Forwarded from ነይ ነይ እምዬ ማርያም መዝሙሮች (𝓟𝓲𝓵𝓾𝓟𝓪𝓭𝓮𝓻)
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁
ነሐሴ 15:
እንኳን
#አምላክን_ለወለደችልን_እመቤታችን_ድንግል_ማርያም ሥጋዋን ለመግነዝ ሐዋርያት ለተሰበሰቡበት ዕለትና #ጌታችን_ከከበሩ_ቅዱሳን_መላእክቶቹ ጋር መጥቶ ላጠመቃት፣ #ቅዱስ_ሚካኤል_በእሳት_ጉጠት #ቅዱስ_ሥጋውን_ክቡር_ደሙን ላቀበላትና ዋስ ለሆናት በተአምራቷም #ሠላሳ_ሺህ_ዐሥራ_ሁለት ሰዎችን ላሳመነችው #ለመኰንን_ርባኖስ ልጅ #ለታላቋ_ሰማዕት_ለቅድስት_ክርስጢ ለዕረፍት በዓል፣ ሴት ሆና እንደ ወንድ መስላ ከወንዶች ገዳም ገብታ ገድሏን ለፈጸመች ታላቅ እናት #ለቅድስት_(ከአባ)_እንባመሪና ለዕረፍት በዓልና #በንጉሥ_ዳንዮስ_ቄሣር ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበለ #ለቅዱስ_ለውረንዮስ_ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪም በዚህች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከሠላሳ_ሺህ_ዐሥራ_ሁለት_ከቅድስት_ክርስጢና_ማኅበረ_ሰማዕታት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
@efeson_2

🔥1
ነሐሴ 15/12/2017 ዓ.ም
✝ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።
፩ ቆሮ ም ፲፪ ቁ ፲፰-ፍ.ም
ይሁዳ ም ፩ ቁ ፲፯-ፍ.ም
ግብ.ሐዋ ም ፩ ቁ ፲፪-፲፭
ውስተ ኩሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ
ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ
ወውስተ ፀሐይ ሤመ ጽላሎቶ
ትርጉም
ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ
ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ
በእነሱም ውስጥ የፀሐይን ድንኳን አደረገ
ወንጌል - ማቴ ፲ ÷ ፩-፲፭
ቅዳሴ - ዘሐዋርያት
@efeson_2
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
✝ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።
፩ ቆሮ ም ፲፪ ቁ ፲፰-ፍ.ም
ይሁዳ ም ፩ ቁ ፲፯-ፍ.ም
ግብ.ሐዋ ም ፩ ቁ ፲፪-፲፭
ምስባክ - መዝ ፲፰-፬
ውስተ ኩሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ
ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ
ወውስተ ፀሐይ ሤመ ጽላሎቶ
ትርጉም
ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ
ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ
በእነሱም ውስጥ የፀሐይን ድንኳን አደረገ
ወንጌል - ማቴ ፲ ÷ ፩-፲፭
ቅዳሴ - ዘሐዋርያት
@efeson_2
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
❤1🔥1
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁
ነሐሴ 17:
እንኳን
#ለአሞራዊው_ለቅዱስ_እንጣዎስ_ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና ከደቡብ ግብጽ አቡስ ከሚባል አውራጃ መኑፍ ከሚባል ታናሽ መንደር #ለቅዱስ_ያዕቆብ_ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በጨማሪም በዚህች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱስ_እንጣዎስ ከወንድሙ #ከቅዱስ_አክራጥስ_ከዕረፍቱ መታሰቢያ፣ #ከቅዱስ_ያዕቀብ ጋር ሰማዕትነት ከተቀበሉ ከገምኑዲ ሀገር ከሆኑ #ቅዱሳን_አብርሃምና_ዮሐንስ #ከቁስጥንጥንያ_ሊቀጳጳሳት_ከእለእስክድሮስ_ከዕረፍቱ መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

🔥2
ነሐሴ ፲፯ /17/
በዚች ቀን አሞራዊ ቅዱስ እንጣዎስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ አስቀድሞ ክርስቶስን የካደ ገንዘብ ለማከማቸትም የሚተጋ ነበር። በአንዲትም ዕለት ወደ ደማስቆ ከተማ ሔደ የበዓላቸው ቀን ነበርና ሕዝቡ ተሰብስበው ሳሉ ወደ ምሥራቃዊው ቅዱስ ቴዎድሮስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገባ ዕቃዎችን ማቃጠል ጀመረ መስቀልንም ሰበረ።
እግዚአብሔር በቸርነቱ አምኖ ይጠመቅ ዘንድ ምልክትን አሳየው እና ከእርሱም ጋራ ብዙዎች አብረው ተጠመቁ።
ከዚህም በኋላ በደማስቆ ጐዳና ሲጓዝ አስቀድሞ የሚያውቁት ያዙት ወደ ንጉሡም ወሰዱት ንጉሡም ክርስቶስን በማመን እንደጸና አይቶ ጥርሶቹ እስቲበተኑ አፉን በበሎታ እንዲመቱት አዘዘ አፉም ደምን ተመላ። ከዚህም በኋላ እህል ውኃን ሳይሰጡ በተበሳ ግንድ ውስጥ ሰባት ቀን ያህል አሠሩት ከዚያም አውጥተው ዲን፣ ሙጫ፣ ዝፍት ከስብ ጋራ ባፈሉበት እሳት ውስጥ ጨመሩት ከእርሱም የመልካም መዓዛ ሽታ ወጣ።
ወታደሮችም ከእሳት ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ አገኙት ። እሳቱም አልነካውም ንጉሡም የሥራይን ኃይል መቼ ተማርክ አለው ቅዱስ እንጣዎስም ንጉሡን እንዲህ አለው ሥራይንስ አላውቅም ነገር ግን ክብር ይግባውና በጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል አሳፍርሃለሁ።
ንጉሡም ቁጣን ተመልቶ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። ከዚህም በኋላ ቅዱስ እንጣዎስ ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ ቆመ እጆቹንም ዘርግቶ ነፍሱን ወደ እግዚአብሔር አማፀነ ሲጸልይም ወደርሱ እንዲህ የሚል ቃል መጣ ከእስጢፋኖስና ከጊዮርጊስ ጋራ ታርፍ ዘንድ አገልጋዬ በሰላም ና። ጸሎቱንም በፈጸመ ጊዜ ራሱን ቆረጡት ምስክርነቱንም ፈጸመ ከሥጋውም ቁጥር የሌላቸው ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
@efeson_2
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫

ነሐሴ ፲፱ /19/
በዚች ቀን ሳስዊር ከሚባል አገር ወደ አስቄጥስ ገዳም የታላቁ አባ መቃርስ የሥጋው ፍልሰት ሆነ።
ከዕረፍቱ በኋላ ከሀገሩ ከሳስዊር ሰዎች መጥተው ሥጋውን ሰርቀው ወደ ሀገራቸው ወሰዱት ቤተ ክርስቲያንም ሠርተውለት ሥጋውን በዚያ አኖሩት እስላሞች እስከ ነገሡበት ዘመንም በዚያ ኖረ ።
ከዚህም በኋላ ወደ ሌላ ቦታ አፍልሰውት በዚያም ቤተ ክርስቲያን ሠሩለት ። ለአባ መቃርስ ገዳም አበ ምኔት ሁኖ አባ ዮሐንስ እስከ ተሾመበት ዘመን ኖረ ።
ሊቀ ጳጳሳቱም የከበረች ጾመ አርብዓን ሊጾም ወደ አባ መቃርስ ገዳም በወጣ ጊዜ ፈጽሞ አለቀሰ እንዲህም ብሎ ጸለየ ። ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የከበረ የአባ መቃርስ ሥጋ በዚህ ገዳም በመካከላችን ይሆን ዘንድ እንድትረዳኝ እመኛለሁ። እግዚአብሔርም ይህን ጸሎቱን ሰምቶት የቅዱሱን ሥጋ እንዲያገኝ አስቻለው።
ባገኘውም ጊዜ በየት እንደሚያኖረው ሲያስብ የአባ መቃርስን ሥጋ የተሸከመ ግመል ወደ አንድ ቦታ ደርሶ በዚያ በረክ አለ ። የከበረ የአባ መቃርስ ሥጋ ያለበትንም ሣጥን ይጥል ዘንድ በራሱ ወዲያና ወዲህ ይዞር ጀመረ ። አረጋውያን መነኰሳትም እግዚአብሔር የፈቀደው ያ ቦታ እንደሆነ አወቁ እጅግም አደነቁ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት ያም ቦታ እስከ ዛሬ የታወቀ ነው ።
ወደ ገዳሙም በቀረቡ ጊዜ መነኰሳቱ ሁሉም ወጡ ወንጌልና መስቀሎችን ይዘው መብራቶችን እያበሩ እየዘመሩና እያመሰገኑ ወደ ቤተ ክርስቲያን እስከ አስገቡት ድረስ በታላቅ ክብር በራሳቸው ተሸክመው ወሰዱት። እግዚአብሔርም በዚያች ሌሊት ተአምራትን አደረገ ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
@efeson_2
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
🔥2🥰1
Forwarded from ነይ ነይ እምዬ ማርያም መዝሙሮች (𝓟𝓲𝓵𝓾𝓟𝓪𝓭𝓮𝓻)
➕ Old telegram group ያለው ማለትም ከተከፈቶ የቆየ Group ያለው እገዛለሁ በውስጥ አናግሩኝ ::
አጭበርባሪዎች ስለበዙ ከአጭበርባሪዎች እራሶን ይጠብቁ
👍Member 1 ቢሆንም ችግር የለውም
ማሳሰቢያ
1.መጀመሪያ owner ማያስተላልፍ አይምጣ.
2.Two step verification ሳትጨርሱ አትምጡ
🥀ከፍታቹ የረሳቹት ማትጠቀሙበት Group ካላቹ በውስጥ አናግሩኝ⤵️⤵️⤵️⤵️
ያላችሁ አምጡ 👉 @Pilu_pilu_p
ልታደክሙ አትምጡ ለስራ ይምጡ
2023 - 600 ብር
ከ 2018 እስከ 2022 - 800 ብር
አጭበርባሪዎች ስለበዙ ከአጭበርባሪዎች እራሶን ይጠብቁ
👍Member 1 ቢሆንም ችግር የለውም
ማሳሰቢያ
1.መጀመሪያ owner ማያስተላልፍ አይምጣ.
2.Two step verification ሳትጨርሱ አትምጡ
🥰 ታማኝነት መለያችን ነው ስጋት አይግባችሁ::
‼️ እጅህ ላይ እያለ old gruop ከሚቀመጥ ና እኔ ልግዛህ መሸጥ የምትፈልጉ ብቻ አናግሩኝ እምነት መታወቂያችን ነዉ first payment ምትሉ አታድክሙኝ ከምንጨቃጨቅ አትምጡ አልገዛችሁም ::
በናንተ ባለቤትነት ስር ያሉ የተረሱ ግሩፖችን ቼክ ለማድረግ 👇በውስጥ ጠይቁኝ እድኛ ጋር መፍትሄ አለ
🥀ከፍታቹ የረሳቹት ማትጠቀሙበት Group ካላቹ በውስጥ አናግሩኝ⤵️⤵️⤵️⤵️
ያላችሁ አምጡ 👉 @Pilu_pilu_p
ልታደክሙ አትምጡ ለስራ ይምጡ
ነሐሴ ፴ /30/
በዚህች ዕለት ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ የሆነው ታላቁ ነቢይ ሚልክያስ አረፈ።
እግዚአብሔር አምላክ በነቢዩ አንደበት አድሮ እንዲህ ይለናል።
ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም። የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው። ትንቢተ ሚልክያስ 3:8
እንዴት አድርጌ ነው ከ5ሺህ ብር ደሞዝ በዛ ላይ የኑሮ ውድነቱ ተጨምሮበት አስራት የማወጣው? ብላችሁ ብትጠይቁም እግዚአብሔር በነቢዩ አድሮ እንዲህ ይለናል።
በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፤ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። ትንቢተ ሚልክያስ 3:10
ቅዱስ ሚልክያስም በበጎ ተጋድሎው እግዚአብሔርን ከአገለገለ በኋላ በዛሬዋ ዕለት ከዚህ ዓለም በመፍለስ በሰላም አረፈ። ሚልክያስ ማለት መልዐክ አንድም የተላከ ማለት ነው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
@efeson_2
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴
እንኳን
#የመላእክት_አለቃ_የከበረ_መልአክ_የሩፋኤል_የበዓሉ_መታሰቢያ ቀን። #ለእግዚአብሔር_ልጅ_ምሳሌው የሆነ #የመልከጼዴቅ_መታሰቢያው በዓል። ሰንዱን ከሚባል አገር ለዐረፈ #ለቅዱስ_ሰራጵዮን_ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል አደረሰን። በተጨማሪም በዚህች ቀን፡- የኢትዮጵያ ንጉሥ መልካም ስም አጠራር ያለው #አጼ_ዘርዐ_ያዕቆብ_የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። እግዚአብሔር አምላክ ከቅዱሳኑ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
@efeson_2
🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜🔱⚜

#ለቅዱስ_አባ_ባይሞን እና ለስድስቱ ወንድሞቹ (#አብርሃም_ያዕቆብ_ዮሴፍ_ኢዮብ_ባስልዮስ_እና_ዮሐንስ) ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪም በዚህች ቀን ከሚታሰብ #የቅዱስ_ሊባርዮስ_ሊቅ_የዕረፍቱ_መታሰቢያ ነው። እግዚአብሔር አምላክ ከቅዱሳኑ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
@efeson

ጳጉሜ ፬ /4/
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም ጷጉሜ አራት በዚች ቀን ተጋዳይ አባ ባይሞን አረፈ።
አባ ባይሞን የተባረኩ ስድስት መነኮሳት ወንድሞች ያሉት ሲሆን እርሱ ሰባተኛና የመጨረሻ ልጅ ነው። የሁሉም ታናሽ ቢሆንም በዕውቀትና በጥበብ ግን ታላቃቸው ነበር።
መንፈስ ቅዱስ አነሳስቷቸው ሁሉም በአንድ ቀን መነኮሱ። ይህን ዓለም ንቀው የክብር ባለቤት የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቀንበር ተሸክመው በጠባብ መንገድ ተጓዙ።
አባ ባይሞን በአስቄጥስ ገዳም ፈተና፣ የሃይማኖት ጥርጥርና ደዌ ያገኘውን ሁሉ ይፈውስ፣ያረጋጋም ነበር።
ስለ ምንኩስና ሕግ፣ስለ መጋደል እና ስለ አምልኮም ብዙ ድርሳናትን ደረሰ። ዕድሜውንም በተጋድሎና በትሩፋት ሥራ ከፈጸመ በኋላ ወደ መልካም ዕርግና ደርሶ እግዚአብሔርን አገልግሎ አረፈ።
"እኛ የወንድማችንን በደል ብንሰውር እግዚአብሔርም በደላችንን ይሠውርልናል።"
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@efeson_2
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
🔥1
🌼 🌿✨🌼 🌿✨🌼 🌿✨🌼 🌿✨
እንኳን ለታላቁ ነብይ ሰማዕት ሐዋርያ ካህን ለመጥምቀ መለኮት ለሰማዕቱ ለቅዱስ ዮሐንስ ሕግ አፍራሽ በሆነ በንጉሥ ሄሮድስ እጅ አንገቱን በመሰየፍ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በዚች ቀን በጨማሪ ከሚታሰቡ፦ በግብጽ ውስጥ ታዕዳ ከሚባል አገር በሰማዕትነት ከዐረፈ ከቅዱስ ዳስያ ከሰማዕት ዲዲሞስና ቅድስትመሪና ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መስከረም ሦስት በዚህች ቀን የከበረ አባት ሊቀ ጳጳሳት አባ ዲዮናስዮስ ከተሾመ በሁለተኛው ዓመት በእስክንድርያ ከተማ የኤጲስቆ ጶሳት የአንድነት ጉባዔ ተደረገ።
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ይህም ጉባዔ የሆነው ነፍስ ከሥጋዋ ጋር ትሞታለች በዕለተ ትንሣኤም ከሥጋዋ ጋር አብራ ትነሣለች ስለሚሉ ክፉዎች በዐረቢያ አገር ስለተነሡ ሰዎች ነው።
@efeson_2
እነርሱም ለከፋችና ብልሹ ለሆነች ሃይማኖታቸው የፈጠራ ድርሰትን ደርሰው በእስክንድርያ ከተማ ወደሚኖሩ ሰዎች ላኩ። አባታችን ሊቀ ጳጳሳት አባ ዲዮናስዮስም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ ከዚህ ከክፉ ሥራም እንዲመለሱ አስተማራቸው ገሠጻቸውም እነርሱ ግን አልሰሙትም አልተመለሱም። ስለዚህም በእነርሱ ላይ ይህን ጉባዔ ሰብስቦ ተከራከራቸው ስሕተታቸውንም ገልጾ አስረዳቸው እነርሱ ግን ሰይጣን አሳውሯቸዋልና ተጸጽተው አልተመለሱም ይህም ጉባኤ ረግሞ ከቤተ ክርስቲ ያን አንድነት ለይቶ አሳደዳቸው። ይህም አባት ዲዮናስዮስ ስለእርሳቸው ድርሳናትን ደረሰ በውስጣቸውም እንዲህ የሚል "በዚህ በቸርነቱ ስጦታ ውስጥ የእግዚአብሔር ፍቅር የጎላ የተረዳ ሆነ ነፍስ ረቂቅ ስለሆነች እንደ መላእክት በሕይወት እንድትኖር እንጂ እንዳትሞት እንዳትጠፋ ማድረጉ ነው። ከሥጋዋም በምትወጣ ጊዜ ስለ በጎ ሥራዋ እንደሚገባት መጠን ወደ ሕይወት ቦታዋ ይወስዷታል ወይም እንደሥራዋ ክፉነት ወደ ሥቃይ ይወስዷታል። በትንሣኤ ቀንም 'ንቃሕ መዋቲ' ተብሎ ዓዋጅ ሲነገር በፈጣሪያቸው ትእዛዝ የሙታን በድኖች ሲነሡ ነፍሳት እንዲህ ይሆናሉ እያንዳንዲቱ ነፍስ ከሥጋዋ ተዋሕዳ አብራ ትነሣለች።"
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባቶቻችን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በዚህችም ቀን የገዳመ ሲሓት አባ ሙሴ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከመነኰሰ ጀምሮ ዓለምን ትቶ ከበረሀ ገብቶ በጾም በጸሎት በመጠመድ ተጋደለ። እግዚአብሔር ዘይቶንና የተምር አትክልት ያለባትን የአትክልት ቦታ በማየት ልቡን ብሩህ እስከ አደረገለት ድረስ በወሩ መባቻም ከዘንባባ ዕንጨትና ከዘይቶን የወደቀውን ፍሬ ወስዶ ይበላል። ምግቡም ታናሽ ወፍ በሚመገበው መጠን ልክ ነው ልብሱም ከዘንባባ ቅጠል የተሠራ ሰሌን ነው። ስለዚህ ለሚያስጨንቅ ለክረምት ቅዝቃዜና ለቃጠሎ የተጋለጠ ሆነ ከዚህም ጋር በጾምና በጸሎት የተጠመደ ነው። ነገር ግን መጻሕፍትን የሚያውቅ አይደለም የዱር አራዊትም በየወገናቸው ወደእርሱ ይመጡ ነበር እርሱም ያረጋጋቸዋል። የጸሎት ጊዜም ሲደርስ በእጁ ሲጠቅሳቸው ይሔዳሉ። ድርቅ የሆነ እንደ ሆነም ሊያነጋግሩት እንደሚሹ ሁነው መጥተው በፊቱ ይቆማሉ እርሱም የሚሹትን በመንፈስ ቅዱስ አውቆ በጸሎቱ ዝናብን ያወርድላቸዋል። እንዲሁም እያደረገ ከእርሳቸው ጋር አርባ አምስት ዓመት ኖረ። ሰይጣንም ቀናበት ዘመኑ በአለፈና እጅግ በአረጀ ሽማግሌ አምሳል በጥቂት በጥቂት ሲያዘግም ከበዓቱ ውስጥ ሁኖ አየው ለዚህ ቅዱስ አባ ሙሴም ገዳማዊ መናኒ መስሎት ወደእርሱ ሔዶ አምጥቶ ወደ በዓቱ አስገባው አራዊት ግን በሽማግሌ የተመሰለውን ሰይጣን በአዩት ጊዜ ከእርሱ ሸሹ።
@efeson_2
ከዚህ በኋላአባ ሙሴን አገሩንና ሃይማኖቱን ጠየቀው እርሱም ሁሉን ነገረው ደግሞ አባ ሙሴ ኑሮው እንዴት እንደሆነ ሽማግሌውን ጠየቀው። በሽማግሌ የተመሰለ ሰይጣንም እንዲህ ብሎ መለሰለት እኔ በዓለም ኃጢአት በመሥራት ብዙ ዘመናት ኖርኩ አንዲት ሴት ልጅንም ወለድኩ። ከዚያም የዓለምን ኃላፊነትና ጠፊነት አሰብኩ ከዓለምም ወጥቼ በበረሀ ውስጥ አርባ ዓመት ኖርኩ። ልጄን ያገባት እንደሌለ በአሰብኩ ጊዜ በዚህ ነገር ፕምክንያት ወዳንተ መጣሁ ከአንተ በቀር የሚያገባት የለምና። በሞትኩም ጊዜ የምትቀብረኝ አንተ ነህ ብዙ ስፍራዎችና የአታክልት ቦታዎችም ስላሉኝ ሁሉንም አንተ ትወርሳለህ። አባ ሙሴም ሰምቶ ደነገጠ እኔ መንኰሴ ስሆን ይህን እንዴት አደርጋለሁ አለ የተመረጡ ጻድቃን ሲሆኑ ሚስቶች የነበሩአቸው አብርሃምን ሙሴን ዳዊትን ከብሉያት መጻሕፍት ምስክር ማስረጃ አድርጎ አመጣለት በዚህም ወደ ተንኰሎ ልቡን አዘነበለው። በውስጡ ያጌጠች ሴት ልጅ ያለችበትን የተሸለመ አዳራሽ አሳየውና ከዚያም በኋላ እንደሞተ ሆነ አባ ሙሴም አይቶ በላዩ አለቀሰ ገንዞም ቀበረው ልጅቷ ወዳለችበት ለመግባት በፈለገ ጊዜ ጥቅል ነፋስ ነፍሶ የኋሊት ጣለው ከዚህ በኋላ ልቡ ሲመለስለት አዳራሹንም ልጅቷንም የአትክልት ቦታዎችንም አጣ ፈጽሞ እያደነቀ ወደ ማደሪያው ተመለሰ ከዕንጨቱም ፍሬ ምግቡን ሊመገብ ፈለገ በአፉም ውስጥ መራራ ሆነበት በረኃብም ስለ ተጨነቀ ወደ ዱር ወጥቶ ሔደ። ከዚህም በኋላ በአህያው ላይ ተቀምጦ ወደ እስክንድርያ በሚሔድ በሽማግሌ ነጋዴ አምሳል ሰይጣን ተገናኘው መብልና መጠጥም ይዞ ነበር አባ ሙሴንም ከርሱ ጋር ወሰደው ወደአንድ አገርም አድርሶ በዚያ ተወው። ዳግመኛም በገዳማዊት በመናኒነት በምትኖር ሴት አምሳል ሰይጣን ታየው እርሷም ውኃ የምትቀዳ መስላ ሥራውን ጠየቀችው ሰይጣን እንደፈተነው ሁሉን ነገራት በልቧም ሣቀችበት ወደቤቷም ወስዳው አብልታ አጠጥታ ከዚያ በኋላ የጋብቻን ነገር አሳሰበችው ብዙ ገንዘብም እንዳላት እርሷም የሟች ንጉሥ ልጅ እንደሆነች ነገረችው ልቡም እንደአዘነበለ አይታ እኔ አይሁዳዊት ነኝ እኛም ብዙዎች ነን ሃይማኖቱንም እስከካደ ድረስ በብዙ ተንኰል ተስፋ አስደረገችው። ዳግመኛም እንዲህ አለችው ና ወደ በረሀ እንውጣና ያኖርኩትን ገንዘብ እንውሰድ ብላ ሰው ወደሌለበት በረሀ ወሰደችው ከተራራ በላይም ወጥታ ተለወጠችበት እንዲህም አለችው እኔ ብዙዎችን ያሳትኩ ሰይጣን ነኝ። አንተንም ከገዳምህ አስወጣሁህ ሃይማኖትህንም አስካድኩህ እነሆ በዚህ በረሀም ሙተህ ነፍስህ ወደገሃነም ትወርዳለች ይህንንም ብሎ ሰይጣን ከርሱ ተሠወረ። በተመለሰም ጊዜ በቀኝም በግራም መንገድ አጣ የሚጠጣውም ውኃን አላገኘም ምድር ጠበበችው በምድር ላይም ወድቆ በፊቱ ውስጥም አፈርን በተነ ነፍሱም ከሥጋው ለመለየት እስከደረሰች ደረስ ተንከባለለ ጮኸ። መሐሪና ይቅር ባይ ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ራራለት ያጽናናው ዘንድ መልአኩን ላከለት እርሱም ኃጢአትህ ተሠረየልህ እስከ ሰባት ቀንም ታርፋለህ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሳሙኤልም ይቀብርሃል ብሎ አጽናናው ሰላምታም ሰጥቶት ዐረገ። ያን ጊዜም ሳሙኤል መጣ ንጉሥ ኢጋቦም በበረሃ ውስጥ ወደ አነፃት ቤተ ክርስቲያን ወሰደው እርሷም ገዳማውያን የሚሰበሰቡባት ተሠውራ የምትኖር ናት ወደርሷም በደረሱ ጊዜ ቅዱሳን ተሰብስበው መሥዋዕትን ሲያሳርጉ አገኙና በአንድነት ሥጋውንና ደሙን ተቀበሉ ስንብትም ከሆነ በኋላ ከቅዱሳን መቃብር በረከትን ሊቀበሉ ከአባ ሳሙኤል ጋራ አብረው ሔዱ ከዚያም ደርሶ አባ ሙሴ ሰገደ ወዲያውም አረፈ። አባ ሳሙኤልም ቀበረው ገድሉንም ጻፈ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሁሉም ቅዱሳን በጸሎታቸው ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በዚህችም ቀን የኢትዮጵያዊው የአባ አንበስ የሰማዕት አባ ዲዮስቆሮስ ሰማዕት የሆነ የሊቀ ጳጳሳት ዲዮናስዮስ የዲያቆን በትንከል የብዙዎች የፋርስ ሰማዕታት የዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው
በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን።
🙏አሜን።🙏
@efeson_2
🍀🍀🍀🍀✨✨✨✨🍀🍀🍀🍀

🔥1👏1
መስከረም ፭ /5/
በዚች ቀን የከበረች ሶፊያ ከሁለት ልጆቿ አክሶስ እና በርናባ ከሚባሉት ጋር በሰማዕትነት አረፈች።
ይችም ቅድስት አስቀድማ አረማዊት ነበረች ወላጆቿም ጣዖታትን የሚያመልኩ ናቸው። እርሷም በልቧ የወላጇቿ ሃይማኖት ከንቱ እንደሆነ መረመረች። ወደ መኖፌ ኤጲስቆጶስም ሄዳ ክብር ይግባውና በጌታችን በክርስቶስ ታመነች።
እርሱም ሃይማኖትን የቤተክርስቲያንን ሕግ አስተማራት። ከዚሕም በኋላ ከልጆቿ ጋር በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም አጠመቃት። ከዚህም በኋላ የሀገሩ ገዢ ለጣዖት መስገድን ትታ ክርስቲያን እንደሆነች በሰማ ጊዜ ከልጇቿ ጋር ብዙ ስቃይን አሰቃያት።
ገዢውም ልጇቿ አይተው ይፈሩ ዘንድ በጅራፍ ይገርፏት ዘንድ አዘዘ። ያን ጊዜም የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ ወርዶ እናታቸውን ከግርፋት ሲሰውራት አዩ።
ከዚህም በኋላ ወደ እስር ቤት ወስደው አሰሯት እራሷንም በሰይፍ ይቆርጡት ዘንድ አዘዘ የድል አክሊልንም ተቀበለች። ከዚህም በኋላ ልጆቿን ወደርሱ ይመለሱ ዘንድ አስፈራራቸው እንቢ ባሉት ጊዜም እያከታተለ አንገታቸውን አስቆረጠ።
ምስክርነታቸውንና ተጋድሏቸውን ፈጸሙ። ከመቃብራቸውም በሽታውንና ደዌውን ሁሉ የሚፈውሱ ብዙ የሆኑ ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@efeson_2
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
❤1🔥1