የትምህርት ዓይነቶችና የመመዝገቢያ
መስፈርቶቻቸዉ link:-
http://www.ecsu.edu.et/download/file/fid/7128
http://www.ecsu.edu.et/notice/%E1%89%A02017-
የመመዝገቢየ ቅጽ link:-
Master's Degree application Link: https://bit.ly/3WEePeQ
PhD Degree application link: https://bit.ly/3PUmulg

የኢሲሰዩ በከፍተኛ ዲፕሎማ መርሃ-ግብር ለ6ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን መምህራን አስመረቀ፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ቁጥራቸው 20 የሚሆኑ መምህራንን ለአንድ አመት አሰልጥኖ በከፍተኛ ዲፕሎማ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም አስመረቀ፡፡
በምረቃ መርሃ-ግብሩ ላይ ተገኝተው የከፍተኛ ዲፕሎማውን ሰርቲፍኬት የሰጡት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ፕ/ር ፍቅሬ ደሳለኝ፣ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ካስተላለፉ በኋላ፣ ስኬት ማብቂያ የሌለው የህይወት ጉዞ መሆኑን ገልጸው፣ "ይህንን ስልጠና በመውሰዳችሁ እንደ አንድ ምሁር ዋጋችሁን ከፍ አድርጋችኋል፤ አቅማችሁን ከፍ አድርጋችኋል፤ አቅማችሁ ከፍ ሲል ዋጋችሁም ከፍ ይላል፡፡" በማለት ተናግረዋል፡፡ አስከትለውም ስልጠናው ለዩኒቨርሲቲያችን መምህራን የማስተማር እና የምዘና ስነዘዴዎችን ዘመናዊ በሆነ ጥበብ እና ሳይንስን መሰረት በማድረግ መተግበር እንዲችሉ አቅም የሚፈጥርላቸው መሆኑን፣ በመማር ማስተማር ስራ ላይ ችግር ሲያጋጥም ችግሩን በምርምር ለመፍታት የሚያስችላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ፕ/ር ፍቅሬ የትምህርት ሚኒስቴር በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የከፍተኛ ዲፕሎማ ስልጠና እንዲሰጥ ማድረጉን አስታውሰው፣ ስልጠናው እንዲሰጥ የተደረገበትን ምክንያት ሲያብራሩ "የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ እና ለማረጋገጥ ቁልፉ መምህር መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ነው፡፡" በማለት ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ተመስገን ቢረጋ የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይክቶሬት ዳይሬክተር በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው በውስጥ አቅም የዛሬውን ጨምሮ በስድስት ዙር 156 መምህራንን አሰልጥኖ ያስመረቀ መሆኑን ገልጸው ይህ አሃዝ ከአጠቃላይ የዩኒቨርሲቲው መምህራን ቁጥር 66% ያህሉ መሰልጠናቸውን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡ መርሃ-ግብሩም 290 ሰዓት የወሰደ እና አምስት ሞጁሎችን ያካተተ እንደነበርም አመላክተዋል፡፡ ዶ/ር ተመስገን አክለውም ዩኒቨርሲቲው ከኢፌዴሪ የትምህርት ሚኒስቴር ጋር ከተፈራረማቸው የቁልፍ ተግባራት አመላካቾች መካከል አንዱ የከፍተኛ ዲፕሎማ ስልጠና በመሆኑ በተያዘው የትምህርት ዘመንም ለሰባተኛ ዙር 25 መምህራንን በመቀበልና በማሰልጠን ላይ መሆኑን ጠቅሰው ሰልጣኞቹም ስልጠናቸውን ሲያጠናቅቁ በተቋሙ ያሉ የከፍተኛ ዲፕሎማ ስልጠናው የወሰዱ መምህራንን ቁጥር ወደ 75 በመቶ እንደሚያደርሰው ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም የከፍተኛ ዲፕሎማ ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሮ አበባ ስዩም ለፕሮግራሙ መሳካት ድጋፍ ያደረጉ አካላትን አመስግነው፣ የተመራቂዎቹን ዝርዝር በማቅረብ ሰርተፍኬት እንዲቀበሉ አድርገዋል፡፡

የኢትዮጲያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ሆነዉ ሲያገለግሉ የቆዩት ፕሮፌሰር ፍቅሬ ደሳለኝ አዲስ ለተመደቡት ፕሬዚዳንት ለ ዶ/ር ንጉሥ ታደሰ ርክክብ አደረጉ
-----------------
የኢትዮጲያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ሆነዉ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ ሲያገለግሉ የቆዩት ፕሮፌሰር ፍቅሬ ደሳለኝ ከየካቲት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጲያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ሆነዉ ለተሾሙት ለ ዶ/ር ንጉሥ ታደሰ ርክክብ አደረጉ፡፡
የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ.ም በተደረገው የስራ ርክክብ ወቅት ፕ/ር ፍቅሬ ዩኒቨርሲቲው እያከናወናቸው ያሉትና በቀጣይም በአዲሱ አመራር ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ያሏቸውን አንኳር ጉዳዮች ባጭሩ አቅርበዋል፡፡ ባቀረቡት ሪፖርትም ዩኒቨርሲቲው በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በፈጸመው የመግባቢያ ስምምነት መሰረት ዩኒቨርሲቲው የተቀበላቸውን ቁልፍ የውጤት አመላካቾች በተቋሙ በየደረጃው እስከ ቡድን መሪ ድረስ የወረዱ መሆናቸውን፣ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመሆን በሚደረገው ጥረትም የተለያዩ ፖሊሲዎችና መመሪያዎች ተዘጋጅተው የተጠናቀቁና በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸው፣ ዩኒቨርሲቲው በተሰጠው ተልዕኮ መሰረትም በመደበኛነት ከሚሰጠው የትምህርት መርሀ ግብር በተጨማሪ የሰው ሀብት ልማት ላይ ያተኮረ የብቃት ማጎልበቻና ምዘና ኢኒስትቲዩት በመቋቋም ላይ መሆኑን በሪፖርታቸው ያመላከቱ ሲሆን ሁለት ትልልቅ አዳዲስ ባለ ስምንት ወለል እና ባለ ሰባት ወለል የግንባታ ፕሮጀክቶች ፣ በወሊሶ ካምፓስም አዳዲስና ነባር ፐሮጀክቶች እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ዩኒቨርሲቲው የተለያዩ የምርምርና የስልጠና ፕሮጀክቶች ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት ጋር በውል ስምምነት ተይዘው እየተሰሩ መሆናቸውን፣ የዩኒቨርሲቲው የበጀት አፈጻጸምም ጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኝ እንደሆነ እና በእስካሁኑ ሂደትም ዩኒቨርስቲው በየጊዜው የሚመደብለትን በጀት በአግባቡ በጥቅም ላይ የሚያውል ተቋም መሆኑ የገለጹት ፕ/ር ፍቅሬ በተቋሙ ሌሎችም ሰፋፊ ሥራዎችም እየተሰሩ መሆናቸውን፣ ዩኒቨርሲቲውም ማንኛው ማህበረሰብ ክፍል ያለ ምንም የፖለቲካ ወገንተኝነት ገብቶ የሚማርበት፣ ተመራጭ ዩኒቨርሲቲ ለመሆን መቻሉን አመላክተዋል፡፡ ፕ/ር ፍቅሬ አክለውም በዩኒቨርሲቲው ያለው አመራርና ሰራተኛም እጅግ በጣም ታታሪ የሆነ እና በጥሩ የስራ መንፈስ ላይ የሚገኝ መሆኑን ጠቁመው ለአዲሱ አመራርም መልካም እና ውጤታማ የሆነ የሥራ ዘመን እንዲሆላቸው ያለቸውን መልካም ምኞት ገልጸዋል፡፡
አዲስ የተሾሙት ዶ/ር ንጉሥ ታደሰ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በጣም የተደራጀ ዩኒቨርሲቲ በመሆኑ ለስራ ምቹ ሁኔታዎችን የሚፈጥር የተረጋጋ ስፍራ በመሆኑ ወደ ዩኒቨርሲቲው በመምጣታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡ ነባሩ አመራር ባደረገው ከፍተኛ ጥረት ዩኒቨርሲቲውን አሁን ካለበት ደረጃ ላይ ለማድረስ የቻለ ሲሆን ያለውን ጠንካራ ጎን አጠናክረን ወደፊት መራመድ ይጠበቅብናል ያሉት ዶ/ር ንጉሥ ታደሰ በቀጣይ በየዘርፎች በሚቀርበው ሪፖርት መነሻነትም ምን መሻሻል እንደሚገባውና ምን ላይ የበለጠ ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ የሚታይ መሆኑን ገልጸው ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጋር በመሆን ተቋሙን የበለጠ ከፍ ለማድረግ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
-------------------
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች እና ሠራተኞች ለዶ/ር ንጉሥ ታደሰ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ምኞትእየገለጹ ለፕ/ር ፍቅሬ ደሳለኝ ላበረከቱት አስተዎጾ ምስጋናቸውን ይገልጻሉ፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ

የኢሲሰዩ ፕሬዚዳንት ከአካዳሚክ እና ምርምር ዘርፍ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ
---------------
በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደቡት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ንጉሥ ታደሰ ከአካዳሚክ እና ምርምር ዘርፍ ካሉ አመራሮች ጋር በ 24/6/2017 በሴኔት አዳራሽ የትውውቅና የውይይት መድረክ አካሄዱ፡፡
በመድረኩ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት ወደፊት በጋራ ዉጤታማ ስራ ለመስራት ትዉዉቅ አስፈላጊ መሆኑን፣ በዩንቨርስቲዉ ባሉ ሁሉም መዋቅሮች ትዉዉቁ እንደሚቀጥል ገልጸዉ ተቋሙ ያሉትን ጥሩ ተሞክሮች ማስቀጠል እና አዳዲስ አሰራሮች መተግበር፤ በተጨማሪም ይህ ተቋም አሁን አለም በደረሰበት ደረጃ ማድረስ እና ዘመኑ የሚፈልገዉን አሰራር በተቋሙ መተግበር ግድ የሚል መሆኑን በመጥቀስ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጡት ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ያለዉ የሰዉ ሀይል እንደተቋም እንደሀገርም ትልቅ ሀብት ስለሆነ ያሉትን አቅም ተጠቅመን እንደ ተቋም የተቀመጡ የትኩረት አቅጣጫዎችን በመገንዘብና ያሉ ሀብቶችን እንዲሁም ዕድሎችን በመጠቀም በትጋት መሥራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ተቋሙን በሁሉም መስኮች በሀገርና በአህጉር ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግም አዲሱ አመራር መዘጋጀቱን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ ይህንን ራዕይ በመገንዘብ በዩኒቨርሲቲው ለምርምር ከሚበጀተው በጀት ባሻገር ሀገር አቀፋዊና ዓለም አቀፋዊ ትብብሮችን በመፍጠር ተጨማሪ የምርምር ፈንዶችን ለማግኘት ትልቅ ትኩረት በመስጠት በእቅድ መሥራት እንደሚጠበቅ አጽንኦት ሰጥተዉ አሳስበዋል፡፡
በመርሃ-ግብሩ ላይ የአካዳሚክ ጉዳዮች ዘርፍ ም/ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶ/ር ለማ ጉዲሳ፣ በዘርፉ ያለውን የስራ አፈጻጸም በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን፣ በመማር ማስተማር ሂደት ያሉትን አሁናዊ መረጃዎች፣ ዋናዋና ተግዳሮቶች፣ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን እና አስቸኳይ ስራዎችን አካተው አቅርበዋል፡፡በማስከተልም በዶ/ር አለማየሁ ደበበ የምርምርና ትብብር ዘርፍ ም/ፕሬዚዳንት በዘርፋቸዉ የተከናወኑ አንኳር አንኳር ስራዎች እና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች አቅርበዋል፡፡ በቀጣይም ተሳታፊ የአካዳሚክ አመራሮች ተጨማሪ አስተያየቶች እና ሃሳቦች አቅርበዋል፡፡
በመጨረሻም በየዘርፉ ያሉ አመራሮች ላቀረቡአቸዉ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ፕሬዚዳንቱ ምላሽ የሰጡ ሲሆን፤ ትኩረት የሚሹ ስራዎች ቅድሚያ እንደሚሰጡ ገልጸዉ ፣የተነሱ ሀሳቦች በመውሰድ እንደተቋም በሚለዩ ስትራቴጂክ የትኩረት አቅጣጫዎች እና የሪፎርም ስራዎች ላይ ለዩኒቨርስቲዉ ማህበረሰብ ግንዛቤ መፍጠር እና የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ወደ ትግበራ መግባት ዋናዉ የውይይቱ እና ትዉዉቁ ዓላማ እንደሆነ ፕሬዝደንቱ ገልጸዋል፡፡

የአለም አቀፍ የሴቶች ቀን በኢሲሰዩ ተከበረ
--------------------
የአለም አቀፍ የሴቶች ቀን በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ (ኢሲሰዩ) ማህበረሰብ በልዩ ልዩ መርሀ- ግብሮች ተከበረ፡፡ ዕለቱም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ114ኛ ጊዜ በሀገራችምን ለ 49ኛ ጊዜ “ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል” በሚል መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን በዩኒቨርሲቲው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ አዘጋጅነት የካቲት 2 ቀን 2017 ዓ.ም ተከብሯል፡፡
በበዓሉ መክፈቻ ላይም ዶ/ር ለማ ጉዲሳ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚደንት ባደረጉት የእንኳን ደስ አላችሁ ንግግር ሴቶች በአለማችን እንዲሁም በአገራችን ላይ የነበሩ ዘርፈ ብዙ የመብት ተግዳሮቶችን በማለፍ ሴቶችን በሁሉም መስክ ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ የዓለም መንግስታትና አገራችንም ምቹ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን በመንደፍ እና ለተግባራዊነቱም የተለያዩ መዋቅራዊ አደረጃጀቶችን በመቅረጽ እንዲሁም በጀት በመመደብ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ሲያከናውኑ መቆየታቸውንና አሁንም እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸው በዚህም በሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ረገድ አበራታች ለውጦች ተመዝግቧል ለማለት እንደተቻል በንግግራቸው አመላክተዋል፡፡ የዕለቱ መከበርም በሴቶች ትግል ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ሴቶች ለማሰብ እና የሴቶችን መብትና እኩልነት ላይ ያስመዘገቡትን አስተዋጽኦ በማውሳትና በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋለ፡፡
የሴቶች ተሳትፎ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሲታይ ከግዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ቢሆንም አሁንም በቂ ደረጃ ላይ እንዳልሆነ እና ከምርምር አንጻርም ሴቶች ያላቸው ተሳትፎ አነስተኛ መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ለማ ጉዲሳ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ይህንን ተግዳሮት ከመቅረፍ እንጻር የታቀዱና በመከናወን ላይ ያሉ በርካታ ጉዳዮች መኖራቸውንና ለአብነት ያህልም ሴቶች አሁን በዩኒቨርሲቲው ያላቸውን የሃያ አምስት በመቶ የአመራርነት ድርሻ በ2017 መጨረሻ ወደ ሰላሳ በመቶ ድርሻ በማሳደግ የሴቶችን የአመራር ሚና ማሳደግ፣ እየተሰጡ ያሉ የሴቶችን አቅም የሚገነቡና ግንዛቤ በሚያስጨብጡ መረሀ-ግብሮች አጠናክሮ ማስቀጠል፣ በመደራጀት ላይ የሚገኘውን የህጻናት ማቆያ በቅርቡ ስራ እንዲጀምር ማድረግ ፣ ለሴቶች ልዩ የምርምር ድጋፍ በ2018 ዓ.ም ተግባራዊ ማድረግና በዩኒቨርሲቲው የሴቶች ጥቃትን ያለምንም ትዕግስት በጽኑ መታገልን እንዲሁም ሌሎችም ጉዳዮችንም በስፋት የሚሰራባቸው እንደሚሆኑ ጠቅሰዋል፡፡
በዝግጅቱ ላይም ዶ/ር አዜብ አሰፋ የስልጠና ኢኒስቲትዩት ዲን ዕለቱን አስመለክቶ ባቀረቡት የመወያያ ሰነድ ዕለቱ የሚከበርበት ዓላማን አስመልክቶ ቀደምት ሴቶች በማህበራዊ ፣ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ላይ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ እና የተመዘገቡ ድሎችን የምንዘክርበትና ሴቶቹን የምናከብርበት፣ ወደፊትስ ምን ለውጥ መምጣት እንዳለበት በጋራ የምንመክርበት ነው ብለዋል፡፡ ለዚህ ቀን መድረስም በርካታ ዋጋ የተከፈለበትና የህግ ማዕቀፎች መሻሻል፣ በየደረጃው ያለም አደረጃጀት መመስረት፣ የሥርዓተ-ጾታ አካቶ ትግበራ በየተቋማቱ መኖር፣ የሴቶች በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣ በማህበራዊና በትምህርት ያላቸው ተሳትፎ ማደግ ብሎም በእናቶችና ህጻናት የጤና አጠባበቅን በማሳደግ ረገድ መሻሻል መኖራቸውንና የበለጠ ሊጠናከሩ እንደሚገባ አመልክተው እንደ ኢ-ፍትሀዊ የሆነ የሥርዓተ-ጾታ አሰራሮች፣ ጦርነትና ግጭቶች፣ ጾታዊ ጥቃቶች እና የመሳሰሉት የሴቶችን በሁለንተናዊነት የማብቃት እንቅስቃሴ ላይ እንደ ተግዳሮት የሚነሱ መሆናቸውን ዶ/ር አዜብ በገለጻቸው አመላክተዋል፡፡
በማስከተልም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሴቶች የምርምር ተሳትፎን በሚመለከት ዶ/ር ትግዛው ላመስግን፣ ዶ/ር መረጊቱ ደበላ፣ ዶ/ር ትህትና አያሌው እና ወ/ሮ ኤደን ቡሽራ ከተሞክሯቸው በመነሳት ያለቸውን ልምድ ለበዓሉ ተሳታፊዎች ያቀረቡ ሲሆን የበዓሉ ተሳታፊዎችም በቀረበው የመወያያ ሰነድና በቀረቡት ሀሳቦች ላይ እንዲሁም በተቋሙ ለወደፊት ሊተገበሩ ይገባሉ ባሏቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲው በሂደት ላይ የሚገኘው የህጸናት ማቆያም ተጠናቆ ሥራ እንዲጀምር እንዲደረግም ተሳታፊዎቹ በአጽንኦት ጠይቀዋል፡፡
በመጨረሻም በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ሴት ተማሪዎች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በኢሲሰዩ የዕጩ ዲፕሎማቶች ስልጠና ተጀመረ
-------------------------------------------------------
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጪ ጉዳይ ስልጠና ኢኒስቲትዩት ጋር በመተባበር ስድስተኛው ዙር የዕጩ ዲፕሎማቶች ስልጠና ጀመረ፡፡ መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም በተደረገው የስልጠና መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይም ክቡር ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቴዎስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር በመገኘት ከሰልጣኖችጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
በስልጠናው መክፍቻ ላይ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር ንጉሥ ታደሰ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ የሲቪል ሰርቫንቱን አቅም ለመገንባት የተቋቋመ ተቋም እንደመሆኑ መጠን ከምስረታው ጀምሮ በርካታ ለሀገር ባለውለታ የሆኑ አመራሮችንና ባለሙያዎችን ያፈራ እና አሁንም በማፍራት ላይ ያለ ተቋም መሆኑን አስታውሰው ከማንኛውም የመንግስት ተቋም ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም ባለፉት ዓመታትም ከኢፌዴሪ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋርም ጠንካራ ግንኙነት ያለው መሆኑንና ያለፉት አምስት ዙር ስልጠናዎችም በስኬት እንዲጠናቀቁ ዩኒቨርሲቲው የበኩሉን ድርሻ መወጣቱን አስታውሰዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ዩኒቨርሲቲው የዲፕሎማሲና ዓለም አቀፍ ግንኙነት የትምህርት ፕሮግራምን በመክፈትና ተማሪዎችን በማሰልጠን ላይ መሆኑን ገልጸዋል።ስድስተኛውን ዙር የዕጩ ዲፖሎማቶች ስልጠናን አስመልክተው እንደተናገሩት ሰልጣኞች በዩኒቨርሲቲው በሚኖራቸው ቆይታ የተሳካ እንዲሆን አመራሩ ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደረግ ገልጸዋል፡፡
በስድስተኛው ዙር ስልጠናም ሃምሳ ዕጩ ዲፖሎማቶች ለአራት ወራት ስልጠና የሚሰጣቸው ሲሆን ከእነዚህ መካከልም ሰላሳ አንድ ሰልጣኞች ሴት ዕጩ ሰልጣኞች ሲሆኑ በአጠቃላይ ሰልጣኞቹም በመጀመሪያው ዙር የፖሊሲ ስልጠና እንዲሁም በቀጣዩ የአካዳሚክና ተግባር ተኮር ሰልጠና የሚወስዱ እንደሚሆን ከመድረኩ ተገልጿል፡፡

የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ለሚወስዱ ዕጩ ተመራቂዎች ይመለከታል
ትምህርት ሚኒስቴር ከሰኔ 2017 ጀምሮ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ለሚወስዱ ዕጩ ተመራቂዎች እና ዳግም ተፈታኞች ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ እንደቅድመ ሁኔታ መቀመጡ ይታወቃል። በመሆኑም በኢሲሰዩ እየተማራችሁ ያላችሁ እና ከዚህ ቀደም ተፈትናችሁ ማለፊያ ውጤት ያላሟላችሁ የዩኒቨርስቲዉ ተፈታኞች ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ምዝገባ እንድታካሂዱ፡፡
ማሳሰቢያ፡
1.ለመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች መረጃ ማስገቢያ ሲስተም (https://eap.ethernet.edu.et ) ላይ ማስተካካያ ስልተደረገ በቅርቡ ORIENTATION የሚሰጥ ይሆናል።
2.ዳግም ተፈታኝ አመልካቾች ከሚያዝያ 14/2017 ዓ.ም -- ግንቦት 05/2017 ዓ.ም ድረስ ከላይ የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት በ https://exam.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ ትችላላችሁ።
3.ዳግም ተፈታኞች የአገልግሎት ክፍያ የምትከፍሉት በቴሌ ብር በኩል ብቻ ነው።

eap.ethernet.edu.et
Ministry of Education
Ministry of Education | Exit exam data hub