ኮድ 3ሜትር ትራንስፖርት አሽከርካሪ ና ባለንብረት ሲቪክ ማህበር
571 subscribers
838 photos
217 videos
6 files
322 links
Download Telegram
Forwarded from Henok $
ክፍል 4 የመጨረሻው የመከራው መጀመሪያ...
ለሰማከው ስትታገል የምትስማማውን ትቀብራለክ
የቤቱ በር ላይ የተሰቀለችው ክራር በ አያቴ እድሜ ልክ ተጎሳቁላለች <<ስትመጣ ትውስዳታለክ>> የሚለው የ አያቴ ቃል ታወሰኝ ወደ ውስጥ ዘለኩ አያታችን ከ ሚስቱ ጎን እርሱም በጠና ታሞ ተኝቶዋል ክራሩን ከደጅ ያስቀመጠለት ምን አልባት ህይወቴ ብያልፍ ቃሌን ማክበሪን እዲያውቅልኝ ሲል ነው አሉኝ>>አያቴ በጣም ነበር የሚወደው ምክኒያቱን ግን አላውቅም
ይመስለኛል እናቱ በልጅነትዋ ካገር በበረሃ ወታ ነበር ተከራታ እናትና አባትዋን የጦረችው እኔ በልጄ እደተከበርኩ ለእሷስ በሴት አቅማ ማን አላት ይል እደነበር እደ ተመኘም አልቀረም እናም አያቴ የልጁን ወግ ማእረግ ቢያይም አንድ ልጅ በመከራ በወግ ማእረግ የወለደችለት ስለዚህም <<የ አክሱም ፂዯን ስጦታዬ>>ይለው ነበር
እነሱን ለማስታመም የመጣች የሩቅ ዘመድ ቤት ነበረች ምን እደተፈጥረ ጠየኳት << አያትክ(አቦይ) ከጦርነቱ ተርፈው በየተመለሱ ቤት እየዞሩ ሲያጥያይቁ ነበር አንድ ቀን ግን መተው ክራሩን እደጅ አቅፈው ስቅስቅ ብለው እያለቀሱ<አደእይቲ ፂዮን(እናቴ ፂዮን) (ስለቴ እስከዚህ ድረስ ነው? በቃ ? እያሉ ለሰዓታት ውጪ ተቀመጡ ከጥቂት ሰዓት ቡሃላ በተቀመጡበት ወድቀው አገኘናቸው አፋፍሰን አስገባናቸው ይህው ከዛ ጊዜ ጀምሮ አያወሩም ዝም እዳሉ ነው>>አለችኝ
አሰብኩት ይህንን ልጅ መምጣቱም ሆነ በዚህ በጦርነት አውድ ላይ መኖሩን የሚያውቅ ማነው? ራሴን ጠየኩ አሁን ክመቼውም በላይ በደንብ ገብቶኛል ይህ ልጅ ቋንቋ ብዙም አይችልም ችግሩ በደንብ አይገባውም አድራሻና መዳረሻውን ነግሬ ብሎ ሊይዝለት የገጠመውን እና የደረሰበትን ጉዳዬ ብሎ ሊነግርለት የሚችል ኬት ይመጣል?
ጦርነት ክፉ ነው‼️ብቻ በማለት የማይታለፍበት ስፍራ ለካ አለ ይህስ ልጅ ለማን እና ማንን ወክሎ ተዋጋ ?
አዲስ አበባን 22 ትን ወይንስ ፣የትግራይ ህዝብን አሊያስ ያባቱን ወገን ይህም አይደለም ሁሉን የሚያስረሳ ፍቅር የሚባል ወድምነት ከራስ አልፎ የሚከፈል ንፁህ በምንም እና በማንም ያልታበየ እውነተኛ መስዋትነት እንጂ‼️
ለካ መልስ የሌላችው ጥያቄዎች አሉ ?
እራሴን በታሪኩ ባለቤት ጫማውስጥ አድርጌ ለማየት ሞከርኩኝ አልቻልኩም አቃተኝ
ድገት ከነበረበት የዋሌት ሰመመን ወቶ ታሪኩን ቀጠለ እኔም ከራስ ግምት አስተሳሰቤ ወጥቼ በትኩረት መስማት ጀመርኩ<<እኔ የማውቃቸው አብረውን የነበሩ ቤተሰብ ጋር እየዞርኩ መጠየቅ ጀመርኩኝ አንዳንዶች ቤት ስሄድ ምርዶ ነጋሪ ስሆን ሌሎች ጋር ደግሞ ደራሽ እየሆንኩ መጣው አያቴ መረጃውን ያገኘበት ቤት ደረስኩ እሱ መምጣቱን እና እዲክ ያለ ልጅ ተመቶ እደወደቀ ተፋላሚ ሃይል ሲመጣባቸው ጥለውት እደሄዱ አካባቢውም በከባድ መሳሪያ እደተደበደበ ሁሉ ነገረኝ ሰማይ ምድሩ ዞረብኝ የምሆነው ጠፍኝ እኔን ብሎ ተከትሎኝ የወጣውን ልጆን ሞትዋል አሊያም አሳምሬ ተሰውቷል ማለት ከበደኝ እናቱ ያለውን ሁሉ የምታረግለት መኖሬ ለሱነው ብላ የምታምን የማይችል የናት አንጀት ያላት መሆንዋን አውቃለው አሁን ደግሞ መብራትና ኔትዎርክ መገድም እየተ ለቀቀ ነው ምን ይሆናል መልሴ አላወኩትም ነበር ድምፃን ከፍ አድርጌ እያለቀስኩ ነበር ለካ ያለሁበት ቤት አካሉ ጎሎ መረጃውን ከሰጠኝ ልጅ ውጪ ሁለት ያልተመለሱ ምሞት መኖራቸው ይልተሰማ ሴትና ወድ ልጆች ኖሯቸው የኔን ጩህት የሰሙ ጎረቤቶች መርዶ ተሰምቶ ነው ብለው እያለቀሱ ምጡ እኔም ወጥቼ ሄድኩ በየመገዱ ባሮጌ ሸራ የተጣሉ የብና ጠጡ የሚመስሉ ዳሶች አሉ እደወትሮ ሃዘን አይደምቅም ሰው ተሰባስቦ አያፅናናም የራሱንስ ማን ያንባለት እድሮች እደወትሮ አያካብቡም ካህናት የመፅናኛ ወጌል አያስተምሩም ፅሎት አያደርሱም ዑለማዎች ቁርሀን አይቀሩም ሀዲስ አያስተምሩም ብቃ ሁሉም ክትት ብሎ በየቤቱ መብከንከን ብቻ😔
ቤት ደረስኩኝ ለካ ኔቶርክ ሰርቶ ኖርዋል አክስቴ በአያቴ ስልክ ደውላ ኖርዋል ያቺ የሩቅ ዝመድ ስልኩን አነሳችው ከወዳኛው ጫፍ ደና ናቹ ድና ናቹ የተደጋጋሚ ጥያቄ ነበር
አክስቴ :-ስልካቸው የሁሉም አይሰራም ዘመድ :- አዎ ገና አሁን ነው የአቦይም ቻርጅ አድርጌ የከፈትኩለት
እናትዋን እኔን ልጆን ጥየቀች ይህን ጊዜ ነበር ያያቴን መተኛትና የ እናትዋን መታመም የነገረቻት አክስቴ ቀጠልች
አክስት:-የልጇን ስም እየጠራች ጠየቀቻት አክስቴም ሆነች ስልኩን ያነሳችው የሩቅ ዘመዳችን በስም እና ዝና ካልሆነ በቀር አይተዋወቁም እዲያውም አክስቴ ሁሌ እድምትልው አባቴ ሲያስቸግር ሲያጠፍ አተይውም ስላት ማን አለው እዳህያ ጡት ሁለት ነን ስትል በደንብ የገባኝ ከመቼውም በላይ አሁን ነው ያያቶቼን መከራተት እና መድከም አይተው በዚህ ባለ ጦርንነት ውስጥ ከጎን የምቆ የሩቅም ዘመድ እራሱ መገኘቱ አስገራሚ ነው ስለዛ ልጁንም ሆነ እናቱን በደንብ እታውቀውም
ዘመድ:-ማነው እሱ ያ ተሰ ው ቷ ል የተባለው ልጅ ይሆን?
አለች እኔ ቤት ስደርስ አያቴ ይህንን ሰምቶ ከ አልጋው ላይ እደምንም ተነስቶ እደተደገፈ ገባው
ዘመድ :-ሀሉ ሀሉ ሀሉ (እደግብው ሁለቱንም ሳይ ግራመጋባት ተሰማኝ ምንድነው ስል ጠየኳት ስልኩን ሰጠችኝ አየሁት የማውቀው ቁጥር ነው
አልተዘጋም ወደ ጆሮዬ አስጠጋሁት ጫጫታ አለ አፑላንስ ...አፕላንስ የሚል ከወዳኛው ጫፍ አያቴ እያቃሰተም ቢሆን ሁሉንም አስረዳኝ እኔ ወደ አክስቴ ጋር መሄድ እዳለብኝ እና እሷ ወደዚህ እዳትመጣ ማድረግ እዳለብኝ እነሱም ደና መሆናቸው እድነግራት ነገረኝ ከደረቱ ውስጥ ብር እያወጣ ማልቀስ ጅመረ ቀጥሎ ስልክ አወጣ ብሯን አገላብጦ አያት እባዎቹ ምንጩ እዲዳልደረቀ ጅረት ዝም ብለው በሞጨሞጩ አይኖቹ ይፈሳሉ ድጋሚ ወደ ደረቱ አስጠጋቸው ሳማቸው ብሮቹን የስንብት ያክል እየሳሳ ሰጠኝ አሁን ሁሉም ነገር ተገለፀልኝ አስተዋይና በሳል ስለነበር እደመጣን <<መመለሻችን ነው አያቴ እዳይጠፍብን ለማነኛውም ያዝልን>> ያለው ትዝ አለኝ ባያቴ ፊት ማልቀስ ባልፈልግም ግን አልቻልኩም እርሱ ከራሱ አልፎ እኔን ሊምልስ ነበር የመጣው ሆኖም ግን ምን አይነት ማስተዋል የተነፈኩ ነገሮች የማይገቡኝ
ለመቀመጫና በ በሰው ተቀማጭ ባሰበውና ባሰበልኝ የምመራ ብኩን ሰው ነኝ አልኩት ራሴን አያቴ ቀጥሎ ስልኩን አወጣ ከ ደረት ኪሱ ይህንን ሁሉ ጊዜ ከደረቱ አልነጠለውም ሲተኛስ እዴት? አልቆረቆረውም? እዴትስ አልተሰበረም?
በጀርባው እንጂ ህፃን እደምታጠባ እናት በደረቱም ይህን ሁሉ ቀናትን አልተኛም ማለት ነው?
ፀጥታ ነገሰ ከ ሁለቱም ስልክ ጫፍ እባዎቼ የኔም ከባለታሪኩ እኩል አብረውኝ ፈሰሱ 😭 እራሴን የታዘብኩት የ እንባዬ ዘለላ ፊቴን በልቶ ሲያሳክከኝ ነበር ::
የእውነት እኛ ግን የየዋዎቹ የአባቶቻችን ልጆች ነን
በፊፁም ልንሆንም አችልም ‼️
ከየት ያመጣነው ከየትስ የወረስነው ክፍት ነው በበዳይነትና በ ክፍት በተኮልና በተኩስ ችግሮቻችንን መፍታት የምንሻ መጀመሩን እጂ መጨረሻው ላይ ጉዳቱ የሚገባን አገርን በሽንቁር ቀዳዳ እንጂ እደስፋቷ አስፍተን የማናውቃት ራሴን እና የኔን ዘመን ትውልድ ሆኜ ወቀስኩት‼️
እኔ ከሰመመን እሱንም ከ ዋላ ታሪክ የመለሰን እራሱ ባለ ታርኩነበር ስልኩን እዳወጣ ሊሰጥኝ ከበደው ደጋግሞ ደጋግሞ ወደ ደርቱ እስጥጋው ራቅ አድርጎ ደግሞ ይምለከተዋል ለካ የሁለትችን የ 12 ተኛ ክፍል የምረቃ ፎቶ ነበር አልቀረም ስልኩን ሰጠኝ እኔም ስለገባኝ ስልኩን ተቀብዬ ፎቶውን ከ ከቨሩ ውስጥ አውጥቼ ሰጠሁት ብልጭ
ብሎ የጠፍ ደስታ እባ ያቀሩ አይኖች .....
ይ ቀ ጥ ላ ል
በ ሔኖክ $
ሔና እንዴት ነህ ሰላም ነው.....ለ Group አባላት discount ያለው ፖኬጅ አዘጋጅቼ ነበር
Total quart 4L=2050
oil filter=200
Air cleaner=200
ሀሳብ ስጥበት
Forwarded from Henok $
ፊልትሮ lexus 300
N2 high copy 420
N2 Genuine 730
air cleaner lexus thailand 250
Forwarded from Henok $
ይሄ ሃሳብ የኛ ጥያቄን የሚያጠናክርና ከ ተጠቃሚው ጋር በጋራ የምንጠይቅበት ጊዜላይ የቆምን ይመስለኛል የሶሻል ሚዲያ ዘመቻችንም ዘርፊ መፈተሽ አለበት የምንለው እዲሁ በከቱ አለመሆኑን ተጠቃሚውም ምስክር እየሆነንም ጭምር ነው ዘርፊ መፈተሽ አለበት ስንል ከሁለቱም ወገን የሚመዘበርና የሚደረግ የቴክኖሎጂ ማጭበርበሮች አይጠፉም ይፈተሹ እያልን ነው አንድ ወቅት ላይ ናኖ ግላስ የሚል በየ ህጋዊ ሱቆችና በየመገዱ አደንቁረውን ነበር በሳይንስ እና ቴክኖ ሎጂ የተረጋገጠ ይባልልካል ተቋሙ ሲጠየቅ አላረጋገጥኩም ሳረጋግጥም ጥቅሙ አልታየኝም ጉዳቱም ያመዝናል አለ ታዲያ የዚህ ዘርፍ ችግሩስ ግብር ከፊዩን እና ህብረተሰቡን ምን ያክል ሲጎዳና ጉዳቱ ሲታይ ነው የሚፈተሸው
ዘርፊ ለመንግስት አገዛዝ እና አዋጅና መመሪያዎች ሳይቀሩ የሚጥሰና የሚጣረሱ አሰራሮች አሉ ዘርፊ ላይ የሚጠቅሳቸውና የሚመለከታቸው ሁሉ ጉዳዩን ከ 60ሺው ሳይሆን ከ መቶዎቹ ድርጅቶች መጀመሩ ተቋማዊ ስራቸውን ሃገራዊ ግዴታንም ለመወጣት ይረዳል
ይህንንም የመግስት ተቋማት ጠፍቷቸው አይደለም የድርጅቶቹ የችግሩ ቁልፍ መፍቻ እዳይገኝ የማደናገር ስራ መታለላቸው እንጂ ‼️
ሁሌም እደሚባለው በሬክን ከሰረቀክ ጋር አትፈልገው ነው ነገሩ ህዝብም ሆነ መግስት ችግሩን በዘላቂነት መፍትሄ ማግኘት ከፈለገ እና ለውጥ ማምጣት ከፈለገ ከግንዱ ሳይሆን ከቅርጫፊ መጀመር ይኖርበታል ግንዱ ሀገር ነው ፣ወጣት ነው፣ስራ አጥ የሚሆን ዓይል ነው እና የነገው ሀገር ቢገነባም ቢወድቅም የዚህ ወጣትና ህዝብ ነው ‼️
ስለዚህም መንግስት የንግድ ተቋማቱንና የድርጆትን ሲስተም ሊፈትሽ ይገባል እያልን የምንጮህው ለሃገር ከማሰብ እንጂ ከግል ጥቅመኝነት የመነጨ አለመሆኑን በስከዛሬው የትግል መስመራችን ማሳያ ነው እና ስሙን ስሙን እላለው ‼️
#የ_ኮድ_3_ስራ_ያለ_ኪሳራ
ሔኖክ $
Forwarded from Henok $
ሁለተኛ እዚህ ገፅ ላይ ለማስተዋወቅና ለመልቅ በአአለመሞክር እራስክን ለመቆጣጠር ሞክር 🙏
መክኒያቱም መመለስ የማትችላቸው 3 ነጥቦች አሉና
1 የደህንነቱ ጉዳይ
# ማነኛውም ከናተጋር ለሚነሱ ጥሪዎች የህይወትና የንብረት ዋስትና እኔ ላባሎቴቼ እፈልጋለው አንተ ደበኛው ስለደወለ ብቻ ሞት እድታሸክመን አንፈልግም ከተረዳከው ልክ ስመዘግብ ካሽከርካሪው
ንግድ ፍቃድ
ቲን ነበር
ንግድ ምዝገባ
እናም ለህይወቱ ሶስተኛ ወገን ኢንሹራንስ እደምጠይቀን ትዛዝ ለምት ቀበለው የ መቶና ሁለት መቶ ብር ደበኛክ ከዚህ በላአይ መስፈርቶችን ልታዘጋጅ ይገባል ይህ ማለት ባተ ድርጅት ጥሪይዞ ለሚሄድ አሽከርካሪ ሁሉ ንብረቱ ቢሰረቅ ሙሉውን ህይወቱ ቢጠፍ የ ህይወት ዋስት ናውን እኢሹራንስ እድትከፍል አካሉ ቢጎድል እደዛው ተሰልቶ ልትከፍል የህግ መሀቀፍ ላይ ፈርመክ በደንብ እንቀበልካለን አንደኛ እኔ ነበርኩ የማስተዋውቅልክ
2 መብቱ
# ያለ አሽከርካሪው ተሳትፎ እና ፍላጉት ምንም አይነት ውሳኔም ሆነ ንግግር ማድረግ አለመቻልክን አምነክ ስትፈርም
3 ጥቅም
# አንተ ስራ ላይ ያልገባ አፕ ይዘክ ስትመጣ ነዳጅ ያልሞላ መኪና እደማትፈልገው ሁሉ እኛም ነዳጅ ሞልተን ንብረት ገዝተን ተግባራዊ ነግድ ውስጥ ከመሆናችን አኳያ የ ድርጅቱን እኩል አሊያም በላይ የትርፍ ተጋሪ ማድረግ ይጠበቅብካል
አደራ የድርጅቱ ቁልፍ ሰው ትሆናለክ ብዬ በማሰብ ነው እዲህ ያሉ ጥያቄዋችን ያቀረብኩልክ የየ አንዳንዱን አሽርካሪ እኢንቨስት መንት አስበክ ቀለል አድርገክ እደ ድርጅት ወረቀት ላይ በተመዘገበ ካፒታል እኛ ይሄንን ያክል ነው ያወጣነው እዳትለኝ አደራክን ሁሉንም ወጪ እደማውቀው ልገርክ ብዬ ነው በመጨረሻም መልስ ካለክ ብቻ አብረን እናወጋለን ተማርበት ወይም ለ አለቆችክ አድርስልን ፍላጎታቸው ይሄ ነው ብለክ
#የ_ኮድ_3_ስራ_ያለ_ኪሳራ
ሔኖክ $
Forwarded from Henok $
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይሄ ነገር ለምሽት ልጆች እዴት ናት በህግ ይፈቀዳል የምታውቁ ካላቹ
#የኮድ_ስራ_ያለኪሳራና_ሞት_‼️
👍1
Forwarded from Henok $
የዘርፊ የተግዳሮት ምክኒያቶች እና
ፈጣን ምላሽ ያለመገኘቱ የብዙሃን አስተዋፅኦ🙏‼️
#የ_ኮድ_3_ስራ_ያለ_ኪሳራ
Forwarded from Henok $
ገበያውና የግብይት መንገዱ ለአሽከርካሪውና ለባለ ንብረቱ የድርጅቶቹ እይታና የተግባር እንቅስቃሴ
ለመረጃ ያክል 🙏‼️
#የ_ኮድ_3_ስራ_ያለ_ኪሳራ
‼️
Forwarded from Henok $
🔴 የኔ ጅግና የገደለው ሳይሆን ስለፍቅር፣ስለ እውነት ፣ስለ ወድማማችነት የሞተው ነው‼️
Forwarded from Henok $
……………ተ ፈ ፀ መ
አያቴ ወደ መቀሌ አንድ ወዳጁ ጋር ደውሎ ትኬት እደሚቆርጥልኝና እዲቀበለኝ ነገረው እኔም የናፈኩትን ያክል በ ኔ ምክኒያት ያሳጣኝን ወድሜን እየጠላሁት የመጣሁትን የትውልድ አካባቢዬን ለቅቄ ጉዞ ጀመርኩ በመገዴ ላይ እጅግ ብዙ አሳዛኝ ነገራትን እየተመለከትኩ አለፍኩ ከታዘብኳቸው መገዱ ሁሉ ጭር ብሏል አልፎ አልፎ የሚቀሳቀሰው ቢኖርም ገና ነብስ ያላወቁ ህፃናትና እድሜ የገፍ አዛውቶች ብቻ የቀሩ እስኪመስል ከቤታቸው ደጃፍና ከ አውራ ጎዳናው ጫፍ ወተው ልጆቻቸውን የሸኙበት መገድ አምጥቶ ይመልስላቸው ይመስል አሻግረው ሲመለከቱ ይስተዋላሉ
ገሚሶች መገድላይ ይማፀናሉ ቤቶቻቸው ፈርሰዋል ከብቶቻቸው ሞተዋል ፣ልጆቻቸው ዘምተዋል ብቸኝነት በዚህ እድሜ አሰብኩት አይደለም የነሱ ብቸኝነት የኔ ወድሜን አጥቼ አዲስ አበባን በብቸኝነት ማሰብ አልፈልግም አለኝ ዝም አለ የሚገጥመውን እያሰበ እና እያሰላሰለ መሰለኝ በመሃል መቐሌ ደረስኩ አለኝ መቐለ የቀድሞ መቐሌ አይደለችም ሬሳ እደወጣበት ቤት እራሱን ሆና ነው ያገኘዋት …ፀጥ አለ ይሄ ፀጥታ ከወትሮው ተለየብኝ አሁን ገባኝ ለትግራይ ለጆች መቐሌ ምን እደሆነች አውቃለሁኝ ሁሉ ነገራቸው ነች መቀሌን በደንብ እኔም አውቃታለው ከ ጦርነቱ መጀመር 4 ዓመት በፊት መቐለ ጎዳናዎችዋ ፣ህዝቡ ፣ወለል ያሉት ካፊዎችዋ የጀበና ቡና ጥላማ ስፍራ ይዘው የሚያወጉ ወጣትና አዛውንት ሰፍፊ የባህል ሬስቱራቶችዋ የወንድ ወጣት ቄጠኛና ወቅቱን እየጠበቀና እየለዋወጠ የሚለብሰው አለባበስ ውበትና ቁመናን ጨምሮ አስፖልቶችዋ የሞዴሊግ መደረክ ያስመስሏቸዋል
የትምህርት መውጫና መግቢያ ሰዓት ከገጠመክ ደግሞ የ አፃ ዩሃንስ ተማሪዎች ሲወጡ አሊያም ሲገቡ ከገጠመክ አበቃ መቐን በአምሮክ አንድ ዘፈን ይመጣል <<አደይ መቐለ ከመይላ ተናፊቂትከይ አደዬ….😭😭😭😭
የእውነት እኳን እሱ እኔ ብዙ መቆዘምና ማለት እችል ነበር ለካ ሱም እያውራኝ ነበር በመሃልየንገረኝን አልሰማሁትም በራስ ትዝታዬ ተጉዥ አዲስ አበባ ግባሁኝ ሲልኝ ነበር እኔ ራሱ የባነንኩት
አዲስ አበባን ስያት የ አብራኳ ክፍይ ከተማ መቐለን ምንም የገጠመባት አትመስልም 😔
ከ ኤርፖርት ወደ ቤት 22 ኮድ 3 ሜትር ትራንስፖርት ይዥ መጣው ምንም የተቀየረ ነገር የለም አካባቢው ላይ ብቻ ግን ቀድሞ የነበረኝ ሁሉም ይጠላኛል የሚለው አመለካከትና የኔም የበቀል ስሜት ባስከፈለኝ ዋጋ ተምሬበታለሁኝ
አሽከርካሪው ጋር በጥሩ እያወጋን መጣን ስራ እዴት ነው አልኩት ?
ጥሩ እዳልሆነና የድርጅቶቹ ፣የ አለምና የ አገራችን ኢኮኖሚ እዚህ ዘርፍ ላይ ያለውን ወጣት ከማንም በላይ እያደቀቀው እደሆነ እያጫወተኝ ያልኩት ቦታ አደረሰኝ ።
ወደቤት መግባት ከበደኝ በሩ ላይ ሳላንኳኳ ቆምኩኝ ፈራው ሁለት ሆነን ወተን አንድ ሆኖ መመለስ ፣ ላተ ብሉ የሄደሰው አተ ጥለከው መምጣት ብቻ ያያቴን አደራ ልወጣና ራሴን ማንም የማያውቀኝ ስፍራ በማራቅ እራሴን እቀጣለሁኝ ብዬ አንኳኳው ተከፈተልኝ አዲስ አጋዥ(ሰራተኛ ነበረች ዝም ብያት ገባው አክስቴ ሶፍላይ ከሆስፖታል መታ ተኝታለች ስታየኝ ደገፍ ብላ እየተቀመጠች እባዋችዋ ብቻ ይፈሳሉ ሮጮ ሄጄ እግሯ ስር ተደፍው ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ ፀጉሮቼን እየዳመሰች አብራኝ አነባች ራሴን ስትስመኝ እባዎችዋ አራሱኝ እቅፍ አድርጋ ወደራሰስዋ እያስጠጋችኝ <<የልጄ የምጨረሻው ቃሉ ምን ነበረ ...>>ተሰቀሰቀች አፈርኩ በራሴ ብቻክን አቴድም ብሉ የተከተልክን ሰው ብቻውን ጥልከው የመጭረሻውን ቃል ምስማት አለመቻል ምንኛ ከባድ ነው ?😭 መልሳ አልጠየቀችኝም ቀና አደረገችኝ ከ እግሯ ላይ ፊቴን ጭንቅላቴን አገላብጣ አየችኝ እግሯን ከሶፍው ላይ አወርድች ተነስቼ ቆምክ እድደግፍት እጆችዋን ሰጠችኝ ከነልበሰችው ጋቢ ተንሳች ቀስ እያለች ወደ በሩ አመራን ከጠረቤዛው አበባ ማስቀመጫ ላይ የሆነ ነግር አንሳች ይህ ሁሉ ሲሆን በሰመመን ነበርኩኝ በረዳው ላይ ቆመች ጊቢውን ስመለከት አንዱ መኪና የለም ዞር ብዬ አየዋት ጥያቄ በሚፈጥር መልኩ ተቸግረው ነብር ማለት ነው እደ ባለፈው ታስረው ተገላተው አካውታቸው ታግዶ ነበር ማለት ነው ስል ራሴን ጠየኩ ዞር ስል የኔ መኪና ነበረች እቦታዋ ላይ ያልነበረችው እጄን ሳብ አድርጋ ሰጠችኝ ከጠረቤዛው ላይ ያነሳችውን የምኪና ቁልፍ << አትጨነቅ ልጄ አሁን ያለከኝ አተነክ አባትክ ሊብሬው በስሙ ስለነበር ያተን መኪና በልኡለሁበት ሸጣታል ብፊትም የሰጠክ ወድምክ ነው አሁንም የሱ መኪና ያተነው >> አንድ ነገር ትዝ አለኝ መኪናው ኬት መጣ ብዬ የጠየኩት ጥያቄ እውነት ነው አባቴ ለኔ ቦታ የለውም ያክስቴ ልጅ እና አክስቴ እኔ ላባቴ ጥሩ አመለካከት እዲኖረኝና የተረጂነት ስሜት ብለው ያደረጉት ነገር እደሆነ ገባኝ አባቴም በስሙ የመሆን አጋጣሚውን ተጠቅሞ በህይወት አይመለሱም ሲልም ጭምር ሸጠው ማለት ነው ?መልሱን ራሴው አገኘሁት
ምንምማድረግ እደማልችል ያወኩት ወደራሷ ጠጋ አድርጋ አቀፈችኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ልጆች በናታቸው እቅፍ የሚያገኙትን እኔ እደ እናት በአክስቴ እቅፍ ውስጥ አገኘሁት <ብህይወት እስካለሁኝ ድረስ አትተወኝ አደራ እዳትጎዳብኝ አንድ ያለከኝ አተነክ ሁሉን ተወው አባትክም ቢሆን አንድ ቀን ይገባዋል ለኔ ስትል ይህቼ የወድምክ መኪና ስራባት ለኔም ሆነ ላተ ማስታወሻችን ናት በደንብ ያዛት አደራ >>አለችኝ አክስቴ ረዘም ያለችና መልከ መልካም ሴት ነበረች በጊዜዋ አሁንም ሃዘኑ እንጂ የጎዳት አይነ ግቡ ነች ወደውስጥ ገባን ::
በረጅሙ ተነፈሰ ይህውውው አሁን በ አክስቴ ልጅ ምቀመጫ ወንበር ላይ ቁጭ ብዬ መኪናዬን አሽከረክራለው ሄኖኬ አንድ ያሳቀኝን ማስታወቂያ ልንገርክ (ደስ አልኝ ምንም ይሁን ምንም እናኔንም ሆነ እሱን ከ ሃዘን አውጥቶ ለሳቅ የሚያበቃን ነገር ካለብዬ እሺሺ
አንዱ ድርጅት ለዘማች ቤተሰብ መዋጮ የሚል ሜሴጅ ገባልኝ የስራ ስልኬን ስከፍት..ፍርስ ብሎ ሳቀ ያለማቋረጥ እእእእእ😁😂🤣🤣
እኔም አብሬው ሳኩኝ እኔኳን ወደ አምሮ ዬ የመጣው ለሁል ጊዜ ዘማችና ሟቹ ኮድ 3 አሽከርካሪውና ባለንብረቱ ዝም ያለ ድርጅት ደርሶ አለሁኝ ባይ ሲሆን ማየቴ ሲሆን ልሱግን እዲህ ሲል ገልፆታል ይህ ልጅ ያዲሳ አበባ ልነው ቤተሰቡ እዚህ ነው ለፍቅር ንጂ ለቢሄሩሲል አልነበረም የሞተው ታዲያ እዲህ ያሉቱን ገዳይ ወይንስ ምኦች ብሎ ይዟቸው ነው የሚረዳው..ሳቅ ፍርስ ብዬ ሳኩኝ ይህንን ጅግና መዘከር ያስፈልጋል ስቶች አሉ ቅን ልቦች ብዚህኛውም በዛኛውም በሚስጥር እውነተኛውን የክተማልጅ ውክልናን እና ሃላፊነት የወሰዱ ክበሩልኝ ባላቹበት 🙏
እባክህን ፎቶውን ላክልኝ የዚህን ጅግና አልኩት እኛም የ ኮድ 3 አባላት ባንዘክረው እኳን እኔ ልየው በማለት
በመሃል ቁርጥ አለ እሺ እልክልካለሁኝ ሰሞኑን ትግራይ ምድር ላይ መርዶ እየተነገረ ነው በሁሉም ቤት ሃዘን ነው
እናቱን ባየዋት ቁጥ ከምሳቀቅ ብዬ ቀንም ማታም እሰራለው ችግር ሲገጥመኝ ከምንም በላይ እናተ ኮድ 3ቶች እዳላቹኝ ይሰማኛል ሁሉንም ስለሆነውና ስለነበረኝ የቀድሞ አመለካከቴ ይቅርታጠይቅልኝ ችግር አይግጠማቹ ከገጠማቹም ግን ላሳያቹኝና ለሰጣቹኝ ፍቅር ከዚህ ቡሃላ ቀድሞ በመገኘት ብድራቴን ለመመለስ ያብቃኝ ያ ምሽት በዛ ጊዜ የደረሰልኝን ልጅ አሁን አመስግንልኝ ሄና በል ቻው
... ስልኩ ተዘጋ እኔ ግን አልኩኝ
😭😭ጽንዓት ይሃብኪ ኦደ ትግራይ
😭😭ጽንዓት ይሃብኪ ኦደ ሃገረይ ኢትዮጵያ🙏
Forwarded from Henok $
🔴 ጦርነት ሲጅመር ፖለቲከኞች ጥይት ያቀብላሉ
ባለሀብቶች ምግብ ይሰጣሉ
ድሆች ልጆቻቸውን ይልካሉ
ጦርነቱ ሲጠናቀቅ ፖለቲከኞች ተጨባብጠው ቀሪ ጥይቶችን ይሰበስባሉ
ባለ ሀብቶች ከጦርነት የተረፈው ሀብታቸው ማደግ ይጅምራል
ድሆች ግን የልጆቻቸውን መርዶና መቃብር በማፈላለግ ይጠመዳሉ
ሄኖክ $
ከ ኮድ 3
👍2
Forwarded from Henok $
እደኔማ ቢሆን ......
የዘርፊ ትርፍማነት ከ አሽከርካሪው ወይስ ባለንብረቱ አንፃር የትጠቃሚነት ልዩነት ከምን እስከምን
እዴትስ ውጤታማ መሆን ይቻላል
#የ_ኮድ_3_ስራ_ያለ_ኪሳራ
‼️
Forwarded from Henok $
ምን እንበል እንግዲህ እደሰማቹት ጥሪው በድርጅት ነው የመጣው ነው እያለን ነው ፖሊስም የምርመራ ጋዜጠኝ ነቱም የሰውን ልጅ የሚያክል ፍጥረት ውሻ ቀብሮ እደቀረ ጥሪው አይመለከተንም ማለታቸው ለበጎ ነው ትላላቹ ወይስ ሞት አከፍፍይ የሆነው አሰራራቸው ላተ የመኖር ዋስትናክ ሲሆን ለነሱ ግን ሆድን የመሙላት ብቻ ነው ስለዚህ ጥሪዎች ህግንና ደህንነትን ጠብቀው እስካልመጡ ድረስ ለባለንብረቱ እና አሽከርካሪው አደጋ እደሆኑ ሊታወቅ ይገባል ‼️
#የኮድ_ስራ_ያለኪሳራና_ሞት_
Forwarded from Henok $
የኛ እይታና አመለካክት በ አዳዲሶቹ እዲሁም ለነባሮቹ ድርጅቶች
#የ_ኮድ_3_ስራ_ያለ_ኪሳራ -ያለ- ሞት-‼️
አንድ ጊዜ የ አንዱን ቤት ድርጅት ሲስተም ኦፖሬተር አክሰፖት ሳላደርግ ስልኩን ወስጄ የትነክ ማለት ደርሼ እዳነሳሁት አንዱ መደወል <<እዴት አነሳከው ማለት
እኔም እሱ የኛ ስራነው ያተ መጥራት ብቻ ካልፈልክ መውረድ ትችላለክ ማለት
አይ እንሂድ ግን እባክህን ንገረኝ ማለት
ይዥው እየሄድኩ ይሄ አሽከርካሪ እደ ለመደው ሊያስፈራራኝ 😏
ሰውዬ ከፈለከው ድርጅት ልትሆን ትችላለክ የድርጅቱ ሲስተም ላይ ነው ምሰራው አላልከኝም ታዲይ ይህንን የማያውቅ ባለሙያ ነው እዴ ያለው ብዬ ጏ 😡ስልበት
ቆይ አተ ማነኝ ነክ የምትለው ታርጋክን ይዥዋለው ሀሁኑኑ ሰስፔንድ ነው የማደርግክ ማለት ሞክረኝ ብዬ ፎቶ ማንሳት 📸 እኔም ቀጠልኩና ኮድ 3 ቶችን ታውቃቸዋለክ ስለው 🤔
ሄኖክ ነክ
አዋ
ትንሽ ቆየና ምን ቢለኝ ጥሩ ነው ለማነኛውም አላገኘህኝም አላገኘሁክም ግን ገርሞኛል በዚህ አያያዛቹ እናተ የኛንም ፔሮልንም ፈርማቹ ብር ትወስዳላቹ ብሎኝ ተከባብረን ተለያየን ይህው የመረጃ ምንጫችን ሆኖ እርፍ
ስለዚህ እደዚህ ያሉትን ሳገኝ ደስ ነው የሚሉኝ እኔ 🥰😍
ከ ፒሲ ጀርባ ሆነው ጀግና ለመሆን ሲሞክሩ በግላጭ የምናገኝበት መንገዳችን አንዱ ይሄነው አንድ ጊዜም ልደትን አግኝተውት እዲሁ ነበር ያሉት ብዙዎች ኮድ3 ቶች አቅማቹን ያውቁታልና በደንብ እስኪገባቸው ድረስ በግል ስናገኛቸው ልናሳውቃቸው ይገባል በ ሰው ህይወትና በዜጎች መቀለድ ለየትኛውም ድርጅት የተፈቀደ አይደለም በሃገራችን::
#የ_ኮድ_3_ስራ_ያለ_ኪሳራ -‼️