መስከረም ፳ /20/
በዚህች ቀን ለሊቃነ ጳጳሳት ሃያ ስምንተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባት አትናቴዎስ አረፈ።
ይህም አባት አስቀድሞ የእስክንድርያ አገር ቤተክርስቲያን መጋቢ ነበር፤ ከእርሱም በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ ጴጥሮስ በአረፈ ጊዜ ይህን አባት ሊቀ ጵጵስና ይሾሙት ዘንድ ሁሉም ኤጲስቆጶሳት መኳንንቱና ሊቃውንቱ ሕዝቡም በአንድ ምክር ተስማሙ።
በእግዚአብሔር ሕግ በመጽናት ያደረገው መልካም ተጋድሎውና ቅድስናው ስለእርሱ ስለተነገረ መንፈስ ቅዱስም እንደ አደረበት ስለ ተረዱ ያለ ፈቃዱም ወስደው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት።
ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና የክርስቶስን መንጋዎች በምክሩ፣ በትምህርቱ፣ በጸሎቱ ከዲያብሎስ ተኵላዎች በመልካም አጠባበቅ ጠበቃቸው እኒህም ሃይማኖትን የሚለውጡ መናፍቃን ናቸው። በሊቀ ጵጵስናውም ፯ ዓመት ኖረ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።
በረከታቸው ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
@efeson_2
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟

🔥1
ውድ ወንድሜ ሰውን በስብከት ማገልገል የግድ ልብሰ ተክህኖ ለብሶ መድረክ ላይ መቆም ብቻ አይደለም፣ ትልቁና ዋነኛው ሰውን በራስ ሕይወት መለወጥ ነው፡፡ ስለዚህ በሕይወትህ ለብዙዎች አብነት እንድትሆን እንጂ የግድ ስብከት አዘጋጅተህ መድረክ ላይ መቆም ብቻ አይጠበቅብህም፡፡ እንዲህ አይነት ሰው ከሆንክ ሰዎች ፊትህን ባዩት ጊዜ የዋህነትን፣ ሩህሩህነትን ይማራሉ፣ ንግግርህንም በሰሙ ጊዜ መንፈሰ ጠንካራነት፣ ታማኝነት፣ ፍፁምነትና ፍቅርን ያገኛሉ፡፡
(ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ - ከመንፈስ ነፃነት የተወሰደ)
@efeson_2
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
(ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ - ከመንፈስ ነፃነት የተወሰደ)
@efeson_2
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨
እንኳን #የእናታች_የእመቤታችን_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም (ለብዙኃን ማርያም)፣ #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል #በግሸን_በመስቀለኛው_ተራራ ላይ ገብቶ ለተቀመጠበት፣ #ሊቃውንተ_ቤተ_ክርስቲያን_ሃይማኖታዊ_ውሳኔ ለመወሰን፤ #በኒቅያ_ጉባኤ_አርዮስን_ለማውገዝ ከሩቅ #ለተሰባሰቡበት_ቀን እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨
እንኳን #ለቅዱሳን_ጻድቃን መነኰሳት #አውናብዮስና_እንድርያኖስ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና #ለሰማዕቱ_ቅዱስ_ኤዎስጣቴዎስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከመርዓተ_ክርስቶስ (ከክርስቶስ ሙሽራ) #ከቅድስት_ድንግል_ቴክላ ለመታሰቢያ በዓል፣ #ከአርባ_አራት_ሰማዕታት፣ #ከመንክራዊ_ጎርጎርዮስ #ከእንጺናና_ከብሊናም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
@efeson_2
✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿

Forwarded from ነይ ነይ እምዬ ማርያም መዝሙሮች (𝕻𝖎𝖑𝖚𝕻ΔDΣR)
ወርኀ ጽጌ🥰
“በምሥራቀ ፀሐይ የምትመሰየሚው፤ እንደ መብረቅ ኃያል የሆነውን ጌታን የወለድሽ፣ ረቂቅ ምሥጢርን የምትችዪ፤ እንደ ፊደል ባለ ብዙ ዘር [ሆሄያት] የሆንሽ፣ ወንጌልን የወለድሽ፥ ነበልባለ እሳትን [ክርስቶስን] የተሸከምሽ ፤ በጽጌ ረዳ አምሳል የምትመሰየሚው ቅድስት ማርያም ሆይ! የዓለሙን እንግዳ ፈጣሪን የወለድሽ፤ ከፍዳ ሞት የምታድኚ፤ የወይን ሐረግ የወይን ዐፀድ [ተክል] አንቺ ነሽ።”
ሀሳብ አስተያየት ካለ @kingo08bot

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇
@ney_ney_emye_maryam
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏
🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊
ሀሳብ አስተያየት ካለ @kingo08bot
❤1
✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿
እንኳን #አስቀድሞ_በማንም_ላይ_ርኅራኄ የሌለው (ንፉግ) ለነበረ፤ በሕልሙ እግዚአብሔር በሳየው ራእይ ተመልሶ ስለ ምጽዋት ሲል ያለው ንብረት በሙሉ ከሰጠ በኋላ እራሱ ለሸጠ ለቀራጭች አለቃ ለነበረ #ለቅዱስ_አንጢላርዮስ_ለዕረፍት_በዓል መታሰቢያ፣ #በሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ ትምህርት አምና ለተጠመቀች ያለ ደም መፍሰሰ ሰማዕት ለሆነች #ለቅድስት_ጤቅላ (ቴክላ) ለዕረፍቷ በዓል መታሰቢያ፣ #ለቅዱስ_ኤዎስጣቴዎስ_ለሁለት_ልጆቹና_ለሚስቱም ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከመድኃኒታችን ከስቅለቱ #ከመድኃኔዓለም ከወራዊ ከመታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

መስከረም ፳፯ (27)
በዚህችም ቀን ያለ ደም ማፍሰስ ሰማዕት የሆነች ቅድስት ጤቅላ አረፈች።
የዚህች ቅድስት ወላጆቿ ከመቄዶንያ ሰዎች ውስጥ ባለጸጎች ናቸው እርሷንም እንደ ሀገራቸው ባህል በተግሣጽ በምክር አሳደጓት እነርሱ ጣዖትን የሚያመልኩ ናቸውና። ሐዋርያ ጳውሎስም ወደዚህች አገር በደረሰ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ አምስትን ሊአስተምር ጀመረ ዐውቀው ድኆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው መንግሥተ ሰማያት ለእነርሱ ናትና።
ይህንንና ይህን የመሰለውን በሰማች ጊዜ ያለ መብልና መጠጥ ሦስት ቀን ኖረች። ከዚህም በኋላ ወደ ቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስ ሔደች። እርሱም በደስታ ተቀብሎ የክርስቶስን ሃይማኖት አስተማራት።
በማግሥቱም እናቷ ከቅዱስ ጳውሎስ ዘንድ አብራ ተቀምጣ አገኘቻት ከዚያም ወደ መኰንን ሒዳ ልጇን ክርስቲያን እንደሆነች ከሰሰቻት። መኰንኑም ከቅዱስ ጳውሎስ ጋራ እንዲያመጧት አዘዘ አስቀድመው ቅዱስ ጳውሎስን ወደ እሳት እንዲወረውሩት አዘዘ እግዚአብሔርም አዳነው።
መኰንኑም ቅድስት ጤቅላን ወደ እሳት እንዲወረውሩዋት አዘዘ። በዚያን ጊዜ በክርስቶስ ማዕተብ ራሷን አማትባ ራስዋን በራስዋ ወደ እሳት ወረወረች ማንም ያያት ሳይኖር ከእሳት ውስጥ ወጥታ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሔደች የራስዋን ጠጒር ቆርጣ ወገቧንም ታጥቃ ቅዱስ ጳውሎስን ተከተለችው።
ከዚህም በኋላ መኰንኑ አንበሳና ድብ ከሚያድርበት ጨመራት እነርሱም ሰገዱላትና የእግሮቿን ትቢያ ላሱ። መኰንኑና ወገኖቹ ይህን አይተው በእግዙአብሔእ አመኑ ቅድስት ጤቅላም ቅዱስ ጳውሎስን አገልግላ በሰላም አረፈች።
በረከታቸው ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@efeson_2
🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋
መስከረም ፳፰ /28/
በዚች ቀን ቅድስት ሶስና አረፈች
ይህችውም ቅድስት የባዕለ ጸጋ ኢዮአቄም ሚስት የኾነች፣ የቅዱስ ሙሴን ሕግ የተማረችና ደጋግ የኾኑን አባትና እናቷም በመልካም ያሳደጓት፣ የኦሪትንም ሕግ ያስተማሯት አስተዋይ ቅድስት ናት።
በዚያም በባልዋ ቤት ብዙ እስራኤላውያን ይመጡ ነበርና የዚያም፡ቤት ቤተኛ ከኾኑት ኹለት የአይሁድ ረበናት ይገኙበታል። እኒህም ኹለት ግብዞች ደጋግመው ሶስናን አዩአት በዚህም ጸላኤ ሰናያት በልቡናቸው አደረና ዐይናቸው ኹሉ ግልብጥብጥ ብሎ በክፉ ሥራ ፈቀዷት።
አንድ እለት ከአትክልት ሥፍራ ዘግታ ስትታጠብ አገልጋዮቿን መልእክት ልካቸው እንደወጡ እኒህ ኹለት ክፉዎች ከተደበቁበት ወጥተው ፈቃዳችንን ፈጽሚ ካልፈጸምሽ ስታመነዝር ይዘናታል ብለን እንከስሻለን አሏት። እርሷም ከእጃቸው ማምለጥ አትችልምና ወደ ሰማይ አንጋጣ ቸሩን አምላክ በጽኑዕ ያድናት ዘንድ ተማጸነች።
እርሷም ፈቃዳቸውን ብፈጽምም ኾነ ባልፈጽም እሞታለሁ፣ ከፈጸምኹ ግን ከነርኲሰት ነውና የምሞተው ብላ አስባ እንደማትፈጽም ነገረቻቸው። ሦስቱም ሲጮኹ ሕዝብ ሲሰበሰብ ስታመነዝር አገኘናት አሉና ከሰሷት። እርሷም እንዲህ ያለ ነውር ተሰምቶባት አይታወቅምና ዘመዶቿ አፈሩ። በኋላም ለፍርድ በአደባባይ አቀረቧትና አየን ያሉትን ተናገሩ።
ሊወግሯትም ብለው ሲኼዱ ታላቁ ነብይ ቅዱስ ዳንኤል ቆይ እኔ ልመርምራቸው ብሎ አራርቆ ቢመረምራቸው አንዱ ከኮክ ዛፍ ሥር ነው ያየኋት፣ አንዱ ደግሞ ከሮማን ዛፍ ሥር ነው አለ። በዚህም ተለያይተዋልና ሕዝቡ እኒህን ኹለት ግብዝ ክፉ ሰዎች ገደሏቸው፣ ቅድስት ሶስናም በቸሩ አምላክ ታላቅ ነቢይ እርዳታ ዳነች።
በረከታቸው ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@efeson_2
🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋
❤1🔥1
🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿
እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ አጽፋቸውን እንደጀልባ ተጠቅመው የኢያሪኮን ባሕር ለተሻገሩት ለታላቁ ጻድቅ የአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ከፋሌ ባሕር ደቀ መዝሙር ለሆኑ #በኤራትራና_በኢትዮጵያ_ገዳም ለመሰረቱ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_አቡሳዲ_ለዕረፍታቸው በዓልና #ከተሰዓቱ_ቅዱሳን አንዱ ለሆኑት #ለአቡነ_ይስሐቅ_ተአምር_ሰረተው #አቡነ_ገሪማ ተብለው እንዳጠሩ ላተረጉበት ቀን መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን።

🔥2
ጥቅምት ፩ /1/
በዚህችም ቀን በጥቅምት አንድ ቅድስት አንስጣሲያ በሰማዕትነት አረፈች።
ይህችም ቅድስት መስተጋድልት ከሮሜ አገር ናት ወላጆቿም ክርስቲያኖች ናቸው ጠቃሚ የሆነ ትምህርትን በማስተማር ክብር ባለው በመልካም ሥርአት አሳደጓት። በአደገችም ጊዜ ወላጆቿ ሊያጋቡአት ፈለጉ እርሷ ግን በሥውር በሮሜ ከሚገኙ ወደ አንዱ ገዳማት ሂዳ የምንኩስና ልብስን በመልበስ በጾም በጸሎት በረኃብ በጽምዕ በመጠመድ ሥጋዋን አደከመች በቀኑ ርዝመት ትጾማለች በየሁለት ቀኖችም ታከፍላለች በጌታችን ጾም ግን ያለ ሰንበታት ቀን አትመገብም።
ከዚሕም በኋላ የንጉስ ዳኬዎስ ወታደሮች ክርስቲያኖችን አሥረው በቁጣ ሲጎትቷቸው አይታ ልቧ በሃይማኖቷ ፍቅር ነደደና እንዲህ ብላ ዘለፈቻቸው የእውነት ፈጣሪን የካዳቹ ልባቹ የደነዘዘ እግዚአብሔር በመልኩና በአምሳሉ በፈጠራቸውና ስለ እነርሱም ነፍሱን አሳልፎ በሰጣቸው ላይ ለምን እንዲህ ትሠራላቹ።
ወታደሮቹም ይሕን ሲሰሙ ተቆጡ ይዘውም ወደ መኮንኑ አቀረቧት እርሱም እንዲህ ብሎ ጠየቃት በእውነት አንቺ የተሰቀለውን የምታመልኪው ክርስቲያን ነሽን እርሷም ስለእኛ የተሰቀለውን ክብር ይግባውና እርሱን አመልከዋለው ብላ መለሰችለት። በዚያን ጊዜ ጽኑ ሥቃይን አሠቃያት በሥጋዋም እሳትን ጨመረ ከዛም ዘቅዝቆ ሰቀላት ከበታቿም አጤሱባት ከሃይማኖቷም ባልተናወጸች ጊዜ ራሷን በሰይፍ ቆረጧት። በመንግስተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለች።
የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን! አሜን

እንኳን #የእመቤታችን_የቅድስት_ድንግል #ማርያም_ቅዳሴ_ለደረሰው ለብህንሳ አገር ኤጲስቆዾስ ለታላቁ አባት #ለአባ_ሕርያቆስ_ለልደትና ለዕረፍት በዓል፣ ለአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት #ለቅዱስ_አቡነ_ሳዊሮስ_ወደ_ግብጽ_አገር_ተሰዶ ለመጣ መታሰቢያ ቀን በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #ከሰማዕቱ_ከቅዱስ_ቴክላ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (ገብረ ሕይወት)
ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ::
አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ562 ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ እህል ያልቀመሱ ልብስ ያልለበሱ ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ አባት ናቸው።
የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ስለ ሀገራችን ፍቅር ሲሉ ለ100 ዓመታት በደብረ ዝቋላ መከራን ተቀብለዋል። ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው።
በ8ኛው ክ.ዘ አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ.ዘ አካባቢ ነው። ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት 5 ቀን ሲያርፉ ግሩማን መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል።
ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍቱ መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ የመጋቢት 27 ስቅለት ጥቅምት 27 ቀን እንደሚከበረው ሁሉ ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር ተደረገ፡፡
የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@efeson_2
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉
ጥቅምት ፭ /5/

🥰1
ጥቅምት ፮ /6/
በዚህች ቀን የታላቁ ነቢይና ካህን የሳሙኤል እናት ቅድስት ነቢይት ሐና አረፈች።
ይችም ቅድስት ከሌዊ ነገድ ናት የታኅርም ልጅ ሕልቃና አገባት ፍናና የምትባልም ሌላ ሚስት አለችው እርሷም ወላድ በመሆኗ ሐና ልጅ ስለሌላት መካንም ስለሆነች ሁልጊዜ ትገዳደራት ነበር። በዚህም አቤቱ ልጅ የሰጠኸኝ እንደሆነ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለአንተ የሚያገለግል አደርገዋለሁ ብላ ተሳለች።
ካህኑ ኤሊም ስትጸልይ ሰምቶ እንዲህ ብሎ ባረካት የእስራኤል ፈጣሪ የለመንሽውን ይስጥሽ በሰላም ሒጂ በቃሉም አምና ወደ ቤቷ ገባች።
ከዚህም በኋላ ፀንሳ ወንድ ልጅን ወለደች ስሙንም ሳሙኤል ብላ ጠራችው። ጡትንም በአስጣለችው ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት ይዛው ወጣች ወደ ካህን ኤሊም አቀረበችውና እንዲህ ብላ አስረዳችው ከአሁን በፊት ልጅን ይሰጠኝ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ስጸልይና ስለምን ያየኸኝ ሴት ነኝ ልመናዬንም ሰምቶ ይህን ልጅ ሰጠኝ አሁንም በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለእግዚአብሔር አገልጋይ ይሆን ዘንድ አመጣሁት ።
ከዚህም በኋላ ሐና እግዚአብሔርን አመሰገነችው። ልቤ በእግዚአብሔርአምኖ ጸና የሚለውን ጸሎትና ትንቢት እስከ መጨረሻው ተናገረች ። ይቺም በዳዊት መዝሙር መጨረሻ ከሙሴ መኀልይ ቀጥላ ተጽፋለች። ከዚህም በኋላ እግዚአብሔርን አገልግላ በሰላም አረፈች።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@efeson_2
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
ጥቅምት ፯ /7/
በዚች ዕለት ጠመው ከሚባል አገር የሆነ የከበረ አባት አባ ባውላ አረፈ።
ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ መስተጋድል መነኲሴ ሆነ የሚኖረውም በላይኛው ግብጽ በአለ በእንጽና ገዳም ነው ስሙ ሕዝቅኤል የሚባል ረድእ አለው። እርሱም ስለ ትሩፋቱና ስለ ተጋድሎው ምስክር ሆነ ይህ አባ ባውላ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ራሱን ሰባት ጊዜ ገድሏልና።
ክብር ይግባውና ጌታችንም አስነሣው እንዲህም ብሎ አጽናናው ወዳጄ ባውላ ሆይ ራስህን ሰባት ጊዜ እስከምትገድል ድረስ ሰውነትህን አደከምክ እንግዲህ ድካምህ ይብቃህ።
አባ ባውላም ለመድኃኒታችን እንዲህ ብሎ መለሰለት ጌታዬ ሆይ ስለ ከበረው ስምህ እደክም ዘንድ ተወኝ አንተ አምላክ ስትሆን ስለኛ በመከራ ደክመህ ስለ ሰው ወገን ሞትክ ለእኛ ይህ አይገባንም ነበር በቸርነትህ ይህን የማዳንህን ሥራ ሠራህልን እንጂ። ጌታችንም ከአጽናናው በኋላ ከእርሱ ወደ ሰማይ ወጣ።
ከዚህም በኋላ አባ ብሶይ ወደ እንጽና ገዳም ሒዶ ከአባ ባውላ ጋር ተገናኘ ጌታችንም ለአባ ባውላ ተገልጾለት ሥጋህ ከአባ ብሶይ ሥጋ ጋር በአንድነት ይኑር አለው ሁለቱም በአረፉ ጊዜ ሥጋቸውን በአንድነት አኖሩ።
ወገኖቹም የአባ ብሶይን ሥጋ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሊወስዱ በወደዱ ጊዜ በመርከብ ጫኑት መርከቢቱ ግን መንቀሳቀስን እምቢ አለች። ከዚህም በኋላ ተመልሰው የአባ ባውላን ሥጋ አምጥተው በመርከብ ላይ ጫኑት ያን ጊዜ መርከቢቱ ተጓዘች። እንዲህም የቅዱሳኑን ሥጋቸውን ወደ አስቄጥስ ገዳም አድርሰው በአባ ብሶይ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአንድነት አኖሩ እስከ ዛሬም በዚያ ይኖራሉ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
@efeson_2
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
ጥቅምት ፲ /10/
በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሰባተኛ የሆነ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት አውማንዮስ አረፈ ።
ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ ንጹሕ ትሑት የሆነ ለዕውነተኛ ሥራ ሁሉ የሚያገለግል ነበር ቅዱስ አብርምዮስም ትሩፋቱን አይቶ ዲቁና ሾመው በዲቁና አገልግሎትም ዐሥር ዓመት ኖረ ።
ዮስጦስም ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ ትሩፋቱንና የሃይማኖቱን ቅንነት ተመለከተ ምእመናንንም ማስተማር እንደሚችል አውቆ ቅስና ሾመው ። ከዚህም በኋላ ቅዱስ ዮስጦስ በአረፈ ጊዜ ይህን አባት አውማንዮስን መርጠው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት የአብያተ ክርስቲያናትንም ሥራ ሁሉ ተረከበ ።
መናፍቃንንም ተከራክሮ የሚረታቸው ሆነ ብዙዎችንም ከስሕተታቸው መለሳቸው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመለኮቱ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል እንደሆነ ግልጽ አድርጎ አስተማራቸው ። በሹመቱም ዐሥራ ሦስት ዓመት ከኖረ በኋላ በአንስጣዮስ ሰባተኛ ዘመነ መንግሥት በዚች ቀን አረፈ ። በዘመኑም የሶፍያ ሦስቱ ልጆቿ በሰማዕትነት አረፉ ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
@efeson_2
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫