ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹
2.95K subscribers
2.46K photos
76 videos
2 files
335 links
ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል

DW AMHARIC NEWS IS A GLOBAL NEWS AND INFORMATION CHANNEL FROM A GERMAN INTERNATIONAL BROADCASTER DEUTSCHE WELLE (DW)
Download Telegram
#BREAKING

በደቡብ ሱዳን በአንድ ቀን 54 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

የደቡብ ሱዳን ጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ባለፉት 24 ሰዓት ሃምሳ አራት (54) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸውን ሪፖርት አድርጓል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 290 ደርሰዋል።

በአጠቃላይ በሀገሪቱ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች አራት (4) ሲሆኑ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ደግሞ የሶስት (3) ሰዎች ናቸው።

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
ለአንድ ላፕቶፕ 152 ሺህ ብር፣ ለአንድ ሞባይል 94 ሺህ ብር ግዢ ተፈጽሟል

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች የማይመለስ ሞባይልና ላፕቶፕ ለአንድ ጊዜ እንዲገዛላቸው ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል:: ሆኖም ከግዥና ንብረት አስተዳደር የተላለፈውን የግዥ መመሪያ በጣሰ መልኩ አንዳንድ ተቋማት በተጋነነ ዋጋ ግዥ መፈጸማቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር የኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ጀነራል አቶ ፍቃዱ አጎናፍር፤ እንደገለፁት ይህንን የፈጸሙ በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑና ልዩነቱንም ሊከፍሉ ይገባል የሚል አስተያየት ለገንዘብ ሚንስቴር ዴኤታ ሐሳብ መቅረቡን ገልጸዋል፡፡

ኦዲተሮች ባደረጉት ልዩ ኦዲት በአፈፃፀም መመሪያው ከተዘረዘረው ውጭ እንደ አይፎን ስልክና አፕል ላፕቶፖች ሕገ ወጥ ግዥ መፈፀሙን በግልጽ ጨረታ መገዛት ሲገባውም በፕሮፎርማ መገዛቱን፤ አንዳንድ ተቋማት ለማይመለከታቸው ኃላፊዎች ጭምር ገዝተው መገኘታቸውን ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።

ግዥ ከፈፀሙት 42ቱ ተቋማት ብቻ 10 ሚሊየን 96 ሺህ 896 ብር ወጪ ሆኗል። በግዥው ከፍተኛው ለአንድ ላፕቶፕ 152 ሺህ፣ለአንድ ሞባይል 94 ሺህ ብር ሲሆን ዝቅተኛ ወጪ ደግሞ ለአንድ ላፕቶፕ 20 ሺህ 254 ብር፣ ለአንድ ሞባይል 12 ሺህ ብር መሆኑን አስታውቀዋል።

#EPA
@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
በእስራኤል የቻይናው አምባሳደር በቴል አቪቭ በሚገኘው በቤታቸው ሞተው ተገኙ!

በእስራኤል የቻይናው አምባሳደር በቴል አቪቭ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው አልጋቸው ላይ ሕይወታቸው አልፎ የተገኘ ሲሆን ለሞታቸው ምክንያቱ ምን እንደሆነ እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

በቅርቡ የካቲት ወር ላይ የተሾሙት አምባሳደሩ ከዚህ በፊት ዩክሬን ውስጥ የቻይና ልኡክ ሆነው ሲሰሩ ነበር። አምባሳደሩ የአንድ ልጅ አባት ሲሆኑ ባለቤታቸውም ሆነ ልጃቸው በአገር ውስጥ እንዳልነበሩ ተገልጿል። አምባሰደር ዱ በቴልአቪቭ ሄርዚሊያ በምትባል አካባቢ ነዋሪ ነበሩ።

የእስራኤል ፖሊስ ቃለ አቀባይ ለሮይተርስ ዜና ወኪል እንደተናገሩት ፖሊስ የሞቱበት ስፍራ ደርሶ ሁኔታውን እያየ መሆኑን ነው። የእስራሌል ቴሌቪዥን ጣቢያ ስሙ ካልተጠቀሰ የህክምና ምንጭ አገኘሁት ባለው መረጃ የመጀመሪያ ምርመራ እንደሚጠቁመው አምባሳደሩ በእንቅልፍ ላይ እንዳሉ በተፈጥሯዊ ሞት መሞታቸውን ነው።

#BBC
@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በቢሾፍቱ ችግኝ ማፍያ ተገኝተው በመጪው ክረምት ለሚካሄደው የ5 ቢሊዮን ችግኞች የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የሚደረገውን ዝግጅት ጎብኝተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት "ፕሪሲሽን ቴክኖሎጂን በመጠቀም እስካሁን የደረስንበት የክንውን ደረጃ የሚደነቅ ሲሆን፣ ሀገራችንን አረንጓዴ ልምላሜ የማልበስ ግባችንን የሚደግፍ ነው" ብለዋል፡፡

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
በአዲስ አበባ የሚገኙ ቁጥራቸው ከ900 በላይ የሚሆኑ የላዳ ታክሲ አሸከርካሪዎች የደም ልገሳ አድርገዋል፡፡ ለዚህ ተግባራቸውም የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ምስጋናቸውን ለአሽከርካሪዎቹ አቅርበዋል።

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
በሊባኖስ ውስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ከዛሬ ጀምሮ አዲስ አበባ መግባት ይጀምራሉ!

(ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8)

በሊባኖስ በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት በአስከፊ ሁኔታ ህይወታቸውን የሚመሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን እንዳሉ ይታወቃል።

በተለይም ኮሮና ቫይረስ በዓለማችን ከመከሰተ ጊዜ ጀምሮ ደግሞ እነዚህ ኢትዮጵያዊያን ለአስከፊ ችግር መዳረጋቸውን የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎቹን እንዲታደግ ተደጋጋሚ ጥያቄ ሲያቀርቡ ነበር።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ እንዳስታወቀው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ቀጣዮቹ አምሰት ቀናት ድረስ በችግር ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው መግባት ይጀምራሉ።

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 11 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4,225 የላብራቶሪ ምርመራ አስራ አንድ (11) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሶስት መቶ አስራ ሰባት (317) ደርሷል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው 5 ወንድ እና 6 ሴት ናቸው። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ከ17 እስከ 45 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 4 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፣ 6 ሰዎች ከሶማሌ ክልል (ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ) እንዲሁም 1 ሰው ከአማራ ክልል (ሰሜን ሸዋ ዞን፣ አጣየ ከተማ ለይቶ ማቆያ) ናቸው።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 7

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው - 3

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው - 1

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
#ATTENTION

መንግስት በጎረቤት ሀገራት ያለውን ከፍተኛ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከግምት ውስጥ በማስገባት በድንበር አካባቢዎች ከፍተኛ ቁጥጥር ማድረግ ካልቻለ በሀገር ደረጃ ከፍተኛ ዋጋ መክፈላችን አይቀርም።

በተለይም ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ሰዎችን አንድ በአንድ እየተከታተሉ ኳረንታይ ማድረግ እጅግ ወሳኝ ነው። ትንሽ ስህተት ብዙ ዋጋ ነው የሚያስከፍለው!

በተጨማሪ የደንበር ተሻጋሪ ሹፌሮችንና ረዳቶችን በከፍተኛ ትኩረት ተከታትሎ የጤናቸውን ሁኔታ በምርመራ ማረጋገጥ ካልተቻለን ከባድ ሁኔታ ውስጥ ይከተናል።

እያንዳንዱን የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎችን አንድ በአንድ እየተከታተሉ መመርመር ቢቻል መልካም ነው ፤ የደንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች ኳራንታይን ሳይደረጉ ወደ ተለያዩ የሀገራችን ከተሞች እንደሚገቡ በተደጋጋሚ ተገልፆልናል።

ጊዜው ረፍዶ ከማዘን ከአሁኑ መፍትሄ ይፈለግ!

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
#TAXIYE

“ታክሲዬ” በባሕር ዳርና ጎንደር ከተሞች የኤሌክትሮኒክ የትራንስፖርት አገልግሎት ሥራ ሊጀምር መሆኑን በላከልን መልዕክቱ ገልጿልናል፡፡

አገልግሎቱን ለመስጠትም በባሕር ዳር ከተማ በአውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት ከሚሰጡ 40 አሽከርካሪዎች፣ 50 ከሚሆኑ የባለ ሦስት እግር አሽከርካሪዎች ጋር መግባባት ላይ መድረሱን ነው ያስታወቀን፡፡

በተመሳሳይም በጎንደር ከተማ ይህንን አገልግሎት ከሚሰጡ 28 ታክሲዎች ጋር በቅርቡ ወደ ሥራ እንደሚገቡና ለተገልጋዮች አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ ገልጸዋል፡፡

#TAXIYE

“ታክሲዬ” በባሕር ዳርና ጎንደር ከተሞች የኤሌክትሮኒክ የትራንስፖርት አገልግሎት ሥራ ሊጀምር መሆኑን በላከልን መልዕክቱ ገልጿልናል፡፡

አገልግሎቱን ለመስጠትም በባሕር ዳር ከተማ በአውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት ከሚሰጡ 40 አሽከርካሪዎች፣ 50 ከሚሆኑ የባለ ሦስት እግር አሽከርካሪዎች ጋር መግባባት ላይ መድረሱን ነው ያስታወቀን፡፡

በተመሳሳይም በጎንደር ከተማ ይህንን አገልግሎት ከሚሰጡ 28 ታክሲዎች ጋር በቅርቡ ወደ ሥራ እንደሚገቡና ለተገልጋዮች አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ ገልጸዋል፡፡

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
የሀይሌ ጋርመንት —ጀሞ መንገድ ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ነው

መንገዱ 4.5 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ሲሆን 6 ተሽከርካሪዎች ማስተናገድ የሚችል፣ 60 ሜትር ስፋት ያለው፣ የእግረኛ መጓጓዧና የብስክሌት መጓጓዧ መንገድን ያካተተ ነው ተብሎለታል። በቀጣይም ሁለተኛው ምእራፍ ግንባታ የሚቀጥል ይሆናል ሲል ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

የመንገዱ ግንባታ በአካባቢው የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ የታሰበና እንዲሁም አዲስ አበባን ከሚያዋስኑ የኦሮሚያ ከተማዎች ጋር በዘመናዊ መንገድ በማስተሳሰር የንግድ ስርአቱን ለማቀላጠፍ ያለመ ነው፡፡

ሼር ➡️ @dwamharic_news
ሼር ➡️ @dwamharic_news
የወልቂጤ ከተማ የጤና ባለሙያዎች በከተማው አውራ ጎዳናዎች በመንቀሳቀስ ህብረተሰቡን ስለ "covid 19 "አኛ ለእናንተ እዚህ አለን እባካችሁን እናንተ ለእኛ እቤታችሁ ሁኑልን"በሚል መሪ ቃል ግንዛቤ ማሰጨበጣቸውን ሰምተናል። በቅስቀሳው ለተሳተፉ የጤና ባለሙያዎች የከተማው ጤና ጽ/ቤት ሃለፊ አቶ አሳያስ ናስር ምስጋናቸውን የቸሩ ሲሆን አክለውም ህብረተሰቡ ከጤና ባለሙያዎች የሚተላለፉ መልእክቶችን እንዲተገብር ጥሪ አስተላልፈዋል።

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
በማዳጋስካር የመጀመሪያው ሞት ተመዘገበ!

በማዳጋስካር የመጀመሪያው #ሞት መመዝገቡን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡ ቅዳሜ ምሽት መሞቱ የተገለጸው ግለሰብ የ57 ዓመት የህክምና ባለሞያ እንደሆነና ተጓዳኝ በሽታዎች እንደነበሩበት CGTN ዘግቧል፡፡

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
ኬንያ ውስጥ በአንድ ቀን 57 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውን የኬንያ ጤና ሚኒስቴር ሪፖርት አድርጓል። አጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 887 ደርሰዋል።

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
በሱማሊያ ተጨማሪ 64 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት በሱማሊያ ተጨማሪ 64 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 1,421 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት አራት (4) ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 152 ደርሷል።

በተጨማሪ የ1 ሰው ህይወት ማለፉን ተከትሎ አጠቃላይ በሀገሪቱ በኮቪድ-19 ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ሃምሳ ስድስት (56) ደርሷል።

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
ካምቦዲያ ከኮቪድ-19 ታማሚዎች #ነፃ ሆነች!

በካምቦዲያ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ 122 ሰዎች መካከል #ሁሉም በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው ማገገማቸው ተገልጿል።

በትላንትናው ዕለት የመጨረሻዋ የኮሮና ቫይረስ ታማሚ (የ36 ዓመት ሴት) ከሆስፒታል ወጥታለች።

ካምቦዲያ ከሚያዚያ 4/2012 ዓ/ም በኃላ አዲስ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ኬዝ ሪፖርት አላደረገችም።

የሀገሪቱ መንግስት አሁንም የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የጣላቸውን ገደቦች አላነሳም። ትምህርት ቤቶች አሁንም እንደተዘጉ ናቸው ፤ በድንበር አካባቢ የሚደረገው ቁጥጥር እንደተጠናከረ ነው፤ ኳረንታይንም ቀጥሏል።

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
የኤርትራ ልዑክ በካርቱም ከፕሬዚዳንት አል ቡርሃን ጋር ተወያየ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዑስማን ሳሌህን እና የፕሬዝዳንቱን ከፍተኛ አማካሪ የማነ ገብረአብን ያካተተው የኤርትራ ልዑክ በካርቱም ከሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አል ቡርሃን ጋር መወያየታቸውን የኤርትራ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ልዑኩ የኮሮና ወረርሽኝን በጋራ መከላከልን ጨምሮ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ የትብብር ጉዳዮችን በተመለከተ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የተላከውን ደብዳቤ ለአል ቡርሃን አስረክቧል። አል ቡርሃንም ለሱዳን የቀረበች ካሏት ኤርትራ ለተላከላቸው ደብዳቤ አመስግነው ተቀብለዋል።

የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ግንኙነትን ይበልጥ ለማሳደግ ጠንከር ያሉ እርምጃዎችን በእርግጥ መውሰድ እንደሚያስፈልግም ነው ቡርሃን የገለጹት። በሱዳን እየተካሄዱ ስላሉ የለውጥ ሂደቶችም ለልዑኩ አስረድተዋል። ዛሬና ትናንት በአዲስ አበባ የኢትዮ ሱዳን ከፍተኛ የፖለቲካ ምክክር መድረክ መካሄዱ የሚታወስ ነው።

#AlAin
@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
በሱዳን ተጨማሪ 302 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

(በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ)

የሱዳን ጤ/ሚ/ር ባወጣዉ መግለጫ ተጨማሪ 302 ሰዎች ላይ ኮሮና ቫይረስ መገኘቱንና የ8 ሰዎች (3 ከካርቱም ግዛት) ህይወት ሲያልፍ 25 ሰዎች (22 ከካርቱም) በተደረገላቸዉ ህክምና ማገገማቸዉን ገልጿል።

ቫይረሱ የተመዘገበባቸዉ ግዛቶች ፦

1. ካርቱም ግዛት 235
2. ጀዚራ 11
3. ሰሜን ኮርዶፋን 11
4. ገዳሪፍ 7
5. ስናር 10
6. ምዕራብ ዳርፉር 10
7. ሰሜን ዳርፉር 5
8. ደቡብ ዳርፉር 5
9. ኒል አዘርገ 3
10. ኒል አብያድ 4
11. ምዕራብ ኮርዶፋን 1

በዚህ መሰረት ባጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2,591 (ካርቱም ግዛት 2,109) መድረሱንና ከዚህ ዉስጥ 105 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ 247 ሰዎች ማገገማቸዉን ታውቋል።

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
#COVID19

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ መሳሪያ ስራ ጀመረ። መሳሪያው በአንድ ጊዜ 92 ሰው የመመርመር አቅም እንዳለውም ተገልጿል።

ቀደም ሲል በክልሉ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ማሽን #ባለመኖሩ የተጠርጣሪ ማህበረሰብ ክፍሎችን ናሙና አዲስ አበባና ባህርዳር ሲላክ ቆይቷል።

ይህንን ለመቅረፍ የክልሉ መንግስት ከጤና ሚኒስቴር ፣ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት እና ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመነጋገር ፒሲአር ማሽኑን ክልሉ አግኝቷል።

ትናንት በሙከራ ደረጃ 9 ሰዎችን መርምሮ ውጤታማ በመሆኑ ዛሬ የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ አሻድሊ ሀሰንና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

(የክልሉ ጤና ቢሮ)
@dwamharic_news @dwamharicnewsbot
በአዲስ አበባ ለሚገኙ ለ8ኛና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሞዴል ፈተና ተዘጋጀ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2012 የትምህርት ዘመን ለ8ኛ ክፍል በ2 ቋንቋዎች እና ለ12ኛ ከፍል ተማሪዎች ሞዴል ፈተና በማዘጋጀት ከነገ ጀምሮ በተዘጋጀው የፈተና ጊዜ ሰሌዳ መሰረት ተደራሽ ለማድረግ ዝግጅቴን ጨርሻለሁ ሲል ገልጿል፡፡

ቢሮው የተዘጋጀውን የሞዴል ፈተና ተማሪዎች በአግባቡ እንዲወስዱና እና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ እንዲሁም ወላጆች ልጆቻችሁ ጥያቄዎቹን በአግባቡ መስራታቸዉን እንዲያረጋግጡ ጥሪ አቅርቧል፡፡ የሞዴል ፈተናው የሚሰጠው ተማሪዎች ራሳቸውን እንዲያዘጋጁበት ብቻ የተዘጋጀ መሆኑን ነው ቢሮው ያሳሰበው፡፡

ፈተናው የሚሰጠው በቢሮው ቴሌግራም ቻናል ላይ ነው https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

@dwamharic_news @dwamharicnewsbot