ኮድ 3ሜትር ትራንስፖርት አሽከርካሪ ና ባለንብረት ሲቪክ ማህበር
574 subscribers
838 photos
217 videos
6 files
322 links
Download Telegram
Forwarded from Henok $
የዛሬው መልክቴ ሃሳብ አስተያየታቹን እጠብቃለው 🙏
#የኮድ_3_ስራ_ያለ_ሞትና_ኪሳራ‼️
Forwarded from Henok $
በአዲስ አበባ ከተማ የተሰረቀ መኪና በመግዛት የራስ ለማድረግ የሚሞክሩ ሰዎች መበራከት ለተሽከርካሪ ስርቆት አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑ ተነገረ!

በአዲስ አበባ ከተማ እለት ከእለት የመኪና ስርቆት እየተበራከተ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። በከተማዋ የሚሰረቁ ተሸከርካሪዎችን ቦታ በመምረጥ  መረጃ የሚሰጡ ሰዎችን ጨምሮ የተሰረቁ ተሽከርካሪዎችን የሚደልሉ ገዢ ከዛም አልፎ ለመጠቀም በሶስተኛ እና በአራተኛ ደረጃ  ሰንሰለት ባለው መልኩ የተዘረጋ የወንጀለኞች ትስስር መኖሩ ተመላክቷል።

የተሰረቀ ተሽከርካሪ መሆኑን እያወቁ  በህገወጥ መንገድ የራስ በማድረግ ወይም የባለቤትነት ማረጋገጫ እያወጡ የሚጠቀሙ ሰዎች መበራከታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን ተናግረዋል፡፡

በዚህ የመኪና ስርቆት ሂደት ውስጥ አንዳንድ ጋራዦች ዋና ተዋንያን ናቸው ያሉት ምክትል ኮማንደር ማርቆስ የተሰረቁ ተሸከርካሪዎችን ለረጅም ወራት ከማሳደር አንስቶ ሙሉ ቀለማቸውን ቀይረው ተሸከርካሪውዎቹን ሌላ በማስመሰል እንዲሸጡ እያደረጉም ይገኛል ተብላል፡፡

የተሰረቀ ተሸከርካሪዎችን በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሚገዙም ሆነ አሳድረው የተሸከርካሪን ቀለም የሚቀይሩ ባለጋራዥ ቤቶች ከተጠያቂነት እንደማይድኑ ፖሊስ አስታውቃል፡፡ ማህበረሰቡ ተሸከርካሪ ሲገዛ ከየት እና ከማን እንደሚገዛ ማወቅ ያለበት ሲሆን ያሉት ማስረጃዎች ትክክልኛ ናቸው ወይ ብሎ ማጣራት እንደሚኖርበት ፖሊስ አሳስቧል፡፡

የመኪና ስርቆት ላይ የጥበቃ ሰራተኞቹ ራሳቸው የወንጀል ተዋንያን የሚሆኑበትም አጋጣሚ መኖሩን የተነገረ ሲሆን አብዛኛውን ግዜ በጥቂት ገንዘብ ተታለው ተባባሪ እንደሚሆኑ ኮሚሽኑ አስታውቋል።አሽከርካሪዎች ተጠያቂነት እና በቂ ጥበቃ ባለበት ቦታ ብቻ ተሽከርካሪዎቻቸውን እንዲያቁሙ እና የጥበቃ ሰራተኞች ሲቀጠሩ ስለግለሰቦቹ በቂ መረጃ መያዝ እንዳለባቸው ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

Via Bisrat FM
@cod_3 @Henok_$
Forwarded from Henok $
አንዳንድ ሰው ሁሌም ይሄን አድርጌልካለው ሲባል ለምን ⁉️
ብሎ የመጠየቅ ብቃት ሲኖረው አንዳንዱ ደግሞ ተቀብሎ ለመኖር የተፈጠረ እስኪመስል ድረስ እጁን ለመዘርጋት ይፈጥንና ጠያቂውን ሰው ያሳጣዋል ‼️
ምንም ጊዜ ቢሆን ሰዎች ዋጋህን ያላንተ ፍቃድ ዋጋ አውጥተውልክ ከመጡ አላከበሩክም ንቀውካል ማለት ነው
ስለዚህም አተ ዋጋክ እስኪገባቸው ድረስ ከመቀበል ይልቅ ሰውኛ ስሜትክን እዲቀበሉክ ስራ ያንጊዜ ሰው መሆንክ እጂ በተቆረጠ ዋጋ የሚሸምቱክ ጥሬ እቃ አለመሆንክ ይገባቸዋል ‼️
ስለዚህ መቼም የተነሳሁበት ሃሳብ ይገባቹሃል የሴቷ ቤት በነሱ አሳብ የሚገዙ ሰዋችን ዋጋ ቆርጠው እየሸመቱ ይመስለኛል ለዚህም ደግሞ እደበሬው ሳሩን እንጂ ገደሉን ያላዩ አሽከርካሪዎች በድርጅቱ ዋጋ ተመን ላይ የነበረውን የ 10% መቀነስ ያለማስተዋላቸውን ሳይ እጅግ ግራመጋባት ውስጥ የሚከት የዘርፊን መረዳት እጠራጠራለሁኝ ‼️
ቀ ጥ ሉ በ ት ....
#የኮድ_3_ስራ_ያለ_ሞትና_ኪሳራ‼️
#Henok_$
Forwarded from Henok $
‼️‼️ትኩረት እቃወማለው‼️‼️
ይህንን መልክት ለሚመለከተው ሁሉ እዲደርስ በተለያዩ ገፆች ላይ በማጋራት ደርጅቱ ማስተካከያና ማሻሺያ እዲያደርግ ይገባል ‼️
1/ ይሄን መልክትና ማስታወቂያ ያያቹ አሽከርካሪና ባለንብረቶች ይህ ከፍተኛ ንቀትና ድርጅቱ በዘርፊላይ ለኛ ያለውን ንቀት ከመቼውም በላይ ያሳየበት መሆኑን ልትረዱት ይገባል ይህ ማለት በ ዘርፊ ውስጥ ያለህን እምነት እድታጣና በህብረተሰቡ ዘንድ መቃቃርን የመፍጠር ዘመቻ ነው አተ ድርጅቶች እድሜልክክን እደ ቦሊቦል ኳስ አተን መረብ አርገው መቀባበል አተም አጋጦ ተመልካች መሆንክ ሳያንስ አሁን የተከፈተብክ መብትክነ‍እ ፣ጥቅምክንና ደህንነትክን ጠክረክ ባለመጠየቅክ ነውና ስለዚህ ንቃ ‼️
ታገል ፣ተቃወም በዚህም በድርጅቱ የጥሪ መአከል ታዘው የበርካቶች ህይወት ያጣናቸውን ግለሰቦችን እና ተሽከርካሪዎችን እያጋራን ፍትህን እደምንፈልግ መጠየቅ እዳለብን እመን ይህ የሚያሳየው መጠየቅ ባለመቻልክ ነው‼️
#2 በዚህ ዘርፊ ላይ የተሰማራቹ እራሳቹን ችላቹ የምትቀሳቀሱ መሆናቹን የምታምኑ ከሆነ ይህንን ማስታወቂያ በይፍ ልታወግዙና ልትቃወሙ ይገባል ካልሆነ ግን የናተን ሎጎና እስቲከር የለጠፊ እደ ወንበዴ የሚታዩበት ጊዜ እሩቅ አይሆን ‼️
#3 መንግስት ለዘርፊ በህጋዊ መገድ ፍቃድ ሰቶ በ መስራት ላይ ያለውን ይህንን ወጣት የንግድ ማህበረሰብ ስጋት ለመፍጠር በሚመስል መልኩ የኔን ማስታወቂያ ያለጠፊ ህገውጥና አጭበርባሪዊች ናቸው ማለት አግባብ አይደለም እና እርምጃ ሊወስድ እዲሁም የትላንት በመግስት የተሰጠን መግለጫ ለራስጥቅም በማዋል በህብረተሰቡላይ ስጋትና ፍራቻን የመስጠት ዝንባሌውን ሊያስቆም ይገባል ‼️
#የኮድ_3_ስራ_ያለ_ሞትና_ኪሳራ‼️

https://t.me/code3drivers

#Henok_$
Forwarded from Henok $
ስለዚህ ነገር የማታውቁ የምታውቁ ደግሞ ምን እና ምን ያክል የግል ሚስጥራቹን አብዴት ባደረጋቹ ቁጥር ከራሳቸው ጥቅም አንፃር ያስተካክሉ ይሆን እንጂነምንም የሚጠቅም ነገር እደማያደርጉ እያጤናቹ ‼️
በ It እዲሁም በቴክኖ ሎጂ ላይ እውቀትና ክህሎት ያላቹ እስኪ በደንብ ተንተን አድርጋቹ የህግ ባለሙያዎች ደግሞ ህጉ ምን ይላል የዜጎችን የግል ሚስጥር አያያዝ ላይ የሚለውን ብታስረዱን 🙏🙏
#የኮድ_3_ስራ_ያለ_ሞትና_ኪሳራ‼️
Forwarded from Henok $
ይሄ መኪና ሁላቹም ስለምታውቁት ስለዚህ እናውራ እስኪ በሰለጠኑት አገር በሚባሉት የሚነዳ ነው አሁን ድረስ እደምታዩት እያገለገለ ነው ስለዚህ አደኛው አለም የሚባሉት መኪና አምራች አገራት ይህንን ካላሶጡና ከተጠቀሙ አተ የሶስተኛው አለም ህዝብ ሆነክ ስጋት የሚጭሩብክ ለምንድን ነው ‼️
ስለምትሰማቸው ምክኒያቱም
<<ድሮም ደላላ በሁለት ይበላ>> ነውና አትደናገር ለማለት ነው ‼️
የሚወድቀው ቀድሞ ብናውቀውም አወዳደቁ ነው የጠፍን በሉልኝ 🙏
የብዙዎች የውስጥ ጥያቄ መልስ ይሰጥበት ወይስ ታውቁታላቹ አዎ ከሆነ አንዱን ይምረጡ ‼️
በተለያየ መገድ ብዥታን ለመፍጠር ይህንን ቃል ሲጠቀሙበትና አንዳንዶችም ውስጥ ጥያቄ ሆኖ እደሚመላለስ ስለገባኝ የቀረበ ጥያቄ ::
Anonymous Quiz
12%
1/ ሔኖክ $ ከ ኮድ 3 ምንድን ነው የምትጠቀመው(ምን አገኘክ)
25%
ስላተ በተጨማሪ ማወቅ የምንፈልገው ነገር አለኝ ይህ መጠየቅ ለሚችል ብቻ የተሰጠ እድል ነው:: መልሱን በተሰጠው የድምፅ ብልጫ ከ ዛሬ 12 :00 ብሃላ ውጤት
Forwarded from Henok $
እነሱ ሁሌም ይሳሳታሉ እኛ እናርማቸዋለን💪‼️
ይህንን ኃይል ኮድ 3
‼️‼️ትኩረት እቃወማለው‼️‼️
ይህንን መልክት ለሚመለከተው ሁሉ እዲደርስ በተለያዩ ገፆች ላይ በማጋራት ደርጅቱ ማስተካከያና ማሻሺያ እዲያደርግ ይገባል ‼️
1/ ይሄን መልክትና ማስታወቂያ ያያቹ አሽከርካሪና ባለንብረቶች ይህ ከፍተኛ ንቀትና ድርጅቱ በዘርፊላይ ለኛ ያለውን ንቀት ከመቼውም በላይ ያሳየበት መሆኑን ልትረዱት ይገባል ይህ ማለት በ ዘርፊ ውስጥ ያለህን እምነት እድታጣና በህብረተሰቡ ዘንድ መቃቃርን የመፍጠር ዘመቻ ነው አተ ድርጅቶች እድሜልክክን እደ ቦሊቦል ኳስ አተን መረብ አርገው መቀባበል አተም አጋጦ ተመልካች መሆንክ ሳያንስ አሁን የተከፈተብክ መብትክነ‍እ ፣ጥቅምክንና ደህንነትክን ጠክረክ ባለመጠየቅክ ነውና ስለዚህ ንቃ ‼️
ታገል ፣ተቃወም በዚህም በድርጅቱ የጥሪ መአከል ታዘው የበርካቶች ህይወት ያጣናቸውን ግለሰቦችን እና ተሽከርካሪዎችን እያጋራን ፍትህን እደምንፈልግ መጠየቅ እዳለብን እመን ይህ የሚያሳየው መጠየቅ ባለመቻልክ ነው‼️
#2 በዚህ ዘርፊ ላይ የተሰማራቹ እራሳቹን ችላቹ የምትቀሳቀሱ መሆናቹን የምታምኑ ከሆነ ይህንን ማስታወቂያ በይፍ ልታወግዙና ልትቃወሙ ይገባል ካልሆነ ግን የናተን ሎጎና እስቲከር የለጠፊ እደ ወንበዴ የሚታዩበት ጊዜ እሩቅ አይሆን ‼️
#3 መንግስት ለዘርፊ በህጋዊ መገድ ፍቃድ ሰቶ በ መስራት ላይ ያለውን ይህንን ወጣት የንግድ ማህበረሰብ ስጋት ለመፍጠር በሚመስል መልኩ የኔን ማስታወቂያ ያለጠፊ ህገውጥና አጭበርባሪዊች ናቸው ማለት አግባብ አይደለም እና እርምጃ ሊወስድ እዲሁም የትላንት በመግስት የተሰጠን መግለጫ ለራስጥቅም በማዋል በህብረተሰቡላይ ስጋትና ፍራቻን የመስጠት ዝንባሌውን ሊያስቆም ይገባል ‼️
#የኮድ_3_ስራ_ያለ_ሞትና_ኪሳራ‼️
https://t.me/code3drivers
#Henok_$
Forwarded from Henok $
የሀገሪቷ የዋጋ ግሽበት ወደ 28.3 በመቶ መቀነሱ ተገለፀ


የሀገሪቷ የህዳር ወር የዋጋ ግሽበቱ 28.3 በመቶ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን ከጥቅም ወር ከነበረበት 29.2 በመቶ አንፃር ቅናሽ ማሳየቱን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አሳዉቋል።

እንደ ተቋሙ መረጃ በወሩ ከተመዘገበው የዋጋ ግሽበት ምግብ ነክ 30 በመቶ ድርሻ ሲይዙ ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች ደግሞ 26 በመቶ መሆናቸው ተገልጿል።

Source: Capital
@cod_3 information
Forwarded from Henok $
ኤርሚሻ ማታ ቮይስ ቻት ጋብዥ ላመሰግን ብጠብቅህ አልገባህልኝም ከልብ ከልብ አመሰግናለው በ ኮድ 3 ስም እና በራሴ የ መሉን ደስታ ያረክለትን መየት ሳያስፈልግ በድምፁ ሁሉ ያደረክለትን በመስማት የማየት ያክል ተመልክተናል 🙏 እና ሁሌም የኔ ፍላጎት እርስበእርስ በየመገዱ ልብ ለልብ በባለን መልካምነት ሳይሆን ድርጅቶች አሰራር የፈጠሩልንን የጎሪጥ መተያየታችን ቀርቶ እርዳታ ፈላጊ ሲመጣ ምን ደርሼ በረዳው የሚል ስሜትን መፍጠር ነው ‼️
ያንጊዜ እርስበእርስ እንቀራረባለን እርስበእርስ እንተማመናለን እርስበእርስ አንዱ ላንዱ እንቆማለን ይህንንም ባተ ለወድማችን መሉ ብዙዎች ከዚህ በፊት እዳደረጉት አተም አደረከው ክበርልኝ ወድሜ ሁላቹንም እያመሰገንኩ አሴ አውቶ ሶልሽንን በተጨማሪ እያመሰገንኩኝ የነገው ድጋፍ ፈላጊ ማነው ⁉️
ተመስጋኝስ አጋር የሚሆን ለወድሞቹ⁉️‼️
ሔኖክ $
#የኮድ_3_ስራ_ያለ_ሞትና_ኪሳራ‼️
Forwarded from Henok $
1,እስፔር አቅራቢዮች
2,ኢንሹራስ(ኤጀንት)
3,ጎማናባትሪ አቅራቢ
4,GPS ገጣሚ(አስመጪ)
5,አበዳሪ ማይክሮ ፊይናስ
እና ሌሎችም ከዘርፊ ጋር ተያያዥ ነት ያላቹ
ኑ አብረን እንስራ 🙏🙏
መስፈርት ለሚሰጡት አገልግሎትም ሆነ ግብይት ሙሉ አላፊነት የሚወስድና ለጥራት ችግር ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚችል
# ለ አሽከርካሪው በ ሚኤድበት ቦታና አገልግሎት መስጫ ተቋሞቻቹ ጋር ልዩ ክብር እና አገልግሎት መስጠት ‼️
#ከገበያው የተለየ ቅናሽ እና ግልፅነት የተሞላበት አቅርቦትን መፍጠር ‼️
#የጥራት ችግር ሲያጋጥም ሀላፊነት እወስዳለው ባሏቸው እቃዎች ላይ አላፊነት መወጣት‼️
#Henok_ $
#የኮድ_3_ስራ_ያለ_ሞትና_ኪሳራ‼️
Forwarded from Henok $
ቶዮታ በዓለም ገበያ የተሸጡ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎቹን  ከገበያ ላይ እንዲሰበሰቡ አዘዘ።

ዓለም አቀፉ ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ ቶዮታ ከ2020 እስከ 2022 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ የተመረቱ ተሽከርካሪዎች የደህንነት ችግር አለባቸው ተብሏል።

ኩባንያው በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ የተመረቱ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎች ከኤርባግ ጋር በተያያዘ ችግር እንዳለባቸው ተደርሶበታል ብሏል።

ድርጅቱ በተለይም ኮሮላ፣ ራቫ4፣ አቫሎን፣ ሌክሰስ፣ ካምሪ፣ ሴና ሀይብሪድ፣ አርኤክስ 350፣ ኢኤስ250፣ ኢኤስ350 የተሰኙ የ2020 እና 2022 ላይ የተመረቱት የኤርባግ ችግር እንዳለባቸው አስታውቋል።

በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱት ተሽከርካሪዎች ያላቸው ሰዎች ኤርባጋቸውን እንዲያረጋግጡ እና ችግር ካጋጠማቸው እስከ ቀጣዩ የካቲት ወር ድረስ እንዲመልሱለት ቶዮታ ጥሪ አቅርቧል።

የቶዮታ ተሽከርካሪዎች ችግር እንዳለባቸው የታወቀው የጃፓን ትራንስፖርት ሚኒስቴር በሀገሪቱ ተሽከርካሪ እምራች ኩባንያዎች ላይ ባደረገው ምርመራ ላይ እንደሆነ ተገልጿል።

በዚህ ምርመራ መሰረት ከቶዮታ ተሽከርካሪዎች በተጨማሪ ዳይሀትሱ በተሰኘው ኩባንያ ላይም ተመሳሳይ ችግር ታይቷልም ተብሏል።

ይህን ተከትሎም የቶዮታ ኩባንያ አክስዮን ዋጋ ቅናሽ አሳይቷልብየተባለ ሲሆን ሌላኛው የጃፓን ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ ጥሩ የገበያ እድል እንደሚያገኝ ተገልጿል።

ከ87 ዓመት በፊት ኪቺሮ ቶዮታ በተባለ ግለሰብ የተመሰረተው ቶዮታ የተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ አሁን ላይ በዓመት 10 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎችን በማምረት ላይ ይገኛል።

ከ360 ሺህ በላይ ሰራተኞች ያሉት ቶዮታ ኩባንያ 300 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ሀብት እንዳለው የኩባንያው ዓመታዊ ሪፖርት ያስረዳል።

Source: Al Ain
@cod_3_ Henok_3
Forwarded from Henok $
ድርጅቱ ከ 2000 ሞዴል ይልካል ላተ የራሱን አርማና መለያ በዚህ መልኩ ያወርደዋል ታዲያ ስለ ብራንዲንግ የገባው ይመስላቹሃል ⁉️
አተ🫵እስቲከር ሳስለጥፍክ ደረጃክን የማወጣልክም የምተምንልክም እኔነኝ እያለክ ነው ነውና አስብበት ቨርችዋሎች😝😁‼️
#የኮድ_3_ስራ_ያለ_ሞትና_ኪሳራ‼️