Ethiopian Association of Civil Engineers
4.99K subscribers
393 photos
14 videos
46 files
226 links
Channel for Ethiopian Association of Civil Engineers members to updated current construction issues, information and opportunities
Download Telegram
Forwarded from Ethiopian Construction Authority (ሲሳይ ደርቤ)
የመንገድ ዘርፍ አፈጻጸም ላይ የሚታዩ ተግዳሮቶች እና ቀጣይ አካሄዶች ላይ ውይይት ተካሄደ

የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚንስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ የኢ መ አ መንገድ ምርምር ማዕከልን ጎብኝተዋል

አዲስአበባ፣ መጋቢት 09፣ 2017 (ኢ መ አ):- የመንገድ ዘርፍ አፈጻጸም ላይ የሚታዩ ተግዳሮቶች እና ቀጣይ አካሄዶች ላይ በኢ መ አ የመንገድ ምርምር ማዕከል ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱ ላይ በመንገድ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ስኬቶች፣ ዘርፉን የገጠሙት ተግዳሮቶች እና ቀጣይ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ ገለጻ ተደርጓል። በተጨማሪም ከሚንስቴር መ/ቤቱ ድጋፍ ሊደረግባቸው የሚችሉ ጉዳዮችም ተለይተው ቀርበዋል።

በዚህም ረገድ የሀገሪቷን የመንገድ ሽፍን የመንገድ ዘርፍ ልማት ፕሮግራሙ በ1989 ከነበረበት 23 ሺህ ኪሎሜትር አሁን ላይ ወደ 171 ሺህ ማድረስ እንደተቻለ ገላጻው ላይ ተጠቁሟል።

ሆኖም ባለፉት ጊዜያት የጋጠሙ የግንባታ ግብዓት ዋጋ መናር፣ የወሰን ማስከበር፣ የጸጥታ ስጋት፣ የመንገድ ጥገና ላይ ያሉ ክፍተቶች(የማሽነሪ እና የባለሞያ እጥረት)፣ ደካማ የፕሮጀክት አመራር እና የሀገር በቀል የሥራ ተቋራጮች ተወዳዳሪነት ማነስ ዘርፉን እንደፈተኑት ተነስቷል።

ይህም ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ዋጋ እና በቀመጠላቸው ጊዜ እንዳይጠናቀቁ እንዲሁም ብቁ እና ተወዳዳሪ ተቋራጮች ገበያ ላይ እንዲቀንሱ ተጽዕኖ አሳድሯል ተብሏል።

የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ማድረግ፣ መጠናቀቅ በሚችሉ ፕሮጀክቶች ላይ ቅድሚያ ትኩረት መስጠት እንዲሁም የግብዓት አቅርቦት ላይ ያሉ ችግሮችን መቅረፍ እንደሚገባ በገለጻው ላይ ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር መሐመድ አብዱራህማን (ኢ/ር)፤ ዘርፉ ላይ የሠው ኃይል እጥረት መኖሩን ጠቁመው፣ አሁን ካለው በተሻለ ዘርፉ ብቁ እና ሥልጡን በኾኑ ባለሞያዎች በሳይንሳዊ መንገድ መመራት ይኖርበታል ብለዋል።

የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚንስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ፤ መንገድ በሀገሪቱ ዕድገት ላይ የማይተካ ሚና እንዳለው አንስተው፣ የዘርፉ ተግዳሮቶች ውስብስብ በመኾናቸው ለመሠረታዊ ችግሮች ቅድሚያ መስጠት ይገባል ብለዋል።

ካለው የሥራ ስፋት እና ውስብስብነት አንጻር ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርቦ በመፍትሄዎቹ ላይ መምከር እንደሚገባም ገልጸዋል።

ቀሪ የወሰን ማስከበር ሥራዎችን ማጠናቀቅ እና ከአዋጁ ጋር በተገናኘ ያሉ ክፍተቶች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ መሥራት፣ የመንገድ ጥገና ዘርፉን ለግል ተቋራጮች ሳቢ ማድረግ እንዲሁም ተቋማዊ ባሕልን ዳግም ማጤን እንደሚገባ ክብርት ሚንስትሯ አሳስበዋል።

በቀጣይም በሚንስቴር መ/ቤቱ በኩል ድጋፍ ሊደረግባቸው የሚቻልባቸውን ጉዳዮች በመለየት አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግም አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል የኢ መ አ የመንገድ ምርምር ማዕከል አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ላይ ገለጻ እና ጉብኝት ተደርጓል።

ማዕከሉ አዳዲስ ሐሳቦችን የሚያመነጭ እና ዘመኑን የዋጀ መኾን እንደሚገባው እንዲሁም ከምርምር በዘለለ የመንገድ ዘርፉን በማዘመን ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተጠቁሟል።
ምንጭ :- የኢት/ያ መንገዶች አስተዳደር

በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
👍4
Forwarded from EACE
Dear Members,
Use this number +251990311800 for membership related questions and to get other information.

Regards,
Ethiopian Association of Civil Engineers
How to Become a Member

Joining EACE is quick and easy! You can register online at https://eacecivil.org/join/basic-info.

Required Documents:

A clear photograph of your face

A copy of your identification

Your degree certificate


Ensure your files are small in size; you can use a compression app like Telegram if needed. Registration can be completed using either a phone or a computer.

Membership Payment:

After registering, send proof of payment to eaceregister@gmail.com. Approval typically takes one to two days.

Collecting Your EACE ID:

Once approved, visit the EACE office at Kazanchis, Ola Station, 1st Floor, Office No. 03 to collect your ID. Bring two passport-sized (3x4) photos. For inquiries, call +251 990 311 800.

We look forward to welcoming you to EACE!
👍7
EACE Statistics
Females 14%
👍32