ኤፌሶን~፩
650 subscribers
75 photos
1 video
23 links
Download Telegram
Forwarded from ነይ ነይ እምዬ ማርያም መዝሙሮች (𝕻𝖎𝖑𝖚𝕻ΔDΣR)
የኦርቶዶክስ ቻናል ስብስብ ላይ wave ማሰራት የምትፈልጉ DM @Pilupadier

2k በላይ ቻናል ያላቹ ብቻ
#ኅዳር_11

#ቅድስት_ሐና

ኅዳር ዐሥራ አንድ በዚች ዕለት አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እናቷ የሆነች የተመሰገነች የቅድስት ሐና የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው።

ይችም ቅድስት ከኢየሩሳሌም አገር ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ትውልድ የሌዊ የሜልኪ ልጅ ለሆነ ለማጣት ልጁ ናት። ለማጣትም ሦስት ሴቶች ልጆች አሉት የታላቂቱም ስሟ ማርያም ናት ሁለተኛዋም ስሟ ሶፍያ ሦስተኛዪቱም ስሟ ሐና ናት ታላቂቱ ማርያምም ለባል ተድራ አዋላጅ የሆነች ሰሎሜን ወለደቻት እርሷም መድኃኒታችንን ከወለደችበት ጊዜ ጀምሮ በስደቷም ወራት ከአረጋዊ ዮሴፍ ጋር እመቤታችንን ድንግል ማርያምን ያገለገለቻት ናት።

ሶፍያም ለባል ተድራ ለመጥመቁ ዮሐንስ እናቱ የሆነች ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደቻት። ይችንም ቅድስት ሐናን ከይሁዳ ነገድ ለሆነ ጻድቅ ስሙ ኢያቄም ለሚባል አጋቧትና እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወለደቻት እሊህም ሰሎሜና ኤልሳቤጥ ለቅድስት ሐና የእኅትማማች ልጆች ናቸው።

የዚችንም የቅድስት ሐናን በሥውር የምትሠራውን ገድሏንና ትሩፋቷን እንዳናስታውሰው አናውቀውም ግን ከሴቶች ሁሉ እንደምትበልጥና እንደምትከብር እናውቃለን እንረዳለን እርሷ አምላክን በሥጋ ለወለደችው ወላጅዋ ትሆን ዘንድ የተገባት ሁናለችና ከሴቶች ሁሉ የሚበልጥና የሚበዛ ትሩፋትና ተጋድሎ ባይኖራት ይህ ታላቅ ጸጋ ባልተገባት ነበር።

ይህችም ጻድቅት ሐና መካን በመሆንዋ ልጅን ይሰጣት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር በጸሎት ትማልድ ነበር እግዚአብሔርም በእርሷ ለዓለም ሁሉ ድኅነት የተደረገባትን ይቺን የተባረከችና የከበረች ልጅን ሰጣት እርሷም አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት።

ስለዚህም ይህን ታላቅ ጸጋ ስለሰጣት የበዓሏን መታሰቢያ በደስታ ልናከብር ይገባናል።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በጸሎቷ የሚገኝ በረከቷም ከእኛ ጋር ይሁን ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር)

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
1🙏1
🌹እንኳን መላእክት አለቃ 🌹
ቅዱስ ሚካኤል
🌸ዓመታዊ በዐል አደረሳችሁ🌸

👇👇👇👇👇
@efeson_2 @efeson_2
3
“ከሰነፍ ሰው ፊት ራቅ፥ በእርሱ ዘንድ የእውቀትን ከንፈር  አታገኝምና።”

ምሳሌ ፲፬፥፯

መልካም አዳር ውድ ኦርቶዶክሳውያን

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇

     #ሼር  @efeson_2
🙏🙏🙏🙏🙏

    
🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊

  
1
➥           "አንበሳ ሲያረጅ..."
◈◈◈◈◈  ◊  ◈◈◈◈◈  ◊  ◈◈◈◈◈
ያዕቆብ ልጆቹን በባረከ ጊዜ ለይሁዳ የሰጠው የበረከት ቃል፦ "ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው ፤ ልጄ ሆይ፥ ከአደንህ ወጣህ ፤ እንደ አንበሳ አሸመቀ፥ እንደ ሴት አንበሳም አደባ ፤ ያስነሣውስ ዘንድ ማን ይችላል? " ዘፍጥ.49፥9 ብሎ ነበር።

በእርግጥም ይሁዳ በአምላኩ ክንድ ተደግፎ ፥ ኃያላኑን ነገሥታት፦ የአሞሬዎንን ንጉሥ ሶዎንን ፣ የባሳንን ንጉሥ ዐግን ድል የነሳ ፣ የፈርዖንም የጭካኔ በትር ያላጠፋው ፥ አንበሳ ነበር።

ዛሬ ግን የድምጹ ግርማ አራዊትን ሁሉ የሚያርድ፣ የሚያንቀጠቅጠው አንበሳ ፥ በአምላኩ በእግዚአብሔር ላይ አምጿልና ብርቱ ክንዱ ዝሎ ፥ ትላንት ከርኅቀት ሰምተው የተሸበሩለት አሕዛብ (ዕርያና የዝንብ መንጋ) ፥ መጫወቻ አድርገውታል።

በዝንብ ፊት ፥ የሚቀመጥ የክብር ዕቃ ሁሉ ፥ ክብር እንደማይኖረው የታመነ ነው። ዝንብ ልባም ሴት በአሰናዳችው ማዕድ ላይ ራሷን ስትሰይም ከብርና መወደድ አይሰማትም ፤ ሙያ የጎደላትም ብታሰናዳው አትጸየፈውም።

አንበሳው ይሁዳ ፥ በኃጢአት ብዛት ስለአረጀ ፥ የዝንብ መንጋ እንዲጫወትበት ፥ ለባቢሎን ተላልፎ ተሰጥቷል።

የይሁዳም ልጅ ዳዊት የመከራውን ጽናት እንዲህ በማለት ዘግቦታል ፥ "በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን ፤
ጽዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን።
በአኻያ ዛፎችዋ ላይ መሰንቆቻችንን ሰቀልን። የማረኩን በዚያ የዝማሬን ቃል ፈለጉብን ፥ የወሰዱንም፦ “የጽዮንን ዝማሬ ዘምሩልን፡” አሉን። የእግዚአብሔርን ዝማሬ በባዕድ ምድር እንዴት እንዘምራለን? ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ብረሳሽ፥ ቀኜ ትርሳኝ። ባላስብሽ፥ ምላሴ በጕሮሮዬ ይጣበቅ ፤ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ።" መዝ.137

▩ ለጠላቶቻችን ፥ ወዳጅ እንጂ ጠላት እንሁንባቸው የሚል ትምህርት የለንም።
ነገር ግን ፥ ጠላት ሕዝብና ታሪክን ሊያጠፋ፣ ከሆነም ሊማርክ እንጂ ሊባርክ እንደማይመጣ ከመገንዘብ መዘግየትም የቅድስና ፍሬ አይደለም።

በጠላት ፊት ያስቀመጥከው የክብርና የቅድስና ሀብት ሁሉ ፥ ለአንተ ክብርና ጌጥ አይሆንህም።

ዝንብ ክብርና ቅድስናን ፣ የጽዮንንም የዝማሬዋን መወደድ አትገነዘብምና ፥ እባክህ ! ክቡር ዕንቁህን በዕርያና ፣ በዝንብ መንጋ ፊት አትጣል ፤ አንተም ወደ ዝንቦች መንደር አትግባ ፣ ዝንቦችም እንዳይቀርቡህ ፥ የክብርህን አጥር በንጹሕ አምላክህ ትዕዛዝ አጽና።

አንበሳው ባያረጅ እጅግ የተሻለ ነበር። ዛሬ ግን ክንዱ ዝሏል ፣ ዝንቦችም በርትተውበታል። ኃይሉ ተለይቶታል ፤ የቀረችለት ሀብቱ ዕንባው ብቻ ናት። በዕንባው ጽናት ግን የአምላኩን ፊት ለማየት የበቃ ነው። አምላኩም ዕንባውን ያብስለታል ፤ ኃይሉንና የድምጹንም ግርማ ይመልስለታል።
በዚህም አንበሳው እንደቀድሞ ከእርጅናው ይታደሳል።

ከይሁዳ ነገድ የተወለደው ፥ የማያረጀው አንበሳ ፥ ክርስቶስ ኢየሱስ ፥ የጠላትን፣ ኃይል በመንፈስ እንረግጥ ዘንድ በምሕረቱ ያሰልጥነን።

         ▩        አሜን !      ▩

✍️              ቴዎሶፊ
📅     ሕዳር 18/2018 ዓ.ም
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇

     #ሼር  @efeson_2
🙏🙏🙏🙏🙏

    
🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊

  
1
"ልጆቼ! ከእሳተ ገሃነም እንዴት ልንተርፍ(ልንድን) እንደሚገባን እንጂ እሳተ ገሃነም የት እንዳለ ለማወቅ እጅግ የምንደክም አንኹን፡፡"

ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

መልካም ቀዳሚት ሰንበት ❤️
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@efeson_2@efeson_2
     #ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏

    
🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊  
#ሰውማ_እናታችን_ጽዮን_ይላል

ሰው በምድር ላይ ያቃተው ነገር ቢኖር ሰው መሆን ብቻ ነው:: ብዙ ነገር መሆን ችሎአል:: እንደ አሣ በባሕር እንደ ወፍ በሰማይ በርሮአል:: እንደ እንስሳ መኖር ችሎአል እንደ አውሬም መጨከን ተሳክቶለታል:: እንደ ንስር ከሩቅ አይቶአል:: እንደ ውኃ ሰርጎ ብዙ ተመራምሮአል:: ለብዙ ሰው የከበደው ነገር ቢኖር ሰው መሆን ነው::

አንዱ ወደ አንድ አባት ቀረብ ብሎ "ድንግል ማርያም እኮ እንደ እኛ ሰው ናት" አላቸው። እርሳቸውም "ልክ ነህ እርስዋ በተፈጥሮዋ  ሰው ናት ፣ አንተ ግን ሰው ነህ?" አሉት።

ነገሩ ስድብ ይመስላል ፣ አስተውሎ ላየው ግን ሰው ነኝ ለማለትም መሥፈርት እንዳለው ያስታውሳል። "ኤልያስ እንደ እኛ ሰው ነበረ" ነገር ግን ዝናምን በጸሎቱ ያቆመ መሆኑን ስንሰማ ግን እኛም እንደርሱ ሰው ነን ለማለት እንፈራለን። 

ንጉሥ ዳዊት ለልጁ ሰሎሞን "ሰው ሁን" ያለው ሰው መሆን ማለት እንደ ሰው ክብርን አውቆ መኖር ስለሆነ ነው። ክቡር ሆኖ ሳለ ካላወቀና በኃጢአቱ ከጸና እንደሚጠፉ እንስሳት ይመስላል።

ሰው በምድር ላይ ያቃተው ነገር ቢኖር "ሰው መሆን ነው"!  አዋቂ መሆን ቀላል ነው! ኃያል መሆንም ይቻላል:: ባለ ጥበብ መሆንና መራቀቅም ይቻላል:: ጀግና መሆንም እንዲሁ:: ሰው ያቃተው ሰው መሆን ብቻ ነው::

ሰው መሆን ትልቅ ዋጋ አለው:: ይህንን ዋጋ ስንዘነጋ በአርኣያ ሥላሴ ለተፈጠረው ሰው ሌላ ሚዛን እንፈልግለታለን:: ሰውነቱን ትተህ በሀብቱ በእውቀቱ በዘሩ በቋንቋው ከመዘንከው አንተም ሰውነትህን ታጣለህ::

ሰው ለመሆን ብዙ መሥፈርቶች በመጽሐፍ ቅዱስ  ተቀምጠዋል ፣ የድንግል ማርያምን እናትነት መቀበልም ሰው የመሆን ምልክት ነው።  "ሰው እናታችን ጽዮን ይላል" ተብሎ እንደተጻፈ "ጽዮን እናታችን" ማለት ያልቻለ ምኑ ሰው ይባላል? በውስጥዋም ሰው ተወለደ የተባለው ስለ ጌታ ነው:: እሱን የሚመስሉ እውነተኛ ክርስቲያኖችም  ሰዎች ናቸው::

ሰው ከሆንክ "እናታችን ጽዮን" ትላለህ:: ጽዮንን "እናታችን" ብሎ ለመጥራት ግን "ወንድሜ ወንድሜ" መባባል ይቀድማል:: ይህን ማለት ያልቻለ ግን ሰው አይደለም:: ጽዮንም እናቱ አይደለችም::

ነቢዩ በባቢሎን ሆኖ ስለ ጽዮን ሲያስብ መዝሙር ለመዘመር ተቸግሮ ነበር። "በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን" ብሎ ነበር::

እኛም የአንዲትዋ የጽዮን ልጆች ሆነን በተለያየንበት ዘመናችን እንዲህ እንላለን :-

በዘረኝነት ወንዝ ውስጥ ሆነን አክሱም ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ አለቀስን

የማረኩን ኃጢአቶቻችን ሳንላቀቃቸው የዝማሬ ቃል ፈለጉብን

የእግዚአብሔርን ዝማሬ እንዴት በጥላቻ ልብ እንዘምራለን?

የጽዮንንስ ዝማሬን ቂምና በቀል አርግዘን እንዴት እንዘምራለን?

ታቦተ ጽዮን ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ
ባላስብሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ
ከዘር ከነገዴ በላይ ቤተ ክርስቲያንን ባልወድድ!

እናታችን ጽዮን ሆይ እባክሽን አንቺን እናታችን ብለን ሰው ለመሆን አብቂን:: ከራሳችን ጠብቂን የጥላቻን ዳጎን ሰባብሪልን::  ፍልስጥኤማውያን በአንቺ ግርማ የተነሣ ፈርተው የዳጎን መድረክን እንዳልረገጡት እልቂትና ደም መፋሰስ በአማላጅነትሽ የኢትዮጵያን ምድር አይርገጥ:: እንደ ጣዖት በልባችን የነገሠውን ክፋት ሰባብረሽ ከእግርሽ በታች አድርጊልን::

(Deacon Henok Haile)

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
2
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት አንዱ ለሆነው በሐዋርያው #በቅዱስ_ጴጥሮስ_እጅ_ለተጠመቀ ለመቶ አለቃ ለነበረው #ለጻድቁ_ቅዱስ_ቆርኔሌዎስና የስሙ ትርጓሜ የእግዚአብሔር አገልጋይ ለሆነ #ለነቢዩ_ቅዱስ_አብድዩ_ለዕረፍታቸው_በዓል በሰላም አደረሰን። ከእነዚህ ቅዱሳን እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
ሕዳር ፳፫ /23/


‎በዚችም ዕለት ዳግመኛ የስሙ ትርጓሜ የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነ የነቢይአብድዩ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው ።

‎ይህም ቅዱስ ከጠፍ በረሀ አቅራቢያ ከአለች ሱሳም በምትባል አገር ካሉ ሰዎች ወገን ነው ለነቢይ ኤልያስም ደቀ መዝሙሩ ሁኖ ብዙ መከራን በእርሱ ላይየመጣውን ታግሦ ከመከራውም በትዕግሥቱ ዳነ ።

‎ይህም ኤልያስን የተለማመጠና ኤልያስም አዝኖለት አብሮት ወደ ንጉሥ አክዓብ የሔደለት ሦስተኛው የሃምሣ አለቃ ነው ። ከዚህም በኋላ ምድራዊ ንጉሥን ማገልገል ትቶ ነቢይን ሆነ የትንቢቱንም ወራት አድርሶ በሰላም አረፈ ።

‎ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
‎ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
1
🍀

''ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ፣ ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረዋልምና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ'' ራዕ ፬፥፲-፲፩

💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

@efeson_2

እንኳን  በእግዚአብሔር ዙፋን ዙሪያ ለሚኖሩ ለሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን🙏

ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ሥጋ የሌላቸው ረቂቃን ካህናት የሆኑና ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ ከፍከፍ ያሉ ፤ ለእግዚአብሔር ቀራቢዎች ፤ ለሰው ወገን የሚማልዱ ከእጃቸው ውስጥ ካለ ማዕጠንት ጋር እንደ እጣን የቅዱሳንን ጸሎት የሚያቀርቡ ናቸው።

የሃያ አራቱ ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ አማላጅነት አይለየን🤲 አሜን!

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
🔥21
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለታላቁ_ሰማዕት_ለቅዱስ_መርቆሬዎስ (ፒሉፓዴር) በንጉሥ ዳኬዎስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ መታሰቢያ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከእስላሞች ወገን ከነበረ #ቅዱስ_መርቆሬዎስ ተአምር አድርጎ ከመለሰው #ከቅዱስ_ዮሐንስ_ከአቃርዎስና #ከሮማኖስ ከመታሰቢያቸወ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
🌿🌿🌿🌿

"እግዚአብሔርን 'ለምን አልሰጠኸኝም?' ብለህ አትጠይቀው፤ ይልቅስ 'እንደ አንተ ፈቃድ ይሁን' በለው። እርሱ ለአንተ የሚጠቅምህን ከአንተ በተሻለ ያውቃልና።"

                  አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

"አእምሮህ በጸሎት ጊዜ ሲበተን አትውቀሰው ይልቅስ እንደ አዲሰ ወታደር መልሰህ ወደ ሰልፍ አስገባው።"

                   ቴዎፋን ዘሬክሉስ


“አንተ ሰው የበደለህን ይቅር ሳትል ወደ ጾም አትግባ፡፡ አንተን በበደለህ ሰው ላይ በቁጣ እያለህ የምትጾመው ጾም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔርም አይቀበለውም፡፡ ጾምህን በፍቅርና እርሱን ተስፋ በማድረግ በእምነት ካላደረግኸው አንተን ፈጽሞ ሊረዳህ አይችልም፡፡ በጠብ ሆኖና በውስጡ ጠላትነትን አንግሦ የሚጾም ጸዋሚ እግዚአብሔርን ይጠላዋል፤ ከመዳንም ፈጽሞ የራቀ ነው፡፡"

                       ቅዱስ ኤፍሬም

"እጅግ ምርጡ ጸሎት 'ጌታ ሆይ አንተ ሁሉን ታውቃለህ የፈቀድከውን አድርግልኝ።' ማለት ነው።"


                       ባሕታዊ ቴዎፋን


ጠዋት ከእንቅልፍህ ተነስተህ ሥራህን ከመጀመርህ በፊት የእግዚአብሔር ቃል አጥና። አንተ የእግዚአብሔር ቃል የዘውትር ወዳጅህ አድርገህ የምትይዘው ከሆንህ በዓለማዊ ነገሮች ባተሌ አትሆንም፥ አትታወክም፥ ኃጢአት አትሠራም ።

                      ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@efeson_2

🌿🌿🌿🌿
🔥2
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን ለአገረ ናግራን ሰማዕታትና ለአባታቸው ለቅዱስ ኂሩት ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው መታሰቢያቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱስ ቢላርያኖስ ከሚስቱ ኪልቅያና ከእኅቱ ታቱስብያ በሰማዕትነት ከዐረፉ፣ ከደሴተ ሰንሲላ ኤጲስቆጶስ ከአባ ጎርጎርዮስ፣ ከጌልዮስ፣ ከምክዋስና ከማርልዮስ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለቊስጥንጥንያ_ሊቀ_ጳጳሳት ለቅዱስ አባት #ለአባ_አካክዮስ_ለዕረፍት#ለቅዱሳን_ለቆዝሞስና_ለድምያኖስም ቤተ ክርስቲያናቸው ለከበረችበት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሰማዕት #ከአባ_መርቆሬዎስ ከመታሰቢያ በዓሉ፣ #ከአናንዮስ_ዘዓምድና_ከአባ_ጴጥሮስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለርእሰ_ባሕታዊ_ለታላቁ_ነቢይ ለቴስብያዊ #ለቅዱስ_ኤልያስ በእስራኤል ፊት ለተገለጠበት ለልደቱ ዓመታዊ በዓል፣ ለእስራኤላዊ #ለቅዱስ_ናቡቴ ለዕረፍት በዓል፣ ለጋዛ አገር ኤጲስቆጶስ ለቅዱስ አባት #ለአባ_ጴጥሮስ_ለዕረፍት_በዓል፣ ለእስክንድርያ አገር ሠላሳኛ ሊቀ ጳጳሳት ለቅዱስ አባት #ለአባ_ዮሐንስና ሰባ ስድስተኛ ሊቀ ጳጳሳት #ለአባ_አትናቴዎስ_ለዕረፍታቸው_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_ጴጥሮስ_ከያዕቆብ_ከመነኰስ_ኤልያስ #ከንጉሥ_ሰሎሞን_እናት_ከቤርሳቤህ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
🔥1
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለኢትዮጽያዊው_ጻድቅ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ዜና_ማርቆስ_ለዕረፍታቸው ዓመታዊ ክብረ በዓላቸው እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ሐዋርያ አንዱ ለሆነው #ለሊቀ_ሐዋርያት_ለቅዱስ_ጴጥሮስ_ወንድም ለተመሰገነ #ለሐዋርያው_ለቅዱስ_እንድርያስ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱሳን #ከአባ_ጻዕ_ከአባ ያዕቆብ_ከዘካርያስ_ከስምዖን፣ #ከታዖድራና_ከታውፍልዖ እግዚአብሔር አምላክ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
Forwarded from ነይ ነይ እምዬ ማርያም መዝሙሮች (𝓟𝓲𝓵𝓾𝓟𝓪𝓭𝓮𝓻)
33k channel መግዛት ለምፈልጉ inbox አውሩኝ @pilupadier