ኤፌሶን~፩
650 subscribers
75 photos
1 video
23 links
Download Telegram

ጥቅምት ፲፮ /16/


‎በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ ዘጠነኛ የሆነ ቅዱስ አባት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ያቃቱ አረፈ ።

‎ከርሱ በፊት የነበረ አባ ብንያሚን በአረፈ ጊዜ ይህን አባት መርጠው በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት በዘመኑም ብዙ ችግር ደርሶበታል ስሙ ቴዎዶስዮስ የሚባል አንድ መለካዊ ሰው ነበረ እርሱም ወደ ደማስቆ ንጉሥ ወደ ዘይድ ሒዶ ብዙ እጅ መንሻ ሰጥቶ ለእስክንድርያ አገረ ገዥ ሁኖ ተሾመ ። ይህንንም አባት አባ ያቃቱን ሊአስጨንቀው ጀመረ በየዓመቱ ግብርሰባት ሺህ የወርቅ ዲናር ከእርሱ እስከተቀበለ ድረስ እግዚአብሔርም እስከ አጠፋው ድረስ ይህን አባት እንዲህ አሠቃየው ።

‎በዘመኑም የብዙዎች ቅዱሳን አባቶች አባት የሆነ የአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን ሕንፃዋ ተፈጸመ ።

‎በአንዲት ሌሊትም ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ለዚህ አባት ተገለጸለት ፍዩም በሚባል አገር በአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግል ዮሐንስ የሚባል ጻድቅ ሰው መነኰስ እንዳለ ነገረው ። ሕዝብን በማስተማርና በመምከርም ይረዳው ዘንድ መልእክተኞችን ልኮ እንዲአስመጣውም አዘዘው ሁለተኛም ከእርሱ በኋላ ሊቀ ጳጳሳት እንደሚሆን ገለጠለት ።

‎በዚያንም ጊዜ መልእክተኞችን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ሥራውንም ሁሉ አስረከበው ይህንንም አባት ከብዙ ድካም የሚያሳርፈው ሆነ በሹመቱ ወንበርዐሥራ ዘጠኝ ዓመት ኑሮ ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈ ።

‎ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
🔥1
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴
እንኳን #ለሀገረ_ቀምስ_ኤጲስቆጶስ #ለቅዱስ_ፊልያስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ ለነቢዩ #ለቅዱስ_ሳሙኤል_እናት ለነቢይት #ለቅድስት_ሐና_ለልደቷ_መታሰቢያ_በዓል#ለቅዱስ_ባስልዮስ_ወንድም_ለቅዱስ_ጎርጎርዮስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓልና #ለእስክንድር_አገር_ሠላሳ_አንደኛ ሊቀ ጳጳሳት #ለቅዱስ_ዲዮስቆሮስ_ካልዕ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #በቆዳ_ገመድ_ከታሠሩ_ከደጋጋጎች ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
‎ጥቅምት ፲፯ /17/



በዚችም ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳ አንደኛ የሆነ የእስክንድርያ አገርሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ዲዮስቆሮስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።

‎ይህም አባት በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ መልእክትን ጽፎ ወደ አንጾኪያ ሊቀ ጳጰሳት ቅዱስ ሳዊሮስ ላካት ። እርሱም ስለ ምስጢረ ሥላሴ እና ስለ ምስጢረ ስጋዌ ጽፎ ላከለት።

‎መልእክቱም ወደ ቅዱስ አባት ሳዊሮስ በደረሰች ጊዜ አነበባትና ፈጽሞ ደስ ተሰኘባት ለአንጾኪያም ሕዝብ አስተማረባት ሁሉም ደስ አለቸው።

‎ከዚህም በኋላ አባ ሳዊሮስ ለአባ ዲዮስቆሮስ የመልእክቱን መልስ እንዲህ ብሎ ጻፈ ። በኒቅያ ከተማ ተሰብስበው ሃይማኖታቸው የቀና 318ቱ ቅዱሳን አባቶቻችን በቀናች ሃይማኖት አጽንተው የሠሩዋትን ቤተ ክርስቲያኑን እንድትጠብቅ ለዚች ለከበረች አገልግሎት የመረጠህ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ ። ዳግመኛም በዚሁ እንዲጸና ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ እንዳይል አስገነዘበው ደግሞም በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ ሕዝቡን ሁል ጊዜ አስተምራቸው አለው ።

‎የአባ ሳዊሮስም መልእክት ወደ አባ ዲዮስቆሮስ በደረሰች ጊዜ ደስ ተሰኘባት በሁሉ ቦታም እንዲአስተምሩባት አዘዘ ይህም አባት ሕዝቡን ሁል ጊዜ የሚያስተምራቸው ሆነ ። ሁል ጊዜም ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ ያስተምራቸዋል ኤጲስቆጶሳቱንና ካህናቱንም መንጋዎቻቸውን ስለ መጠበቅ ያዛቸዋል መልካም አገልግሎቱንም አድርሶ እግዚአብሔርንም ደስ አሰኝቶ አረፈ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
‎ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
🔥1
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴
እንኳን #ለእስክድርያ_ሃያ_ሦስተኛ_ሊቀ_ጳጳስ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ቴዎፍሎስና ክርስቲያኖችን በአሳደደ በመኰንን አስቅልጵያኖስ ዘመን በሰማዕትነት ለዐረፈ ለከበረ #ለመነኰስ_ቅዱስ_ሮማኖስ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከሰማዕት_ቅዱስ_ዮሐንስ#ከቅዱሳን_አድራኒ_ከአርቴማዎስ_ከአርስጦስ #ከሉዲኖስ_ከአስማኒትና
_ከሰባቱ ልጆቿ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
ጥቅምት ፲፰ /18/


‎በዚህች ቀን ክርስቲያኖችን በአሳደደ በመኰንን አስቅልጵያኖስ ዘመን የከበረ መነኰስ ሮማኖስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ የክርስቲያን ወገኖችን መኰንኑ እንዳሳደዳቸው በሰማ ጊዜ ከቀሳውስትና ከዲያቆናት ጋር የክርስቲያን ወገኖችን ሁሉ በአንድነት ሰበሰባቸው ስለ ክርስቶስ ሃይማኖትም መክሮ አጸናቸው።

‎አስቅልጵያኖስም ይህን ሰምቶ እንዲአመጡት አዘዘ በፊቱም በቆመ ጊዜ አስቅልጵያኖስ በወገን የከበርክ ሮማኖስ አንተ ነህን አለው ቅዱሱም የወገን ክብር ምን ይጠቅመኛል ክብሬ ግን ክርስቶስ ነው ብሎ መለሰለት። መኰንኑም ሰምቶ እንዲሰቅሉትና ጉንጮቹን ይሰነጣጥቁ ዘንድ አዘዘ ጉንጮቹንም ሲሰነጣጥቁት ምንም አልተናገረምና መኰንኑ ትዕግሥቱን አደነቀ።

‎በዚያንም ጊዜ ሮማኖስ መኰንኑን እንዲህ አለው እነሆ ስንፍናህን እዘልፍ ዘንድ ፈጣሪዬ አፌን ከፈተ በዚያንም ጊዜ የሕፃኑን ራስ በሰይፍ እንዲቆርጡ የቅዱስ ሮማኖስንም ምላሱን ከግንዱ እንዲቆርጡ መኰንኑ አዘዘ። ያን ጊዜ መኰንኑን ይዘልፍ ዘንድ ለአባ ሮማኖስ ረቂቅ አንደበት ተሰጠው ሲዘልፈውም መኰንኑ ሰምቶ ምላሱ እንዳልተቆረጠ ተጠራጠረ።

ወታደሩንም ጠርቶ ምላሱን ያልቆረጥክ ለምንድን ነው አለው ወታደሩም የምላሱን ቁራጭ ያመጡ ዘንድ እዘዝ አለው አምጥተውለትም አይቶ መኰንኑም ወደ ወህኒ ቤት አስገብተው በዚያ አንቀው እንዲገድሉት አዘዘ። እንዲህም ምስክርነቱን ፈጽሞ የምስክርነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።

‎የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
‎ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለታላቁ_ለትሕትናና_ለትዕግስተኛው አባት ለክቡሩ፤ ለገናና ለሆነ #ለአባ_ዮሐንስ_ሐጺር_ለዕረፍት በዓልና የስሙ ትርጓሜ ጠባቂና አዳኝ ለሆነ #ለታላቁ_ነቢይ_ለቅዱስ_ኤልሳዕ_ለልደቱ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት_አንዱ_ለሆነ ለብልሁና ለጥበበኛው #ለወንጌላዊው_ለሐዋርያው_ለቅዱስ_ሉቃስ በንጉሥ ኔሮን ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለየዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱስ_ሉቃስ_ጋር_በሰማዕትነት_ከዐረፋ_ከአራት°መቶ ሰባ ሰባት ሰዎች ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
ጥቅምት ፳፪ /22/


በዚህች ቀን ብልህ ጥበበኛ የሆነ ቅዱስ ወንጌላዊ ሉቃስ በሰማዕትነት አረፈ።

ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስም ከተገደሉ በኋላ በሮሜ ሀገር የሚያስተምር ሆነ በቀናች ሃይማኖትም ይጸኑ ዘንድ ለምእመናን መልእክትን ይጽፍ ነበር። ጣዖት አምላኪዎች ከአይሁድ ጋር በመስማማት አንድ ግምባር ፈጠሩ በንጉሥ ኔሮን ፊት ቁመው ጮኹ ይህ ሉቃስ ብዙዎች ሰዎችን በሥራዩ ወደ ትምህርቱ አስገባቸው። ንጉሥ ኔሮንም ወደ ፍርድ አደባባይ ሉቃስን እንዲአቀርቡት አዘዘ።

በኔሮንም ፊት ቀርቦ በቆመ ጊዜ ንጉሡ በሥራይህ ሕዝቡን የምታስት እስከመቼ ነው አለው ቅዱስ ሉቃስም እኔ ለሕያው እግዚአብሔር ልጅ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያው ነኝ እንጂ ሥራየኛ አይደለሁም ብሎ መለሰለት።

ንጉሥ ኔሮንም እየጻፈች ሰዎችን የምታስት ይቺን እጅህን እኔ እቆርጣታለሁ ይህንንም ብሎ የቀኝ እጁን እንዲቆርጡ አዘዘ በቆረጡትም ጊዜ ንጉሥ ሆይ እኛ የዚህን ዓለም ሞት እንደማንፈራ እወቅ ነገር ግን የጌታዬንና የፈጣሪዬን ኃይሉን ታውቅ ዘንድ አሳይሃለሁ። ይህንንም ብሎ የተቆረጠች የቀኝ እጁን በግራ እጁ አንሥቶ ከተቆረጠችበት ቦታዋ ላይ አገናኝቶ እንደ ቀድሞዋ ደኅነኛ አደረጋት።

በኋላ ለያት በዚያም የነበሩ አደነቁ የሠራዊት አለቃውና ሚስቱ ብዙዎችም ሰዎች ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ቁጥራቸውም አራት መቶ ሰባ ሰባት ነፍስ ሆነ ንጉሡም ከቅዱስ ሉቃስ ጋር ራሶቻቸውን እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጡአቸው የምስክርነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
ቅዱስ ያሬድ በድጓው

‹‹ኀበሩ ቃለ ወንጌላውያን ሉቃስ ባሕቲቱ ተናገረ ወእስከ አዳም አልዓለ በስብከተ ቃሎሙ አድመፁ ውስተ ኵሉ ዓለም።

ወንጌላውያን በቃል ተባበሩ፤ በዓለሙ ሁሉ ላይ በቃላቸው ስብከትን አሰሙ፤ ሉቃስ ብቻውን እስከ አዳም አረዘመ ከፍ ከፍ አለ።>> በማለት ተናግሯል

@efeson_2

🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለእስክንድርያ_አገር_ኀምሳ_ሁለተኛ #ሊቀ_ጳጳሳት_ለአባ_ዮሴፍ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ፣ በዐላውያን ነገሥታት በዲዮቅልጥያኖስና በመክስምያኖስ ዘመን በሰማዕትነት ለተቀበለ #ለቆሮንቶስ_አገር_ኤጺስቆጶስ_ለቅዱስ_ዲዮናስዮስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓልና ለከሀዲ ንጉሥ ለዱድያኖስ ለሚስት #ለቅድስት_እለእስክንድርያ መታሰቢያዋ በዓልና በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_ኢላርዮስ_ከጣንቅያቅ#ከቴዎደስዮስ_ከቴዎላስ_ከዮሳብና_ከገድላ ከሰማዕት እስክድርያም ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
🍂🌿

ወንድምህን አትናቀው

ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ በፍጹም ወንድምህን አትናቀው። እህትህን አትናቃት። ምንም ይሁን ምን ሰው አትናቅ። ይህ የምትንቀው ወንድም በተለይ ክርስቲያን ከሆነ ክርስቶስን እየሰደብከዉ እንደሆን አስተውል።

"እንዴት?"  ያልከኝ እንደሆንም ይህ የምትንቀው ወንድምህ የከደርስቶስ ሕዋስ (ብልት) ኾኗል። የክርስቶስ ሕዋስ ከኾነ ደግሞ እሱን ናቅኸው ማለት ክርቶስን ናቅኸው ማለት ነው።

ወንድምህን የምትንቅ ከሆነም በጲላጦስ አደባባይ ጌታን ከገረፉት፣ እራቁቱን ከሰቀሉት፣ ሐሞትንና ከርቤን ቀላቅለው ከሰጡት፣ በፊቱ ላይም ከተፉበት ሰዎች በምንም አትተናነስም። ስለዘህ ወንድምህን ከመናቅ ተጠንቀቅ።

📝ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@efeson_2

🍂🌿

ጥቅምት ፳፬ /24/


‎በዚች ቀን መስተጋድል መነኰስ አባ አብላርዮስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ጋዛ  ከሚባል አገር ነው። ወላጆቹም አረማውያን ናቸው የዮናናውያንንም ትምህርታቸውንና ፍልስፍናቸውን አስተማሩት ሰውነቱ ለጥበብ ማደሪያዋ እስከሆነ ድረስ በዕውቀቱ ከጓደኞቹ በላይ ሆነ።

‎ ከዚህም በኋላ ለጥበብ ትምህርት ወደ  እስክንድርያ ሔዶ በዛው የክርስትናን ተምሮ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ወደ አባ እንጦንዮስም ሔዶ መንፈሳዊ የሆነ ጥምቀት ተጠመቀ ከዚያም መንኵሶ የትሩፋትን ሥራ እየተማረ በእርሱ ዘንድ ብዙ ወራት ኖረ።

‎ወላጆቹም እንደሞቱ በሰማ ጊዜ ሒዶ የተዉለትን ገንዘባቸውን ሁሉንም ወስዶ ለድኆችና ለችግረኞች መጸወተ ከዚህም በኋላ ከሶርያ ገዳማት ወደ አንዱ ገዳም ገባ በዚያም በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት በመትጋት ፍጹም ገድልን ተጋድለ በየሰባት ቀን እስቲመገብ ድረስ ምግቡም የዱር ሣር ነበር።

‎እግዚአብሔርም ሀብተ ትንቢትን ሰጥቶት ልቡናው ብሩህ  ሆነ  ድንቆች ተአምራትንም  የሚያደርግ ሆነ ኤጲፋንዮስንም ያመነኰሰውና ለደሴተ ቆጵሮስም ኤጲስቆጶስ እንደሚሆን ትንቢት የተናገረለት እርሱ ነው።

‎የዚህም አባት መላ ዕድሜው ሰማንያ ዓመት ነው፡ከክርስትናውና ከምንኵስናው በፊት ዐሥራ ሰባት ዓመት በምንኵስናም ስልሳ ሦስት ዓመት ነው።ክብር ይግባውና እግዚአብሔርንም ካገለገለ በኋላ በሰላም አረፈ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
‎ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳ #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ነድያንን ለሚወዱ #ለአቡነ_ብርሃነ_መስቀል (አብርሃም) በሚያደርጉት ድንቅ ድንቅ ተአምራት #አባ_ዘግሩም ለተባሉት ሙሴ ጽላትን እንደተቀበለ ሁሉ #የእግዚአብሔር_መልአክ ከሰማይ አመጥቶ የብርሃን መስቀልና #የመድኃኔዓለምን_ታቦት_ለተሰጡበት_መታሰቢያ_በዓል በሰላም አደረሰን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
‎ጥቅምት ፳፭/25/


‎በዚች ቀን ታላቅና ክቡር  የሆነ አቢብ የተባለ መስተጋድል አባ ቡላ አረፈ።

‎የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አብርሃም  የእናቱም ስም ሐሪክ ነው። እነርሱም ልጅ በአጡ ጊዜ የተባረከ ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ በጾም በጸሎት ተወስነው ወደ እግዚአብሔር ለመኑ የእግዚአብሔርም መልአክ በሕልም ተገለጠላቸውና ፍሬ የመላበትን ዘለላ ሰጣቸው።

‎ይህም ቅዱስ በተፀነሰ ጊዜ በቤታቸው አጠገብ ታላቅ ዛፍ በቀለ በቅጠሉም ላይ በሮማይስጥ ቋንቋ ቡላ የእግዚአብሔር አገልጋይ በጽዮንም አድሮ የሚኖር የያዕቆብ ፈጣሪ ያከበረው የሚል ጽሑፍ ነበረበት።

‎በተወለደም ጊዜ ክርስትና ሳያስነሡ ዓመት ሙሉ አኖሩት እመቤታችን ማርያምም ለሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ለሰለባስትርዮስ ተገልጣ ወደ አብርሃም ቤት ሒዶ ሕፃኑን እንዲአጠምቀው አዘዘችው።

አጠመቀው ስሙንም ቡላ ብሎ ሰየመው ሕፃኑም ገና ዐሥር ዓመት በሆነው ጊዜ ከሀዲ መኮንን ተነስቶ በብዙ አሰቃየው የመላእክት አለቃ ሚካኤልም መጥቶ አዳነው ያለ ጉዳትም ጤነኛ አደረገው።

‎ዕድሜውንም ፈጽሞ ከዚሀ ዓለም የሚወጣበት ጊዜ ሲደርስ ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስ በእጁ ልዩ የሆኑ አክሊሎችን የሚያበሩ ልብሶችንም ይዞ ተገለጠለትና እስከ ዐሥር ትውልድ የሚያስምር ቃልኪዳን ተቀበለ። ይህንም ብሎ  በደረቱም ላይ አድርጎ ወደ አየር አወጣው ፡ ፡ የመላእክትንም ምስጋና በሰማች  ጊዜ ነፍሱ  ከሥጋው ተለየች ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ገባች።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
‎ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
🔥1
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴
እንኳን #ጌታችን_ከመረጣቸውናና በሽተኞችን ሁሉ ይፈውሱ ዘንድ አጋንንትንም ያወጡ ዘንድ ሥልጣን ከሰጣቸው #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእትና_ከሰባቱ_ዲያቆናት አንዱ ለሆነው #ለቅዱስ_ለሐዋርያው_ቅዱስ_ጢሞና ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና #ለጌታችን_ወንድም ለተባለው #ለሐዋርያው_ለቅዱስ_ያዕቆብ ለመታሰቢያ በዓሉ በሰላም አደረሰን፡፡ በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከፊልጶስና ከሰማዕት አግናጥዮስ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
🤲🤲🤲
ሰው የሆነና በእኛ ያደረ ቃል ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በአባቱም ዘንድ ፥ ያለ'ውን እንደ_አንድ ልጅ ፥ ያለ' ክብሩን አየን። ይቅር ይለንም ዘንድ ወደደ።
◈◈◈◈◈ ◊ ◈◈◈ ◊ ◈◈◈◈◈
በሦስት_ወገን (በሥጋና በነፍስ ፣ በሕሊናም) ፥ ድንግል የሆንሽ ፣ በቅድስናም ያጌጥሽ ፥ እመቤታችን ሆይ ፥ ይቅር ይለን ዘንድ የወደደ ልጅሽ ፥ ጸጋውን እና ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን። ቅዱሱን እውቀትና ጥበብም ፥ ሳዪብን ፣ አሳድሪብን።
🤲🤲🤲
⨳የሰኞ_ውዳሴ_ማርያም ፥ ማር ኤፍሬም ሶርያዊ
◈◈◈◈◈ ◊ ◈◈◈ ◊ ◈◈◈◈◈
🕯የእግዚአብሔር ወልድ ቸርነት ይብዛልን 🕯
🤲🤲🤲
🥰3
2
‎ኅዳር ፲ /10/


‎በዚች ቀን ቅዱሳት ንጹሐት መነኰሳይያት ደናግል እናታቸው ሶፍያም በሰማዕትነት አረፉ።

እኚህም ቅዱሳት ከተለያዩ አገሮችና ቦታዎች ሲሆኑ መለኮታዊ ፍቅርበአንድነት ሰበሰባቸው የምንኲስናንም ልብስ ለበሱ ይኸውም የመላእክት ልብስ ነው። በሮሜ አገር ከአሉ ገዳማትም በአንዱ የሚኖሩ ሆኑ ቅድስት ሶፍያም በእነርሱ ላይ እመ ምኔት ሆነች።

‎እርሷም ጸጋንና ዕውቀትን የተመላች ናት የቅዱሳን መነኰሳትን ገድል በማንበብ እየጾሙ እየጸለዩ በምድር ላይ እንደ መላእክት እስከ ሆኑ ድረስ መንፈሳዊ ዕድገትን አሳደገቻቸው ከእነርሱም በአንድ ገዳም ውስጥ ሰባ ዓመት ያህል የኖሩ አሉ ከውስጣቸውም ልጅ እግሮች የሆኑ አሉ።

‎ከሀዲ ንጉሥ ዑልያኖስም ከፋርስ ንጉሥ ከሳቦር ጋር ሊዋጋ በሮሀ ሀገር በኩል በሚያልፍ ጊዜ እርሱ ሳቦር ሊወጋው ወደርሱ እንደሚመጣ ሰምቷልና አልፎ ሲሔድም በውስጡ እሊህ ደናግል ያሉበትን ገዳም አይቶ ይህ ምንድን ነው ብሎ ጠየቀ ሰዎችም ይህ የደናግሎች ገዳም ነው አሉት።

‎በዚያንም ጊዜ ወደዚያ ገዳም ገብተው ደናግሎችን እንዲገድሏቸው በገዳሙ ውስጥም ያለ ገንዘባቸውን ሁሉ እንዲዘርፉ ወታደሮቹን አዘዘ ወታደሮችም ገብተው እሊያን ደናግል በሰይፍ ገደሏቸው ገዳሙንም አጠፉ የገዳሙን ገንዘብ ሁሉንም ዘረፉ።

‎ከሀዲውን ንጉሥ ግን ስለ መንጋዎቹ በቀል እግዚአብሔር ተበቀለው ይህም እንዲህ ነው ያጠፋው ዘንድ ሰማዕት መርቆሬዎስን አዘዘው መርቆሬዎስም በአካለ ነፍስ ሒዶ በጦር ወጋውና በክፉ አሟሟት ሙቶ ወደ ዘላለም ሥቃይ ሔደ። እሊህ ቅዱሳት ደናግል ግን ወደ ዘላለም ተድላ ደስታ ገቡ።

‎ወስብሐት ለእግዚአብሔር

@efeson_2

🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
🔥1
Forwarded from ነይ ነይ እምዬ ማርያም መዝሙሮች (𝕻𝖎𝖑𝖚𝕻ΔDΣR)
የኦርቶዶክስ ቻናል ስብስብ ላይ wave ማሰራት የምትፈልጉ DM @Pilupadier

2k በላይ ቻናል ያላቹ ብቻ
#ኅዳር_11

#ቅድስት_ሐና

ኅዳር ዐሥራ አንድ በዚች ዕለት አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እናቷ የሆነች የተመሰገነች የቅድስት ሐና የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው።

ይችም ቅድስት ከኢየሩሳሌም አገር ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ትውልድ የሌዊ የሜልኪ ልጅ ለሆነ ለማጣት ልጁ ናት። ለማጣትም ሦስት ሴቶች ልጆች አሉት የታላቂቱም ስሟ ማርያም ናት ሁለተኛዋም ስሟ ሶፍያ ሦስተኛዪቱም ስሟ ሐና ናት ታላቂቱ ማርያምም ለባል ተድራ አዋላጅ የሆነች ሰሎሜን ወለደቻት እርሷም መድኃኒታችንን ከወለደችበት ጊዜ ጀምሮ በስደቷም ወራት ከአረጋዊ ዮሴፍ ጋር እመቤታችንን ድንግል ማርያምን ያገለገለቻት ናት።

ሶፍያም ለባል ተድራ ለመጥመቁ ዮሐንስ እናቱ የሆነች ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደቻት። ይችንም ቅድስት ሐናን ከይሁዳ ነገድ ለሆነ ጻድቅ ስሙ ኢያቄም ለሚባል አጋቧትና እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወለደቻት እሊህም ሰሎሜና ኤልሳቤጥ ለቅድስት ሐና የእኅትማማች ልጆች ናቸው።

የዚችንም የቅድስት ሐናን በሥውር የምትሠራውን ገድሏንና ትሩፋቷን እንዳናስታውሰው አናውቀውም ግን ከሴቶች ሁሉ እንደምትበልጥና እንደምትከብር እናውቃለን እንረዳለን እርሷ አምላክን በሥጋ ለወለደችው ወላጅዋ ትሆን ዘንድ የተገባት ሁናለችና ከሴቶች ሁሉ የሚበልጥና የሚበዛ ትሩፋትና ተጋድሎ ባይኖራት ይህ ታላቅ ጸጋ ባልተገባት ነበር።

ይህችም ጻድቅት ሐና መካን በመሆንዋ ልጅን ይሰጣት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር በጸሎት ትማልድ ነበር እግዚአብሔርም በእርሷ ለዓለም ሁሉ ድኅነት የተደረገባትን ይቺን የተባረከችና የከበረች ልጅን ሰጣት እርሷም አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት።

ስለዚህም ይህን ታላቅ ጸጋ ስለሰጣት የበዓሏን መታሰቢያ በደስታ ልናከብር ይገባናል።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በጸሎቷ የሚገኝ በረከቷም ከእኛ ጋር ይሁን ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር)

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
1🙏1
🌹እንኳን መላእክት አለቃ 🌹
ቅዱስ ሚካኤል
🌸ዓመታዊ በዐል አደረሳችሁ🌸

👇👇👇👇👇
@efeson_2 @efeson_2
3