Ethiopian Coffee and Tea Authority
6.81K subscribers
6.46K photos
30 videos
68 files
395 links
Ethiopian Coffee and Tea Authority
Download Telegram
የደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን አርሶ አደሮች ያረጁ የቡና ተክሎች ምርታማነታቸው በምርምር በተረጋገጡ የቡና ዝርያዎች በመተካት ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የጅማ ግብርና ምርምር ማዕከል በበኩሉ አርሶ አደሮች እያለሙት ያለው የቡና ዝርያ በሽታ የሚከላከልና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን በዘላቂነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልጿል።

ማዕከሉ ከ50 በላይ የሚሆኑ የተሻሻሉ ዝርያዎችን በማውጣት ለአካባቢው አርሶ አደሮች እያሰራጨ ነው።

በዞኑ ጎማ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮች ያለሟቸው የቡና ዝርያዎች በ3 ዓመት ጊዜ ውስጥ ምርት የሚሰጡ ናቸው።

ዝርያዎቹ ከአካባቢ ስነ ምህዳር ጋር ተስማሚ መሆናቸውን የገለጸው የማዕከሉ መረጃ፤ ዝርያዎቹ ተገቢው እንክብካቤ ከተደረገላቸው በሄክታር እስከ 20 ኩንታል ምርት ይሰጣሉ ብሏል።
በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን በጮራ ወረዳ ሸንገላ ቀበሌ የሻይ ቅጠል ልማት ኢኒሼቲቭን ለማሳካት የሚደረገው እንክብካቤ በግብርና አመራሮች ተጎበኘ። በግብርናው ዘርፍ ተቀርፀው ወደ ሥራ የገቡት ኢኒሼቲቮች የሀገርን ኢኮኖሚ ከመደገፍ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የወጪ ንግድን (ኤክስፖርትን) ለማሳደግ እና የሥራ ዕድል ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳላቸው ይህ ትልቅ ማሳያ ነው።
Godina Kibba Lixa Oromiyaa Aanaa Cooraa Ganda Shengelaatti inisheetivii Misoomaa baala shaayee milkeessuuf kunuunsa taasifamaa jiru hoggantootaa qonnaan daawwatameera.Inisheetiviiwwan damee qonnaatiin bocamanii hojiirra oolaa jiran diinagdee biyyaa utubuu, wabii nyaataa mirkaneessuu, al-ergee guddisuu fi carraa hojii uumuu keessatti qooda ol'aanaa akka qaban kun agarsiiftuu guddaadha.
በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን ከ779 ሺህ ቶን በላይ የቡና ምርት ለመሰብሰብ እየተሰራ ይገኛል
​የደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን ከፍተኛ አመራሮች በሊሙ ኮሳ ወረዳ የሚገኘውን የቡና ልማት እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።
​በጉብኝቱ ላይ የተገኙት በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የዞኑ አስተዳዳሪ ዶክተር ረሻድ ካማል እንደገለጹት፤ ጥራቱን የጠበቀ ቡና በመሰብሰብ በምርት ጥራትና በብዛት ለውጭ ገበያ በማቅረብ ለሀገር የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት እንዲሁም የገበሬውን ገቢ ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል። በተለይም የተመረጡ የቡና ዝርያዎችን ማስፋፋትና የሚገኘውንም ምርት በጥራት በመሰብሰብ በኩል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በመሆኑም ለአገር ውስጥ ገበያ የሚቀርበውን ምርት በላቀ ደረጃ ለውጭ ገበያ ማሳደግ በሚያስችል መልኩ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
​በዞኑ በያዝነው ዓመት ከ779 ሺህ ቶን በላይ ምርት ለማግኘት ታቅዶ የምርት ስብሰባው መጀመሩን የዞኑ ግብርና መሪያ ቤት መረጃ ያመለክታል።

Godina Kibba Lixa Oromiyaatti oomisha bunaa toonii kuma 779 ol sassaabuuf hojjetamaa jira.Hoggantoonni Ol'aanoon Godina Kibba Lixa Oromiyaa Aanaa Limmuu Kossaatti hojii misooma bunaa daawwataa jiru.Daawwannaa kanaarratti kan argaman Sadarkaa Pirezidaantii Ittaanaatti Bulchaa Godinichaa Doktar Rashaad Kamaal buna qulqullina qabu funaanuun qulqullinaaf baayyinaan gabaa alergiif oolchuun sharafa alaa biyyaaf argamsiisuu fi galii qonnaan bulaas guddisuuf hojjetamaa jiraa jedhan.Keessumaa buna sanyii filatamaa babal'isuu fi oomisha argamus qulqullinaan sassaabuurratti hojjetamaa jiraa jedhan. Kanaafis oomisha biyya keessaaf olu aleriidhaan guddisuuf hojjetamaa jiraa jedhan.Godinicjatti bara kana oomisha toonii kuma 779 ol argachuuf karoorfamee sassaabbiin oomishaa eegalamuu ragaan waajjira qonna godinichaa nii mul'isa.

Waajjira qonna Godina jiima
በሲዳማ ክልል ከ34 ሺህ 500 ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ እየተሰራ ነው።
የክልሉ ቡና፣ ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን እንዳስታወቀው፤ የምርት ጥራትን ለመጠበቅ ትኩረት ተሰጥቷል።
በክልሉ የሚገኙ ቡና ላኪ አርሶ አደሮችና ቡና የሚያዘጋጁ ኢንዱስትሪዎች ዘንድሮ ቡና ፈጥኖ በመድረሱ ምርት የማሰባሰብ ሥራ መጀመራቸውንም ኢዜአ ዘግቧል
ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን በዌራ ዲጆ ወረዳ ለይኛዉ ጡቃ ቀበሌ በአርሶአደሮች ማሠልጠኛ ማዕከል የለማ ቡና ምርት መሰብሰብ ጀምሯል።

በዞኑ ባለፉት ዓመታት የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ በተሰራው ስራ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ መረጃ ጠቁሟል።

የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ ከተሰራው ስራ መካከል በአርሶአደሮች ማሠልጠኛ ማዕከላት ውስጥ ቡናን በሰርቶ ማሳያ ደረጃ በማልማት አርሶ አደሩ ስለ ቡና ተክል ልማት ያለው ግንዛቤ እንዲያደርግ የተሰራው ስራ አንዱ ነው።

አሁንም በማዕከላቱ የቡና ምርት ጥራት አጠባበቅና አዘገጃጀትና አሰባሰብ የቡና አምራች አርሶአደሮች እሸት ቡና ለቀማና ጥራት አዘገጃጀት ግንዛቤ እንዲኖራቸው ተደርጓል።

የቡና ምርት የገበያ ተወዳዳሪነት ከፍ ለማድረግ የቡና ምርት ጥራት አጠባበቅና አዘገጃጀት፣ በቡና ጉንዳላ የአርሶአደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ይገኛል።

ኢትዮ አግሪ ኒውስ