EECMY Youth Ministry
1.83K subscribers
3.51K photos
8 videos
269 links
Fellowship - Discipleship - Evangelism

1Thimothy 4:12

This is the official telegram channel of EECMY Head Office - Youth Ministry
Download Telegram
EECMY Youth Ministry
Photo
'የሀገራችሁ ወጣቶች ለምን በህገወጥ መልኩ ይሰደዳሉ? ለምን በበረሃ ይሞታሉ...?'
===
ይሄን ጥያቄ የጠየቁኝ ቄስ ካኖን ኢማኑኤል ይባላሉ: የዛምቢያ አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ዋና ጸሐፊ ናቸው። በናይጄሪያ አቡጃ በተካሄደው የመላው አፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ኮንፈረንስ በሕገወጥ ስደትና በሚያስከትለው ጉዳት ላይ በተደረገው አውደ ጥናት ላይ ተገናኘን።
በአውደ ጥናቱ ላይ ኢትዮጵያዊ መሆኔን ካወቁ በኋላ ቀረቡኝና፣ ‘ግን ለምን የሀገራችሁ ወጣቶች በብዛት ከሀገር ይወጣሉ፣ ለምን ይሰደዳሉ፣ ለምን በበረሃ መሞትን መረጡ?... ችግሩ ምንድን ነው? ባለፈው አመት በኮንቴነር ወደ ደቡብ አፍሪካ በህገ ወጥ ስደት ጉዞ ላይ ከነበሩ ወጣቶች መካከል 27ቱ ዛምቢያ ውስጥ በመንገድ ላይ ነበር ሞተው ሬሳቸው የተጣለው። ዜናው በመላ ሀገሪቱ ትልቅ ሀዘንን የፈጠረ ሲሆን በወቅቱም በመገናኛ ብዙሃን አጀንዳ ሆኖ ነበር። በተመሳሳይ መልኩ ባለፈው አመት በማላዊ የ30 ኢትዮጵያውያን የጅምላ መቃብር ተገኘ። ከዚያ በፊት ከ2 አመት በፊትም እንዲሁ በሞዛምቢክ በኮንቴነር ውስጥ 64 ወጣቶች ሞተው መገኘታቸውን ስንሰማ በጣም አዝነን ነበር።
ግን ይህ ሁሉ የሆነው ለምንድነው? ትውልዱ በኮንቴይነር ውስጥ ተጭኖ ታፍኖ እስኪሰደድ፣ ያለ ምግብና መጠጥ፣ ያለ አየር... ተስፋ ቆርጦ እንዲሞት ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው? ምን እየተፈጠረ ነው...?›› ብለው በሀዘን ስሜት ጠየቁኝ። እኔም እያዘንኩኝ እንዲህ ብዬ መለስኩላቸው፡- “ወጣቶቻችን ራዕይ አላቸው፣ ሰርተው መለወጥ ይፈልጋሉ፣ ማደግ ይፈልጋሉ፣ ስኬታማ መሆን ይፈልጋሉ። ለቤተሰቦቻቸው እና ለሀገራቸው በረከት መሆን ይፈልጋሉ .... ግን በሀገሪቱ ውስጥ ያለው ሁኔታ ብዙም ምቹ አይደለም ፣ ስራ አጥነቱ በዛ ፣ ተሯሩጠው የራሳቸውን ለመጀመርም ያስባሉ : ያለው ሁኔታ ግን ​​አልፈቀደላቸውም ፣ ቢሮክራሲውና ሙስናው እንቅፋት ይሆንባቸዋል ፣ የሰላም እና ጸጥታ ሁኔታው ደግሞ ይበልጥ ነገሮችን አስቸጋሪ አደረገ፣ ይህ ሁሉ ተደምሮ ነው እንግድህ ትውልዱን ተስፋ አስቆርጦ በህገ ወጥ መልኩ እንዲሰደድ ያደረገው... ሲል መለስኩለት።

ቀጥለውም ‹ይህ በጣም ያሳዝናል: እናንተ ለእኛ ወንድሞቻችን ናችሁ፤ እናም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በንደዚህ አይነት አሳዛኝ ሁኔታ በረሃ ላይ ሲሞቱ፣ ሬሳቸውም በምድረ በዳ ሲጣል ማየት በጣም ያሳዝናል። ነገር ግን እንዳልከው በአገራችሁ ያለው ሁኔታ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ ሁኔታዎቹ ምቹ ባይሆኑም ሕገወጥ ስደትን መምረጥ መፍትሔ ሊሆን አይገባም። ወጣቶች በማይመች ሁኔታ ውስጥም ቢሆን ተስፋ ሳይቆርጡ ራሳቸውን ለመለወጥ መሞከር አለባቸው: ወደ ሌላ ሀገር ለመሰደድ ቢያስቡ እንኳ በህጋዊ መንገድ እንጂ ህገ-ወጥ ስደት ምርጫ ውስጥ ፈጽሞ መግባት የለባቸውም:: በሕገወጥ ስደት ውስጥ የሚጠቀሙት ህገወጥ ደላላዎች ብቻ ናቸው። ይህ መለወጥ አለበት: በዚህ መቀጠል የለበትም::

በአገሪቱ ውስጥ ለወጣቶች ዕድል መፍጠር አስፈላጊ ነው: ወጣቶች ህገ ወጥ ስደትን እንዳይመርጡ ህጋዊ ስደትን ማመቻቸት እና በህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል። ይሄ ሁሉ ብዙ ስራ ይጠይቃልና በርቱ..." ብለው ምክራቸውን ቋጩ። እዚህ ላይ ብዙ የሚጨምረው ነገር የለኝም: ወጣቱ በሀገሬ ሰርቼ መለወጥ እችላለሁ የሚል አስተሳሰብ እንዲይዝ በትውልዱ አእምሮ ላይ መስራት ያስፈልጋል። በአስተሳሰብ ላይ ከተሰራ በኃላ በተቻለ መጠን ለወጣቱ ሁኔታዎችን ማመቻቸት እና ድጋፍ መስጠት ከሁሉም ይጠበቃል:... እና ቤተሰቦች: መንግስታት: መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የግል ድርጅቶች... ሁሉም ሚናቸውን መጫወት አለባቸው::
በወጣቶች ከመፍረድ ይልቅ ወጣቶችን ማዳመጥና መረዳት፣ ለስኬታቸው ሁኔታዎችን ማመቻቸትና አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ላይ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መልኩ ትኩረት ሊሰጥ እና ሊሰራ ይገባል እላለሁ። እግዚአብሔር ለሀገራችን ሰላምን: ለወጣቶቻችን ተስፈ እና ስኬትን ይስጥ። ጤና ይስጥልኝ!

Via @wondmagegnudessa
#EECMY #AACC #Africa #Youth #Dargaggoo #ወጣት #AddressingIllegalMigration #Entrepreneurship