Forwarded from ነይ ነይ እምዬ ማርያም መዝሙሮች (𝕻𝖎𝖑𝖚𝕻ΔDΣR)
ወርኀ ጽጌ🥰
“በምሥራቀ ፀሐይ የምትመሰየሚው፤ እንደ መብረቅ ኃያል የሆነውን ጌታን የወለድሽ፣ ረቂቅ ምሥጢርን የምትችዪ፤ እንደ ፊደል ባለ ብዙ ዘር [ሆሄያት] የሆንሽ፣ ወንጌልን የወለድሽ፥ ነበልባለ እሳትን [ክርስቶስን] የተሸከምሽ ፤ በጽጌ ረዳ አምሳል የምትመሰየሚው ቅድስት ማርያም ሆይ! የዓለሙን እንግዳ ፈጣሪን የወለድሽ፤ ከፍዳ ሞት የምታድኚ፤ የወይን ሐረግ የወይን ዐፀድ [ተክል] አንቺ ነሽ።”
ሀሳብ አስተያየት ካለ @kingo08bot

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇
@ney_ney_emye_maryam
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏
🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊
ሀሳብ አስተያየት ካለ @kingo08bot
❤1
✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿
እንኳን #አስቀድሞ_በማንም_ላይ_ርኅራኄ የሌለው (ንፉግ) ለነበረ፤ በሕልሙ እግዚአብሔር በሳየው ራእይ ተመልሶ ስለ ምጽዋት ሲል ያለው ንብረት በሙሉ ከሰጠ በኋላ እራሱ ለሸጠ ለቀራጭች አለቃ ለነበረ #ለቅዱስ_አንጢላርዮስ_ለዕረፍት_በዓል መታሰቢያ፣ #በሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ ትምህርት አምና ለተጠመቀች ያለ ደም መፍሰሰ ሰማዕት ለሆነች #ለቅድስት_ጤቅላ (ቴክላ) ለዕረፍቷ በዓል መታሰቢያ፣ #ለቅዱስ_ኤዎስጣቴዎስ_ለሁለት_ልጆቹና_ለሚስቱም ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከመድኃኒታችን ከስቅለቱ #ከመድኃኔዓለም ከወራዊ ከመታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
@efeson_2
✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨

መስከረም ፳፯ (27)
በዚህችም ቀን ያለ ደም ማፍሰስ ሰማዕት የሆነች ቅድስት ጤቅላ አረፈች።
የዚህች ቅድስት ወላጆቿ ከመቄዶንያ ሰዎች ውስጥ ባለጸጎች ናቸው እርሷንም እንደ ሀገራቸው ባህል በተግሣጽ በምክር አሳደጓት እነርሱ ጣዖትን የሚያመልኩ ናቸውና። ሐዋርያ ጳውሎስም ወደዚህች አገር በደረሰ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ አምስትን ሊአስተምር ጀመረ ዐውቀው ድኆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው መንግሥተ ሰማያት ለእነርሱ ናትና።
ይህንንና ይህን የመሰለውን በሰማች ጊዜ ያለ መብልና መጠጥ ሦስት ቀን ኖረች። ከዚህም በኋላ ወደ ቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስ ሔደች። እርሱም በደስታ ተቀብሎ የክርስቶስን ሃይማኖት አስተማራት።
በማግሥቱም እናቷ ከቅዱስ ጳውሎስ ዘንድ አብራ ተቀምጣ አገኘቻት ከዚያም ወደ መኰንን ሒዳ ልጇን ክርስቲያን እንደሆነች ከሰሰቻት። መኰንኑም ከቅዱስ ጳውሎስ ጋራ እንዲያመጧት አዘዘ አስቀድመው ቅዱስ ጳውሎስን ወደ እሳት እንዲወረውሩት አዘዘ እግዚአብሔርም አዳነው።
መኰንኑም ቅድስት ጤቅላን ወደ እሳት እንዲወረውሩዋት አዘዘ። በዚያን ጊዜ በክርስቶስ ማዕተብ ራሷን አማትባ ራስዋን በራስዋ ወደ እሳት ወረወረች ማንም ያያት ሳይኖር ከእሳት ውስጥ ወጥታ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሔደች የራስዋን ጠጒር ቆርጣ ወገቧንም ታጥቃ ቅዱስ ጳውሎስን ተከተለችው።
ከዚህም በኋላ መኰንኑ አንበሳና ድብ ከሚያድርበት ጨመራት እነርሱም ሰገዱላትና የእግሮቿን ትቢያ ላሱ። መኰንኑና ወገኖቹ ይህን አይተው በእግዙአብሔእ አመኑ ቅድስት ጤቅላም ቅዱስ ጳውሎስን አገልግላ በሰላም አረፈች።
በረከታቸው ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@efeson_2
🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋
መስከረም ፳፰ /28/
በዚች ቀን ቅድስት ሶስና አረፈች
ይህችውም ቅድስት የባዕለ ጸጋ ኢዮአቄም ሚስት የኾነች፣ የቅዱስ ሙሴን ሕግ የተማረችና ደጋግ የኾኑን አባትና እናቷም በመልካም ያሳደጓት፣ የኦሪትንም ሕግ ያስተማሯት አስተዋይ ቅድስት ናት።
በዚያም በባልዋ ቤት ብዙ እስራኤላውያን ይመጡ ነበርና የዚያም፡ቤት ቤተኛ ከኾኑት ኹለት የአይሁድ ረበናት ይገኙበታል። እኒህም ኹለት ግብዞች ደጋግመው ሶስናን አዩአት በዚህም ጸላኤ ሰናያት በልቡናቸው አደረና ዐይናቸው ኹሉ ግልብጥብጥ ብሎ በክፉ ሥራ ፈቀዷት።
አንድ እለት ከአትክልት ሥፍራ ዘግታ ስትታጠብ አገልጋዮቿን መልእክት ልካቸው እንደወጡ እኒህ ኹለት ክፉዎች ከተደበቁበት ወጥተው ፈቃዳችንን ፈጽሚ ካልፈጸምሽ ስታመነዝር ይዘናታል ብለን እንከስሻለን አሏት። እርሷም ከእጃቸው ማምለጥ አትችልምና ወደ ሰማይ አንጋጣ ቸሩን አምላክ በጽኑዕ ያድናት ዘንድ ተማጸነች።
እርሷም ፈቃዳቸውን ብፈጽምም ኾነ ባልፈጽም እሞታለሁ፣ ከፈጸምኹ ግን ከነርኲሰት ነውና የምሞተው ብላ አስባ እንደማትፈጽም ነገረቻቸው። ሦስቱም ሲጮኹ ሕዝብ ሲሰበሰብ ስታመነዝር አገኘናት አሉና ከሰሷት። እርሷም እንዲህ ያለ ነውር ተሰምቶባት አይታወቅምና ዘመዶቿ አፈሩ። በኋላም ለፍርድ በአደባባይ አቀረቧትና አየን ያሉትን ተናገሩ።
ሊወግሯትም ብለው ሲኼዱ ታላቁ ነብይ ቅዱስ ዳንኤል ቆይ እኔ ልመርምራቸው ብሎ አራርቆ ቢመረምራቸው አንዱ ከኮክ ዛፍ ሥር ነው ያየኋት፣ አንዱ ደግሞ ከሮማን ዛፍ ሥር ነው አለ። በዚህም ተለያይተዋልና ሕዝቡ እኒህን ኹለት ግብዝ ክፉ ሰዎች ገደሏቸው፣ ቅድስት ሶስናም በቸሩ አምላክ ታላቅ ነቢይ እርዳታ ዳነች።
በረከታቸው ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@efeson_2
🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋
❤1🔥1
🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿
እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ አጽፋቸውን እንደጀልባ ተጠቅመው የኢያሪኮን ባሕር ለተሻገሩት ለታላቁ ጻድቅ የአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ከፋሌ ባሕር ደቀ መዝሙር ለሆኑ #በኤራትራና_በኢትዮጵያ_ገዳም ለመሰረቱ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_አቡሳዲ_ለዕረፍታቸው በዓልና #ከተሰዓቱ_ቅዱሳን አንዱ ለሆኑት #ለአቡነ_ይስሐቅ_ተአምር_ሰረተው #አቡነ_ገሪማ ተብለው እንዳጠሩ ላተረጉበት ቀን መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን።

🔥2
ጥቅምት ፩ /1/
በዚህችም ቀን በጥቅምት አንድ ቅድስት አንስጣሲያ በሰማዕትነት አረፈች።
ይህችም ቅድስት መስተጋድልት ከሮሜ አገር ናት ወላጆቿም ክርስቲያኖች ናቸው ጠቃሚ የሆነ ትምህርትን በማስተማር ክብር ባለው በመልካም ሥርአት አሳደጓት። በአደገችም ጊዜ ወላጆቿ ሊያጋቡአት ፈለጉ እርሷ ግን በሥውር በሮሜ ከሚገኙ ወደ አንዱ ገዳማት ሂዳ የምንኩስና ልብስን በመልበስ በጾም በጸሎት በረኃብ በጽምዕ በመጠመድ ሥጋዋን አደከመች በቀኑ ርዝመት ትጾማለች በየሁለት ቀኖችም ታከፍላለች በጌታችን ጾም ግን ያለ ሰንበታት ቀን አትመገብም።
ከዚሕም በኋላ የንጉስ ዳኬዎስ ወታደሮች ክርስቲያኖችን አሥረው በቁጣ ሲጎትቷቸው አይታ ልቧ በሃይማኖቷ ፍቅር ነደደና እንዲህ ብላ ዘለፈቻቸው የእውነት ፈጣሪን የካዳቹ ልባቹ የደነዘዘ እግዚአብሔር በመልኩና በአምሳሉ በፈጠራቸውና ስለ እነርሱም ነፍሱን አሳልፎ በሰጣቸው ላይ ለምን እንዲህ ትሠራላቹ።
ወታደሮቹም ይሕን ሲሰሙ ተቆጡ ይዘውም ወደ መኮንኑ አቀረቧት እርሱም እንዲህ ብሎ ጠየቃት በእውነት አንቺ የተሰቀለውን የምታመልኪው ክርስቲያን ነሽን እርሷም ስለእኛ የተሰቀለውን ክብር ይግባውና እርሱን አመልከዋለው ብላ መለሰችለት። በዚያን ጊዜ ጽኑ ሥቃይን አሠቃያት በሥጋዋም እሳትን ጨመረ ከዛም ዘቅዝቆ ሰቀላት ከበታቿም አጤሱባት ከሃይማኖቷም ባልተናወጸች ጊዜ ራሷን በሰይፍ ቆረጧት። በመንግስተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለች።
የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@efeson_2
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫

🔥1
✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿
እንኳን #የእመቤታችን_የቅድስት_ድንግል #ማርያም_ቅዳሴ_ለደረሰው ለብህንሳ አገር ኤጲስቆዾስ ለታላቁ አባት #ለአባ_ሕርያቆስ_ለልደትና ለዕረፍት በዓል፣ ለአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት #ለቅዱስ_አቡነ_ሳዊሮስ_ወደ_ግብጽ_አገር_ተሰዶ ለመጣ መታሰቢያ ቀን በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #ከሰማዕቱ_ከቅዱስ_ቴክላ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
@efeson_2
✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (ገብረ ሕይወት)
ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ::
አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ562 ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ እህል ያልቀመሱ ልብስ ያልለበሱ ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ አባት ናቸው።
የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ስለ ሀገራችን ፍቅር ሲሉ ለ100 ዓመታት በደብረ ዝቋላ መከራን ተቀብለዋል። ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው።
በ8ኛው ክ.ዘ አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ.ዘ አካባቢ ነው። ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት 5 ቀን ሲያርፉ ግሩማን መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል።
ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍቱ መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ የመጋቢት 27 ስቅለት ጥቅምት 27 ቀን እንደሚከበረው ሁሉ ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር ተደረገ፡፡
የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@efeson_2
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉
ጥቅምት ፭ /5/

🥰1
ጥቅምት ፮ /6/
በዚህች ቀን የታላቁ ነቢይና ካህን የሳሙኤል እናት ቅድስት ነቢይት ሐና አረፈች።
ይችም ቅድስት ከሌዊ ነገድ ናት የታኅርም ልጅ ሕልቃና አገባት ፍናና የምትባልም ሌላ ሚስት አለችው እርሷም ወላድ በመሆኗ ሐና ልጅ ስለሌላት መካንም ስለሆነች ሁልጊዜ ትገዳደራት ነበር። በዚህም አቤቱ ልጅ የሰጠኸኝ እንደሆነ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለአንተ የሚያገለግል አደርገዋለሁ ብላ ተሳለች።
ካህኑ ኤሊም ስትጸልይ ሰምቶ እንዲህ ብሎ ባረካት የእስራኤል ፈጣሪ የለመንሽውን ይስጥሽ በሰላም ሒጂ በቃሉም አምና ወደ ቤቷ ገባች።
ከዚህም በኋላ ፀንሳ ወንድ ልጅን ወለደች ስሙንም ሳሙኤል ብላ ጠራችው። ጡትንም በአስጣለችው ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት ይዛው ወጣች ወደ ካህን ኤሊም አቀረበችውና እንዲህ ብላ አስረዳችው ከአሁን በፊት ልጅን ይሰጠኝ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ስጸልይና ስለምን ያየኸኝ ሴት ነኝ ልመናዬንም ሰምቶ ይህን ልጅ ሰጠኝ አሁንም በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለእግዚአብሔር አገልጋይ ይሆን ዘንድ አመጣሁት ።
ከዚህም በኋላ ሐና እግዚአብሔርን አመሰገነችው። ልቤ በእግዚአብሔርአምኖ ጸና የሚለውን ጸሎትና ትንቢት እስከ መጨረሻው ተናገረች ። ይቺም በዳዊት መዝሙር መጨረሻ ከሙሴ መኀልይ ቀጥላ ተጽፋለች። ከዚህም በኋላ እግዚአብሔርን አገልግላ በሰላም አረፈች።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@efeson_2
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
ጥቅምት ፯ /7/
በዚች ዕለት ጠመው ከሚባል አገር የሆነ የከበረ አባት አባ ባውላ አረፈ።
ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ መስተጋድል መነኲሴ ሆነ የሚኖረውም በላይኛው ግብጽ በአለ በእንጽና ገዳም ነው ስሙ ሕዝቅኤል የሚባል ረድእ አለው። እርሱም ስለ ትሩፋቱና ስለ ተጋድሎው ምስክር ሆነ ይህ አባ ባውላ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ራሱን ሰባት ጊዜ ገድሏልና።
ክብር ይግባውና ጌታችንም አስነሣው እንዲህም ብሎ አጽናናው ወዳጄ ባውላ ሆይ ራስህን ሰባት ጊዜ እስከምትገድል ድረስ ሰውነትህን አደከምክ እንግዲህ ድካምህ ይብቃህ።
አባ ባውላም ለመድኃኒታችን እንዲህ ብሎ መለሰለት ጌታዬ ሆይ ስለ ከበረው ስምህ እደክም ዘንድ ተወኝ አንተ አምላክ ስትሆን ስለኛ በመከራ ደክመህ ስለ ሰው ወገን ሞትክ ለእኛ ይህ አይገባንም ነበር በቸርነትህ ይህን የማዳንህን ሥራ ሠራህልን እንጂ። ጌታችንም ከአጽናናው በኋላ ከእርሱ ወደ ሰማይ ወጣ።
ከዚህም በኋላ አባ ብሶይ ወደ እንጽና ገዳም ሒዶ ከአባ ባውላ ጋር ተገናኘ ጌታችንም ለአባ ባውላ ተገልጾለት ሥጋህ ከአባ ብሶይ ሥጋ ጋር በአንድነት ይኑር አለው ሁለቱም በአረፉ ጊዜ ሥጋቸውን በአንድነት አኖሩ።
ወገኖቹም የአባ ብሶይን ሥጋ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሊወስዱ በወደዱ ጊዜ በመርከብ ጫኑት መርከቢቱ ግን መንቀሳቀስን እምቢ አለች። ከዚህም በኋላ ተመልሰው የአባ ባውላን ሥጋ አምጥተው በመርከብ ላይ ጫኑት ያን ጊዜ መርከቢቱ ተጓዘች። እንዲህም የቅዱሳኑን ሥጋቸውን ወደ አስቄጥስ ገዳም አድርሰው በአባ ብሶይ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአንድነት አኖሩ እስከ ዛሬም በዚያ ይኖራሉ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
@efeson_2
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
ጥቅምት ፲ /10/
በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሰባተኛ የሆነ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት አውማንዮስ አረፈ ።
ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ ንጹሕ ትሑት የሆነ ለዕውነተኛ ሥራ ሁሉ የሚያገለግል ነበር ቅዱስ አብርምዮስም ትሩፋቱን አይቶ ዲቁና ሾመው በዲቁና አገልግሎትም ዐሥር ዓመት ኖረ ።
ዮስጦስም ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ ትሩፋቱንና የሃይማኖቱን ቅንነት ተመለከተ ምእመናንንም ማስተማር እንደሚችል አውቆ ቅስና ሾመው ። ከዚህም በኋላ ቅዱስ ዮስጦስ በአረፈ ጊዜ ይህን አባት አውማንዮስን መርጠው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት የአብያተ ክርስቲያናትንም ሥራ ሁሉ ተረከበ ።
መናፍቃንንም ተከራክሮ የሚረታቸው ሆነ ብዙዎችንም ከስሕተታቸው መለሳቸው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመለኮቱ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል እንደሆነ ግልጽ አድርጎ አስተማራቸው ። በሹመቱም ዐሥራ ሦስት ዓመት ከኖረ በኋላ በአንስጣዮስ ሰባተኛ ዘመነ መንግሥት በዚች ቀን አረፈ ። በዘመኑም የሶፍያ ሦስቱ ልጆቿ በሰማዕትነት አረፉ ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
@efeson_2
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
ጥቅምት ፲፪ /12/
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥቅምት ዐሥራ ሁለት በዚች ዕለት የመላእክት አለቃ የከበረ መልአክ የሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።
በዚችም ቀን ወደ ነቢይ ሳሙኤል እግዚአብሔር ልኮታልና የዳዊት አባት ወደሆነ በቤተ ልሔም ወደሚኖርወደእሴይ ቤት ይሔድ ዘንድ በቂስ ልጅ በሳኦልም ፈንታ ለእስራኤል ልጆች እንዲነግሥ ልጁ ዳዊትን ይቀባው ዘንድ አዘዘው።
ሳሙኤልም ወደ እሴይ ቤት ሔዶ ልጆችህን ሁሉንም አቅርብልኝ ብለው እሴይም ከዳዊት በቀር ሁሉንም አቀረባቸው እርሱ በእርሻ ውስጥ በጎችን ይጠብቅ ነበርና።
ሳሙኤልም የመንግሥት ቅባት ያለበትን ብልቃጥ በራሳቸው ላይ ከፍ ከፍ በአደረገ ጊዜ እግዚአብሔር አልመረጣቸውም። ሳሙኤልም እሴይን ልጆችህ እነዚህ ብቻ ናቸውን አለው ዕሴይም በጎች የሚጠብቅ አንድ ትንሽ ልጅ አለ አለው።
ሳሙኤልም ደግሞ ዕሴይን እሱ ሳይመጣ ምሳ አልበላምና ልከህ አስመጣው አለው ። እሱም ልኮ አስመጣው መልኩም ቀይ ዐይኖቹም የተዋቡ አርአያውም ያማረ ነው እግዚአብሔርም ሳሙኤልን ይህ ይበልጣቸዋልና ተነሥተህ ቅባው አለው። በዚያንም ጊዜ ሳሙኤል የመንግሥት ቅባት ያለበትን ቀንድ አምጥቶ በወንድሞቹ መካከል ቀባው ከዚያችም ቀን ጀምሮ ለሁል ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በዳዊት ላይአደረበት በእስራኤል ልጆችም ላይ ነገሠ።
ደግሞ ሁለተኛ በዚች ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ሚካኤልን ወደ ዳዊት ላከው ረዓይታይ ጎልያድን እስኪገድለውና የእስራኤልን ልጆች እስከሚያድናቸው ረድቶ ኃይልን ሰጠው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
@efeson_2
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
◈◈◈◈◈◈ ስለ አንተ ▣▣▣▣▣▣▣
▣▣▣▣▣▣ 📜🌷📜 ◈◈◈◈◈◈◈
ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ። ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም ፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም። በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ ፥ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና ፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል ፣ በእጆቻቸው ያነሡሃል። በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ። በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ። ይጠራኛል እመልስለትማለሁ ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ ፤ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ።
ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።
◈◈◈◈◈ 🤲🤲🤲 ▣▣▣▣▣▣▣
➥ መዝ.91፥9-16
▣▣▣▣▣ 📖 📖📖 ◈◈◈◈◈◈◈

🥰3
ጥቅምት ፲፬ /14/
በዚችም ቀን የታላቁና የከበረው አባታችን አረጋዊ ዘሚካኤል መታሰቢያው ነው። ይህም ቅዱስ ከእርሱ ጋር ዘጠኝ የሆኑትን ቅዱሳን የእግዚአብሔር አገልጋዮችን ወደ ኢትዮጵያ አገር እስከ አደረሳቸው ድረስ በመንገድ የመራቸው እርሱ ነው።
እርሱም የዘንዶ ጅራት በመያዝ ከደብረ ዳሞ ተራራ ላይ ወጣ በዚያም ፍጹም የሆነ ተጋድሎውን ፈጸመ ክብር ይግባውና ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውንም ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ተቀበለ።
ከመምህሩ ከአባ ጳኵሚስ ዘንድ እንደተማረ ለልጆቹ መነኰሳት ሥርዓተ ማኅበርን ሠራላቸው። ከዚህም በኋላ በእግዚአብሔር ቸርነት እንደ ኄኖክና እንደ ኤልያስ ከሞት ገጽ ተሠወረ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
@efeson_2
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸

በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ ዘጠነኛ የሆነ ቅዱስ አባት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ያቃቱ አረፈ ።
ከርሱ በፊት የነበረ አባ ብንያሚን በአረፈ ጊዜ ይህን አባት መርጠው በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት በዘመኑም ብዙ ችግር ደርሶበታል ስሙ ቴዎዶስዮስ የሚባል አንድ መለካዊ ሰው ነበረ እርሱም ወደ ደማስቆ ንጉሥ ወደ ዘይድ ሒዶ ብዙ እጅ መንሻ ሰጥቶ ለእስክንድርያ አገረ ገዥ ሁኖ ተሾመ ። ይህንንም አባት አባ ያቃቱን ሊአስጨንቀው ጀመረ በየዓመቱ ግብርሰባት ሺህ የወርቅ ዲናር ከእርሱ እስከተቀበለ ድረስ እግዚአብሔርም እስከ አጠፋው ድረስ ይህን አባት እንዲህ አሠቃየው ።
በዘመኑም የብዙዎች ቅዱሳን አባቶች አባት የሆነ የአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን ሕንፃዋ ተፈጸመ ።
በአንዲት ሌሊትም ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ለዚህ አባት ተገለጸለት ፍዩም በሚባል አገር በአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግል ዮሐንስ የሚባል ጻድቅ ሰው መነኰስ እንዳለ ነገረው ። ሕዝብን በማስተማርና በመምከርም ይረዳው ዘንድ መልእክተኞችን ልኮ እንዲአስመጣውም አዘዘው ሁለተኛም ከእርሱ በኋላ ሊቀ ጳጳሳት እንደሚሆን ገለጠለት ።
በዚያንም ጊዜ መልእክተኞችን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ሥራውንም ሁሉ አስረከበው ይህንንም አባት ከብዙ ድካም የሚያሳርፈው ሆነ በሹመቱ ወንበርዐሥራ ዘጠኝ ዓመት ኑሮ ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈ ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@efeson_2
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
ጥቅምት ፲፮ /16/

🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴
እንኳን #ለሀገረ_ቀምስ_ኤጲስቆጶስ #ለቅዱስ_ፊልያስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ ለነቢዩ #ለቅዱስ_ሳሙኤል_እናት ለነቢይት #ለቅድስት_ሐና_ለልደቷ_መታሰቢያ_በዓል፣ #ለቅዱስ_ባስልዮስ_ወንድም_ለቅዱስ_ጎርጎርዮስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓልና #ለእስክንድር_አገር_ሠላሳ_አንደኛ ሊቀ ጳጳሳት #ለቅዱስ_ዲዮስቆሮስ_ካልዕ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #በቆዳ_ገመድ_ከታሠሩ_ከደጋጋጎች ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
@efeson_2
🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ጥቅምት ፲፯ /17/
በዚችም ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳ አንደኛ የሆነ የእስክንድርያ አገርሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ዲዮስቆሮስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።
ይህም አባት በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ መልእክትን ጽፎ ወደ አንጾኪያ ሊቀ ጳጰሳት ቅዱስ ሳዊሮስ ላካት ። እርሱም ስለ ምስጢረ ሥላሴ እና ስለ ምስጢረ ስጋዌ ጽፎ ላከለት።
መልእክቱም ወደ ቅዱስ አባት ሳዊሮስ በደረሰች ጊዜ አነበባትና ፈጽሞ ደስ ተሰኘባት ለአንጾኪያም ሕዝብ አስተማረባት ሁሉም ደስ አለቸው።
ከዚህም በኋላ አባ ሳዊሮስ ለአባ ዲዮስቆሮስ የመልእክቱን መልስ እንዲህ ብሎ ጻፈ ። በኒቅያ ከተማ ተሰብስበው ሃይማኖታቸው የቀና 318ቱ ቅዱሳን አባቶቻችን በቀናች ሃይማኖት አጽንተው የሠሩዋትን ቤተ ክርስቲያኑን እንድትጠብቅ ለዚች ለከበረች አገልግሎት የመረጠህ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ ። ዳግመኛም በዚሁ እንዲጸና ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ እንዳይል አስገነዘበው ደግሞም በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ ሕዝቡን ሁል ጊዜ አስተምራቸው አለው ።
የአባ ሳዊሮስም መልእክት ወደ አባ ዲዮስቆሮስ በደረሰች ጊዜ ደስ ተሰኘባት በሁሉ ቦታም እንዲአስተምሩባት አዘዘ ይህም አባት ሕዝቡን ሁል ጊዜ የሚያስተምራቸው ሆነ ። ሁል ጊዜም ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ ያስተምራቸዋል ኤጲስቆጶሳቱንና ካህናቱንም መንጋዎቻቸውን ስለ መጠበቅ ያዛቸዋል መልካም አገልግሎቱንም አድርሶ እግዚአብሔርንም ደስ አሰኝቶ አረፈ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
@efeson_2
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
🔥1