Ethiopian Coffee and Tea Authority
4.36K subscribers
3.91K photos
25 videos
63 files
314 links
Ethiopian Coffee and Tea Authority
Download Telegram
በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የቡና፣ ሻይና ቅመማቅመም ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሄደ

መጋቢት 11/2017 ዓ.ም
አርባ ምንጭ

ክቡር መሪሁን ፍቅሩ(ዶ/ር) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል መስተዳድር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ፣ ክቡር አቶ ታጋይ ኑሩ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ም/ዋ ዳይሬክተር እና ክቡር ደምሴ አድማሱ (ዶ/ር) የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በተገኙበት ከኦሮሚያ፣ ከሲዳማ፣ ከደቡብ ኢትዬጵያ፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ከአማራ፣ ከትግራይ እና ከጋምቤላ ክልሎች የመጡ የቡና ሻይና ቅመማቅመም የስራ ኃላፊዎችና ባለሞያዎች በሳተፉበት የሻይ ቡና እና ቅመማቅመም የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሂዷል።

መድረኩን የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር ደምሴ አድማሱ (ዶ/ር) በእንኳን ደህና መጣቹ ንግግር የከፈቱ ሲሆን በንግግራቸው ከአስራ ሶስቱ የዞኑ ወረዳዎች በአስራ ሁለቱ በ14 ሺ 497 ሄክታር መሬት ላይ 10ሺ 148 ቶን ኩንታል እንደሚመረት ገልጸዋል። አማካይ ዞናዊ የቡና ምርት በሄክታር 7 ኩንታል እንደሆነ የገለጹት ዋና አስተዳዳሪው ምርቱ ዝቅተኛ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል ብለዋል። በተያዘው በጀት ዓመትም የቡና ሽፋን በማሳደግ 1834 ሄክታር በበልግ ወቅት በአዲስ ተከላ የሚለማ እንደሆነና የታቀደ ሲሆን በዚህም በቁጥር 1.7 ሚሊዮን የቡና ችግኝ ተከላ ይካሄዳል ብለዋል። ባለፈው በጀት ዓመት ምንም ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ያልቀረበ ሲሆን በተያዘው በጀት ዓመት ወደ 720 ሺ ጀንፈል ቡና ማቅረብ እንተቻለ ተናግረው በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ወደ 142 ቶን ለማድረስ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ገልጸዋል።

በቅመማቅመም ዘርፍም በተለይ ዝንጅብልና ኮረሪማ ሮዝመሪና ጤናዳም ምርቶች ዞኑ እንሚታወቅ ገልጸው በተያዘው በጀት ዓመት 2 ሺ 79 ሄክቴር ማሳ ላይ ከሚመረተው 802 ቶን በላይ በጥራት ለሀገር ውስጥ ገበያ ለማቅረብ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ክቡር አቶ ታጋይ ኑሩ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው በመንደርደሪያቸው የባለስጣን መስሪያቤቱ ተግባርና ኃላፊነት ላይ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን በገለጻቸውም መስሪያቤቱ የቁጥጥር ስራ ብቻ ሳይሆን በልዩነት የልማት ስራውንም የሚያከናውን መሆኑን ተናግረዋል፤ በዚህም አወቃቀሩ የተለየ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም ከልማት ስራው ጋር በተያያዘ በተያዘው በጀት ዓመት ብቻ በገንዘብ ወደ 170 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ግብአቶች ለማሟላት ተችሏል ብለዋል። በበጀት ዓመቱ ለማሳካት የታቀደው 2 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ከዳር ማድረስ የሚቻለው ልማቱ ላይ በአግባቡ ሲሰራ እንደሆነ አሳስበው በተለይ በብዛት ሸጦ ገቢ ማግኘት እንዳለ ሆኖ አዋጭ አፈጻጸም የሚሆነው ግን ጥራት ላይ መስራት መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል። ይህም ተፈጻሚ ይሆን ዘን ከአመራር ጀምሮ እስከ አርሷደር ድረስ ጥራት ተኮር የሆነ የልማት ስራ እንዲሰራ በንቅናቄ ደረጃ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ሆኖም ጥራት ማስጠበቅ ላይ ችግሮች እንዳሉና ሊታሰብበት እንደሚገባ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

ካሉት ተግዳሮቶች አንዱ ቦና ደብቆ ማቆየት ችግር እንደሆነና በዚህ አጉል ብልጠትም አንዳንድ ነጋዴዎች የቡና ግብይቱ ላይ ችግር ለመፍጠር እየሞከሩ እንደሆነ ተናግረዋል። ይህ ከሚሆን ይልቅ 150 ብር ሲሸጥ የነበረው ኪሎ ቡና በዚህ ዓመት 450 ብር ድረስ እየተሸጠ በመሆኑ አውተው መሸጡ እሚያዋጣቸው እንደሆነ መክረዋል። በቡና በባህሪው ዋጋው ሲወጣና ሲወርድ በአንድ ጊዜ በመሆኑ ወቅቱን ጠብቆ መሸጡ እንሚሻል አሳስበዋል።

በማስከተል ንግግር ያሰሙት ክቡር መሪሁን ፍቅሩ(ዶ/ር) በምክትል ርዕሰ መስተዳድር የዲላ ክላስተር አስተባባሪ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ሲሆኑ በንግግራቸው በቡና ልማት ረገድ በክላስተር ለማልማት ጥረት እየተደረገ እንደሆነና ወጥ የሆነ የልማት ስራ በየአካባቢው እንዲሰራ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ወጥ በሆነ መልኩ ከለማ ግብይቱንም ወጥ በሆነ መልኩ ማካሄድ ያስችላል ብለዋል። እንደክልል 228 ሺ ሄክታር ላይ ቡና እየለማ እንደሚገኝና ከፍተኛው ምርት ያለው ጌዲዮ ዞን እንደሆነ ገልጸው 75 ሺ 773 ሄክታር እሚሸፍን ነው ብለዋል። የዚህን ያህል እምቅ ሃብት ቢኖርም ማዘመኑ ላይ ግን ብዙ ስራዎች ይቀራሉ ብለዋል።

ከግብይት አንጻር ባወሱበት ምዕራፍም ግብይቱን ጤናማ ለማድረግ ኮንትሮባንድን የመከላከል እና ጥራት ማስጠበቅ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል። በስተመጨረሻም የብድር አገልግሎትን ጨምሮሌሎች ግብአቶችን ከማሟላት አንጻር የፌደራል ቡናና ሻይ ባለስልጣን ድጋፍ እያደረገ እንደቆየና በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

ንግግሮቹ ከተደመጡ በኋላም የባለስልጣን መስሪያቤቱ እና ከተለያዩ ክልሎች የመጡ የቡና ሻይና ቅመማቅመም ኃላፊዎች ዕቅድ አፈጻጸማቸውን ያቀረቡ ሲሆን በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ውይይት ተደርጎ የመርሀግብሩ ፍጻሜ ሆኗል።
ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር በላይ ዋጋ ያለው የቡና ምርት ወደ ውጭ ተልኳል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2017 በጀት ዓመት ባለፉት 8 ወራት ብቻ ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር በላይ ዋጋ ያለው የቡና ምርት ወደ ውጭ መላኩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 21ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።…

https://www.fanabc.com/archives/286930
ከዚህ በላይ በተያያዘው ዜና መሠረት በውድድሩ አሸናፊ ለሆናችሁት ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት እንወዳለን!!
Group of technical experts discussed on how to work together to implement EUDR Compliance!!
21 March 2025
Addis Ababa
A group of experts from various institutions held an extensive discussion on the implementation of the European Union regulation by using modern technology. The Ethiopian Coffee and Tea Authority, GIZ, Ministry of Agriculture, Space Science and Geospatial Institute, Ministry of Water and Energy, and other relevant governmental and non-governmental institutions participated in the discussion.
During the discussion, it was explained that the European Union Deforestation-free Regulation (EUDR) requires accurate geo-location data to ensure products come from areas not subject to deforestation. It was mentioned that, previously, software called MIMS was developed by ECTA and being used to control and facilitate coffee related information. So that the aim of today’s meeting was how expanding this software further and linking it with the EUDR directive that the European Union has decided to implement soon.
Accordingly, a software developer company called Vulcan provided relevant explanations on the issue. Based on the explanations provided, a discussion was held and an agreement was reached to work together to ensure that future work is streamlined and reliable.