Ethiopian Civil Service University
10.8K subscribers
338 photos
5 files
25 links
The first public service university in Ethiopia.
Download Telegram
👍29❤1
👍11👏3🔥2❤1
👍19❤1
በኢሲሰዩ የዕጩ ዲፕሎማቶች ስልጠና ተጀመረ
-------------------------------------------------------
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጪ ጉዳይ ስልጠና ኢኒስቲትዩት ጋር በመተባበር ስድስተኛው ዙር የዕጩ ዲፕሎማቶች ስልጠና ጀመረ፡፡ መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም በተደረገው የስልጠና መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይም ክቡር ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቴዎስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር በመገኘት ከሰልጣኖችጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

በስልጠናው መክፍቻ ላይ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር ንጉሥ ታደሰ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ የሲቪል ሰርቫንቱን አቅም ለመገንባት የተቋቋመ ተቋም እንደመሆኑ መጠን ከምስረታው ጀምሮ በርካታ ለሀገር ባለውለታ የሆኑ አመራሮችንና ባለሙያዎችን ያፈራ እና አሁንም በማፍራት ላይ ያለ ተቋም መሆኑን አስታውሰው ከማንኛውም የመንግስት ተቋም ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም ባለፉት ዓመታትም ከኢፌዴሪ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋርም ጠንካራ ግንኙነት ያለው መሆኑንና ያለፉት አምስት ዙር ስልጠናዎችም በስኬት እንዲጠናቀቁ ዩኒቨርሲቲው የበኩሉን ድርሻ መወጣቱን አስታውሰዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ዩኒቨርሲቲው የዲፕሎማሲና ዓለም አቀፍ ግንኙነት የትምህርት ፕሮግራምን በመክፈትና ተማሪዎችን በማሰልጠን ላይ መሆኑን ገልጸዋል።ስድስተኛውን ዙር የዕጩ ዲፖሎማቶች ስልጠናን አስመልክተው እንደተናገሩት ሰልጣኞች በዩኒቨርሲቲው በሚኖራቸው ቆይታ የተሳካ እንዲሆን አመራሩ ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደረግ ገልጸዋል፡፡

በስድስተኛው ዙር ስልጠናም ሃምሳ ዕጩ ዲፖሎማቶች ለአራት ወራት ስልጠና የሚሰጣቸው ሲሆን ከእነዚህ መካከልም ሰላሳ አንድ ሰልጣኞች ሴት ዕጩ ሰልጣኞች ሲሆኑ በአጠቃላይ ሰልጣኞቹም በመጀመሪያው ዙር የፖሊሲ ስልጠና እንዲሁም በቀጣዩ የአካዳሚክና ተግባር ተኮር ሰልጠና የሚወስዱ እንደሚሆን ከመድረኩ ተገልጿል፡፡
👍12❤6
👍15❤5
👍31❤10
የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ለሚወስዱ ዕጩ ተመራቂዎች ይመለከታል

ትምህርት ሚኒስቴር ከሰኔ 2017 ጀምሮ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ለሚወስዱ ዕጩ ተመራቂዎች እና ዳግም ተፈታኞች ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ እንደቅድመ ሁኔታ መቀመጡ ይታወቃል። በመሆኑም በኢሲሰዩ እየተማራችሁ ያላችሁ እና ከዚህ ቀደም ተፈትናችሁ ማለፊያ ውጤት ያላሟላችሁ የዩኒቨርስቲዉ ተፈታኞች ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ምዝገባ እንድታካሂዱ፡፡


ማሳሰቢያ፡
1.ለመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች መረጃ ማስገቢያ ሲስተም (https://eap.ethernet.edu.et ) ላይ ማስተካካያ ስልተደረገ በቅርቡ ORIENTATION የሚሰጥ ይሆናል።
2.ዳግም ተፈታኝ አመልካቾች ከሚያዝያ 14/2017 ዓ.ም -- ግንቦት 05/2017 ዓ.ም ድረስ ከላይ የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት በ https://exam.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ ትችላላችሁ።
3.ዳግም ተፈታኞች የአገልግሎት ክፍያ የምትከፍሉት በቴሌ ብር በኩል ብቻ ነው።
👍29❤14🔥3
👍23❤18
❤39👍34
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ግንዛቤ ማስጨበጫ
👍7
👍23❤7👏1
👍41👏9❤8😁4
የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ መልቀቂያ ፈተና በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ ነው::
-------------------------------------

የ2017 ዓ.ም. 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በበይነ መረብና በወረቀት ከ23/10/2017 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰጠ ይገኛል ፡፡የመጀመሪያ ቀን የጠዋት ፈተናም ያለምንም እንከን ተጠናቋል፡፡
❤16👍1
🙏14❤13👍7🔥1