የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዋልታ፡- የጥቁሩ ወርቅ አስደናቂ ዕድገት
*******
ኢትዮጵያ በቡና ወጪ ንግድ ታሪካዊውን የ3 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገደብ ማለፏ፣ በምስራቅ አፍሪካም ሆነ በዓለም አቀፍ የንግድ መድረክ ላይ ያላትን የኢኮኖሚ እና የጂኦፖለቲካዊ አቅም በተግባር ያሳየችበት አጋጣሚ ሆኗል።
ይህ ታሪካዊ ስኬት በቁጥር የሚገለጽ የንግድ መረጃ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም የሀገራችን የብራንድ ልዕልና፣ የተፈጥሮ መገኛነት ሀብት፣ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ፍሬ እንዲሁም የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን የሚያስመሰክር ታላቅ አምባሳደር መሆኑን ያበስራል።
ባላፉት አምስት ዓመታት በስፋት ሲተገበር የቆየው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ደኖችን ከመንከባከብና የአፈር መሸርሸርን ከመከላከል ባሻገር፣ ለአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ የማይበገር የቡና እርሻ እንዲስፋፋ፣ የምርት መጠን እንዲጨምር እና ጥራቱ ተጠብቆ ለዓለም ገበያ እንዲቀርብ አስችሏል።
ይህ የተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃ በቡናው ጣዕም እና መዓዛ ላይ ያመጣው በጎ ተጽዕኖ፣ የኢትዮጵያ ቡና በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ የሌለው ልዩ ምርት ሆኖ እንዲቀጥልና ለአርሶ አደሮች ተጨባጭ የኢኮኖሚ ጥቅም እንዲያስገኝ አድርጓል።
ቡና ለኢትዮጵያ የሀገር ምስል መገንቢያ እና የዲፕሎማሲያዊ ትሥሥር ዋነኛ ድልድይ ሆኗል። የቡና መገኛ የሆነችው ሀገራችን በቻይና፣ በመካከለኛው ምስራቅና በአውሮፓ የነበራትን ገበያ በማስፋት የብራንድ አቅሟን ገንብታለች። ይህ የቡና ዲፕሎማሲ ምርቱን ቀጥታ ለዓለም አቀፍ ገዢዎች በማቅረብ የውጭ ምንዛሪ ገቢን ለማጎልበትና የገበያ መሪነትን ለማረጋገጥ አስችሏል።
ለኢትዮጵያ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ አዲስ መንገድ የከፈተው የዘርፉ ዕድገት የኢትዮጵያውያን የቡና ሥነ ሥርዓት የባህል፣ የእንግዳ ተቀባይነትና የታሪክ መገለጫ በመሆን ጎብኚዎችን የሚስብ፣ የሀገር ውስጥ ገበያን እና የሆቴል ዘርፍ የሚያነቃቃ ትልቅ ኃይል ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል።
በመሆኑም የኢትዮጵያ ቡና ዛሬ ላይ የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ ብቻ ሳይሆን የቱሪስቶች መሳቢያ፣ የአረንጓዴ ልማት ማረጋገጫ እንዲሁም የሀገራችን ጂኦፖለቲካዊና የብራንድ ልዕልና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያስከብር የዲፕሎማሲያችንና የኢኮኖሚያችን ዋና ምሰሶ ሆኗል።
EBC

ክልሉ በ2019 የምርት ዘመን 74 ሺህ 200 ቶን ቡና ለማዕከላዊገበያ ለማቅረብ አቅዶ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ አዘጋጅነት "ምርትና ምርታማነትን ማረጋገጥ ለክልላችን ከፍታ" በሚል መሪ ቃል ክልል አቀፍ የግብርና ልማት ሥራዎች ንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ የክልሉ ቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አስራት መኩሪያ የዘርፉን የአፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 በጀት ዓመት የልማትና ግብይት ዕቅድ ሰነድ አቅርበዋል።
የቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ልማትን በማስፋፋት፣ የምርትና ምርታማነት አቅምን በማሳደግ የክልሉን የወጪ ንግድ ገቢና የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም በ2019 የምርት ዘመን 74 ሺህ 200 ቶን ቡና፣ 68 ሺህ 540 ቶን ቅመማ ቅመምና 7 ሺህ 210 ቶን ሻይ ለገበያ ለማቅረብ ዕቅድ መያዙን አብራርተዋል።
በቡና ልማት ዘርፍ 96 ሚሊዮን 600 ሺህ ችግኞችን ለማዘጋጀትና ለመትከል፣ 8 ሺህ 769 ሄክታር ያረጀ የቡና ማሳን በጉንደላና በነቅሎ ተከላ ለማደስ ታቅዷል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ለዚህም 890 ሺህ 120 ቶን ኮምፖስት የማዘጋጀት ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።
በቅመማ ቅመም ልማት ዘርፍም 47 ሺህ 995 ሄክታር መሬት ላይ በርበሬ፣ ዝንጅብል፣ ዕርድ፣ ሚጥሚጣ፣ ኮረሪማና ቁንዶ በርበሬ ለማልማት ዕቅድ መያዙን ነው የገለፁት።
በበጀት ዓመቱ በካፋ፣ ቤንች ሸኮና ሸካ ዞኖች 112 ሄክታር መሬት ላይ 1 ሚሊዮን 555 ሺህ 456 የሻይ ችግኞችን ለመትከል መታቀዱንም የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ጠቅሰዋል።
በዘርፉ ያለውን የተፈጥሮ ፀጋና የልማት አቅም በአግባቡ ከመጠቀም አንጻር የግብዓትና የሎጂስቲክስ እጥረት፣ የምርታማነት ፓኬጆችን በስፋት አለመተግበር፣ የባለሙያዎች እጥረትና የመዋቅር ድክመቶች ዋና ዋና ተግዳሮቶች መሆናቸውን አንስተዋል።
በድህረ-ምርት አሰባሰብና አዘገጃጀት ላይ የሚታዩ የጥራት ችግሮች፣ የአየር ንብረት መዛባት፣ የበሽታና ተባይ መከሰት፣ እንዲሁም ገበያው ለጥራት ተገቢውን ዋጋ አለመስጠት በዘርፉ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶች መሆናቸውም አመላክቷል ።
እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ተስማሚ የቡና ዝርያዎችን መለየት፣ ማዕከላዊ የችግኝ ጣቢያዎችን ማጠናከር፣ የጥላ ዛፎችን በአግባቡ ማመጣጠንና ምርታማነትን ከ30 እስከ 40 በመቶ ማሳደግ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውም አቶ አስራት መኩሪያ ተናግረዋል።
በግብይት በኩልም የኮንትራት እርሻና ቀጥታ የገበያ ትስስርን ማጠናከር፣ የህብረት ሥራ ማኅበራትን ተሳትፎ ማሳደግ፣ የአውሮፓ ሕብረት የደን ጭፍጨፋ ቁጥጥር ሕግ (EUDR) መስፈርቶችን ማሟላትና ሕገወጥ የቡና ምርት ዝውውርን መከላከል በትኩረት እንደሚሰራባቸው ተመላክቷል።
በቡና ግብይት ረገድም እስካሁን ከ25 ሺህ ቶን ቡና ወደ ማዕከላዊ ገበያ ማቅረብ መቻሉን የገለጹት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ይህም በዓመቱ የተቀመጠውን የ74 ሺህ 200 ቶን የገበያ አቅርቦት ግብ ለማሳካት የሚደረገው ጥረት አካል መሆኑንም አብራርተዋል።
በንቅናቄ መድረኩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የግብርና አመራሮችና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
south west communication

የፕሬስ ሪሊዝ
ለሚዲያዎች እና ለህዝብ ግንኙነት አገልግሎት የሚውል!!!
ጥቅምት 27/2019
የኢትዮጵያ ቡና ኤክስፖርት አበረታች በሆነ ሁኔታ ላይ ይገኛል።፡ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሶስት ወራት ብቻ 878.52 ሚሊዮን ዶላር ተገኘ – ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት አንጻር ሲታይ የ15 በመቶ ዕድገት ተመዝግቦበታል!
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27/2019 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ የጥቁር ወርቅ ሀብት የሆነው የቡና ዘርፍ በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ውስጥ ከፍተኛ እና አበረታች አፈጻጸም ማስመዝገቡን ቀጥሎበታል። ይህም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን ከፍ በማድረግ ሂደት ውስጥ የኢትዮጵያ ቡና ፍላጎት በበርካታ የዓለም ገበያዎች ላይ እየጨመረ መምጣቱን የሚያሳይ አስደሳች ሪፖርት እንደሆነ ያሳያል።
በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሶስት ወራት ውስጥ 144,433.0 ቶን ቡና በመላክ 1.033 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ፤ 131,069.51 ቶን (ከዕቅዱ 91%) ቡና ለውጭ ገበያ የቀረበ ሲሆን፣ 878.52 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር (ከዕቅዱ 85%) ገቢ ተገኝቷል።
ይህ አፈጻጸም ከባለፈው በጀት ዓመት (2018) ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ሲታይ፡
በመጠን (Volume): 17,527.7 ቶን ወይም 15% ጭማሪ፣
በገቢ (Revenue): 115.77 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወይም 15% ዕድገት ተመዝግቧል።
ዋና ዋና የቡና መዳረሻ አገራት አፈጻጸም፤
በ2019 በጀት ዓመት ሶስት ወራት የተላከው ቡና በመዳረሻ አገራት ሲታይ፤ ነባር እና አዳዲስ ገበያዎች አብረው በማደግ የላቀ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡
ሳውዲ አረቢያ: በመጠን 28,362.77 ቶን (22%) እና በገቢ 196.85 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር (22%) ድርሻ በመያዝ 1ኛውን ደረጃ ይዛለች።
ጀርመን: በመጠን 22,924.18 ቶን (17%) እና በገቢ 136.69 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር (16%) ድርሻ በማስመዝገብ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
ቻይና: በመጠን 15,125.54 ቶን (12%) እና በገቢ 103.0 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር (12%) አፈጻጸም በማስመዝገብ 3ኛውን ደረጃ ተቆናጣለች።
የቀሩት ዋና ዋና መዳረሻዎች:
ከ4ኛ እስከ 10ኛ ደረጃዎችን የያዙት አገራት ቅደም ተከተል፡
4ኛ - አሜሪካ
5ኛ - ደቡብ ኮሪያ
6ኛ - ቤልጅየም
7ኛ - ጃፓን
8ኛ - ዩናይትድ አረብ ኤሚሬትስ
9ኛ - ጣልያን
10ኛ - ራሺያ ፌዴሬሽን ናቸው።
እነዚህ 10 ታላላቅ የኢትዮጵያ ቡና መዳረሻ አገራት በአጠቃላይ ከሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ግኝት ውስጥ 82% በመጠን እና 82% በገቢ ድርሻ ይሸፍናሉ። ከባለፈው 2018 ዓ.ም አፈጻጸም ጋር ሲወዳሩም በእነዚህ 10 አገራት ብቻ በመጠን እና በገቢ የ 19% ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየት ተችሏል።
የባለሥልጣኑ መልዕክት
ይህ ውጤት የኢትዮጵያ ቡና ጥራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን፣ የግብይት ሥርዓቱ በቴክኖሎጂ መደገፉን እና የባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት አበረታች ፍሬ ማፍራት መጀመሩን ያሳያል። የኢፌዲሪ መንግስት የቡናን ኤክስፖርት መጠንና ዋጋ ማሳደግ የሚያስችሉ ስልታዊ ሥራዎችን አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፣ አዳዲስ ዓለም አቀፍ ገበያዎችን ለመድረስ የሚደረገው ጥረትም ተጠናክሮ ይቀጥላል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ በጮባሬ ሜዕኖ ቀበሌ በአርሶአደሩ ማሳ በመልማት ላይ የሚገኝ የሀላባው ብራንድ ዛላ በርበሬ አሁናዊ ገጽታ!!
የዓለም የቡና ገበያ ዥዋዥዌ ጨዋታ እና የኢትዮጵያ ቡና አስደናቂ የግስጋሴ ጉዞ!!!
የትላንቱን የዓለማቀፍ የቡና ገበያ ውሎ እና የአገራችንን የሶስት ወራት አፈጻጸም መሠረት በማድረግ የቀረበ አጭር ትንታኔ!
(ጥቅምት 28/2019)
ሳህለማርያም ገ/መድህን (ኢ/ቡ/ሻ/ባለስልጣን)
የዓለም አቀፉ የቡና ገበያ በአሁኑ ወቅት የሁለት ተቃራኒ አቅጣጫዎች ፍጭት እያስተናገደ ይገኛል፡ በወደፊት የንግድ ውሎ (futures market) የሮቡስታ ዋጋ በአቅርቦት እጥረትና በዶላር መዳከም ምክንያት እያገገመ ሲሆን፣ የአረቢካ ዋጋ ግን ከብራዚል በወረደው ከፍተኛ የምርት አቅርቦት ሳቢያ ባለፉት አምስት ሳምንታት አይቶት ወደማያውቀው ዝቅተኛ ደረጃ ወርዷል።፣
ሆኖም ይህ የዓለም አቀፍ ገበያ የታችኛው ጫና ባለበት ሁኔታ የኢትዮጵያችን አረቢካ ቡና የዓለምን አዝማሚያ በመጣስ፣ ከፍተኛ ፍላጎት ባለው ልዩና ጥራት ባለው (specialty) የቡና ገበያ ላይ አስደናቂ የዕድገት ጉዞ እያስመዘገበ ይገኛል።
1. ዋና ዋና የትንተና ነጥቦች
ከዓለም አቀፍ ገበያ መለያየት አንፃር ሲታይ የብራዚል የኤክስፖርት መጠን መጨመርና የሪያል መዳከም የአረቢካ የፊውቸርስ ዋጋን ወደ ታች ቢገፋውም፤ በመካከለኛው አሜሪካ እና ሜክሲኮ የሚጠበቀው የ9.3% የምርት ቅናሽ በጥራት ደረጃቸው የላቁ የአረቢካ ቡናዎች ላይ ከፍተኛ የአቅርቦት ክፍተት ፈጥሯል።
ከአገራችን የገበያ ጥንካሬ አንጻር ስንመለከተው፤ በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሶስት ወራት ብቻ ኢትዮጵያ 131,069.51 ቶን ቡና በመላክ 878.52 ሚሊየን ዶላር ገቢ አግኝታለች። ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በመጠንም ሆነ በገቢ የ15% (የ115.77 ሚሊየን ዶላር) የጎላ ዕድገት ማሳየቱን ያረጋግጣል።
ከስትራቴጂካዊ የጥራት ብልጫ አንፃር ሲታይ ደግሞ፤ ዓለም አቀፍ ገበያ ገዢዎች በመካከለኛው አሜሪካ የታየውን የጥራት ስጋት ለማካካስና አስተማማኝ ጣዕም ያለው ቡና ለማግኘት በስፋት ወደ ኢትዮጵያ አረቢካ እየዞሩ መሆናቸውን በቀላሉ ለመገመት ይቻላል።
2. የዓለም አቀፍ ገበያ አዝማሚያ ከኢትዮጵያ አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር፤
በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፉ የቡና ገበያ አዝማሚያ እና በኢትዮጵያ የኤክስፖርት አፈጻጸም መካከል ያለው ልዩነት የኢትዮጵያ አረቢካ ቡና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ጠንካራ የገበያ ቦታ በግልጽ ያሳያል። የዓለም አቀፉ የፊውቸርስ ገበያ (በተለይም ICE) በብራዚል ከፍተኛ የምርት አቅርቦትና የሪያል ገንዘብ መዳከም ሳቢያ የታችኛው የዋጋ ጫና ደርሶበት ባለፉት አምስት ሳምንታት አይቶት ወደማያውቀው ዝቅተኛ ደረጃ ወርዶ ይገኛል። በሌላ በኩል ግን፣ የኢትዮጵያ የቡና ኤክስፖርት ይህንን የዓለም አቀፍ ዋጋ ውድቀት በመቋቋም በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ብቻ 878.52 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማስገኘት ችሏል፤ ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ115.77 ሚሊዮን ዶላር ወይም የ15 በመቶ አስደናቂ የገቢ ዕድገት ያሳያል።
በኤክስፖርት መጠንና በአቅርቦት ሁኔታ በኩል ሲታይም፣ የብራዚል የኤክስፖርት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር የዓለምን የቡና አቅርቦት በማጥለቅለቅ አጠቃላይ ዋጋውን ወደ ታች እንዲወርድ አድርጎታል፤ በተጨማሪም በመካከለኛው አሜሪካ የታየው የ9.3 በመቶ የምርት ቅናሽ የቡና አቅርቦቱ ላይ ስጋት ፈጥሯል። በአንጻሩ ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሶስት ወራት 131,069.51 ቶን ቡና ለውጭ ገበያ ማቅረብ የቻለች ሲሆን፣ ይህም የዕቅዷን 91 በመቶ ማሳካት ብቻ ሳይሆን ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ15 በመቶ የመጠን ጭማሪ ማሳየቷን ያረጋግጣል።
በመጨረሻም፣ ይህ የውጤት ልዩነት የመነጨው ከሁለቱ ወገኖች የገበያ አቀራረብና የቡና ጥራት ባህሪ ነው ብሎ የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ያምናል። የዓለም አቀፉ ገበያ በዋናነት በብራዚል ተራ (Commodity) አረቢካ ቡና አቅርቦት ላይ የተመሠረተና ለዋጋ መዋዠቅ ተጋላጭ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ቡና ግን በተፈጥሯዊ የአበቃቀል ልዩነቱ፣ በተለየ የጣዕም መገለጫው እና መነሻው በሚታወቅ ከፍተኛ ጥራት ባለው (Specialty) የቡና ዘርፍ ላይ የተመሠረተ ነው። በመሆኑም ኢትዮጵያ በዓለም ገበያ ላይ ከፍተኛ የውድድር ብልጫ እና ተጨማሪ የዋጋ ማካካሻ (premium price) በማግኘት አዎንታዊ አፈጻጸሟን ማስቀጠል ያስችላታል።
3. ለኢትዮጵያ ስኬት መንስኤ የሆኑ ዋና ዋና ምክንያቶች ይሆናሉ ብሎ ፀሀፊው የሚያምነው፤
በመካከለኛው አሜሪካ የ1.7 ሚሊዮን ኩንታል (9.3%) የምርት ቅናሽና የጥራት መጓደል (በተባይና በሙቀት ምክንያት) መከሰቱ፣ የዓለም ጥራት ያለው የታጠበና የደረቀ ቡና ገዢዎች ፊታቸውን ወደ ኢትዮጵያ ልዩ የይርጋጨፌ፣ ሊሙ፣ ሲዳማ፣ ጉጂ እና ሌሎችም የአገራችን ቡናዎች እንዲያዞሩ አስገድዷቸዋል።
የብራዚል ከፍተኛ ኤክስፖርት የዓለም የቡና ዋጋን ቢያወርደውም፣ መንግስት እየተከተለ ካለው ጥራት የማስጠበቅ ጠንካራ አቅጣጫ፣ የኢትዮጵያ ቡና ባለው ተፈጥሯዊ የዝርያ ልዩነትና የተለየ ጣዕም ምክንያት በከፍተኛ ተጨማሪ ዋጋ (premium price) ይሸጣል። ይህም የዓለም ዋጋ ቢወርድም ኢትዮጵያ የ15% የገቢ ዕድገት እንድታስመዘግብ አስችሏታል።
ነባርን የማቆየት አዳዲስ ገበያዎችን የማስፋት ስትራቴጂያችንም ለዚህ እንደምክንያትነት ሊጠቀስ የሚችል ነው። ቁጥር አንድ የህዝብ ብዛት ያላት እና ዜጎቿን የቡና ጠጪ (በተለይም የኢትዮጵያን ቡና) በማድረግ ላይ የምትገኘው ቻይና በብርሀን ፍጥነት ተምዘግዝጋ 3ኛ የኢትዮጵያ ቡና ገዢ መሆ፣ የሩስያ ፌዴሬሽንም ብቅ ማለቷ እንደ አብነት ይጠቀሳል።
በዓለም አቀፍ ንግድ ልውውጦች (ICE) መጋዘኖች ያለው ክምችት ዝቅተኛ በመሆኑ፣ የአውሮፓና የእስያ ልዩ ቡና ገዢዎች ምርቱ ሳያልቅ ቀድመው ከኢትዮጵያ ውል በመግባት አቅርቦታቸውን እያረጋገጡ ይሆናል ብሎ ይገመታል።
4. የቀጣይ ጊዜ ስትራቴጂካዊ እይታ
የጥራት እና መጠን ብልጫን ማስጠበቅ፡ ቪየትናም በሮቡስታ መጠን፣ ብራዚል ደግሞ በአረቢካ ብዛት ገበያውን በሚጫኑበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ ዋና የውድድር ብልጫ የላቀ የቡና ጥራት እና መነሻው የሚታወቅ/ traceable ምርት ማቅረብ ልክ አሁን እየተከተልን ያለው የጥራት ስትራቴጂ ለነገ ተብሎ የሚተው የቤት ስራ መሆን የለበትም። ምርታማነቱን በማሳደግ ገበያውን መቆጣጠርም ወሳኝ ይሆናል።
የቅድመ ሽያጭ ውሎችን በማጠናከር ረገድ እንደ ብራዚል እና ቪየትናም (ምንም እንኳ የሮቡስታ ቡና አቅራቢ አገር ብትሆንም) አዲስ ምርት ገበያ መግባት በሚፈጥረው አጭር ጊዜ መዋዠቅ ሳይበገሩ፣ የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች አሁን ያለውን ጠንካራ የዓለም አቀፍ ፍላጎት በመጠቀም አትራፊ የቅድመ-ሽያጭ ውሎችን ማሰር ይኖርባቸዋል።
የልዩ ጣዕም (speciality) ገበያዎችን በማስፋፋት በኩልም መጀመሪያው ሩብ ዓመት 878.52 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንደሚያሳየው፣ ገዢዎች ለኢትዮጵያ ጥራት ያለው ቡና ተገቢውን ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ የሆኑ መሆናቸውን ለመገመት ይቻላል። በተለይም በፍጥነት እያደጉ ባሉት የእስያ ገበያዎች ላይ ትኩረት ማድረግ አጠቃላይ የገበያ ስጋትን ይቀንሳል።
ቸር ያውለን!!!❤