ኤፌሶን~፩
650 subscribers
75 photos
1 video
23 links
Download Telegram
ነሐሴ ፴ /30/


በዚህች ዕለት ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ የሆነው ታላቁ ነቢይ ሚልክያስ አረፈ።

እግዚአብሔር አምላክ በነቢዩ አንደበት አድሮ እንዲህ ይለናል።
ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም። የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው። ትንቢተ ሚልክያስ 3:8

እንዴት አድርጌ ነው ከ5ሺህ ብር ደሞዝ በዛ ላይ የኑሮ ውድነቱ ተጨምሮበት አስራት የማወጣው? ብላችሁ ብትጠይቁም እግዚአብሔር በነቢዩ አድሮ እንዲህ ይለናል።
በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፤ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። ትንቢተ ሚልክያስ 3:10

ቅዱስ ሚልክያስም በበጎ ተጋድሎው እግዚአብሔርን ከአገለገለ በኋላ በዛሬዋ ዕለት ከዚህ ዓለም በመፍለስ በሰላም አረፈ። ሚልክያስ ማለት መልዐክ አንድም የተላከ ማለት ነው።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን
#የመላእክት_አለቃ_የከበረ_መልአክ_የሩፋኤል_የበዓሉ_መታሰቢያ ቀን።  #ለእግዚአብሔር_ልጅ_ምሳሌው የሆነ #የመልከጼዴቅ_መታሰቢያው በዓል። ሰንዱን ከሚባል አገር ለዐረፈ #ለቅዱስ_ሰራጵዮን_ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል አደረሰን። በተጨማሪም በዚህች ቀን፡- የኢትዮጵያ ንጉሥ መልካም ስም አጠራር ያለው #አጼ_ዘርዐ_ያዕቆብ_የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። እግዚአብሔር አምላክ ከቅዱሳኑ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱
🔥2
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን
#ለቅዱስ_አባ_ባይሞን እና ለስድስቱ ወንድሞቹ (#አብርሃም_ያዕቆብ_ዮሴፍ_ኢዮብ_ባስልዮስ_እና_ዮሐንስ) ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪም በዚህች ቀን ከሚታሰብ #የቅዱስ_ሊባርዮስ_ሊቅ_የዕረፍቱ_መታሰቢያ ነው። እግዚአብሔር አምላክ ከቅዱሳኑ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson

🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱
🔥1
ጳጉሜ ፬ /4/


አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም ጷጉሜ አራት በዚች ቀን ተጋዳይ አባ ባይሞን አረፈ።

አባ ባይሞን የተባረኩ ስድስት መነኮሳት  ወንድሞች ያሉት ሲሆን እርሱ ሰባተኛና የመጨረሻ ልጅ ነው። የሁሉም ታናሽ ቢሆንም በዕውቀትና በጥበብ ግን ታላቃቸው ነበር።

መንፈስ ቅዱስ አነሳስቷቸው ሁሉም በአንድ ቀን መነኮሱ። ይህን ዓለም ንቀው የክብር ባለቤት የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቀንበር ተሸክመው በጠባብ መንገድ ተጓዙ።

አባ ባይሞን በአስቄጥስ ገዳም ፈተና፣ የሃይማኖት ጥርጥርና ደዌ ያገኘውን ሁሉ ይፈውስ፣ያረጋጋም ነበር።

ስለ ምንኩስና ሕግ፣ስለ መጋደል እና ስለ አምልኮም ብዙ ድርሳናትን ደረሰ። ዕድሜውንም በተጋድሎና በትሩፋት ሥራ ከፈጸመ በኋላ ወደ መልካም ዕርግና ደርሶ እግዚአብሔርን አገልግሎ አረፈ።

"እኛ የወንድማችንን በደል ብንሰውር እግዚአብሔርም በደላችንን ይሠውርልናል።"


ወስብሐት ለእግዚአብሔር

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
🔥1
👏1
🌼 🌿🌼 🌿🌼 🌿🌼 🌿

እንኳን ለታላቁ ነብይ ሰማዕት ሐዋርያ ካህን ለመጥምቀ መለኮት ለሰማዕቱ ለቅዱስ ዮሐንስ ሕግ አፍራሽ በሆነ በንጉሥ ሄሮድስ እጅ አንገቱን በመሰየፍ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በዚች ቀን በጨማሪ ከሚታሰቡ፦ በግብጽ ውስጥ ታዕዳ ከሚባል አገር በሰማዕትነት ከዐረፈ ከቅዱስ ዳስያ ከሰማዕት ዲዲሞስና  ቅድስትመሪና ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🌼 🌿🌼 🌿🌼 🌿🌼 🌿


አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መስከረም ሦስት በዚህች ቀን የከበረ አባት ሊቀ ጳጳሳት አባ   ዲዮናስዮስ ከተሾመ በሁለተኛው ዓመት በእስክንድርያ ከተማ የኤጲስቆ ጶሳት የአንድነት ጉባዔ ተደረገ።



ይህም ጉባዔ የሆነው ነፍስ ከሥጋዋ ጋር ትሞታለች በዕለተ ትንሣኤም ከሥጋዋ ጋር አብራ ትነሣለች ስለሚሉ ክፉዎች በዐረቢያ አገር ስለተነሡ ሰዎች ነው።

@efeson_2

እነርሱም ለከፋችና ብልሹ ለሆነች ሃይማኖታቸው የፈጠራ ድርሰትን ደርሰው በእስክንድርያ ከተማ ወደሚኖሩ ሰዎች ላኩ። አባታችን ሊቀ ጳጳሳት አባ ዲዮናስዮስም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ ከዚህ ከክፉ ሥራም እንዲመለሱ አስተማራቸው ገሠጻቸውም እነርሱ ግን አልሰሙትም አልተመለሱም። ስለዚህም በእነርሱ ላይ ይህን ጉባዔ ሰብስቦ ተከራከራቸው ስሕተታቸውንም ገልጾ አስረዳቸው እነርሱ ግን ሰይጣን አሳውሯቸዋልና ተጸጽተው አልተመለሱም ይህም ጉባኤ ረግሞ ከቤተ ክርስቲ ያን አንድነት ለይቶ አሳደዳቸው። ይህም አባት ዲዮናስዮስ ስለእርሳቸው ድርሳናትን ደረሰ በውስጣቸውም እንዲህ የሚል  "በዚህ በቸርነቱ ስጦታ ውስጥ የእግዚአብሔር ፍቅር የጎላ የተረዳ ሆነ ነፍስ ረቂቅ ስለሆነች እንደ መላእክት በሕይወት እንድትኖር እንጂ እንዳትሞት እንዳትጠፋ ማድረጉ ነው። ከሥጋዋም በምትወጣ ጊዜ ስለ በጎ ሥራዋ እንደሚገባት መጠን ወደ ሕይወት ቦታዋ ይወስዷታል ወይም እንደሥራዋ ክፉነት ወደ ሥቃይ ይወስዷታል። በትንሣኤ ቀንም 'ንቃሕ መዋቲ' ተብሎ ዓዋጅ ሲነገር በፈጣሪያቸው ትእዛዝ የሙታን በድኖች ሲነሡ ነፍሳት እንዲህ ይሆናሉ እያንዳንዲቱ ነፍስ ከሥጋዋ ተዋሕዳ አብራ ትነሣለች።"

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባቶቻችን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።



በዚህችም ቀን የገዳመ ሲሓት አባ ሙሴ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከመነኰሰ ጀምሮ ዓለምን ትቶ ከበረሀ ገብቶ በጾም በጸሎት በመጠመድ ተጋደለ። እግዚአብሔር ዘይቶንና የተምር አትክልት ያለባትን የአትክልት ቦታ በማየት ልቡን ብሩህ እስከ አደረገለት ድረስ በወሩ መባቻም ከዘንባባ ዕንጨትና ከዘይቶን የወደቀውን ፍሬ ወስዶ ይበላል። ምግቡም ታናሽ ወፍ በሚመገበው መጠን ልክ ነው ልብሱም ከዘንባባ ቅጠል የተሠራ ሰሌን ነው። ስለዚህ ለሚያስጨንቅ ለክረምት ቅዝቃዜና ለቃጠሎ የተጋለጠ ሆነ ከዚህም ጋር በጾምና በጸሎት የተጠመደ ነው። ነገር ግን መጻሕፍትን የሚያውቅ አይደለም የዱር አራዊትም በየወገናቸው ወደእርሱ ይመጡ ነበር እርሱም ያረጋጋቸዋል። የጸሎት ጊዜም ሲደርስ በእጁ ሲጠቅሳቸው ይሔዳሉ። ድርቅ የሆነ እንደ ሆነም ሊያነጋግሩት እንደሚሹ ሁነው መጥተው በፊቱ ይቆማሉ እርሱም የሚሹትን በመንፈስ ቅዱስ አውቆ በጸሎቱ ዝናብን ያወርድላቸዋል። እንዲሁም እያደረገ ከእርሳቸው ጋር አርባ አምስት ዓመት ኖረ። ሰይጣንም ቀናበት ዘመኑ በአለፈና እጅግ በአረጀ ሽማግሌ አምሳል በጥቂት በጥቂት ሲያዘግም ከበዓቱ ውስጥ ሁኖ አየው ለዚህ ቅዱስ አባ ሙሴም ገዳማዊ መናኒ መስሎት ወደእርሱ ሔዶ አምጥቶ ወደ በዓቱ አስገባው አራዊት ግን በሽማግሌ የተመሰለውን ሰይጣን በአዩት ጊዜ ከእርሱ ሸሹ።

@efeson_2

ከዚህ በኋላአባ ሙሴን አገሩንና ሃይማኖቱን ጠየቀው እርሱም ሁሉን ነገረው ደግሞ አባ ሙሴ ኑሮው እንዴት እንደሆነ ሽማግሌውን ጠየቀው። በሽማግሌ የተመሰለ ሰይጣንም እንዲህ ብሎ መለሰለት እኔ በዓለም ኃጢአት በመሥራት ብዙ ዘመናት ኖርኩ አንዲት ሴት ልጅንም ወለድኩ። ከዚያም የዓለምን ኃላፊነትና ጠፊነት አሰብኩ ከዓለምም ወጥቼ በበረሀ ውስጥ አርባ ዓመት ኖርኩ። ልጄን ያገባት እንደሌለ በአሰብኩ ጊዜ በዚህ ነገር ፕምክንያት ወዳንተ መጣሁ ከአንተ በቀር የሚያገባት የለምና። በሞትኩም ጊዜ የምትቀብረኝ አንተ ነህ ብዙ ስፍራዎችና የአታክልት ቦታዎችም ስላሉኝ ሁሉንም አንተ ትወርሳለህ። አባ ሙሴም ሰምቶ ደነገጠ እኔ መንኰሴ ስሆን ይህን እንዴት አደርጋለሁ አለ የተመረጡ ጻድቃን ሲሆኑ ሚስቶች የነበሩአቸው አብርሃምን ሙሴን ዳዊትን ከብሉያት መጻሕፍት ምስክር ማስረጃ አድርጎ አመጣለት በዚህም ወደ ተንኰሎ ልቡን አዘነበለው። በውስጡ ያጌጠች ሴት ልጅ ያለችበትን የተሸለመ አዳራሽ አሳየውና ከዚያም በኋላ እንደሞተ ሆነ አባ ሙሴም አይቶ በላዩ አለቀሰ ገንዞም ቀበረው ልጅቷ ወዳለችበት ለመግባት በፈለገ ጊዜ ጥቅል ነፋስ ነፍሶ የኋሊት ጣለው ከዚህ በኋላ ልቡ ሲመለስለት አዳራሹንም ልጅቷንም የአትክልት ቦታዎችንም አጣ ፈጽሞ እያደነቀ ወደ ማደሪያው ተመለሰ ከዕንጨቱም ፍሬ ምግቡን ሊመገብ ፈለገ በአፉም ውስጥ መራራ ሆነበት በረኃብም ስለ ተጨነቀ ወደ ዱር ወጥቶ ሔደ። ከዚህም በኋላ በአህያው ላይ ተቀምጦ ወደ እስክንድርያ በሚሔድ በሽማግሌ ነጋዴ አምሳል ሰይጣን ተገናኘው መብልና መጠጥም ይዞ ነበር አባ ሙሴንም   ከርሱ ጋር ወሰደው ወደአንድ አገርም አድርሶ በዚያ ተወው። ዳግመኛም በገዳማዊት በመናኒነት በምትኖር ሴት አምሳል ሰይጣን ታየው እርሷም ውኃ የምትቀዳ መስላ ሥራውን ጠየቀችው ሰይጣን እንደፈተነው ሁሉን ነገራት በልቧም ሣቀችበት ወደቤቷም ወስዳው አብልታ አጠጥታ ከዚያ በኋላ የጋብቻን ነገር አሳሰበችው ብዙ ገንዘብም እንዳላት እርሷም የሟች ንጉሥ ልጅ እንደሆነች ነገረችው ልቡም እንደአዘነበለ አይታ እኔ አይሁዳዊት ነኝ እኛም ብዙዎች ነን ሃይማኖቱንም እስከካደ ድረስ በብዙ ተንኰል ተስፋ አስደረገችው። ዳግመኛም እንዲህ አለችው ና ወደ በረሀ እንውጣና ያኖርኩትን ገንዘብ እንውሰድ ብላ ሰው ወደሌለበት በረሀ ወሰደችው ከተራራ በላይም ወጥታ ተለወጠችበት እንዲህም አለችው እኔ ብዙዎችን ያሳትኩ ሰይጣን ነኝ። አንተንም ከገዳምህ አስወጣሁህ ሃይማኖትህንም አስካድኩህ እነሆ በዚህ በረሀም ሙተህ ነፍስህ ወደገሃነም ትወርዳለች ይህንንም ብሎ ሰይጣን ከርሱ ተሠወረ። በተመለሰም ጊዜ በቀኝም በግራም መንገድ አጣ የሚጠጣውም ውኃን አላገኘም ምድር ጠበበችው በምድር ላይም ወድቆ በፊቱ ውስጥም አፈርን በተነ ነፍሱም ከሥጋው ለመለየት እስከደረሰች ደረስ ተንከባለለ ጮኸ። መሐሪና ይቅር ባይ ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ራራለት ያጽናናው ዘንድ መልአኩን ላከለት እርሱም ኃጢአትህ ተሠረየልህ እስከ ሰባት ቀንም ታርፋለህ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሳሙኤልም ይቀብርሃል ብሎ አጽናናው ሰላምታም ሰጥቶት ዐረገ። ያን ጊዜም ሳሙኤል መጣ ንጉሥ ኢጋቦም በበረሃ ውስጥ ወደ አነፃት ቤተ ክርስቲያን ወሰደው እርሷም ገዳማውያን የሚሰበሰቡባት ተሠውራ የምትኖር ናት ወደርሷም በደረሱ ጊዜ ቅዱሳን ተሰብስበው መሥዋዕትን ሲያሳርጉ አገኙና በአንድነት ሥጋውንና ደሙን ተቀበሉ ስንብትም ከሆነ በኋላ ከቅዱሳን መቃብር በረከትን ሊቀበሉ ከአባ ሳሙኤል ጋራ አብረው ሔዱ ከዚያም ደርሶ አባ ሙሴ ሰገደ ወዲያውም አረፈ። አባ ሳሙኤልም ቀበረው ገድሉንም ጻፈ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሁሉም ቅዱሳን በጸሎታቸው ይማረን ለዘላለሙ አሜን።



በዚህችም ቀን የኢትዮጵያዊው የአባ አንበስ የሰማዕት አባ ዲዮስቆሮስ ሰማዕት የሆነ የሊቀ ጳጳሳት ዲዮናስዮስ የዲያቆን በትንከል የብዙዎች የፋርስ ሰማዕታት የዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው

በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን።

                 🙏አሜን።🙏

@efeson_2

🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
🔥1👏1
‎መስከረም ፭ /5/


‎በዚች ቀን የከበረች ሶፊያ ከሁለት ልጆቿ አክሶስ እና በርናባ ከሚባሉት ጋር በሰማዕትነት አረፈች።

‎ይችም ቅድስት አስቀድማ አረማዊት ነበረች ወላጆቿም ጣዖታትን የሚያመልኩ ናቸው። እርሷም በልቧ የወላጇቿ ሃይማኖት ከንቱ እንደሆነ መረመረች። ወደ መኖፌ ኤጲስቆጶስም ሄዳ ክብር ይግባውና በጌታችን በክርስቶስ ታመነች።

‎እርሱም ሃይማኖትን የቤተክርስቲያንን ሕግ አስተማራት። ከዚሕም በኋላ ከልጆቿ ጋር በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም አጠመቃት። ከዚህም በኋላ የሀገሩ ገዢ ለጣዖት መስገድን ትታ ክርስቲያን እንደሆነች በሰማ ጊዜ ከልጇቿ ጋር ብዙ ስቃይን አሰቃያት።

‎ገዢውም ልጇቿ አይተው ይፈሩ ዘንድ በጅራፍ ይገርፏት ዘንድ አዘዘ። ያን ጊዜም የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ ወርዶ እናታቸውን ከግርፋት ሲሰውራት አዩ።

‎ከዚህም በኋላ ወደ እስር ቤት ወስደው አሰሯት እራሷንም በሰይፍ ይቆርጡት ዘንድ አዘዘ የድል አክሊልንም ተቀበለች። ከዚህም በኋላ ልጆቿን ወደርሱ ይመለሱ ዘንድ አስፈራራቸው እንቢ ባሉት ጊዜም እያከታተለ አንገታቸውን አስቆረጠ።

‎ምስክርነታቸውንና ተጋድሏቸውን ፈጸሙ። ከመቃብራቸውም በሽታውንና ደዌውን ሁሉ የሚፈውሱ ብዙ የሆኑ ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
1🔥1
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

🌼 እንኳን ከዐበይት ነቢያት አንዱ ለሆነው ለታላቁ ነቢይ ለአሞጽ ልጅ ለቅዱስ ኢሳይያስ ለዕረፍት በዓልና በከሀዲ ንጉሥ በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበለች ቅድስት ሰብልትንያ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን ። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከመነኰስ ያዕቆብ፣ ከኤጲስቆጶስ ከአናቲሞስ ከባስሊስና ከአሮጦስ ከውርዋና፣ ከሳውልስ ከሰማዕቱ ከሰውላስም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱
🔥2🥰1
 🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን ስለ ተዋሕዶ ሃይማኖት በጉባኤ ኬልቄዶን (ከለባት)  በ_451 ዓ.ም በንጉሥ መርቅያኖስና በሚስቱ በንግሥት ብርክልያ (በሊዮናውያን) ጢሙን ለተነጨና ጥርሱንም ለተነቀለ  ለእስክድርያ ሃያ አምስተኛ ጳጳስ #ለታላቁ_ሊቅ_ለአቡነ_ዲዮስቆሮስ ለዕረፍት በዓል፣ ለገብላ ኤጴስቆጶስ ለከበረ አባት #ለአባ_ሳዊርያኖስ ለዕረፍት በዓል፣ ለከበሩ #ቅዱሳን_ሰማዕታት_ለአጋቶንና #ጴጥሮስ_ለዮሐንስና_ለአሞን_ለእናታቸው_ራፈቃ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦#ከቅዱስ_ፋሲለደስ ጋር በሰማዕትነት ከዐረፉ #ከሁለት_ሺህ_ሰዎች፣ ከጋንግራ ሰው #ዳሳ #ከአንጾኪያ_ኤጲስቆጶስ_ከናውላ፣ ከመነኵሴውም #ከአባ_ጴጥሮስ_ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

@efeson_2

🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱
1🥰1
መስከረም ፯ /7/


‎በዚህች ቀን የመጥምቁ ዮሐንስ እናት፤ የከበረች ኤልሳቤጥ አረፈች።

‎ቅድስት ኤልሳቤጥ እድሜዋ በደረሰ ግዜ ካህን ለሆነው ለቅዱስ ዘካርያስ አጋቧት። ነገር ግን እስከ እርጅና ዘመናቸው ልጅ መውለድ አልቻሉም ነበር። የኤልሳቤጥ እድሜ 90 የዘካርያስም 100 ደርሶ ነበር። እግዚአብሔርም ትዕግስታቸውን እና ጽድቃቸውን ተመልክቶ በመልዐኩ ገብርኤል አብሳሪነት ታላቅ የሆነ ነቢይን ሰጣቸው።

‎የኤልሳቤጥ የስድስት ወር ጽንስም የድንግል ማርያምን ድምጽ በሰማ ግዜ በደስታ ዘሏል። ቅዱስ ዮሐንስም 2 ዓመት ከ6 ወር በሞላው ግዜም ንጉስ ሔሮድስ የተወለደውን ንጉስ ለማጥፋት ተነሳ። አይሁዶችም ለንጉሱ
‎ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ ሲወለድ ደግሞ የከፈተ ዮሐንስ የሚባል አለና እርሱን ግደል አሉት።

‎ቅድስት ኤልሳቤጥም ቅዱስ ዮሐንስን ይዛው ሸሸች። አባቱ ካህኑ ዘካርያስን ግን በቤተመቅደስ ውስጥ ገደሉት። ቅድስት ኤልሳቤጥም ዮሐንስን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ3 ዓመታት ቆየች። ቅዱስ ዮሐንስም 5 ዓመት በሞላው ግዜ በዚህች ዕለት ቅድስት ኤልሳቤጥ በዚያው በበርሃ አረፈች። በረከቷ ይደርብን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
🔥1🥰1
መስከረም ፰

በዚህች ቀን ደግሞ የእግዚአብሔር ሰው የሆነ፤ ቅን፤ የዋህ፤ ጻድቅ፤ የነቢያት አለቃ የቅዱስ ሙሴ ዕረፍቱ ነው።

ከኮከብም ኮከብ እንደሚበልጥ ከነቢያት ሁሉ ደግሞ ቅዱስ ሙሴ ይበልጣል። የቅዱስ ሙሴ አባት እንበረም እናቱ ደግሞ ዮካብድ ይባላሉ። ቅዱስ ሙሴ በተወለደ ወቅትም የእስራኤል ወንድ ልጆች ይገደሉ ነበር። ወላጆቹም እርሱን ለማሸሽ ሲሉ ገና በ3ወሩ በግብጽ /ዓባይ/ ወንዝ ውስጥ ጣሉት።

የፈርዖን ልጅም ከወንዝ ላይ ባገኘችው ግዜ ለእርሷ ልጅ ይሆናት ዘንድ ወስዳ በመልካም አስተዳደግ አሳደገችው። ስሙንም ሙሴ ያለችው እርሷ ናት፤ ትርጉሙም ከውሃ የተገኘ ማለት ነው። ወላጆቹ ግን በተወለደ ወቅት ፊቱ ያበራ ነበርና ምልክአም ብለው ስም አውጥተውለት ነበር። እናቱ ዮካብድም በሞግዚትነት ገብታ ልጇን ማንም ሳያውቅ አሳድጋዋለች።

በቅዱስ መጽሐፍ እንደምናነበው ቅዱስ ሙሴ ኮልታፋ ነው፤ ይህም ገና በ5 አመቱ ፈርኦንን በጥፊ በመምታቱ እሳት አበሉት በዚህም ኮልታፋ ሆኖ ቀርቷል። 40 አመት በሞላው ግዜም አንድ የግብጽ ሰው አንዱን ዕብራዊ ሲያጠቃው ተመልክቶ ለዕብራዊው ተበቅሎ ግብጻዊውን ገደለው ከዚያም ወደ ምድያም ሸሽቷል።

ቅዱስ ሙሴ በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ግብጻውያን ላይ ዘጠኝ መቅሰፍት በአስረኛውም ሞተ በኩር መታ። እሥራኤልንም ነጻ አወጣ። መልካም ተጋድሎንም ፈጽሞ በዚህች ዕለት ዐረፈ። በረከቱ ይደርብን! አሜን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
‎መስከረም ፱ /9/


‎በዚህች ቀን መጺል የምትባል አገር ኤጲስ ቆጶስ፤ ቅዱስ አባት አባ ቢሶራ በሰማዕትነት አረፈ።

‎በወቅቱ ዲዮቅልጥያኖስ የተባለ ክፉ ሰው ንጉስ የነበረበት ግዜ ነበር። በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከሰይጣን ቀጥሎ እንደዚህ የከፋ ስም የለም። የዓለም ክርስቲያኖችን የጨፈጨፈ ሰው ነው። መከራውም እየገፋ ሲመጣ ቅዱሱ በመፍራት ፈንታ የሰማዕትነት ፍቅር አደረበት:: በክርስቶስ ስም ደሙን ያፈስ ዘንድ ወደደ።

‎ሕዝቡንም ሰብስቦ አቆማቸው፤ ሊጠብቁት የሚገባውን ለጽድቅ የሚያበቃቸውን ትዕዛዝ ሁሉ አዘዛቸው። ከዚህም በኋላ ለሰማዕትነት እንደተዘጋጀ ነገራቸው። ይህንንም በሰሙ ግዜ ሁሉም አለቀሱ። የሙት ልጆች እንሆን ዘንድ ለምን ትተወናለህ፤ እንድትሄድ አንለቅህም አሉት ሊይዙትም ቃጡ። ቅዱሱም ሰላምታ ሰጥቷቸው ከእነርሱ ዘንድ ወጥቶ ተጓዘ። አንዳንድ አባቶችም አብረን እንሞታለን ብለው አብረውት ሄዱ።

‎በኋላም መኰንኑ ጽኑ የሆነ መከራ አደረሰባቸው ፤አባቶች ግን በታላቅ ትዕግስት ጸኑ። ከዚህም በኋላ ራሶቻቸውንም በሰይፍ ይቆርጧቸው ዘንድ  አዘዘ። በዚህች ዕለትም የሕይወት አክሊልን በመንግስተ ሰማያት ተቀበሉ።

‎በረከታቸው ይደርብን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
🔥1
በሰው ላይ አትፍረድ ያ ሰው በምን አይነት መከራ እና ስቃይ ውስጥ እያለፈ እንደሆነ አታውቅምና

አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ
3
‎መስከረም ፲ /10/


‎በዚህች ዕለት ጼዴንያ በምትባል አገር ሥጋ የለበሰች ከምትመስል፤ ከሠሌዳዋም ቅባት የሚንጠፈጠፍባት የእመቤታችን የድንግል ማርያም ሥዕል ተዐምር ተገለጠ።

‎ይህችን ሥዕል የሳላት ቅዱስ ሉቃስ ነው። ወደ ጸዴንያ እንዴት መጣች ቢሉ፤ አንዲት ማርታ የምትባል ሴት ነበረች በቤቷም እንግዳ ትቀበል ነበር። ድንግል ማርያምንም አብዝታ ትወዳት ነበር። በአንዲት ቀንም ስሙ ቴዎድሮስ የሚባል መነኩሴ በእንግድነት መጣ። በማግስቱ ስትሸኘው ወዴት ነህ ብላ ጠየቀችው። እርሱም ወደ ኢየሩሳሌም እንደሆነ ነገራት። እርሷም ሲመለስ የእመቤታችንን ሥዕል አምጣልኝ አለችው።

‎ከዚህም በኋላ ከቦታው ደርሶ ሥዕሏን ሳይገዛ ተመለሰ፤ በመንገድም ሥዕሏን ለምን አልገዛህም? የሚል ድምጽ ሰምቶ ተመልሶ ገዛ። በጎዳናው እየተመለሰ ሳለም የሚያስፈሩ ወንበዴዎች፤ ኋላም አንበሳ ገጠመው፤ የያዛት ሥዕልም ቃል አውጥታ አዳነችው። አባ ቴዎድሮስም ይህን ድንቅ ተአምር ባየ ግዜ ሥዕሏን ወደ ሀገሩ ሊወስዳት ወደደ። በሌላ ከተማም አድርጎ ሊሄድ መርከብ ተሳፈረ።

‎በመርከቧ ሳለም ታላቅ ነፋስ ተነስቶ አቅጣጫውን አስቀይሮ ወደ ጸዴንያ ወሰደው። ኋላም ቢመሽበት ማርታ ቤት ሄደ እራሱን ግን አልገለጠም። በማግስቱም ተሰውሮ ከከተማው ሊወጣ ቢሞክር መውጫው ጠፍቶት ሲዞር ውሎ ተመለሰ። እንዲህም እያለ ሶስት ቀን ሆነው። ማርታም ይህን ተመልክታ ምን እንደሆነ ጠየቀችው። እርሱም ሁሉንም ነገራት።

በኋላም የመነኩሴውን እጅና እግር ስማ ሥዕሏን ተቀበለች። በታላቅ ክብርም አስቀመጠቻት። ያም መነኩሴ እስከሚሞትበት ቀን ድረስ የእመቤታችን ድንግል ማርያምን ሥዕል እያገለገለ ኖረ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
‎ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
ሰላም ለሥዕልኪ ፥ ሶበ ጸለየት ማርታ
አጽነነት ርዕሳ ከመ_ትትመጠው ስእለታ
ምክሐ ታዴዎስ አንቲ ማርያም ፤ ወሞገሰ ቶማስ ስሙየ መንታ። አመ ኢታድኅን ፥ እም ወለታ ፤ ወአመ_ታገብእ ምድር ማኅፀንታ ፤ ኵንኒ_ለመዋቲ ሐገፋ ወወልታ።

◈◈_◈◈◈_◈◈◈◈_◈◈◈◈◈__◈◈
ስሙ ሁለት የሆነ ፥ የቶማስና ፥ የሐዋርያው የታዴዎስ ትምክህት ማርያም ሆይ ፥ (በጼዴንያ አገር የምትኖር) ቅድስት ማርታ ፥ በጸለየች ጊዜ ፥ ጸሎቷን ለመስማት ራሷን ዘለስ ፥ ለአደረገች ሥዕለ_አድኅኖሽ ሰላም እላለሁ። ምድር አደራዋን ስትመልስ ፣ እናትም ፥ ሴት ልጇን በማታድንበት ዕለት ፣ ያን ዕለት ለሟች ለእኔ መደገፊያና ጋሻ ሁኚኝ።

መልክዓ_ስዕል
2


አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መስከረም ዐሥራ አራት በዚህች ቀን ቅዱስ አባት አባ አጋቶን ዘዓምድ አረፈ።

ይህም ቅዱስ ለግብጽ አገር ደቡብ ከሆነ ተንሳ ከሚባል መንደር የሆነ ነው፤ ወላጆቹም እግዚአብሔርን የሚፈሩ ለድኆችና ለችግረኞች መመጽወትን የሚወዱ ደጎችና ቸሮች ነበሩ። የአባቱም ስም መጥራ የእናቱም ስም ማርያ ነው የምንኵስና ልብስን ይለብስ ዘንድ የሚተጋና በልቡም ሁል ጊዜ የሚያስብና የሚታወክ ሆነ። ዕድሜውም ሠላሳ አምስት ዓመት በሆነው ጊዜ ቅስና ተሾመ ከዚህ ዓለምም የሚወጣበትን መንገድ ይጠርግለት ዘንድ ወደ ገዳም ሒዶ በዚያ እንዲመነኵስ እግዚአብሔርን እየለመነው የከበረች ቤተ ክርስቲያንን በማገልገል የተጠመደ ሆነ። ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት ሰጥቶት ከሀገሩ ወጣ መርዩጥ ወደሚባልም አገር ገባ ከዚያም ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ በመነኰስ አምሳል ከእርሱ ጋር በመጓዝ ወደ ቅዱስ አባ መቃርስ ገዳም እስከ አደረሰው ድረስ እየመራው ወደ እስቄጥስ ገዳም ሔደ። ለከበሩ አረጋውያንም ለአባ አብርሃምና ለአባ ገዐርጊ ደቀመዝሙር ሁኖ ከእሳቸው ጋር ሦስት ዓመት ያህል ኖረ። ከዚህም በኋላ በአባ ዮሐንስ ቤተ መቅደስ ፊት አቆሙት በምንኵስናው ልብስና በአስኬማው ላይ ሦስት ቀኖች ያህል ጸልየው አለበሱት ከዚያችም ቀን ወዲህ ተጋድሎውንና የእግዚአብሔርን አገልግሎት እጥፍ ድርብ አደረገ። ተጋድሎውም ሁል ጊዜ በቀንና በሌሊት በመጾም፥ በመጸለይ፥ የሥጋው ቆዳ ከዐጥንቱ እስኪጣበቅ ያለ ምንጣፍም በምድር ላይ በመተኛት ሆነ። ሁል ጊዜም የአባ ስምዖን ዘዓምድን ገድል ያነብ ነበረ መንፈሳዊ ቅናትንም ቀንቶ ራሱን በገድል እሥረኛ ሊያደርግ በልቡ አስቦ ለከበሩ አባቶች አማከራቸው እነርሱም ይህ ሀሳብ መልካም ነው አሉት በላዩም ጸለዩ ከእርሳቸውም በረከትን ተቀብሎ ከገዳም ወጣ ለዓለም ቅርብ ወደ ሆነ ስካ ወደሚባል አገር ሒዶ በአንዲት ትንሽ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተቀመጠ ምእመናንም ዓምድ ሠሩለት። በዚያ ላይም ወጥቶ እየተጋደለና እያገለገለ ሃምሳ ዓመት ያህል ቆመ። በዘመኑም ሰይጣን ያደረበት ሰው ተገለጠ ብዙ ወገኖችንም አሳታቸው እርሱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚቀመጥ ሁኖ ትምህርቱን የሚሰሙ ሕዝቦች የዕንጨት ቅርንጫፎችን በመያዝ በዙሪያው ይቀመጣሉ አባ አጋቶንም ልኮ ወደእርሱ አስመጣው በላዩም ጸለየና በሰውዬው ላይ አድሮ ለሰዎች በመናገር የሚያስተውን ሰይጣን ከእርሱ አስወጣው። እንዲሁም ሰማዕት ሚናስ ያነጋግረኛል የምትል ሴት ተነሥታ በቅዱስ ሚናስ ስም የውኃ ጒድጓድ እንዲቆፍሩ በጠበሉ ውኃ ተጠምቀው ከደዌያቸው እንዲፈወሱ የአገርዋን ሰዎች አዘዘቻቸው ያቺንም ሴት ወደርሱ አስመጥቶ በላይዋ ጸለየ ርኵስ መንፈስንም ከእርሷ አስወጣው። ዳግመኛም ሌላ ሰው ተነሣ እርሱም ጋኔን ይዞ ያሳበዳቸውን ሰበሰባቸው ሲደበድባቸውም ለጥቂት ጊዜ ጋኔኑን ያስተዋቸዋል ብዙዎችም ጋኔን የያዛቸው ወደእርሱ ተሰበሰቡ ቅዱስ አባ አጋቶንም ወደእርሱ እንዲመጣ ወደ ሰውዬው ላከ ሰውዬውም ትእዛዙን ሰምቶ አልመጣም የስሕተት ሥራውንም አልተወም። የዚያችም አገር ገዥ ሲያልፍ የሰበሰባቸው እብዶች ሰደቡት ረገሙትም ስለዚህ ያን ሰው መኰንኑ ይዞ ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየውና በሥቃዩ ውስጥ ሞተ። ሌላው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንድ ቄስ ነበረ እርሱም ከአንዲት ሴት ጋር በዝሙት ወደቀ የአካሉም እኩሌታ በደዌ ተበላሸ ተሸክመውም ወደ አባ አጋቶን አደረሱት እርሱም ጸልዮለት በእግዚአብሔር ስም አዳነው ያንንም ቄስ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ እንዲጠነቀቅና በክህነቱም እንዳያገለግል አዘዘው። ይህም ቅዱስ አባ አጋቶን ብዙ ተአምራትን አደረገ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳናቸው።

@efeson_2

ከዚህም በኋላ በመላእክት አምሳል በመልካም ዝማሬ በመዘመር እያመሰገኑት ሰይጣናት ተገለጡለት እርሱ ግን የክብር ባለቤት ክርስቶስ በሰጠው ጸጋ ሽንገላቸውን አውቆ አዳኝ በሆነ በመስቀል ምልክት አማተበባቸው ፈጥነውም ከፊቱ ተበተኑ። ክብር ይግባውና እግዚአብሔርም ከዚህ ዓለም ድካም ሊያሳርፈው በወደደ ጊዜ ጥቂት ታሞ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ አስረከበ። ከዚህም በፊት ሕዝቡ ወደእርሱ ይሰበሰቡና የእግዚአብሔርን መንገድ ያስተምራቸውና በጸሎቱም ከበሽታቸው ይፈውሳቸው ስለነበር አሁን በአረፈበት ላይ በአገኙት ጊዜ መሪር ልቅሶን አለቀሱ እነርሱ የሚያጽናናቸውን አባታቸውን በማጣት ከእርሱ ከቅዱስ አባት በመለየት የሙት ልጆች ሁነዋልና።
መላው የሕይወቱ ዘመንም መቶ ዓመት ሆነ ከርሱም ሠላሳ አምስቱን በዓለም ውስጥ ኖረ። ዐሥራ አምስቱን ዓመት በገዳም ኖረ አምሳውን በዓምድ ላይ ቁሞ ኖረ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛ ንም በዚህ ጻድቅ ጸሎት ይማረን በረከ ቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።



በዚህችም ቀን ቀሲስ ዴግና አረፈ። ደግሞ የሰማዕት መቃራ፥ የበርተሎሜዎስ፥ የአውዳራና የናሶን መታሰቢያቸው ነው። እግዚ አብሔርም በጸሎታቸው ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

@efeson_2



በዚህችም ቀን ደግሞ የፃና መምህራን ለሆኑ አባቶች ዐሥራ አንደኛ የሆነ የፃና መምህር ቅዱስ አባት አባ ጴጥሮስ አረፈ።

ይህም በሥራው ሁሉ እውነተኛና ንጹሕ በቀንና በሌሊትም በጾምና በጸሎት የተጠመደ ሆነ። ሕዝቡም በጎ ሥራውንና ቅድስናውን በአዩ ጊዜ ለመምህርነት መርጠው ሾሙትና በሹመቱ ወንበር አርባ ስምንት ዓመት በሰማዕት ገላውዴዎስ መቅደስ ኖረ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሁሉ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

                     🙏አሜን።🙏

@efeson_2

🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
🔥1🥰1
መስከረም ፲፭ /15/


በዚችም ቀን ጠራው ከሚባል አገር ለከበረ ጻድቅ አባት አባ ጴጥሮስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ። ይህም ቅዱስ ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተሰጠ የስእለት ልጅ ነው። በአደገም ጊዜ ለታላቅ ተጋድሎ ከልቡ በቆራጥነት ተነሣ። በቀንና በሌሊትም በጾም በጸሎት ተወስኖ ሁል ጊዜ እግዚአብሔርን የሚያገለግል ሆነ።

ሰው የሚመገበውንም ምንም አይመገብም በዱር ያገኘውን ጥቂት ሣርን ይመገባል እንጂ። ደገኛው ምግቡ ግን ክብር ይግባውና የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ማመስገን ነበረ። በዚህም ምግባቸው የእግዚአብሔር ምስጋና የሆነ መላእክትን መሰላቸው።

አሎን በሚባል የወንዝ ውኃ ላይም ይመላለስ ዘንድ ውሀ ውስጥ የገቡት እግሮቹ አይርሱም ነበር ሥጋ እንደሌለው መንፈስ እስከሚሆን በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ከችግር ብዛትና ከሚለብሰው የብረት ልብስ ክብደት የተነሣ ሥጋው እጅግ ደርቆ የረቀቀም ሁኖ ነበርና በእንዲህ ያለ ተጋድሎም እግዚአብሔርን ከአገለገለው በኋላ በዚህች ቀን በክብር አርፏል።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2

🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊
​​መስከረም ፲፮ የደመራ ክብረ በዓል


ጥንተ ጠላታችን ዲያቢሎስ የቅዱስ መስቀሉን ሀይል ስለሚያውቅ አጥብቆ ይቃወመዋል፤ ስለዚህም አይሁድን አነሳሥቶ ከ፫፻ ዓመታት በላይ ተቀብሮ እንዲቆይ አድርጓል፡፡

ቀራንዮም ለመስቀሉ መትከያነት የተመረጠችውም ቀዳሜ ፍጥረት አዳም የተቀበረው በዚያ ስለ ነበረ ነው፡፡ ቦታው ‹‹የራስ ቅል ሥፍራ›› /ማቴ.፳፯፥፴፪/ መባሉም የኹላችን ራስ አዳም ዓፅሙ በዚያ ስላረፈ ነው፡፡ መስቀሉ በአዳማውያን ፍጥረታት አእምሮ ውስጥ እንጂ ከዚያ ውጪ የሚኖር ባለመኾኑ ተቀብሮ በቆየባቸው ዓመታት ውስጥም ፍቅሩ ከሰው ልጆች ልቡና አልወጣም፡፡

ጠላት በሠራው ተንኮል ተቀብሮ እንዳይቀር መስቀሉን እንድታወጣ መንፈስ ቅዱስ ንግሥት ዕሌኒን አስነሣት፡፡

ንግሥት ዕሌኒም የመስቀሉን ነገር ታስብ፤ ብርሃነ መስቀሉም ዘወትር በልቧ ያንጸባርቅ ነበር፡፡ ሐሳቧን እንዲያሳካላት የለመነችው አምላክም ኪራኮስ የተባለውን አይሁዳዊ ሽማግሌ ልኮ አቅጣጫውን አመላከታት፤ ኪራኮስ የጀመረውን ምሥጢርም መልአኩ ‹‹ደመራ ደምረሽ፣ ሰንድሮስ የሚባል ነጭ ዕጣን ጨምረሽ አቃጥዪው›› ብሎ ተረጐመላት፡፡ እርሷም መልአኩ እንደ ነገራት መስከረም ፲፮ በዕኩለ ሌሊት ደመራን ብታደርግ ጢሱ ሰማይ ደርሶ ወደ ምድር ተመልሶ መስቀሉ ወደሚገኝበት ተራራ ሰገደ፡፡ በጢሱ ምልክትነት መስከረም ፲፯ ቀን የተጀመረው ቍፋሮ መጋቢት ፲ ቀን አልቆ ዕሌኒ መስቀሉን ከልበ ምድር ለማውጣት ችላለች።

መልካም በዓል ያድርግልን።
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
       @efeson_2

🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉
🔥1
መስከረም ፳ /20/

በዚህች ቀን ለሊቃነ ጳጳሳት ሃያ ስምንተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባት አትናቴዎስ አረፈ።

ይህም አባት አስቀድሞ የእስክንድርያ አገር ቤተክርስቲያን መጋቢ ነበር፤ ከእርሱም በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ ጴጥሮስ በአረፈ ጊዜ ይህን አባት ሊቀ ጵጵስና ይሾሙት ዘንድ ሁሉም ኤጲስቆጶሳት መኳንንቱና ሊቃውንቱ ሕዝቡም በአንድ ምክር ተስማሙ።

በእግዚአብሔር ሕግ በመጽናት ያደረገው መልካም ተጋድሎውና ቅድስናው ስለእርሱ ስለተነገረ መንፈስ ቅዱስም እንደ አደረበት ስለ ተረዱ ያለ ፈቃዱም ወስደው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት

ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና የክርስቶስን መንጋዎች በምክሩ፣ በትምህርቱ፣ በጸሎቱ ከዲያብሎስ ተኵላዎች በመልካም አጠባበቅ ጠበቃቸው እኒህም ሃይማኖትን የሚለውጡ መናፍቃን ናቸው። በሊቀ ጵጵስናውም ፯ ዓመት ኖረ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።

በረከታቸው ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር

@efeson_2
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
🔥1
ውድ ወንድሜ ሰውን በስብከት ማገልገል የግድ ልብሰ ተክህኖ ለብሶ መድረክ ላይ መቆም ብቻ አይደለም፣ ትልቁና ዋነኛው ሰውን በራስ ሕይወት መለወጥ ነው፡፡ ስለዚህ በሕይወትህ ለብዙዎች አብነት እንድትሆን እንጂ የግድ ስብከት አዘጋጅተህ መድረክ ላይ መቆም ብቻ አይጠበቅብህም፡፡ እንዲህ አይነት ሰው ከሆንክ ሰዎች ፊትህን ባዩት ጊዜ የዋህነትን፣ ሩህሩህነትን ይማራሉ፣ ንግግርህንም በሰሙ ጊዜ መንፈሰ ጠንካራነት፣ ታማኝነት፣ ፍፁምነትና ፍቅርን ያገኛሉ፡፡

(ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ - ከመንፈስ ነፃነት የተወሰደ)

@efeson_2

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫