Dr. Estifanos(MD, Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ
2.76K subscribers
358 photos
44 videos
12 files
195 links
Download Telegram
ወራቤ ኮ/ስ/ሆ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ እና ከስልጤ ዞን ጤና መምሪያ ጋር በመተባበር የ mhGAP ስልጠናን:  ከስልጤ፣ ከሃዲያ፣ ከንባታ እና ጉራጌ ዞኖች ለተውጣጡ ባለሙያዎች መስጠት ተችሏል::

ይህን ስልጠና የአዕምሮ ጤና ባለሙያ ላልሆኑ ሌሎች የጤና ባለሙያዎች በመስጠት የአዕምሮ ህክምና አገልግሎትን በመጀመሪያ የጤና አሃዶች ለማዳረስ እንደ ስልት በአለም የጤና ድርጅት የተነደፈ ፕሮግራም ነው::

ይህ ስልጠና በወራቤ ኮ/ስ/ሆ ሲዘጋጅ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን፤ ከዚህ በፊት ከስልጤ፣ ከምስራቅ ጉራጌ እና ማረቆ ወረዳ ለተውጣጡ ባለሙያዎች በመስጠት በነዚህ አካባቢዎች ያሉ ጤና ጣቢያዎች የአዕምሮ ህክምና አገልግሎት እንዲጀምሩ ማድረግ ተችሏል::

በስልጠናው የመዝጊያ ስነስርዓት ላይ ዶ/ር ጀማል(የወ/ኮ/ስ/ሆ ተወካይ)፣ አቶ ፍስሃ(የማእከላዊ ኢ/ክ/መ ጤና ቢሮ በሽታ መከላከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር)፣ አቶ ማንደፍሮ(የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ የህክምና አገልግሎት ሃላፊ) በመገኘት ንግግር አድርገዋል::

ይህን ፕሮጀክት ከባልደረቦቼ ጋር በመሆን መምራት በመቻሌ ደስታ ይሰማኛል::
👍85
Morality

Morality ትክክል የሆነውን ካልሆነው፣ ጥሩን ከመጥፎ፣ ብስሉን ከጥሬው የመለየት ስነልቦናዊ እና ማህበራዊ ክህሎት ነው::

በስነልቦናው: Morality በዋነኝነት የ Super-ego ስራ ነው::

የሞራል እሴቶች የመጀመሪያ ምንጮቻችን ወላጆቻችን ሲሆኑ፤ ከዚያም በመቀጠል በምንኖርበት ማህበረሰብ ዘዬ እና መስተጋብሮቻችን እየተቃኘ የራሱ የእድገት ሂደቶችን ያልፋል::

Kohlberg የሞራል እድገት ደረጃዎችን እንዲህ ያርቀምጣል:-

Stage 1- Pre-Conventional

ሞራሊቲን ከሚያስከትለው ቅጽበታዊ ቅጣት ወይንም ማበረታቻ አንጻር(reward and punishment) እንዲሁም 'ከጥቅማችን አንጻር?' የምንመዝንበት ወቅት ነው::

ልጅ እያለን ego-centeric መሆናችን የሚጠበቅ ቢሆንም አድገን ካልተውነው አደገኛ ነው::

2nd Stage- Conventional Morality

ሞራሊቲን 'በሰዎች ዘንድ ሞገስን እና ተወዳጅነትን ያስገኝልናል?' ከሚል እሳቤ አንጻር እንመዝናለን:: በመቀጠልም ህግጋትን ከግምት ውስጥ ማስገባት እንጀምራለን::

3- Post-Conventional

የራሳችንን ጥልቅ የሞራል እሴቶች የምንገነባበት እና ከማህበረሰቡ የስምምነት እሴቶች ጋር አቀናጅተን ማስኬድ የምንጀምርበት ወቅት ነው :: በስተመጨረሻ Morality አለማቀፋዊ ብያኔ እንዳለው በመረዳት ለህሊና(conscience) ዳኝነት ተገዢ እንሆናለን:: ይህ ትልቅ የሰውነት እሴት ነው!

አሻም!

ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው: የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት

https://www.facebook.com/DrEstif
https://t.me/DrEstif
👍52🙏1
ሰላም!

በአንዳንድ ምክንያቶች ላለፉት ወራት ተቋርጦ የነበረው የ ቴሌግራም ውይይታችን ከዚህ ወር ጀምሮ እንደሚቀጥል ማሳሰብ እፈልጋለሁ::

ይህ ውይይታችን በወር አንዴ በተመረጡ ርዕሶች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት የምናደርግበት ይሆናል::

በዚህ ዙር እንድንወያይበት የመረጥኩት ርዕስ Obsessive Compulsive Personality Disorder ነው::

ይህ ውይይት በዚህ ሳምንት ቅዳሜ መጋቢት 12 ከ 1:30 ጀምሮ የሚደረግ ይሆናል::

መልካም ጊዜ!
👍82
ለእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች በሙሉ: መልካም በዓል!
6
Live stream scheduled for
በ Obsessive compulsive personality disorder ዙሪያ ጥሩ ተማምረናል::

ቀጣይ እንድንወያይበት የምትፈልጉትን ርዕስ መጠቆም ትችላላችሁ
👍2🥰1
Official statement from Ethiopian Psychiatric Association
9😁1
ለሁሉም ህዝበ ክርስትያን
መልካም የትንሳኤ በዓል ይሁንላችሁ
🙏86
የአዕምሮ ጤና እና የውስጥ ደዌዎች
***
  የአዕምሮ ህመም ያለባቸው ሰዎች ለተጓዳኝ የውስጥ ደዌዎች የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ ነው::

ለምሳሌ:-

ስር የሰደደ ድብርት(Major depressive Disorder) ያጋጠማቸው ሰዎች:-

     ⛔️ለልብ ህመም በ 2 እጥፍ ፣
     ⛔️ለ Stroke በ 1.8 እጥፍ፣ 
     ⛔️ለካንሰር በ 1.9 እጥፍ፣
     ⛔️ ለስኳር ህመም በ 1.4 እጥፍ  ከፍ ያለ የመጋለጥ ምጣኔ አላቸው::

እንደ ስኪዞፍሬኒያ፣*የባይፖላር ህመም እና መሰል ህመሞችም ለተለያዩ አካላዊ ህመሞች (medical conditions) ተጋላጭነትን ይጨምራሉ::

ለዚህም እንደመንስኤ:

🔸የማያቋርጥ የውጥረት ስሜት የሚያስከትለው የሆርሞን መዛባት እና ያለአግባብ መረጨት (እንደ cortisol የመሳሰሉትን) በተለያዩ የሰውነት አካላችን ላይ የሚያስከትለው ጫና

🔸 ጤናማ የህይወት ዘይቤን ካለመከተል ጋር የተያያዘ የጤና ችግር ማጋጠሙ

🔸 ከጭንቀት ወይንም ከድብርት ለመውጣት በሚል ሰበብ ሱስ የሚያስይዙ ነገሮችን መጠቀም መጀመራቸው የሚያስከትለው ጉዳት

🔸 ከማግለልና መድልዖ ጋር በተያያዘ: በጤና ተቋማት እኩል ለመስተናገድ አለመቻላቸው እና የመሳሰሉ ምክንያቶች ይቀርባሉ::

***

በተመሳሳይ ሁኔታ: የተለያዩ የውስጥ ደዌዎች ለተጓዳኝ የአዕምሮ ህመም ተጋላጭነትን ከፍ ያደርጉታል::

ለምሳሌ ያህል:-

🔸የእንቅርት ህመም ( የታይሮይድ ሆርሞን መዛባት) ያለባቸው ሰዎች: የጭንቀት፣ የድብርት እና የሜኒያ(ምክንያት አልባ ፈንጠዝያ/መነጫነጭ) ምልክቶችን ሊያሳዩ ይችላሉ::

🔸የልብ ህመም ያለባቸው ሰዎች ለጭንቀትና ድብርት ህመሞች ተጋላጭነታቸው ከፍ ያለ ነው::

🔸የመተንፈሻ እና የሳምባ ህመም (እንደ አስም እና የመሳሰሉት) ያለባቸው ሰዎች የእንቅልፍ ችግር፣  ድንገተኛ የመረበሽ ስሜት(panic attack) እና የመሳሰሉት ሊያጋጥማቸው ይችላል::

🔸 እንደ Stroke፣ የጭንቅላት አደጋ (Traumatic brain injury)፣ የጭንቅላት ኢንፌክሽኖች(Encephalitis, ቂጥኝ/Neurosyphilis..)፣ አዙሪት (epilepsy) የመሳሰሉ ህመሞች : የአንጎል ስራን በማዛባት የሳይኮሲስ፣ የድብርት፣ የባይፓላር እና መሰል የአዕምሮ ጤና ችግሮችን ሊያስከትሉ ይችላሉ::

🔸በጽኑ የታመሙ ሰዎች : ድንገተኛ ግራ የመጋባት እና የባህርይ መለዋወጥ( Delerium) ሊታይባቸው ይችላል::

መውጫ:-

🔴  የውስጥ ደዌ  ያጋጠማቸውን ሰዎች ተጓዳኝ የአዕምሮ ጤና ችግር አጋጥሟቸው እንደሆነ መመርመር እና ማከም: ህክምናቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ እና ቶሎ ህመማቸው  እንዲያገግሙ ያደርጋቸዋልና አስፈላጊውን ትኩረት መስጠት ተገቢ ነው::

አሻም!

https://t.me/DrEstif
https://www.facebook.com/DrEstif
3
ስትሮክ
***
ስትሮክ የአንጎል ደም ስሮች ደም ለማስተላለፍ እክል ሲገጥማቸው የሚከሰት ህመም ነው::

ስትሮክ ሁለት አበይት አይነቶች አሉት:-

Ischemic Stroke(90% ገደማ):- የአንጎል ደም ስሮች ደም ለማስተላለፍ በመቸገራቸው( የደም ስር በመዘጋቱ..)የሚከሰት ነው::

Hemorrhagic Stroke(10% ገደማ):- በተለያዩ ምክንያቶች የአንጎል የደም ስር በመተርተሩ የሚከሰት (በከፍተኛ የደም ግፊት፣ Aneurysm/የደም ስር አባጭ ሲፈነዳ..) የሚከሰት

🔴 ስትሮክ በአብዛኛው ከከፍተኛ የደም ግፊት(Hypertension) እና የልብ ህመሞች(Cardiovascular disease) ጋር ይገናኛል:: ስለዚህም የደም ግፊት እና የልብ ህመሞችን መከላከል እና መቆጣጠር ወሳኝ ጉዳይ ነው❗️

ስትሮክ ሲከሰት የአንጎል ሴሎች ይጎዱ እና የተለያዩ ምልክቶች መታየት ይጀምራሉ:: እነዚህ ምልክቶች የደም ዝወውሩ እንደታወከበት የአንጎል ክፍል ይለያያሉ:: ድንገተኛ የእጅ እና የእግር መስነፍ(weakness)፣ ለመናገር ያለመቻል(Aphasia)፣ ራስን መሳት... የመሳሰሉ ምልክቶችን መጥቀስ ይቻላል::

ከአካላዊ እና የነርቭ ምልክቶች በተጨማሪ የተለያዩ የአዕምሮ ህመሞች ስትሮኩን ተከትለው ሊከሰቱ ይችላሉ:: (በአንጻሩም ደግሞ የተለያየ የአዕምሮ ህመም ያጋጠማቸው ሰዎች የተለያዩ ምክንያቶች ለስትሮክ ተጋላጭነታቸውን ሊጨምሩት ይችላሉ::)

ከሰትሮክ በኋላ ሊከሰቱ የሚችሉ የአዕምሮ ህመሞችን ለመጥቀስ ያህል:-

1️⃣ የድብርት ህመም:- እስከ 33% ገደማ ሰዎች ላይ ሊታይ ይችላል::

▪️ስትሮኩ የ ነርቭ ኬሚካል እና የመልዕክት ስርአትን በማዛባቱ፣ ችግሩ ያጋጠማቸው ሰዎች ህይወታቸው ላይ የተከሰተውን ለውጥ ለመልመድ በመቸገራቸው እና የመሳሰሉ ምክንያቶች ይጠቀሳሉ::

▪️በሌላ በኩል ደግሞ: ከፍተኛ የድብርት ህመም የሰውነት ስርዓትን በማዛባት የስትሮክ ተጋላጭነትን ይጨምራል::

2️⃣ የባይፖላር አይነት ህመም:- የሜኒያ ምልክቶችን: ማለትም ከፍተኛ የመነጫነጭ/ የፈንጠዝያ ስሜት፣ ሃይል መጨመር፣ ብዙ ማውራት፣ ራስን መካብ፣ የእንቅልፍ ፍላጎት መቀነስ፣ ግልፍተኝነትን ሊያሳዩ ይችላሉ

3️⃣ የጭንቀት እና ፍርሃት ህመሞች:- እስከ 24% ገደማ ሰዎች ላይ ሊታይ ይችላል::

4️⃣ ሳይኮሲስ:- የሌለ ነገር እንደታያቸው/እንደተሰማቸው/እንደሸተታቸው/ መናገር፣ ከእውነታ የራቁ አረዳዶችን ማንጸባረቅ ሊታይባቸው ይችላል::

5️⃣ስሜት አልባነት/Apathy

6️⃣ የመርሳት ችግር/Vascular dementia:-

7️⃣ Delerium :- :- ድንገተኛ ግራ የመጋባት እና ትኩረት የማጣት ሁኔታ: ተያይዞም መረበሽ እና ሃይለኝነት

.... እና የመሳሰሉ የአዕምሮ ህመሞች ስትሮክን ተከትለው ሊከሰቱ ይችላሉ:: ስለሆነም ከዋናው የስትሮክ ህክምና በተጨማሪ: ከላይ የተጠቀሱ ተጓዳኝ የአዕምሮ ህመም ምልክቶችን ማጤን፣ ከተስተዋሉ የአዕምሮ ህክምና ባለሞያን ማማከር የተገባ ነው::

አሻም አሻም!

ምንጭ:- Kaplan and Sadocks comprehensive textbook of psychiatry, 10th edition

ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው:- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት

ለበለጠ መረጃ የሚከተሉትን ገጾች ይወዳጁ:-
https://t.me/DrEstif
https://www.facebook.com/DrEstif
👍63👏3
🌍 CALL FOR RESEARCH ABSTRACTS 🧠

As part of Mental Health Awareness Month, Alenelachehu invites researchers, academics, and practitioners to submit research abstracts that explore mental health and psychosocial support (MHPSS) in humanitarian and displacement settings, with particular focus on women and children affected by conflict, displacement, and prolonged crises.

🔍We welcome abstracts that address:

* Mental health risks and protective factors in humanitarian and emergency settings
* Barriers to accessing MHPSS services
* Community-based and culturally responsive mental health approaches
* Resilience, lived experience, and social support in recovery
* Practical, evidence-informed pathways for integrating MHPSS into humanitarian action

Selected abstracts will contribute to a forum connecting stakeholders.

🗓 Submission deadline: May 01, 2026

🔗 Submit your abstract here:
https://forms.gle/F6SbBSdvuxxNNfdh7
📱 Or scan the QR code

📩 For inquiries, contact us: Alenelachehuco@gmail.com or+251 965 579 192
3
Together with my team, I delivered training on Basic MHPSS concepts and Psychological First Aid, with a focus on helping children. The training took place in Debre Birhan Town for trainees who are MIND SKILLZ coaches from various schools in the North Shoa Zone of the Amhara Region, as well as for staff of the Amhara Developmental Association (አልማ) and stakeholders from the Zonal Health Department.

The training was organized by IOM in collaboration with Grass Root Soccer and the Amhara Developmental Organization (አልማ).

Debre Birhan is a historic city and industrial hub in Ethiopia’s Amhara Region, located approximately 120–140 km northeast of Addis Ababa. Founded in the 15th century, it served as the capital of Ethiopia during the reign of Emperor Zara Yaqob.
👍4