ኤፌሶን~፩
650 subscribers
75 photos
1 video
23 links
Download Telegram
ሕዳር ፳፫ /23/


‎በዚችም ዕለት ዳግመኛ የስሙ ትርጓሜ የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነ የነቢይአብድዩ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው ።

‎ይህም ቅዱስ ከጠፍ በረሀ አቅራቢያ ከአለች ሱሳም በምትባል አገር ካሉ ሰዎች ወገን ነው ለነቢይ ኤልያስም ደቀ መዝሙሩ ሁኖ ብዙ መከራን በእርሱ ላይየመጣውን ታግሦ ከመከራውም በትዕግሥቱ ዳነ ።

‎ይህም ኤልያስን የተለማመጠና ኤልያስም አዝኖለት አብሮት ወደ ንጉሥ አክዓብ የሔደለት ሦስተኛው የሃምሣ አለቃ ነው ። ከዚህም በኋላ ምድራዊ ንጉሥን ማገልገል ትቶ ነቢይን ሆነ የትንቢቱንም ወራት አድርሶ በሰላም አረፈ ።

‎ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
‎ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
1
🍀

''ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ፣ ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረዋልምና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ'' ራዕ ፬፥፲-፲፩

💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

@efeson_2

እንኳን  በእግዚአብሔር ዙፋን ዙሪያ ለሚኖሩ ለሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን🙏

ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ሥጋ የሌላቸው ረቂቃን ካህናት የሆኑና ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ ከፍከፍ ያሉ ፤ ለእግዚአብሔር ቀራቢዎች ፤ ለሰው ወገን የሚማልዱ ከእጃቸው ውስጥ ካለ ማዕጠንት ጋር እንደ እጣን የቅዱሳንን ጸሎት የሚያቀርቡ ናቸው።

የሃያ አራቱ ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ አማላጅነት አይለየን🤲 አሜን!

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
🔥21
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለታላቁ_ሰማዕት_ለቅዱስ_መርቆሬዎስ (ፒሉፓዴር) በንጉሥ ዳኬዎስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ መታሰቢያ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከእስላሞች ወገን ከነበረ #ቅዱስ_መርቆሬዎስ ተአምር አድርጎ ከመለሰው #ከቅዱስ_ዮሐንስ_ከአቃርዎስና #ከሮማኖስ ከመታሰቢያቸወ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
🌿🌿🌿🌿

"እግዚአብሔርን 'ለምን አልሰጠኸኝም?' ብለህ አትጠይቀው፤ ይልቅስ 'እንደ አንተ ፈቃድ ይሁን' በለው። እርሱ ለአንተ የሚጠቅምህን ከአንተ በተሻለ ያውቃልና።"

                  አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

"አእምሮህ በጸሎት ጊዜ ሲበተን አትውቀሰው ይልቅስ እንደ አዲሰ ወታደር መልሰህ ወደ ሰልፍ አስገባው።"

                   ቴዎፋን ዘሬክሉስ


“አንተ ሰው የበደለህን ይቅር ሳትል ወደ ጾም አትግባ፡፡ አንተን በበደለህ ሰው ላይ በቁጣ እያለህ የምትጾመው ጾም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔርም አይቀበለውም፡፡ ጾምህን በፍቅርና እርሱን ተስፋ በማድረግ በእምነት ካላደረግኸው አንተን ፈጽሞ ሊረዳህ አይችልም፡፡ በጠብ ሆኖና በውስጡ ጠላትነትን አንግሦ የሚጾም ጸዋሚ እግዚአብሔርን ይጠላዋል፤ ከመዳንም ፈጽሞ የራቀ ነው፡፡"

                       ቅዱስ ኤፍሬም

"እጅግ ምርጡ ጸሎት 'ጌታ ሆይ አንተ ሁሉን ታውቃለህ የፈቀድከውን አድርግልኝ።' ማለት ነው።"


                       ባሕታዊ ቴዎፋን


ጠዋት ከእንቅልፍህ ተነስተህ ሥራህን ከመጀመርህ በፊት የእግዚአብሔር ቃል አጥና። አንተ የእግዚአብሔር ቃል የዘውትር ወዳጅህ አድርገህ የምትይዘው ከሆንህ በዓለማዊ ነገሮች ባተሌ አትሆንም፥ አትታወክም፥ ኃጢአት አትሠራም ።

                      ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@efeson_2

🌿🌿🌿🌿
🔥2
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን ለአገረ ናግራን ሰማዕታትና ለአባታቸው ለቅዱስ ኂሩት ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው መታሰቢያቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱስ ቢላርያኖስ ከሚስቱ ኪልቅያና ከእኅቱ ታቱስብያ በሰማዕትነት ከዐረፉ፣ ከደሴተ ሰንሲላ ኤጲስቆጶስ ከአባ ጎርጎርዮስ፣ ከጌልዮስ፣ ከምክዋስና ከማርልዮስ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለቊስጥንጥንያ_ሊቀ_ጳጳሳት ለቅዱስ አባት #ለአባ_አካክዮስ_ለዕረፍት#ለቅዱሳን_ለቆዝሞስና_ለድምያኖስም ቤተ ክርስቲያናቸው ለከበረችበት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሰማዕት #ከአባ_መርቆሬዎስ ከመታሰቢያ በዓሉ፣ #ከአናንዮስ_ዘዓምድና_ከአባ_ጴጥሮስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለርእሰ_ባሕታዊ_ለታላቁ_ነቢይ ለቴስብያዊ #ለቅዱስ_ኤልያስ በእስራኤል ፊት ለተገለጠበት ለልደቱ ዓመታዊ በዓል፣ ለእስራኤላዊ #ለቅዱስ_ናቡቴ ለዕረፍት በዓል፣ ለጋዛ አገር ኤጲስቆጶስ ለቅዱስ አባት #ለአባ_ጴጥሮስ_ለዕረፍት_በዓል፣ ለእስክንድርያ አገር ሠላሳኛ ሊቀ ጳጳሳት ለቅዱስ አባት #ለአባ_ዮሐንስና ሰባ ስድስተኛ ሊቀ ጳጳሳት #ለአባ_አትናቴዎስ_ለዕረፍታቸው_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_ጴጥሮስ_ከያዕቆብ_ከመነኰስ_ኤልያስ #ከንጉሥ_ሰሎሞን_እናት_ከቤርሳቤህ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
🔥1
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለኢትዮጽያዊው_ጻድቅ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ዜና_ማርቆስ_ለዕረፍታቸው ዓመታዊ ክብረ በዓላቸው እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ሐዋርያ አንዱ ለሆነው #ለሊቀ_ሐዋርያት_ለቅዱስ_ጴጥሮስ_ወንድም ለተመሰገነ #ለሐዋርያው_ለቅዱስ_እንድርያስ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱሳን #ከአባ_ጻዕ_ከአባ ያዕቆብ_ከዘካርያስ_ከስምዖን፣ #ከታዖድራና_ከታውፍልዖ እግዚአብሔር አምላክ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
Forwarded from ነይ ነይ እምዬ ማርያም መዝሙሮች (𝓟𝓲𝓵𝓾𝓟𝓪𝓭𝓮𝓻)
33k channel መግዛት ለምፈልጉ inbox አውሩኝ @pilupadier
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለኢትዮጵያኑ_ጻድቃን ለደብረ ድማሕ(ዲማ) ገዳም አበምኔት በፊትም በኋላም የሚያዩ ለሆኑ #ለታላቁ_አባት_ለአቡነ_ለተክለ_አልፋ ለዕረፍት በዓል፣ የኢትዮጵያ ሕዝብን ማልኝ ብለው በአባይ ወንዝ ውስጥ ለዘጠኝ ዓመት ለጸለዩ #ለአቡነ_እስትፋሰ_ክርስቶስ_ለልደት በዓል፣ በክርስቶስ ለሚታመንየሰማዕታትንና የጻድቃንን በየዕረፍታቸው ቀን ለእያንዳንዳቸው ርኁባንን በማጥገብ የተራቆቱትን በማልበስ መታሰቢያቸውን ለሚያደርግ ለነበረ #ለቅዱስ_ገብረ_ማርያምና፣ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ኪሮስና ከግብጽ ለኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ተሾመው ለመጡ በኢትዮጵያ ብዙ የዋሻ ቤተ ክርስቲያንን ላነጹ #ለብጹዓዊ_ለአቡነ_ሙሴ_ዘድባ ለልደታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
Forwarded from ነይ ነይ እምዬ ማርያም መዝሙሮች (𝓟𝓲𝓵𝓾𝓟𝓪𝓭𝓮𝓻)
33k channel መግዛት ለምፈልጉ inbox አውሩኝ @pilupadier
ታሕሳስ ፲፭ /15/


በዚች ቀን ያለ ደም መፍሰስ ሰማዕት የሆነ የአርማንያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ጎርጎርዮስ አረፈ።

ይህንንም ቅዱስ ለንጉሡ አማልክት አልሠዋም ስላለ የአርማንያ ንጉሥ ድርጣድስ ደረቅ ጒድጓድ ውስጥ ጨመረውና በዚያ 15 ዓመት ኖረ። አንዲት ሴትም በድብቅ ምግቡን ታመጣለት ነበር።

ድርጣድስም ቅድስት አርሴማን ሊአገባት ሽቶ ነበርና በእርሷ ምክንያት ደናግሎችን ገደላቸው። ሥጋቸውም በተራራ ወድቆ ቀረ። ንጉሡም ስለ ገደላቸው ደናግል ይልቁንም ስለ ቅድስት አርሴማ አብዝቶ የሚያዝን ሆነ። ከዚህም በኋላ ወገኖቹ እንዲህም አሉት አውሬ ታድን ዘንድ ወደ ዱር እንውጣ የልብህም ኀዘን ይወገድልሃል። እርሱም ወደ ዱር ወጣ ። ወዲያውኑ ሰይጣን አደረበትና እንደ እሪያ አደረገው።

@efeson_2

የንጉሡ እኅት ግን ጎርጎርዮስን ከጒድጓድ ካላወጡ እንደማይድኑ በራዕይ አየችና ነገረቻቸው። ጎርጎርዮስም ከዚያ አውጥተው ወደ ቤተ መንግሥት አደረሱት። በዚያንም ጊዜ ንጉሱ ያስገደላቸውን የደናግሉን ስጋ ሰብስቦ በክብር አኖረው። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ጸለየ ከንጉሡም ላይ በእሪያ አምሳል የነበረውን ሰይጣንን አስወጣው።
ዳግመኛ እንዳይታበይ ከእግሩ ላይ የእሪያ ጥፍር አስቀረ ከዚህ በኋላም የቤተ መንግሥት ሰዎችን ሁሉንም አዳናቸው ከላያቸውም አጋንንትን አስወጥቶ ሰደዳቸው።

ከዚህም በኋላ ያጠምቋቸው ዘንድ ወደ አርማንያ ሊቀ ጳጳስ መልክተኞችን ልኮ አጠመቃቸው ዳግመኛም ሊቀ ጳጳሳቱ የአርማንያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ይሆን ዘንድ ቅዱስ ጎርጎርዮስን ሾመው። በዚያም መልካም ጎዞውን ፈጸሞ በሰላም አረፈ። በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦  መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
ታሕሳስ ፲፯ /17/


በዚች ቀን የቅዱስ ሉቃስ ዘዓምድ የሥጋው ፍልሰት ሆነ።

እርሱም ከፋርስ አገር ነው በመጀመሪያ በመቶ ጭፍራ ላይ መኰንን ሁኖ ተሹሞ ነበር ከዚህም በኋላ ሹመቱን ትቶ የምንኵስና ልብስን ለበሰ። በአንድ ገዳም ውስጥ ገብቶ በብዙ መጋደል ጀመረ በዚያም ቅስና ተሾመ። ከዚህም በኋላ ከዓምድ ላይ ወጥቶ በላዩ ሦስት ዓመት ቆመ በስሙም መልአክ ጠርቶት ከአንድ ገዳም አደረሰው።

ከዚህም በኋላ የማይናገር ሆነ ከሰው ጋር ከቶ እንዳይናገር ከአፉ ውስጥ ደንጊያ ጐረሰ ዳግመኛም ወደ ቊስጥንጥንያ አገር ዳርቻ ይሔድ ዘንድ መልአክ አዘዘው። ለእርሷም አቅራቢያ ወደ ሆነች ወደ አንዲት ቦታ ሔደ ከምሰሶ ላይም ወጥቶ ታላቅ ተጋድሎን እየተጋደለ በላዩ አርባ አምስት ዓመት ኖረ እግዚአብሔርም የመፈወስን ሀብት ሰጠው አስደናቂዎች ተአምራትን በማድረግ ወደርሱ የሚመጡትን ብዙዎች በሽተኞችን ፈወሳቸው።

እግዚአብሔርም ከዚህ ዓለም ድካም ሊአሳርፈው በፈቀደ ጊዜ በዚህ ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን አረፈ የሚያገለግለውም ረድ ለጳጳሳት አለቆችና ለካህናት አለቆች ስለ ዕረፍቱ ነገራቸው እነርሱም መስቀሎችን፣ ጽንሐዎችን፣ መብራቶችን ከመያዝ ጋር በዚያን ጊዜ ተነሥተው ወደ መኖሪያው ሔዱ በላዩም ጸልየው ተሸክመው ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ ወሰዱት።

በአረፈ በሦስተኛው ቀን ታኅሣሥ ዐሥራ ሰባት በዚች ቀን አደረሱት ወደ ቤተ መቅደስም አስገብተው የከበረ ሥጋው በአለበት እንደ ሚገባ ጸሎትን ፈጸሙ። ከእርሱም ተባረኩ የተሰበሰቡትም ሁሉ ተባረኩ ከዚህም በኋላ ከእርሱ አስቀድሞ የቅዱሳን ሥጋቸው ወዳለበት ሣጥን ውስጥ ጨመሩት።

የቅዱሳን በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦  መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
*🗝በልብ የተሸሸገ አፍ🔑 *
                📖🔔📖🔔📖

የለፍላፊ ከንፈር የማይመለከተውን ይናገራል ፤ የጠቢባን ቃል ግን በሚዛን የተመዘነች ናት። አላዋቂዎች ልባቸው በአፋቸው ነው ፤ የአዋቂዎች አፍ ግን በልባቸው ነው። ኃጢአተኛ ሰው ሰይጣንን ቢረግመው ራሱን መርገሙ ነው።
ሐሜተኛ ሰው ሰውነቱን ያረክሳል ፤ ባደረበትም ቦታ ራሱን ያስጠላል።
   🔔 📘📖🔔📖🔔📖📔

          📌(መ.ሲራክ 21፥25-28)
1
ታሕሳስ ፳፩ /21/

በዚችም ቀን የስሙ ትርጓሜ የመረጋጋት ልጅ የሆነ ቅዱስ ሐዋርያ በርናባስ በሰማዕትነት አረፈ።

ይህም ቅዱስ ሐዋርያ ከሌዊ ነገድ የሆነ ሀገሩ ቆጵሮስ ነው የቀድሞ ስሙ ዮሴፍ ነው ክብር ይግባውና ጌታችን ከመከራው በፊት ይሰብኩ ዘንድ ከላካቸው ከሰባ ሁለት አርድእት ጋር መረጠው ስሙንም በርናባስ ብሎ ጠራው።

በባለ ሃምሳ ጊዜ እርሱም ከሐዋርያት ጋር የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ተቀብሎ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አስተማረ ። የእርሻ ቦታ ነበረውና ሽጦ ዋጋውን አምጥቶ ከሐዋርያት እግር በታች አኖረው።

ቅዱስ ጳውሎስም በጌታችን አምኖ ወደ ሐዋርያት በመጣ ጊዜ ክብር ይግባውና ለክርስቶስ እርሱ ደቀ መዝሙሩ እንደሆነ ሐዋርያት አላመኑትም ነበር። ይህ በርናባስ ጌታችን በመንገድ እንደ ተገለጸለትና እንደአነጋገረው እርሱም በጌታ ኢየሱስ ስም በደማስቆ እንደ አስተማረ ነገራቸው።

ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔርን ሥራ ሲሠሩ ሲጾሙ ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ ሳውልንና በርናባስን እኔ እነርሱን ለመረጥኩለት ሥራ ለዩልኝ አላቸው። ከዚህም በኋላ ጹመው ጸልየው እጆቻቸውን በራሳቸው ላይ ጭነው ሾሟቸው።

በቆጵሮስ አገር የሚኖሩ አይሁድም ቀኑበት በመኳንንቱም ዘንድ ወንጅለው እጅግ ብዙ  ስቃይን አሰቃዮት በመጨረሻም ከእሳት ጨመሩት ምስክርነቱንም ፈጸመ ማርቆስም ከርሱ ጋር አለ ግን እግዚአብሔር ጠብቆ አተረፈው። እርሱም ቅዱስ በርናባስን ከእሳት ውስጥ አወጣው ሥጋውንም እሳት ከቶ አልነካውም በአማሩ ልብሶችም ገነዘውና ተሸክሞ ወስዶ ከቆጵሮስ ከተማ ውጭ በዋሻ ውስጥ አኖረው።

የቅዱሳን በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦  መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
ታሕሳስ ፳፪ /22/


በዚች ቀን የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ የገብርኤል የበዓሉ መታሰቢያ ዳናህ በሚባል አገርም ቤተ ክርስቲያኑ የተሠራችበት ተአምራትም ያሳየበትና በዚች ቀን ቤተ ክርስቲያኒቱ የከበረችበት ነው የዚያች ሀገር ኤጲስቆጶስ አርኬላዎስም ምስክር የሆነበት ነው።

ይህም መልአክ ስለ ወልደ እግዚአብሔር ሰው መሆን ምሥጢር የታመነ ሆኖ ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተላከ የደስታ መገኛ ደስ ይበልሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው አንቺም ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ አላት።

ስለ መጥምቁ ዮሐንስ መወለድም ካህኑን ዘካርያስን ያበሠረው እርሱ ነው ይህ መልአክ እጅግ የከበረ የተመረጠ ገናና የሆነ ነውና ስለ እኛ ወደ እግዚአብሔር ይማልድ ዘንድ ልባችንን አንጽተን ወደዚህ የከበረ መልአክ እየለመንን መታሰቢያውን ልናደርግ ይገባናል።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ መልአክ አማላጅነት ይማረን በረከቱ ረድኤቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦  መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለልበ_አምላክ_ለእሴይ_ልጅ ለእስራኤል ንጉሥ ለነቢዩ #ለቅዱስ_ዳዊት_ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል፣ ለከበረ ተጋዳይ አባት ለገዳማዊ #ለአባ_ጢሞቴዎስ_ዕረፍት በዓል፣ ለቅዱሳን #ለአባ_ሳሙኤል_ለአባ ስምዖን_ለአባ ገብርኤል ለዕረፍታቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_ከይስሐቅ_ከአባ_አሞን#ከአባ_አቦሊ_ከመቃርስ_ከአይተለአትካ_ከፊልጦስ_ከመርቆሬዎስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
🔥1
ታሕሳስ ፳፫ /23/

በዚችም ቀን የእሴይ ልጅ ንጉሥ ዳዊት አረፈ።

ንጉሥ ዳዊት ቤተልሔም የሆነች ከይሁዳ ነገድ ነው። ሳሙኤልም በእግዚአብሔርን ትእዛዝ ዳዊትን ከእረኝነት አስጠርቶ ቅብዐ መንግስትን ቀብቶ አነገሰው። ከፍልስጤማውያንም ጋራ ሰልፍ በሆነ ጊዜ ብርቱ ሰው ስሙ ጎልያድ የሚባል ከጌት ሰዎች የተወለደ ቁመቱ ስድስት ክንድ ከስንዝር የሆነ ከኢሎፍላውያን ሰፈር ወጣ።

በዚያም ወራት ዳዊት ወንድሞቹን ሊጐበኝ ወጣ ጎልያድንም በአየው ጊዜ አምላካዊ ቅናትን ቀና ሳኦልንም እንዲህ አለው እኔ ሔጄ ይህን ያልተገረዘ ቈላፍ ገድዬ ዛሬ ከእስራኤል ሽሙጥን አርቃለሁ አለው። ሕያው የሚሆን የእግዚአብሔርን አርበኞች ይገዳደር ዘንድ ይህ ቈላፍ ምን ቁም ነገር ነው ከድብ አፍና ከአንበሳ አፍ ያዳነኝ እርሱ እግዚአብሔር ከዚህ ካልተገረዘ ኢሎፍላዊ እጅ ያድነኛል።ሳኦልም ሒድ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሁን አለው።

ዳዊትም ዛሬ የእስራኤልን አርበኞች የተገዳደርክ አንተን ዛሬ እግዚአብሔር በእጄ ይጥልሃል እገድልህምአለሁ ራስህንም እቆርጣለሁ አለው። ዳዊትም አንዲት ደንጊያ አውጥቶ ወነጨፋት ያንንም ኢሎፍላዊ ግንባሩን ገመሰው በግንባሩም ተደፋ። ዳዊትም ሩጦ የገዛ ሰይፉን አንሥቶ ራሱን ቆረጠው ከእስራኤልም ልጆች ስድብን አራቀ።

የዳዊትም መላው ዕድሜው ሰባ ነው መንግሥትን ሳይይዝ ሠላሳ ዓመት ኖረ ከዚያ በኋላ አርባ ዓመት ኖሮ በሰላም አረፈ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከቱ ረድኤቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦  መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
1