ኤፌሶን~፩
651 subscribers
75 photos
1 video
23 links
Download Telegram
🌿🌿🌿🌿🌿🌿
እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ አጽፋቸውን እንደጀልባ ተጠቅመው የኢያሪኮን ባሕር ለተሻገሩት ለታላቁ ጻድቅ የአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ከፋሌ ባሕር ደቀ መዝሙር ለሆኑ #በኤራትራና_በኢትዮጵያ_ገዳም ለመሰረቱ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_አቡሳዲ_ለዕረፍታቸው በዓልና #ከተሰዓቱ_ቅዱሳን አንዱ ለሆኑት #ለአቡነ_ይስሐቅ_ተአምር_ሰረተው #አቡነ_ገሪማ ተብለው እንዳጠሩ ላተረጉበት ቀን መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን።

@efeson_2

🌿🌿🌿🌿🌿
🔥2
"ዲያብሎስን የሚያስጨንቀው በወደቁት ሳይሆን ለመነሳት በሚታገሉት ነው"

(ምክረ አበው)

@efeson_2

🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋
ጥቅምት ፩ /1/

በዚህችም ቀን በጥቅምት አንድ ቅድስት አንስጣሲያ በሰማዕትነት አረፈች።

ይህችም ቅድስት መስተጋድልት ከሮሜ አገር ናት ወላጆቿም ክርስቲያኖች ናቸው ጠቃሚ የሆነ ትምህርትን በማስተማር ክብር ባለው በመልካም ሥርአት አሳደጓት። በአደገችም ጊዜ ወላጆቿ ሊያጋቡአት ፈለጉ እርሷ ግን በሥውር  በሮሜ ከሚገኙ  ወደ አንዱ ገዳማት ሂዳ የምንኩስና ልብስን በመልበስ በጾም በጸሎት በረኃብ በጽምዕ በመጠመድ ሥጋዋን አደከመች በቀኑ ርዝመት ትጾማለች በየሁለት ቀኖችም ታከፍላለች በጌታችን ጾም ግን ያለ ሰንበታት ቀን አትመገብም።

ከዚሕም በኋላ የንጉስ ዳኬዎስ ወታደሮች ክርስቲያኖችን አሥረው በቁጣ ሲጎትቷቸው አይታ ልቧ በሃይማኖቷ ፍቅር ነደደና እንዲህ ብላ ዘለፈቻቸው የእውነት ፈጣሪን የካዳቹ ልባቹ የደነዘዘ እግዚአብሔር በመልኩና በአምሳሉ በፈጠራቸውና ስለ እነርሱም ነፍሱን አሳልፎ በሰጣቸው ላይ ለምን እንዲህ ትሠራላቹ።

ወታደሮቹም ይሕን ሲሰሙ ተቆጡ ይዘውም ወደ መኮንኑ አቀረቧት እርሱም እንዲህ ብሎ ጠየቃት በእውነት አንቺ የተሰቀለውን የምታመልኪው ክርስቲያን ነሽን እርሷም ስለእኛ የተሰቀለውን ክብር ይግባውና እርሱን አመልከዋለው ብላ መለሰችለት። በዚያን ጊዜ ጽኑ ሥቃይን አሠቃያት በሥጋዋም እሳትን ጨመረ  ከዛም ዘቅዝቆ ሰቀላት ከበታቿም አጤሱባት ከሃይማኖቷም ባልተናወጸች ጊዜ ራሷን በሰይፍ ቆረጧት። በመንግስተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለች።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
🔥1
🌿🌿🌿🌿🌿🌿

እንኳን #የእመቤታችን_የቅድስት_ድንግል #ማርያም_ቅዳሴ_ለደረሰው ለብህንሳ አገር ኤጲስቆዾስ ለታላቁ አባት #ለአባ_ሕርያቆስ_ለልደትና ለዕረፍት በዓል፣ ለአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት #ለቅዱስ_አቡነ_ሳዊሮስ_ወደ_ግብጽ_አገር_ተሰዶ ለመጣ መታሰቢያ ቀን በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #ከሰማዕቱ_ከቅዱስ_ቴክላ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🌿🌿🌿🌿🌿🌿
     

ጥቅምት ፭ /5/


‎አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (ገብረ ሕይወት)

‎ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ::

‎አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ562 ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ እህል ያልቀመሱ ልብስ ያልለበሱ ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ አባት ናቸው።

‎የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ስለ ሀገራችን ፍቅር ሲሉ ለ100 ዓመታት በደብረ ዝቋላ መከራን ተቀብለዋል። ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው።

‎በ8ኛው ክ.ዘ አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ.ዘ አካባቢ ነው። ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት 5 ቀን ሲያርፉ ግሩማን መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል።

‎ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍቱ መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ የመጋቢት 27 ስቅለት ጥቅምት 27 ቀን እንደሚከበረው ሁሉ ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር ተደረገ፡፡

‎የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

@efeson_2

🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉
🥰1
‎ ጥቅምት ፮ /6/


‎በዚህች ቀን የታላቁ ነቢይና ካህን የሳሙኤል እናት ቅድስት ነቢይት ሐና አረፈች።

‎ይችም ቅድስት ከሌዊ ነገድ ናት የታኅርም ልጅ ሕልቃና አገባት ፍናና የምትባልም ሌላ ሚስት አለችው እርሷም ወላድ በመሆኗ ሐና ልጅ ስለሌላት መካንም ስለሆነች ሁልጊዜ ትገዳደራት ነበር። በዚህም አቤቱ ልጅ የሰጠኸኝ እንደሆነ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለአንተ የሚያገለግል አደርገዋለሁ ብላ ተሳለች።

‎ካህኑ ኤሊም ስትጸልይ ሰምቶ እንዲህ ብሎ ባረካት የእስራኤል ፈጣሪ የለመንሽውን ይስጥሽ በሰላም ሒጂ በቃሉም አምና ወደ ቤቷ ገባች።

‎ከዚህም በኋላ ፀንሳ ወንድ ልጅን ወለደች ስሙንም ሳሙኤል ብላ ጠራችው። ጡትንም በአስጣለችው ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት ይዛው ወጣች ወደ ካህን ኤሊም አቀረበችውና እንዲህ ብላ አስረዳችው ከአሁን በፊት ልጅን ይሰጠኝ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ስጸልይና ስለምን ያየኸኝ ሴት ነኝ ልመናዬንም ሰምቶ ይህን ልጅ ሰጠኝ አሁንም በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለእግዚአብሔር አገልጋይ ይሆን ዘንድ አመጣሁት ።

‎ከዚህም በኋላ ሐና እግዚአብሔርን አመሰገነችው። ልቤ በእግዚአብሔርአምኖ ጸና የሚለውን ጸሎትና ትንቢት እስከ መጨረሻው ተናገረች ። ይቺም በዳዊት መዝሙር መጨረሻ ከሙሴ መኀልይ ቀጥላ ተጽፋለች። ከዚህም በኋላ እግዚአብሔርን አገልግላ በሰላም አረፈች።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

@efeson_2

🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
‎ጥቅምት ፯ /7/


‎በዚች ዕለት ጠመው ከሚባል አገር የሆነ የከበረ አባት አባ ባውላ አረፈ።

‎ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ መስተጋድል መነኲሴ ሆነ የሚኖረውም በላይኛው ግብጽ በአለ በእንጽና ገዳም ነው ስሙ ሕዝቅኤል የሚባል ረድእ አለው። እርሱም ስለ ትሩፋቱና ስለ ተጋድሎው ምስክር ሆነ ይህ አባ ባውላ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ራሱን ሰባት ጊዜ ገድሏልና።

‎ክብር ይግባውና ጌታችንም አስነሣው እንዲህም ብሎ አጽናናው ወዳጄ ባውላ ሆይ ራስህን ሰባት ጊዜ እስከምትገድል ድረስ ሰውነትህን አደከምክ እንግዲህ ድካምህ ይብቃህ።

‎አባ ባውላም ለመድኃኒታችን እንዲህ ብሎ መለሰለት ጌታዬ ሆይ ስለ ከበረው ስምህ እደክም ዘንድ ተወኝ አንተ አምላክ ስትሆን ስለኛ በመከራ ደክመህ ስለ ሰው ወገን ሞትክ ለእኛ ይህ አይገባንም ነበር በቸርነትህ ይህን የማዳንህን ሥራ ሠራህልን እንጂ። ጌታችንም ከአጽናናው በኋላ ከእርሱ ወደ ሰማይ ወጣ።

‎ከዚህም በኋላ አባ ብሶይ ወደ እንጽና ገዳም ሒዶ ከአባ ባውላ ጋር ተገናኘ ጌታችንም ለአባ ባውላ ተገልጾለት ሥጋህ ከአባ ብሶይ ሥጋ ጋር በአንድነት ይኑር አለው ሁለቱም በአረፉ ጊዜ ሥጋቸውን በአንድነት አኖሩ።

‎ወገኖቹም የአባ ብሶይን ሥጋ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሊወስዱ በወደዱ ጊዜ በመርከብ ጫኑት መርከቢቱ ግን መንቀሳቀስን እምቢ አለች። ከዚህም በኋላ ተመልሰው የአባ ባውላን ሥጋ አምጥተው በመርከብ ላይ ጫኑት ያን ጊዜ መርከቢቱ ተጓዘች። እንዲህም የቅዱሳኑን ሥጋቸውን ወደ አስቄጥስ ገዳም አድርሰው በአባ ብሶይ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአንድነት አኖሩ እስከ ዛሬም በዚያ ይኖራሉ።

‎ወስብሐት ለእግዚአብሔር
‎ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
‎ጥቅምት ፲ /10/


‎በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሰባተኛ የሆነ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት አውማንዮስ አረፈ ።

‎ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ ንጹሕ ትሑት የሆነ ለዕውነተኛ ሥራ ሁሉ የሚያገለግል ነበር ቅዱስ አብርምዮስም ትሩፋቱን አይቶ ዲቁና ሾመው በዲቁና አገልግሎትም ዐሥር ዓመት ኖረ ።

‎ዮስጦስም ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ ትሩፋቱንና የሃይማኖቱን ቅንነት ተመለከተ ምእመናንንም ማስተማር እንደሚችል አውቆ ቅስና ሾመው ። ከዚህም በኋላ ቅዱስ ዮስጦስ በአረፈ ጊዜ ይህን አባት አውማንዮስን መርጠው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት የአብያተ ክርስቲያናትንም ሥራ ሁሉ ተረከበ ።

‎መናፍቃንንም ተከራክሮ የሚረታቸው ሆነ ብዙዎችንም ከስሕተታቸው መለሳቸው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመለኮቱ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል እንደሆነ ግልጽ አድርጎ አስተማራቸው ። በሹመቱም ዐሥራ ሦስት ዓመት ከኖረ በኋላ በአንስጣዮስ ሰባተኛ ዘመነ መንግሥት በዚች ቀን አረፈ ። በዘመኑም የሶፍያ ሦስቱ ልጆቿ በሰማዕትነት አረፉ ።

‎ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
‎ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
ጥቅምት ፲፪ /12/


‎አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥቅምት ዐሥራ ሁለት በዚች ዕለት የመላእክት አለቃ የከበረ መልአክ የሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።

በዚችም ቀን ወደ ነቢይ ሳሙኤል እግዚአብሔር ልኮታልና የዳዊት አባት ወደሆነ በቤተ ልሔም ወደሚኖርወደእሴይ ቤት ይሔድ ዘንድ በቂስ ልጅ በሳኦልም ፈንታ ለእስራኤል ልጆች እንዲነግሥ ልጁ ዳዊትን ይቀባው ዘንድ አዘዘው።

‎ሳሙኤልም ወደ እሴይ ቤት ሔዶ ልጆችህን ሁሉንም አቅርብልኝ ብለው እሴይም ከዳዊት በቀር ሁሉንም አቀረባቸው እርሱ በእርሻ ውስጥ በጎችን ይጠብቅ ነበርና።

‎ሳሙኤልም የመንግሥት ቅባት ያለበትን ብልቃጥ በራሳቸው ላይ ከፍ ከፍ በአደረገ ጊዜ እግዚአብሔር አልመረጣቸውም። ሳሙኤልም እሴይን ልጆችህ እነዚህ ብቻ ናቸውን አለው ዕሴይም በጎች የሚጠብቅ አንድ ትንሽ ልጅ አለ አለው።

‎ሳሙኤልም ደግሞ ዕሴይን እሱ ሳይመጣ ምሳ አልበላምና ልከህ አስመጣው አለው ። እሱም ልኮ አስመጣው መልኩም ቀይ ዐይኖቹም የተዋቡ አርአያውም ያማረ ነው እግዚአብሔርም ሳሙኤልን ይህ ይበልጣቸዋልና ተነሥተህ ቅባው አለው። በዚያንም ጊዜ ሳሙኤል የመንግሥት ቅባት ያለበትን ቀንድ አምጥቶ በወንድሞቹ መካከል ቀባው ከዚያችም ቀን ጀምሮ ለሁል ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በዳዊት ላይአደረበት በእስራኤል ልጆችም ላይ ነገሠ።

‎ደግሞ ሁለተኛ በዚች ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ሚካኤልን ወደ ዳዊት ላከው ረዓይታይ ጎልያድን እስኪገድለውና የእስራኤልን ልጆች እስከሚያድናቸው ረድቶ ኃይልን ሰጠው።

‎ወስብሐት ለእግዚአብሔር
‎ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
◈◈◈◈◈◈  ስለ አንተ  ▣▣▣▣▣▣▣
▣▣▣▣▣▣  📜🌷📜  ◈◈◈◈◈◈◈
ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ። ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም ፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም። በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ ፥ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልናእግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል ፣ በእጆቻቸው ያነሡሃል። በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ። በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁይጠራኛል እመልስለትማለሁ ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁአድነዋለሁ አከብረውማለሁ።
ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ
ማዳኔንም አሳየዋለሁ
◈◈◈◈◈   🤲🤲🤲    ▣▣▣▣▣▣▣
➥             መዝ.91፥9-16
▣▣▣▣▣    📖 📖📖    ◈◈◈◈◈◈◈
🥰3
‎ጥቅምት ፲፬ /14/

‎በዚችም ቀን የታላቁና የከበረው አባታችን አረጋዊ ዘሚካኤል መታሰቢያው ነው። ይህም ቅዱስ ከእርሱ ጋር ዘጠኝ የሆኑትን ቅዱሳን የእግዚአብሔር አገልጋዮችን ወደ ኢትዮጵያ አገር እስከ አደረሳቸው ድረስ በመንገድ የመራቸው እርሱ ነው።

‎እርሱም የዘንዶ ጅራት በመያዝ ከደብረ ዳሞ ተራራ ላይ ወጣ በዚያም ፍጹም የሆነ ተጋድሎውን ፈጸመ ክብር ይግባውና ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውንም ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ተቀበለ።

‎ከመምህሩ ከአባ ጳኵሚስ ዘንድ እንደተማረ ለልጆቹ መነኰሳት ሥርዓተ ማኅበርን ሠራላቸው። ከዚህም በኋላ በእግዚአብሔር ቸርነት እንደ ኄኖክና እንደ ኤልያስ ከሞት ገጽ ተሠወረ።

‎ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
‎ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
1

ጥቅምት ፲፮ /16/


‎በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ ዘጠነኛ የሆነ ቅዱስ አባት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ያቃቱ አረፈ ።

‎ከርሱ በፊት የነበረ አባ ብንያሚን በአረፈ ጊዜ ይህን አባት መርጠው በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት በዘመኑም ብዙ ችግር ደርሶበታል ስሙ ቴዎዶስዮስ የሚባል አንድ መለካዊ ሰው ነበረ እርሱም ወደ ደማስቆ ንጉሥ ወደ ዘይድ ሒዶ ብዙ እጅ መንሻ ሰጥቶ ለእስክንድርያ አገረ ገዥ ሁኖ ተሾመ ። ይህንንም አባት አባ ያቃቱን ሊአስጨንቀው ጀመረ በየዓመቱ ግብርሰባት ሺህ የወርቅ ዲናር ከእርሱ እስከተቀበለ ድረስ እግዚአብሔርም እስከ አጠፋው ድረስ ይህን አባት እንዲህ አሠቃየው ።

‎በዘመኑም የብዙዎች ቅዱሳን አባቶች አባት የሆነ የአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን ሕንፃዋ ተፈጸመ ።

‎በአንዲት ሌሊትም ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ለዚህ አባት ተገለጸለት ፍዩም በሚባል አገር በአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግል ዮሐንስ የሚባል ጻድቅ ሰው መነኰስ እንዳለ ነገረው ። ሕዝብን በማስተማርና በመምከርም ይረዳው ዘንድ መልእክተኞችን ልኮ እንዲአስመጣውም አዘዘው ሁለተኛም ከእርሱ በኋላ ሊቀ ጳጳሳት እንደሚሆን ገለጠለት ።

‎በዚያንም ጊዜ መልእክተኞችን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ሥራውንም ሁሉ አስረከበው ይህንንም አባት ከብዙ ድካም የሚያሳርፈው ሆነ በሹመቱ ወንበርዐሥራ ዘጠኝ ዓመት ኑሮ ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈ ።

‎ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
🔥1
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴
እንኳን #ለሀገረ_ቀምስ_ኤጲስቆጶስ #ለቅዱስ_ፊልያስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ ለነቢዩ #ለቅዱስ_ሳሙኤል_እናት ለነቢይት #ለቅድስት_ሐና_ለልደቷ_መታሰቢያ_በዓል#ለቅዱስ_ባስልዮስ_ወንድም_ለቅዱስ_ጎርጎርዮስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓልና #ለእስክንድር_አገር_ሠላሳ_አንደኛ ሊቀ ጳጳሳት #ለቅዱስ_ዲዮስቆሮስ_ካልዕ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #በቆዳ_ገመድ_ከታሠሩ_ከደጋጋጎች ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
‎ጥቅምት ፲፯ /17/



በዚችም ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳ አንደኛ የሆነ የእስክንድርያ አገርሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ዲዮስቆሮስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።

‎ይህም አባት በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ መልእክትን ጽፎ ወደ አንጾኪያ ሊቀ ጳጰሳት ቅዱስ ሳዊሮስ ላካት ። እርሱም ስለ ምስጢረ ሥላሴ እና ስለ ምስጢረ ስጋዌ ጽፎ ላከለት።

‎መልእክቱም ወደ ቅዱስ አባት ሳዊሮስ በደረሰች ጊዜ አነበባትና ፈጽሞ ደስ ተሰኘባት ለአንጾኪያም ሕዝብ አስተማረባት ሁሉም ደስ አለቸው።

‎ከዚህም በኋላ አባ ሳዊሮስ ለአባ ዲዮስቆሮስ የመልእክቱን መልስ እንዲህ ብሎ ጻፈ ። በኒቅያ ከተማ ተሰብስበው ሃይማኖታቸው የቀና 318ቱ ቅዱሳን አባቶቻችን በቀናች ሃይማኖት አጽንተው የሠሩዋትን ቤተ ክርስቲያኑን እንድትጠብቅ ለዚች ለከበረች አገልግሎት የመረጠህ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ ። ዳግመኛም በዚሁ እንዲጸና ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ እንዳይል አስገነዘበው ደግሞም በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ ሕዝቡን ሁል ጊዜ አስተምራቸው አለው ።

‎የአባ ሳዊሮስም መልእክት ወደ አባ ዲዮስቆሮስ በደረሰች ጊዜ ደስ ተሰኘባት በሁሉ ቦታም እንዲአስተምሩባት አዘዘ ይህም አባት ሕዝቡን ሁል ጊዜ የሚያስተምራቸው ሆነ ። ሁል ጊዜም ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ ያስተምራቸዋል ኤጲስቆጶሳቱንና ካህናቱንም መንጋዎቻቸውን ስለ መጠበቅ ያዛቸዋል መልካም አገልግሎቱንም አድርሶ እግዚአብሔርንም ደስ አሰኝቶ አረፈ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
‎ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
🔥1
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴
እንኳን #ለእስክድርያ_ሃያ_ሦስተኛ_ሊቀ_ጳጳስ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ቴዎፍሎስና ክርስቲያኖችን በአሳደደ በመኰንን አስቅልጵያኖስ ዘመን በሰማዕትነት ለዐረፈ ለከበረ #ለመነኰስ_ቅዱስ_ሮማኖስ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከሰማዕት_ቅዱስ_ዮሐንስ#ከቅዱሳን_አድራኒ_ከአርቴማዎስ_ከአርስጦስ #ከሉዲኖስ_ከአስማኒትና
_ከሰባቱ ልጆቿ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
ጥቅምት ፲፰ /18/


‎በዚህች ቀን ክርስቲያኖችን በአሳደደ በመኰንን አስቅልጵያኖስ ዘመን የከበረ መነኰስ ሮማኖስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ የክርስቲያን ወገኖችን መኰንኑ እንዳሳደዳቸው በሰማ ጊዜ ከቀሳውስትና ከዲያቆናት ጋር የክርስቲያን ወገኖችን ሁሉ በአንድነት ሰበሰባቸው ስለ ክርስቶስ ሃይማኖትም መክሮ አጸናቸው።

‎አስቅልጵያኖስም ይህን ሰምቶ እንዲአመጡት አዘዘ በፊቱም በቆመ ጊዜ አስቅልጵያኖስ በወገን የከበርክ ሮማኖስ አንተ ነህን አለው ቅዱሱም የወገን ክብር ምን ይጠቅመኛል ክብሬ ግን ክርስቶስ ነው ብሎ መለሰለት። መኰንኑም ሰምቶ እንዲሰቅሉትና ጉንጮቹን ይሰነጣጥቁ ዘንድ አዘዘ ጉንጮቹንም ሲሰነጣጥቁት ምንም አልተናገረምና መኰንኑ ትዕግሥቱን አደነቀ።

‎በዚያንም ጊዜ ሮማኖስ መኰንኑን እንዲህ አለው እነሆ ስንፍናህን እዘልፍ ዘንድ ፈጣሪዬ አፌን ከፈተ በዚያንም ጊዜ የሕፃኑን ራስ በሰይፍ እንዲቆርጡ የቅዱስ ሮማኖስንም ምላሱን ከግንዱ እንዲቆርጡ መኰንኑ አዘዘ። ያን ጊዜ መኰንኑን ይዘልፍ ዘንድ ለአባ ሮማኖስ ረቂቅ አንደበት ተሰጠው ሲዘልፈውም መኰንኑ ሰምቶ ምላሱ እንዳልተቆረጠ ተጠራጠረ።

ወታደሩንም ጠርቶ ምላሱን ያልቆረጥክ ለምንድን ነው አለው ወታደሩም የምላሱን ቁራጭ ያመጡ ዘንድ እዘዝ አለው አምጥተውለትም አይቶ መኰንኑም ወደ ወህኒ ቤት አስገብተው በዚያ አንቀው እንዲገድሉት አዘዘ። እንዲህም ምስክርነቱን ፈጽሞ የምስክርነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።

‎የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
‎ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለታላቁ_ለትሕትናና_ለትዕግስተኛው አባት ለክቡሩ፤ ለገናና ለሆነ #ለአባ_ዮሐንስ_ሐጺር_ለዕረፍት በዓልና የስሙ ትርጓሜ ጠባቂና አዳኝ ለሆነ #ለታላቁ_ነቢይ_ለቅዱስ_ኤልሳዕ_ለልደቱ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት_አንዱ_ለሆነ ለብልሁና ለጥበበኛው #ለወንጌላዊው_ለሐዋርያው_ለቅዱስ_ሉቃስ በንጉሥ ኔሮን ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለየዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱስ_ሉቃስ_ጋር_በሰማዕትነት_ከዐረፋ_ከአራት°መቶ ሰባ ሰባት ሰዎች ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️
ጥቅምት ፳፪ /22/


በዚህች ቀን ብልህ ጥበበኛ የሆነ ቅዱስ ወንጌላዊ ሉቃስ በሰማዕትነት አረፈ።

ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስም ከተገደሉ በኋላ በሮሜ ሀገር የሚያስተምር ሆነ በቀናች ሃይማኖትም ይጸኑ ዘንድ ለምእመናን መልእክትን ይጽፍ ነበር። ጣዖት አምላኪዎች ከአይሁድ ጋር በመስማማት አንድ ግምባር ፈጠሩ በንጉሥ ኔሮን ፊት ቁመው ጮኹ ይህ ሉቃስ ብዙዎች ሰዎችን በሥራዩ ወደ ትምህርቱ አስገባቸው። ንጉሥ ኔሮንም ወደ ፍርድ አደባባይ ሉቃስን እንዲአቀርቡት አዘዘ።

በኔሮንም ፊት ቀርቦ በቆመ ጊዜ ንጉሡ በሥራይህ ሕዝቡን የምታስት እስከመቼ ነው አለው ቅዱስ ሉቃስም እኔ ለሕያው እግዚአብሔር ልጅ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያው ነኝ እንጂ ሥራየኛ አይደለሁም ብሎ መለሰለት።

ንጉሥ ኔሮንም እየጻፈች ሰዎችን የምታስት ይቺን እጅህን እኔ እቆርጣታለሁ ይህንንም ብሎ የቀኝ እጁን እንዲቆርጡ አዘዘ በቆረጡትም ጊዜ ንጉሥ ሆይ እኛ የዚህን ዓለም ሞት እንደማንፈራ እወቅ ነገር ግን የጌታዬንና የፈጣሪዬን ኃይሉን ታውቅ ዘንድ አሳይሃለሁ። ይህንንም ብሎ የተቆረጠች የቀኝ እጁን በግራ እጁ አንሥቶ ከተቆረጠችበት ቦታዋ ላይ አገናኝቶ እንደ ቀድሞዋ ደኅነኛ አደረጋት።

በኋላ ለያት በዚያም የነበሩ አደነቁ የሠራዊት አለቃውና ሚስቱ ብዙዎችም ሰዎች ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ቁጥራቸውም አራት መቶ ሰባ ሰባት ነፍስ ሆነ ንጉሡም ከቅዱስ ሉቃስ ጋር ራሶቻቸውን እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጡአቸው የምስክርነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
ቅዱስ ያሬድ በድጓው

‹‹ኀበሩ ቃለ ወንጌላውያን ሉቃስ ባሕቲቱ ተናገረ ወእስከ አዳም አልዓለ በስብከተ ቃሎሙ አድመፁ ውስተ ኵሉ ዓለም።

ወንጌላውያን በቃል ተባበሩ፤ በዓለሙ ሁሉ ላይ በቃላቸው ስብከትን አሰሙ፤ ሉቃስ ብቻውን እስከ አዳም አረዘመ ከፍ ከፍ አለ።>> በማለት ተናግሯል

@efeson_2

🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለእስክንድርያ_አገር_ኀምሳ_ሁለተኛ #ሊቀ_ጳጳሳት_ለአባ_ዮሴፍ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ፣ በዐላውያን ነገሥታት በዲዮቅልጥያኖስና በመክስምያኖስ ዘመን በሰማዕትነት ለተቀበለ #ለቆሮንቶስ_አገር_ኤጺስቆጶስ_ለቅዱስ_ዲዮናስዮስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓልና ለከሀዲ ንጉሥ ለዱድያኖስ ለሚስት #ለቅድስት_እለእስክንድርያ መታሰቢያዋ በዓልና በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_ኢላርዮስ_ከጣንቅያቅ#ከቴዎደስዮስ_ከቴዎላስ_ከዮሳብና_ከገድላ ከሰማዕት እስክድርያም ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️