ ግንባሩን ገመሰው በግንባሩም ተደፋ። ዳዊትም ሩጦ የገዛ ሰይፉን አንሥቶ ራሱን ቆረጠው ከእስራኤልም ልጆች ስድብን አራቀ።

የዳዊትም መላው ዕድሜው ሰባ ነው መንግሥትን ሳይይዝ ሠላሳ ዓመት ኖረ ከዚያ በኋላ አርባ ዓመት ኖሮ በሰላም አረፈ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከቱ ረድኤቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦  መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
1
✨️️️️✨️️️️✨️️️️ 🌸🌼🌺✨️️️️✨️️️️✨️️️️ 🌸🌼🌺✨️️️️✨️️️️


✨️️️️ 🌸🌼🌺

ሰላም ለፅንሰትከ ወለልደትከ እምከርሥ÷
አመ ዕሥራ ወረቡዑ ለወርኃ ታኅሣሥ÷|

ተክለ ሃይማኖት በኵሉ ወበ ውስተ ኵሉ ውዱስ÷
ናሁ ወጠንኩ ወዕቤ ለስብሐቲከ ሐዲስ÷
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ::

✨️️️️ 🌸🌼🌺

ከተቀደሰችው ማኅፀን ስለሆነው የመጸነስህና የመወለድህ ነገር ሰላምታ ይገባል፥

ይኸውም በታኅሣሥ ወር በሃያ አራተኛው ቀን ተፈጸመ፥
ተክለ ሃይማኖት ሆይ በሁሉ እና በሁሉም ውሥጥ የተመሰገንክ ነህ፥

✨️️️️ 🌸🌼🌺

አንተ ያቀረብከው የሆነውን አዲስ ምሥጋና አመሠግን ዘንድ እንዲህ ብዬ ጀመርኩ፥
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በማለት።

✨️️️️ 🌸🌼🌺

መልክአ ተክለ ሃይማኖት
ለጽንሰትከ

@efeson_2

✨️️️️✨️️️️✨️️️️ 🌸🌼🌺✨️️️️✨️️️️✨️️️️ 🌸🌼🌺✨️️️️✨️️️️
🔥1
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለታላቁ_አባት ለተመሰገኑ አባት አርባ ዓመት ሙሉ የሴቶች ፊት ሳያይ ለኖረ #ለአቡነ_ዮሐንስ ለዕረፍት በዓል፣ በአባ መቃርስ ገዳም በአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ለሆነ ለከበረ አባት #ለአቡነ_ዮሐንስ ለዕረፍት በዓል፣ ከመኰንኑ ከአርያኖስ የጭፍሮቹ ታላላቆች #ለቅዱሳን_ለኮርዮንና_ፊልሞና ከእናርሳቸው ጋር ካሉ #ከአርባ_ወታደሮች ጋር ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና ተጋድይ ለሆነ #ለአባ_ዘካርያስ ዕረፍትና በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰቡ፦ ሄሮድስ ከገደላቸው #ከከበሩና_ከነጹ_ሕፃናት ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
1🙏1
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለሊቀ_ዲያቆናት_ለቀዳሜ_ሰማዕት #ለቅዱስ_እስጢፋኖስ_ለልደቱና_ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና #ከሶርያ_አገር_ለሆነ በከሀዲው መክስምኖስ ዘመነ መንግስት ሰማዕትነት ለተበቀበለ #ለቅዱስ_ለውንድዮስ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከእስክድርያ ስልሳ ዘጠነኛ ሊቀ ጳጳስ #ከአባ_መቃርስ ዕረፍት፣ #ከከበሩ_ከአክሚም_ሰማዕታት የምስክርነታቸውን ተጋድሎ ከፈጸሙ ስማቸው #ቅዱሳን_ዲዮስቆሮስና_ሰከላብዮስ ዕረፍት፣ በዲዮቅልጥያኖስ እጅ ሰማዕትነት ከተቀበሉ ቊጥራቸው #ከካህናት_ስምትት_መቶ#ከዲያቆናት_መቶ_ሠላሳ_ከመምህራን_ኃምሳ#ከሦስት_ከቤተ_ክርስቲያን_ሹማምንት_ከሰማንያ_መሳፍንት_ከሠላሳ_ሁለት_ንፍቅ_ዲያቆናትና_ከመቶ_ኃምሳ_ሕዝባውያን ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
ጥር ፬ /4/

የተመሰገነ ዮሐንስም ከዚህ ዓለም የሚወጣበት ሰዓት እንደ ቀረበ በአወቀ ጊዜ ሕዝቡን ጠራቸው ጸሎትንም ጸለየና ኅብስቱን ባርኮ ቆረሰ ይህም የጌታችን ሥጋውንና ደሙን ሰጣቸው በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አዘዛቸው ባረካቸው አጽናናቸውም ።

ከዚህም በኋላ ደቀ መዝሙሩ አብሮኮሮስን ከወንድሞችም ሌሎች ሁለትን መቆፈሪያ ይዘው ይከተሉት ዘንድ አዘዘ ። ከኤፌሶንም ከተማ ውጭ ወጣ ጕድጓድ እንዲቆፍሩም አዘዘ ከውስጥዋም ወርዶ ቆመ ልብሱንም አስወገደ ከአንድ የበፍታ ቀሚስ በቀር አላስቀረም ። እጆቹንም አንሥቶ ጸለየና ወደ ከተማ ይመለሱ ዘንድ አሰናበታቸው በክርስቶስም ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ ለሕዝቡ ይነግሩአቸው ዘንድ አዘዛቸው በጎ ሥራዎችንም ይሠሩ ዘንድ ጌታችን ለሁሉም እንደ ሥራው ይከፈለው ዘንድ አለውና ።

ይህንንም በተናገረ ጊዜ አለቀሱ እጆቹንና እግሮቹን ስመው በጒድጓዱ ውስጥ ትተውት ወደ መንገድ ተመለሱና የሆነውን ሁሉ ለሰዎች ነገሩዋቸው ሁሉም ደንግጠው መጡ ግን ልብስና ጫማ እንጂ መቃብሩን አላገኙም እጅግም አደነቁ ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስን በዚህ በጎ ዕረፍት ያሳረፈው እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦  መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
✨️️️️️️🌻✨️️️️️️🌻✨️️️️️️🌻✨️️️️️️🌻✨️️️️️️🌻✨️️️️️️🌻✨️️️️️️🌻

በዚች ቀን

✨️️️️️️🌻✨️️️️️️
#የክብር_ባለቤት_ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ #በሥጋው_ወደ_ቤተ_ግዝረት በመግባት የኦሪትን ሕግ ፈጸመ

✨️️️️️️🌻✨️️️️️️
ልሳነ ዕረፍት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "ጌታ ክርስቶስ በሥጋው ግዝረትን ተቀበለ ለአባቶች የተሰጠውን ቃል ኪዳን ይፈጽም ዘንድ" ብሎ እንደተናገረ።

✨️️️️️️🌻✨️️️️️️
ለብዙዎችም ጌታችን ወደ ቤተ ግዝረት እንዳልገባና እንዳልተገረዘ ይመስላቸው ነበር እነርሱ እንዳሰቡት ሁኖ ቢሆን ኑሮ አይሁድ ታላቅ ምክንያትን የሚያገኙ በሆኑ ነበር

✨️️️️️️🌻✨️️️️️️
ጌታችን ግን ግዝረትን ሕግ ፈጸመ ለእኛ በግዝረት ፈንታ የክርስትና ጥምቀትን ሰጠን የፋሲካውንም ቂጣ በላ በእርሱም ፈንታ ሥጋውንና ደሙን ሰጠን።

ተጨማሪ ያንብ

✨️️️️️️🌻✨️️️️️️🌻✨️️️️️️🌻✨️️️️️️🌻✨️️️️️️🌻✨️️️️️️🌻✨️️️️️️🌻
1
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለአጋዕዝተ_ዓለም_ለቅድስት_ሥላሴ የሰናዖር (የባቢሎንን) ቋንቋቸው ለደባለቁበትና የሠሩት ግንብ ላፈረሱበት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል (ታሪኩ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ዘፍ11፥1-9)፣ ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስን የክርስትና ጥምቀት ላጠመቀው ለሮሜ አገር ሊቀ ጳጳስ ለከበረ አባት #ለአቡነ_ሶል_ጴጥሮስ ለዕረፍት በዓልና ለታላቁ አባት #ለቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ ለመታሰቢያው  በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከሰሎሞን#ከጎርጎርዮስ_ከማርቆስ_ከአትያኖስ_ከሉያ#ከመልይን_ከሱስዮስና_ከማርትይ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴


እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ደቂቀ_ነቢያት አንዱ ለሆነው #ለቅዱስ_ሚክያስ ለመታሰቢያ በዓል፣ #የአባ_መቃርስ_ቤተ_ክርስቲያን በከበረና በተመሰገነ በእስክድርያው ሊቀ ጳጳሳት #በአባ_ብንያሚን እጅ ለከበረችበትና ለእስክድርያ ሠላሳ ስምንተኛ ሊቀ ጳጳስ #ለአባ_ብንያሚን_ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ  በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ ፦ከእስክንድርያ  ሠላሳ ሰባተኛ ሊቀ ጳጳስ #ከአባ_እንድራኒቆስ ዕረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                       

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴


እንኳን ለከበሩ አባት ጌታችን በኪሩቤል ሠረገላ ተቀምጦ በቤታቸው ጣራ ለገባላቸው #ለአባ_አብርሃም_ግብፃዊ  ዕረፍቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበሩ አባቶች #ከአባ_ጊዮርጊስ_ከአባ_ኖስሞስና ከሮሜ ሰው #ዲዮስቅርስ ዕረፍት፣ #ከአባ_ኪናፎርያ_ከበጥሪቃና_ከጥምያኒ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
💫💦💫💦💫💦💫💦💫💦💫💦💫💦💫💦💫💫💦💫💦💫💦💫💦💫💦💫

@efeson_2

ከተራ መቼ ተጀመረ? ሃይማኖታዊ ትርጉሙስ ምንድነው?


ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን ደምፀ




የጥምቀት አከባበር በሀገራችን ኢትዮጵያ ታቦት ተሸክሞ ወንዝ ወርዶ የክርስቶስን በዓለ ጥምቀት ማክበር የተጀመረው በአባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ሲሆን ይበልጥ ተጠናክሮ በሜዳና በውኃ ዳር ማክበር የተጀመረው በዐፄ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት (ከ፭፻፭ - ፭፸፩ ዓ.ም) እንደ ሆነ ይነገራል። ይኸውም ከማኅሌታዊው ቅዱስ ያሬድ (፭፻፭ - ፭፻፸፪ ዓ.ም) ዜማ መስፋፋት ጋር ተያይዞ ታቦታቱ በየዓመቱ ጥር ፲፩ ቀን ጠዋት ወደ ወንዝ ወርደው ማታ ወደ መንበረ ክብራቸው እንዲመለሱ ይደረግ ነበር።               

ተጨማሪ ያንብቡ              

@efeson_2

💫💦💫💦💫💦
🙏 ከአንዱ ወዳጄ🙏 መልክት 🥹

ሁለት ጊዜ ቀላል (Minor surgery) እንዲሆም ህመሙ በነዚህ ሁለት ቀዶ ጥገና ሊፈታ ባለመቻሉ በቅርቡ ከባድ ቀዶ ጥገና(major surgery)  ተደርጎለት ነበር።እግዚአብሔር ይመስገን አሁን ደህና ሆኗል፣ ክብር ለመድኃኔዓለም ይሁን! 🥹

ነገር ግን ይህ የጤና መታመም ከፍተኛ የገንዘብ ጫና ፈጥሮበታል።ቤተሰቦቹ ለህክምና ወጪዎች ሲሉ ያለውን ሁሉ አውጥተዋል፣ እሱም ምንም አልያዘም። በአሁኑ ወቅት አካውንቱ ላይ ያለው ገንዘብ የገንዘብ መጠን በጣም ትንሽ ነው። 😢 ቤተሰቡም ለዛ ሕክምና ወጪ ያወጡት ተበደረው ነውና እሱን በትምህርቱ ለሚያስፈልገው ነገር እገዛ ማድረግ እጅጉን ከባድ ሆኖባቸዋል::

አሁን ደግሞ ዩኒቨርሲቲ ገብቷል።የመጀመሪያ ሳምንት ለሚያስፈልገው ሰርተፍኬት ፕሪንት ለማድረግ ከነበረችው 200 ብር ላይ አውጥቶ አሁን 100 ብር ብቻ ነው የቀረው።እንደ ማንኛውም ተማሪ ፕሪንት እንኳ ማድረግ አልቻለም።

"ይህ ሁሉ የኃጢአቴ ውጤት ነው፣ እሄ ሲያንሰኝ ነውና ጸልዩልኝ" በማለት የመንፈስ ጭንቀቱንና ትህትናውን አሳይቷል።ስመ ክርስትናውም ኃይለኢየሱስ ይባላል በፀሎት በቆምን ሰዓት ሁሉ በፀሎት እንድናስበው ጠይቆናል 🙏🙏🙏::"ለሰው መድኃኒቱ ሰው ይባል የለ፣ አደራችሁን" በማለት ከእኛ እርዳታን ይፈልጋል።

ቢያንስ ለመማሪያ የትምህርት ግብዓት ሚያሟላበት እና ለፕሪንት ለኮፒ ሚሆን ነገር ብናግዘው መልካም ነው።ወንድማችን "ማርያምን 50 ብር ቢሆን ለእኔ ትልቅ ነገር ነው!" ብሏል።
የቻልነውን ያህል በጸሎትም ሆነ በገንዘብ እንርዳው።እያንዳንዱ ትንሽ እርዳታ ትልቅ ለውጥ ያመጣለታል። 🙏

የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥሩ:
1000670545788
ስለ እናታችን ስለ እማምላክ ስለ ኪዳነምህረት ስንል ሁላችንም ከጉድለታችን ላይ ያቅማችንን እንርዳው እናግዘው በፀሎትም እናስበው::
ጥር ፳፫ /23/


በዚች ዕለት የጳውሎስ ደቀ መዝሙሩ የሆነ ሐዋርያው ጢሞቴዎስ በሰማዕትነት ሞተ። የዚህም ቅዱስ ልደቱና እድገቱ ልስጥራን ከሚባል አገር ነው አባቱም ከዋክብትን የሚያመልክ ዮናናዊ ነው እናቱ ግን በኦሪት ሕግ ጥላ ሥር ያለች ናት።

የከበረ ሐዋርያ ጳውሎስም በልስጥራን ሀገር በሰበከ ጊዜ ይህ ጢሞቴዎስ ስብከቱንና ትምህርቱን ሰማ እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያደርጋቸውን ድንቆች ተአምራቶችን አይቶ እሊህም ተአምራቶች አስተዋዮችና ጥበበኞች የሚደነግጡባቸው ናቸው ስለዚህም ወደ ሐዋርያ ጳውሎስ ሒዶ በእርሱ ትምህርት በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ተጠምቆ የሐዋርያ ጳውሎስ ደቀ መዝሙሩ ሆነ ወደ ብዙ አገሮችም ተከትሎት በመሔድ ከእርሱ ጋር ደከመ ታላቅ መከራና ብዙ ኀዘንም ደርሶበታል ሐዋርያው ጳውሎስም በኤፌሶን ውስጥ በአንዲት አገር ላይ ኤጲስቆጶስነት ሾመው።

በዚያንም ጊዜ ወደርሷ ገብቶ ለሰዎቿ በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰበከ ብዙዎችንም ወደ ቀናች ሃይማኖት መልሶ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው ከዚህም በኋላ በዙሪያዋ ወዳሉ ብዙዎች አገሮች በርቀትም ለሚገኙ አገሮችም የከበረ ወንጌልን ሰበከላቸው።

በትምህርቱም አይሁድንና ዮናናውያንን ይገሥጻቸውና ይዘልፋቸው ነበር እነርሱም ቀንተውበት ሁሉም በጠላትነት ተነሡበት ተሰብስበውም ገደሉት ምእመናንም ሥጋውን አንሥተው ቀበሩት ጻድቅ ቈስጠንጢኖስም እስከ ነገሠ በዚያው ኖረ እርሱም ስለ ሥጋው አስቦ ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ በጥር ወር በሃያ ሰባት ቀን አፈለሰው በዚያችም ቀን በዓል አደረገለት።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
ጥር ፳፯ /27/


በዚችም ዕለት የአዳም ልጅ ኄኖክን መላእክት ይዘው አሳረጉት።

ይኸውም በመባርቅትና በነፋሳት ላይ ተጭኖ በመብረር ወደ ሰማይ ወስደው ከረቂቃን መላእክት ጋር አኖሩት የእግዚአብሔርም ትእዛዝ ጸሐፊ ተባለ።

በደብር ቅዱስ ለነበሩ ለኃጢአት ለሚተጉ ለሴት ልጆች ይዘልፋቸው ዘንድ ቃል እንደጠራውና እንዳሳየው ተናገረ።  በእሳት ቅጽርም የተሠራ በክብር ከሁሉ የሚበልጥ በውስጡም ከፍ ያለ የእግዚአብሔርን ዙፋን አየሁ መልኩም እንደ ውርጭ ነው አጎበሩም እንደሚያበራ ፀሐይ ነው። ከዙፋኑም በታች የኪሩቤል ድምፅ ይሰማል።

በሰማይ ገጽ ስለሚመላለሱ ብርሃናት እንዲህ አለ አንዱም አንዱ በየወገናቸው በሠለጠኑበትና በተሠየሙበት ጸንተው ይኖራሉ ስለ ነፋሳትም መውጫዎች እንዲህ ብሎ ተናገረ ሦስቱ በሰማይ ገጽ ሦስቱ በምድር ገጽ ሦስቱ በቀኝ ሦስቱ በግራ ናቸው። ስለ አዳምም እንዲህ አለ እነሆ በሬ ከምድር ወጣ ፀዓዳም ሆነ ስለ ሔዋንም ደግሞ ሴት እምቦሳ ከርሱ ወጣች አለ።

ስለ ምኵራብም ያንን አሮጌ ቤት እስከሚአሳንሰው ድረስ አየሁ አለ ምሰሶዎቹንም ከውስጡ አወጣ። ስለ ቤተክርስቲያንም ጌታ አዲስ የበጎች ቤት አምጥቶ እስቲሠራ ድረስ አየሁ ከቀድሞውም ቤት የበለጠ ነው በጎችም ሁሉ በውስጧ ይሠማራሉ አለ ። ስለ ምእመናንም የእሊህም በጎች ፀጕራቸው ንጹሕ ነጭ ነው የተበተኑትም ከአራዊት ጋራ ይሠማራሉ ሁሉም በአንድነት ተሰብስበው ገራሞች ሆነዋልና።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር


@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
መድኃኔዓለም ሆይ አስቀድሞ ፈያታዊ ዘየማንን እንዳስብከው አቤቱ አዳኝ ቤዛ በሚሆን መስቀልህ አስበኝ፤ ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ አቤቱ ቸር ጠባቂ ነህና እንደ ዓይን ብሌን ጠብቀኝ፤ አቤቱ እኔን መከረኛውን ሃዘንተኛውን በምስጋናህ የወይን ጠጅ አስደስተኝ አረጋጋኝ።
    
                "መልክአ መድኃኔዓለም"



@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁

እንኳን ጌታችን በአካል ተገልጦ በደሃ ሰው ተመስሎ ከማኅበረ ዴጔ ጋር በመካከላቸውም ተገኝቶ የጽዋ ማኅበር እየጠጣ ተራው ደርሶ ተዓምር አድርጎ  አምላክነቱ ለገለጠበት ቀን ለመታሰቢያ በዓል፣  የስሟ ትርጓሜ መጻተኛ ለሆነ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በራእይ ለተገለጠላትና ከከበሩ ነገሥታት ወገን ለሆነችው ዓለምን ንቃ በመመንኰስ በምትተኛ ጊዜ ያለ ምንጣፍ በምድር ላይ እየተኛችና ጥሬ ባቄላን ብቻ እየተመገበች በታላቅ ተጋድሎ ለኖረችው ለከበረች ቅድስት አክሳኒ ለዕረፍቷ በዓል መታሰቢያ፣ ተጋዳይ ለሆነ በበረሃ ውስጥ የሞተ ሰው ራስ ቅል አግኝተው የራስ ቅሉን ላነጋገሩና ሥራውን መርምረው ለተረዱ በኋላም አማልደውት ምሕረትን ላሰጡት አባ እስጢፍኖስ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከድንግል እመቤታችን ማርያም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ከተወለደበት ከልደቱ መታሰቢያ፣ ከመስተጋድል ከከበረ ሰማዕት ከሰርያኮስ ከመታሰቢያው፣ ከሮሜ ሰዎች ውስጥ ከንጹሐት ሴቶች ከመታሰቢያቸው፣ ከፊልንማ፣ ከኢያልኒ፣ ከሰረባሞኒና ከቃውት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁
🔥1