+++ ‹‹ወንጌሉን ተወው!›› +++
የትሕርምት ሕይወትን በሚመለከት በጻፋቸው አያሌ ድርሰቶቹ የምናውቀው ሶርያዊው አባት ማር ይስሐቅ ነነዌ በተባለችው አገር ሊቀ ጳጳስ ሆኖ ተሹሞ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በመንበረ ጵጵስናው ግን የቆየው ለአምስት ወራት ያህል ብቻ ነው፡፡ በቅዱሱ ሕይወት ዙሪያ ጥናት ያደረጉ ጥቂት የማይባሉ የነገረ አበው ሊቃውንት ‹ለምን በአጭር ጊዜ ውስጥ መንበረ ጵጵስናውን ትቶ ሄደ?› ለሚለው ጥያቄ መልስ እንዳላገኙ ይገልጻሉ፡፡
ነገር ግን ከወደ ሶርያ የሚነገር አንድ ታሪክ አለ፡፡ ይኸውም በአንድ ወቅት በብድር ምክንያት መስማማት ያልቻሉ ሁለት ክርስቲያኖች ይዳኛቸው ዘንድ ወደ ማር ይስሐቅ ይመጣሉ፡፡ ገንዘብ አበደራዊው ሰው እየተበሳጨ ተበዳሪው መክፈል ካለበት ጊዜ አሳልፎ ጭማሪ ቀናት እየጠየቀው በመሆኑ፣ አሁን የማይከፍለው ከሆነ ጉዳዩን ወደ ሸንጎ እንደሚወስደው ለቅዱሱ ተናገረ፡፡ ማር ይስሐቅም ከወንጌል ትምህርት በመጥቀስ ለወንድሙ እንዲያዝንለትና ተጨማሪ ቀናት በመስጠት እንዲታገሰው ተማጸነው፡፡ አበዳሪው ግን በሊቀ ጳጳሱ ንግግር እየተናደደ ‹አሁን ከዚህ ውስጥ ወንጌሉን አውጣው!› ሲል መለሰ፡፡ የነነዌው ሊቀ ጳጳስ ማር ይስሐቅም በዚህ ሰው መልስ በጣም በማዘን ‹‹በወንጌል የተነገረውን የጌታን ትዕዛዝ ስነግርህ ሰምተህ ካልተቀበልክ፣ ታዲያ የእኔ እዚህ መሆን ምን ይጠቅማል?!›› አለው፡፡ ከዚያ ጊዜም በኋላ የብቸኝነትና የጽሙናን ሕይወት ፍለጋ መንበረ ጵጵስናውን ትቶ ወደ አስቄጥስ በረሃ ገብቷል፡፡
ከራሳችን ሐሳብ ጋር የሚስማማውን ብቻ ሳይሆን የማይስማማውንም የወንጌል ትምህርት ሰምቶ ለመቀበል ስንቶቻችን ዝግጁዎች ነን? ልክ እንደዚህ አበዳሪ ጆሮዎቻችን ለወንጌል ትምህርት ክፍት የማይሆኑባቸው ጊዜያቶች የሉም? ‹እዚህ ላይ ወንጌሉን ተወው!›፣ ‹አሁን ወንጌልን መጥቀስ ምን አመጣው!›፣ እያልን ሳግና ቁጣ ተናንቆን የጮኽንባቸውን ሁኔታዎች አታስታውሱም?
ከራሳችን ጠባይና አኗኗር ጋር ብቻ የሚስማማውን የወንጌል ክፍል መርጠን እየተቀበልን ሌላውን ግን አትጥቀሱብኝ የምንል ከሆነ፣ ‹በቅዱስ ወንጌልህ ቃል አምናለሁ› ብለን እንዴት ልንናገር እንችላለን?! ጌታችን ወደ ጌርጌሴኖን አገር መጥቶ በመቃብር ስፍራ ይኖሩ የነበሩ ሁለት አጋንንት ያደሩባቸውን ሰዎች ፈውሶ ነበር፡፡ ከእነዚያም ሰዎች ላይ የወጡት አጋንንት ወደ እሪያዎቹ ስለ ገቡ፣ መንጋውን አጣድፈው ከውኃ ሰጥመው እንዲሞቱ አደረጓቸው፡፡ ታዲያ በከተማው የሚኖሩ ሰዎች ይህን የክርስቶስን ሥራ በሰሙ ጊዜ ወዲያው እርሱ ወዳለበት መጥተው ‹ከአገራቸው እንዲሄድላቸው ለመኑት›፡፡ በጣም ይገርማል፤ በዓለም ውስጥ ተነጻጻሪ የማይገኝላት የከበረችውን ነፍስ ከአጋንንት፡ እስራት ማላቀቁ ቢያስደንቃቸውም፣ የእሪያዎቹ መንጋው መጥፋት ግን የበለጠ ስላሳሳቸው እንዲሄድላቸው ለመኑት፡፡(ማቴ 8፡34) ፈውሱ ገንዘባቸውን ከሚነካባቸው ይልቅ የድኅነታቸውን አምላክ አባርረው ከነእስራታቸው መኖር ምርጫቸው ሆነ፡፡ ለእኛ የወንጌል መልካምነት የእኛ የሆኑት ገንዘቦቻችንን፣ ክብራችንን፣ የበላይነታችንን እስካልነካብን ድረስ ነው፡፡ ወንጌሉ ለእኛ እንዲመች እንጂ፣ የእኛ ሕይወት ለወንጌሉ የተመቸ እንዲሆን አንፈልግም፡፡ ይህ ካልሆነ ግን እንደ ጌርጌሴኖን ሰዎች ከፊታችን ዘወር እንዲያደርጉልን ‹ወንጌሉን ተዉት!› እያልን በቁጣም ይሁን በልመና መናገራችን የማይቀር ነው፡፡
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com
አዲስ አበባ

❤176🙏30💔10👍4🥰4🔥2👏2
የእግዚአብሔር ሰው ሰሎሞን ለአምላኩ ሕንፃ መቅደስን ሊያንጽ በተነሣ ጊዜ ፤ "በጥበብና በማስተዋል በብልሃትም የተሞላ" የናሱን ሠራተኛ ኪራምን ከጢሮስ አስመጥቶ ነበር። ከዚህም ጥበበኛ ጋር ሆኖ እጅግ አስደናቂ የሆነውን መቅደስ በታላቅ ጥንቃቄ አንጿል። በእውነት ይህን ሰሎሞን ያሳነጸውን ውብ መቅደስ ማየት ምንኛ ያጓጓ ይሆን? በእርግጥም መቅደሱንና የመሥዋዕቱን ሥርዓት የተመለከተች ንግሥተ አዜብ ማክዳ "ነፍስ አልቀረላትም" ነበር (1ኛ ነገ 10:5)።
ሆኖም ግን እግዚአብሔር በነቢዩ ኢሳይያስ አድሮ "ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ ለእኔ ምን ዓይነት ቤት ትሠራላችሁ?" ብሎ መጠየቁ አልቀረም (ኢሳ 66:48)። ለጊዜው በረድኤት የሚያድርበትን መቅደስ ንጉሥ ሰሎሞን ውብ አድርጎ ቢያንጽለትም ፤ በኋላ ግን የሰውን ልጆች ለመቤዠት በአካል የሚያድርበትን ሕያው መቅደስ ማንም ማዘጋጀት አልቻለም ነበር። ስለዚህም "ልዑል የሰው እጅ በሠራችው አይኖርም" ተብሎ ተጻፈ (ሐዋ 7:50)። በመሆኑም መቅደሱን ላነጹ ለሰሎሞን እና ለኪራም ጥበብን የሰጠው ጥበበኛ "ለራሱን ቤት ሊሠራ ፣ሰባት ምሰሶዎችንም ሊያቆም" ፈቃዱ ሆነ። የመቅደሱንም መሠረት እንቁ አደረገ። ቤቱንም እጅግ በከበሩ ድንጊያዎች አነጸ።
ይህች በአምላክ እጅ የታነጸች ፣እግዚአብሔር በረድኤት ሳይሆን በአካል የሚያድርባት ሕያው መቅደሱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። የተመሠረተችባቸውም አዕናቁ (እንቁዎች) ቅዱሳን ቤተሰቦቿ ናቸው። የታነጸችበትም የከበሩ ድንጊያዎች ንጽሕና ፣ቅድስና ናቸው።
"ይህች ዓለም አይቶ የማያውቃት በተስፋ ትጠበቅ የነበረችው ድንቅ አማናዊት መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህች ምድር ላይ የታየችው በዛሬው ቀን ነበር"
ኪራም ያነጸው የሰሎሞንን መቅደስ መጎብኘት "ነፍስ የማያስቀር" ፣ልብን በሐሴት የሚሞላ ከሆነ ፤ በእግዚአብሔር እጅ የታነጸች ፣የአምላክ ጥበብ የፈሰሰባት እውነተኛ መቅደሱን የእመቤታችንን መወለድ የማየትና የመስማት የደስታ ጥጉ ምን ያህል ይሆን?
እንኳን ደስታን ወደ ዓለም ይዞ ለመጣ ተናፋቂው ለድንግል ማርያም ልደት አደረሳችሁ!!!

❤196🙏22🥰10🔥1
ከመላእክት ጋር አብረን የምንዘምርበትን የዜማ ሥርዓት ለሠራልን፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ የወረደውን የምስጋና ማዕድ ለእኛ እንደሚገባ አድርጎ ላደረሰ ታማኝ መጋቢ፣ ለዘማሪው፣ ለተርጓሚው፣ ለባለ ቅኔው ለቅዱስ ያሬድ ማኅሌታይ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን።
-የአንደበት አመጽ ጸጋን አስገፍፎ እንዴት የመልአክነትን ክብር እንደሚያሳጣ በሳጥናኤል አየን!
-የአንደበት ፍሬ እንዴት እንደሚያከብር እና ምድራዊ መልአክ እንደሚያደርግ ደግሞ በቅዱስ ያሬድ ማኅሌታይ ተመለከትን!
አቤቱ የያሬድን ልሳን ስጠኝ!
ዲያቆን አቤል ካሣሁን
https://t.me/Dnabel

❤266🙏41🥰10👍6
"በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን" ኤፌ 2፥6-7
እንኳን ለበዓለ ዕርገት በሰላም አደረሰን!
እንኳን ለበዓለ ዕርገት በሰላም አደረሰን!
❤271🙏45🥰37🔥5
"አርእይኒ ገጸ ዚአኪ ማርያም ምእረ፤ ዘኢይሰምዖ ካልዕ እንግርኪ ነገረ"
"ማርያም ሆይ፣ ለሌላው የማልነግረውን ነገር እነግርሽ ዘንድ አንድ ጊዜ ፊትሽን አሳይኝ"
መልክአ ማርያም
እንኳን ለበዓለ ደብረ ምጥማቅ በሰላም አደረሳችሁ!
https://t.me/Dnabel
"ማርያም ሆይ፣ ለሌላው የማልነግረውን ነገር እነግርሽ ዘንድ አንድ ጊዜ ፊትሽን አሳይኝ"
መልክአ ማርያም
እንኳን ለበዓለ ደብረ ምጥማቅ በሰላም አደረሳችሁ!
https://t.me/Dnabel
❤280🙏46🥰13❤🔥6🔥5👍3👏1
+++"እውነትም የመከር በዓል"+++
ጌታችን ከትንሣኤው በኋላ በጋራም በተናጠልም ለሐዋርያቱ እየታያቸው የትንሣኤውን አማናዊነትና ‹ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ነገር እየነገራቸው› አርባ ቀን ቆይቷል፡፡(ሐዋ 1:3) በአርባኛውም ቀን ሲያርግ ‹የሚያጸና፣ የሚያነጻ እና የሚያጽናና መንፈስ ቅዱስን› እንደሚልክላቸው ተስፋን ሰጣቸው፡፡ ነገር ግን ከላይ ኃይልን እስከሚቀበሉባት ቀን ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ እንዲቆዩ አዘዛቸው፡፡ (ሉቃ 24፡49-51) ሐዋርያቱም ከጌታ ዕርገት በኋላ በጽዮን አዳራሽ (ጽርሐ ጽዮን) ውስጥ በአንድ ልብ ሆነው በጸሎት ይተጉ ጀመር፡፡
ለሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ የወረደበት ቀን ማለት አይሁድ በዓመት ውስጥ ከሚያከብሯቸው ታላላቅ በዓላት መካከል አንዱ የሆነውን ‹በዓለ ሃምሳ› የሚውልበት ዕለት ነበር፡፡ ይህም በዓል አይሁድ ፋሲካቸውን ካከበሩ ከሰባት ሳምንታት በኋላ ባለው ሰንበት ማግስት (በእሁድ፣ በ50ኛው ቀን) ስለሚከበር ‹‹ጰንጠቆስጤ››/‹‹በዓለ ሃምሳ›› ተብሎ ይጠራል፡፡ በዚህም ቀን እስራኤላውያን አርሰው ካመረቱት ላይ አዲሱን የእህል ቁርባን ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡበትም ዕለት ስለሆነ በሌላ ስያሜ ‹የመከር በዓል› ተብሎ ይጠራል፡፡ በተጨማሪም የእስራኤል መስፍን የነበረው ሊቀ ነቢያት ሙሴ በሲና ተራራ ከአምላኩ ዘንድ ሕገ ኦሪት መቀበሉንም የሚያስቡበት ቀን ነው፡፡
በተለያዩ የዓለም ክፍላት የሚኖሩ አይሁድ ከያሉበት አገር ተጉዘው በመምጣት የፋሲካንና የመቅደስ መታደስ በዓላትን በኢየሩሳሌም ተሰብስበው ለማክበር ይቸገሩ ነበር፡፡ የችግሩም ምክንያት እነዚህ በዓላት በሚውሉበት ወቅት ያለው የአየር ጠባይ በጣም አስቸጋሪና ነፋሱም ማዕበል የሚቀሰቅስ በመሆኑ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዚሁ ጊዜ ወደ ኢጣልያ ለመሄድ በመርከብ በተሳፈረ ጊዜ ስላጋጠመው እንግልትና ስቃይ በሐዋርያት ሥራ ላይ ተጽፏል፡፡(ሐዋ 27፡9) እርሱ ራሱም በመንገዱ መካከል አብረውት ይጓዙ የነበሩትን ሰዎች ‹‹እናንተ ሰዎች ሆይ ይህ ጉዞ በጥፋትና በብዙ ጉዳት እንዲሆን አያለሁ፤ ጥፋቱም በገዛ ሕይወታችን ነው እንጂ በጭነቱና በመርከቡ ብቻ አይደለም›› ሲል ጉዞውን ለጥቂት ጊዜ እንዲያዘገዩት መክሯቸው ነበር፡፡ በዓለ ሃምሳ ግን የመጀመሪያዎቹ የፀደይና የመከር ወቅት ላይ ስለሚውል የአየሩ ሁኔታ ለመርከብ ጉዞ የተመቸ ነው፡፡ ስለዚህም የፋሲካና የመቅደስ መታደስ በዓላት ላይ በኢየሩሳሌም መገኘት ያልቻሉ አይሁድ ሁሉ በጉጉት የሚጠባበቁትና ወደ ቅድስቲቱ ከተማ በመግባት ተሰብስበው የሚያከብሩት ታላቅ በዓል ነው፡፡
"በዓለ ሃምሳ" የሚለው መጠሪያ አስቀድመን እንደ ተናገርነው በኦሪቱ ለሚከበረው በዓል መታወቂያነት የሚያገለግል ስያሜ ቢሆንም፣ የጌታ ሐዋርያትም መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉት ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በሃምሳኛው ቀን በመሆኑ ለሐዲስ ኪዳኑም ታላቅ በዓል መጠሪያነት ቢውል የሚያውክ አይሆንም፡፡ ይሁን እንጂ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህንን ቀን ‹በዓለ ጰራቅሊጦስ› ስትል ለሐዋርያት በወረደው ቅዱስ መንፈስ ልዩ ስም ትጠራዋለች፡፡ ‹‹ጰራቅሊጦስ›› የሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን ‹‹መጽንዒ፣ መንጽሒ››/‹‹የሚያጸና፣ የሚያነጻ›› የሚል ትርጉም አለው፡፡
ወደ ቀደመ ነገራችን እንመስና ሐዋርያቱ በጽርሐ ጽዮን ተሰብስበው ሲጸልዩ ሳሉ ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምጽ መጣ፣ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው፡፡(ሐዋ 2፡2) በዚህ ክፍል ይህን ታሪክ የሚጽፍልን ቅዱስ ሉቃስ የመንፈስ ቅዱስ መውረድ ‹ድንገት› እንደ ሆነ ይነግረናል፡፡ ለመሆኑ ‹ድንገት› ሲል ምን ለማለት ፈልጎ ነው? ጸሐፊው ቅዱስ ሉቃስ ‹ድንገት› የሚለውን ቃል የተጠቀመው ነገሩ በሰው ቀጠሮ ሳይሆን ‹በእግዚአብሔር ጊዜ› የተፈጸመ መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ ሐዋርያት አጽናኙ መንፈስ እንደሚላክላቸው ቢነገራቸውም በየትኛው ቀን ግን እንደሚወርድ የሚያውቁት ነገር አልነበረም፡፡ ስለዚህም ‹ድንገት› የሚለው ቃል ሐዋርያቱ ቀኑን ፈጽመው አለማወቃቸውን ያሳያል፡፡ ሁል ጊዜ ጸጋን የሚሰጠው እግዚአብሔር ስለሆነ የሚሰጥበት ቀነ ቀጠሮ በሰጪው እንጂ በተቀባዩ አይወሰንም፡፡ ስለዚህ የተቀባዩ ሰው ድርሻ ሳይዝል ተስፋም ሳይቆርጥ የአምላኩን የሥራ ቀን በትዕግሥት መጠባበቅ ነው፡፡
የዓውሎ ነፋሱም ድምፅ ልክ ኤልያስ የምድሩን መናወጥና እሳቱን ሲመለከት በመጎናጸፊያው ተሸፍኖ ከዋሻው በመውጣት እግዚአብሔርን ለማናገር ራሱን እንዳዘጋጀ፣ ሐዋርያቱም የመንፈስ ቅዱስን መውረድ እንዲያስተውሉና ለዚያም ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ የተሰማ የማንቂያ ድምፅ ነው፡፡(1ኛ ነገ 19፡12) በተጨማሪም ድምፅ ‹ኃይልን› ያመለክታል፡፡ ስለዚህ እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ የተሰማው ድምጽ ሐዋርያቱ ከመንፈስ ቅዱስ ኃይል መቀበላቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ እዚህ ላይ ጌታችን በዮርዳኖስ ወንዝ ከተጠመቀ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በእርሱ ላይ ሲያርፍ ያሰማው አንዳች ድምፅ አለመኖሩን ልብ ይሏል፡፡(ማቴ 3፡16) ይህም እርሱ ለደካሞች ጽንዕ የሚሆን እንጂ እንደ ፍጡር ኃይል የሚቀበል አለመሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡
አስቀድሞ መድኃኒታችን ለኒቆዲሞስ ‹‹ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል›› ሲል እንዳስተማረው፣ በዚህች ቀን በነፋስ የተመሰለ መንፈስ ቅዱስ በወደዳቸው በሐዋርያት ሰውነት ያድር ዘንድ ወደ ጽርሐ ጽዮን ነፈሰ(መጣ፣ ወረደ)፡፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ መንፈስ ቅዱስን ከነፋሳትም መርጦ ከደቡብ አቅጣጫ በሚነፍሰው ነፋስ ይመስለዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ከሰሜኑ የሚነሣው ነፋስ ቀዝቃዛና ሰብል የሚያጠፋ በመሆኑ በመካከለኛው ምሥራቅ የሚኖሩ ገበሬዎች ይፈሩታል፡፡ ከደቡብ አቅጣጫ የሚነፍሰው ነፋስ ግን ከምድር ወገብ የሚወጣውን ሞቃታማ አየር ይዞ ስለሚነፍስ የተዘራውን ሰብል ያበስለዋል፡፡ በዚህም ገበሬዎቹ ደስ ይሰኙበታል፡፡ ሊቁ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ መንፈሳዊ ብስለትን የሚሰጠው መንፈስ ቅዱስ ልክ በደቡብ እንደሚነፍሰውና ሰብሎችን እንደሚያበስለው ያለ ተወዳጅ ነፋስ ነው ይላል፡፡
ቀጥሎም ለሐዋርያቱ እንደ እሳት የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፡፡ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው፡፡ በሁሉም ላይ መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፡፡ አስተውሉ በዚህ አንድ ታሪክ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ በእሳትም በነፋስም ተመስሎ ሲቀርብ እናገኛለን፡፡ ታዲያ መንፈስ ቅዱስ የተመሰለባቸው ምሳሌዎች መብዛታቸው ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ እንዳብራራው የመንፈስ ቅዱስ ባሕርይ በምልዓት የማይታወቅ መሆኑን ያመለክታል፡፡
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን በእሳት መመሰል አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በዕብራውያን መልእክቱ ‹‹አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና›› ሲል ስለ እርሱ ተናግሯል፡፡(ዕብ 12፡29) መንፈስ ቅዱስ በእሳት መመሰሉ፣ ከከርሰ ምድር መዓድናትን የሚያወጣ ባለሙያ ከመሬት ቆፍሮ ያወጣውን መዓድን ከትቢያው የሚለየው በእሳት እንደ ሆነ እንዲሁ፣ መንፈስ ቅዱስም ነፍሳችንን ትቢያ ከተባለ ኃጢአት ሁሉ ለይቶ ያነጻታልና በእሳት ተመሰለ፡፡ ይህንንም በተመለከተ ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ ‹‹የእስራኤልም ብርሃን እንደ እሳት፣ ቅዱሱም እንደ ነበልባል ይሆናል፡፡ እሾኹንና ኩርንችቱን በአንድ ቀን ያቃጥላል›› ሲል ይናገራል።(ኢሳ 10፡17) አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም በመጽሐፈ ምሥጢሩ ለሐዋርያቱ በሃምሳኛው ቀን በእሳት አምሳል የወረደው መንፈስ ቅዱስ ‹‹ሥጋቸውን ሳይሆን የኃጢአታቸውን እሾኽ አቃጠለ›› በማለት ይገልጻል፡፡

❤51🙏8
እነዚያ እንደ እሳት ላንቃ የተከፋፈሉት ልሳኖች ከመታየትም አልፈው በሐዋርያቱ ላይ መቀመጣቸው፣ ደቀ መዛሙርቱ የሚያዩት ነገር ሁሉ ቅዠት ወይም ምናባዊ ሳይሆን እውነተኛ የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ መሆኑን እንዲገነዘቡ ነው፡፡ ከዚያም በኋላ በሁሉም ላይ መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ልጅ በረገጡና አመጽ ወዳድ በነበሩት አይሁድ ቅንዓትና ቁጣ ሲሞላ፣ የሰላም ልጆች በነበሩት ሐዋርያት ግን መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፡፡ ስለዚህም መንፈስ ቅዱስ ይናገሩ ዘንድ (በየአቅማቸው) እንደ ሰጣቸው በሌሎች ቋንቋዎች ይናገሩ ጀመር፡፡
እግዚአብሔር አሕዛብ ያለ ሐዋርያት ስብከት በሥላሴ ማመን እንደማይችሉ፣ ሐዋርያትም ያለ መንፈስ ቅዱስ መውረድ በየአገሩ ቋንቋዎች ሁሉ መስበክ እንደማይችሉ ዐወቀ፡፡ ስለዚህም በሰናዖር ሜዳ የተበተኑትን የዓለምን ቋንቋዎች በሐዋርያት አንደበት ሰብስቦ ያኖር ዘንድ ቅዱስ መንፈሱን ላከ፡፡ የተላከውም መንፈስ ያለ አንድ ቋንቋ የማይናገረውን የሐዋርያቱን አንደበት በቅጽበት አሰለጠነው። በእውነት እንደ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ያለ አስማሪ ማን ነው?!በዚህችም እለት ሐዋርያቱ በዓለም ሁሉ ቋንቋዎች ተሞልተው ከእርሷ የወጡባት የጽዮን አዳራሽ (ጽርሐ ጽዮን) እንደ ምን ያለች ናት?! መንፈስ ቅዱስ ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ ታይታ የማትታወቅ ልዩ ትምህርት ቤት አደረጋት፡፡
ሐዋርያቱም በመንፈስ ቅዱስ ተሟሙቀው በሰበኩት በመጀመሪያ ዕለት ስበከት ብዙዎችን አሳምነው አጠመቁ። በዚህ የመከር በዓል አይሁድ ከአዲሱ እህል ለእግዚአብሔር ቁርባን ሲያቀርቡ፣ ሐዋርያቱ ግን የክርስቶስ አካል ለሆነችው ለሐዲሲቷ ቤተ ክርስቲያን ከእህል ቁርባን ይልቅ የሚወደዱ ምእመናንን ስጦታ አድርገው አቀረቡ። በአይሁድ የመከር በዓል ቀን በሐዋርያቱ በተሰጠ ትምህርት የእግዚአብሔር እርሻ የሆኑ ምዕመናን በዝተው አብበው ተገኙ። እውነትም የመከር በዓል!!!

100❤81🙏24👏4
‹‹ራሱም የወደዳቸውን ወደ እርሱ ጠራ›› ማር 3፥13
ጌታችን በሰንበት ወደ ምኩራብ ገብቶ እጁ የሰለለችበትን ሰው ባዳነ ጊዜ፣ በሥራው የተቆጡ አይሁድ እንዴት እንዲያጠፉት ከሄሮድስ ወገን ጋር ይማከሩ ጀመር፡፡ እነርሱ በሰንበት የተመጠነ መንገድ (የሰንበት መንገድ) ከመሄድ ጀምሮ ቀላል የሆኑ የሰውነት እንቅስቃሴ የሚፈልጉ ተግራትን በነጻነት ሲያከናውኑ፣ እርሱን ግን በቃሉ እንኳን ተናግሮ ሕሙማንን እንዳይፈውስ ይከላከሉት ነበር፡፡ በዚህም ጊዜ መድኃኒታችን ደቀ መዛሙርቱን ይዞ ወደ ገሊላ ባሕር ፈቀቅ አለ፡፡ ከእርሱ ጋር የነበሩት ደቀ መዛሙርቱ ብቻ አይደሉም፡፡ ያደረጋቸውን ታላላቅ ተአምራት የሰሙ ብዙዎችም ከተለያዩ ቦታዎች እርሱ ወዳለበት መጥተው ነበር፡፡
ጌታችን ኢየሱስ የተሰበሰቡትሰዎቹ እንዳያጋፉት ታንኳ ያዘጋጁለት ዘንድ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው፡፡ ከዚህ ታሪክ መፈጸም በፊትም ሆነ በኋላ ጌታችን በብዙ ሰዎች መካከል ተከቦ አስተምሯል፡፡ የልብሱንም ጫፍ ለመዳሰስ የለመኑትን ሳያሳፍራቸው ዳሰሰዉት እንዲፈወሱ አድርጓል፡፡ አሁን ግን ሰዎቹ ‹እንዳያጋፉት› ሐዋርያቱ ታንኳ እንዲያዘጋጁለት አዘዘ፡፡ ልብ በሉ ‹እንዳይዳስሱት› አላለም፣ ‹እንዳያጋፉት› እንጂ፡፡ ይህ ስለ ምን ሆነ? ካላችሁ፣ ልብሱን ለመዳሰስ የሚቀርቡት ሰዎች አቀራረባቸው ‹በልመና›/‹በጸሎት› ሲሆኑ፣ የሚጋፉት ሰዎች ግን ቃሉም እንደሚገልጸው ወደ እርሱ ለመቅረብ የሚሞክሩት በጉልበታቸው ነው፡፡ ስለዚህ በትሕትና ሆነው ለሚለምኑት ቅርብ ሆኖ ሲዳሰስላቸው፣ በጉልበታቸው ለሚጋፉት ግን ሊደርሱበት ወደማይችሉት ባሕር ተሳፍሮ ይርቅባቸዋል፡፡ እግዚአብሔርን በእምነት ብርሃንነት ስትፈልገው ቅርብ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡ በራስህ ማስተዋል ግን በመደገፍ ላስሰው ብትል መሰወሪያውን ጨለማ ያደርግብሃል፡፡
በሕዝቡም መካከል ሲያልፍ በሥጋ ደዌ የሚሰቃዩ ሰዎች ዳስሰውት ከሕመማቸው ይፈወሱ ዘንድ ከፊቱ ይወድቁ ነበር፡፡ ርኩሳት መናፍስትም ባዩት ጊዜ በፊቱ እየሰገዱ ‹አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ› እያሉ ጮኹ፡፡ አይሁድ በላያቸው የወደቀውን የርግማን ቀንበር ለማንሣት የመጣውን የአብ ልጅ ‹የዮሴፍ ልጅ› እያሉ ሲያናንቁ፣ የጥፋታቸው አጋፋሪዎች የሆኑ አጋንንት ግን ‹አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ› ሲሉ ስለ እርሱ መሰከሩ፡፡ ‹አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ› የሚለው ንግግር በቤተ ክርስቲያን ያለው ቦታ ቀላል አይደለም፡፡ ከዚህ የሚበልጥ የምስክር ቃልም የለም፡፡ በዚህ ቃል ቅዱስ ጴጥሮስ ‹አንተ ብፁዕ ነህ!› ተብሎ ተመስግኖበታል፣ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ባኮስ ጥምቀተ ክርስትናን አግኝቶበታል፡፡ ታዲያ ቅዱስ ጴጥሮስ ተናግሮ ሳይመሰገንበት፣ ባኮስም መስክሮ ሳይጠመቅበት በፊት ይህንን ቃል ለተናገሩ ለአጋንንት ጌታችን ምን መልስ ሰጣቸው? መልሱ ግልጽ ነው፤ ‹እንዳይገልጡት በጣም አዘዛቸው›፡፡(ማር 3፡12) ለምን? ምክንያቱም ፍቅርና ትሕትናን የማያውቁ አጋንንት መቼም ቢሆን የእውነት ምስክር መሆን ስለማይችሉ ነው፡፡ የሚናገሩት ነገር እንኳን በቤተ ክርስቲያን የሚታመን እውነት ቢሆንም፣ አጋንንቱ ግን ይህን የሚሉት እውነትን ወድደው ሳይሆን ቀጥለው ለሚያቀርቡት መርዝ ማጣፈጫነት ያህል ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ እነርሱን እንደ ጌታችን ‹እውነትን እንዳይገልጡ በጣም ከማዘዝ› ውጭ መቼም ቢሆን ጆሮ ሰጥተን ልናደምጣቸው አይገባም፡፡
የአጋንንት ምስክርነትን ጠልቶ እንዳያገልጡት ያዘዛቸው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወዲያውኑ የወደዳቸውን ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ጠርቶ ምስክሮች ይሆኑት ዘንድ የጽድቅ ሐዋርያት አደረጋቸው፡፡ በዚህም ተግባሩ ከአጋንንት ይልቅ የሐዋርያቱና በሐዋርያት እግር የሚተኩ የካህናትና የመምህራነ ቤተ ክርስቲያን ምስክርነትን በእርሱ ዘንድ የተወደደ እንደሆነ አሳየን፡፡ ደግሞም ሐዋርያቱን ወደ እርሱ የጠራቸው እንዲሰብኩ ብቻ ሳይሆን ‹ከእርሱም ጋር እንዲኖሩ› ጭምር ነው፡፡(ማር 3፡14) ከጌታው ጋር መኖር የማይችል ስለ ጌታው መስካሪ ሆኖ ሊጠራ አይችልም፡፡ የአጋንንት ትልቁ ድክመታቸውም ይህ ነው፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሊናገሩ ይችላሉ፤ ከእግዚአብሔር ጋር ግን መኖር (በቅድስና) አይችሉም፡፡
በመጨረሻም ውሸት የማይቀላቅሉ የእውነት ሐዋርያት ከተመረጡ በኋላ በመንገዳቸው ሁሉ የሚፈታተኗቸው የሐሰት ምስክሮች አጋንንት ሊወገዱ ይገባቸዋል። ስለዚህ ክርስቶስ ወድዶ ለመረጣቸው አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አጋንንትን ያወጡ ዘንድ ሥልጣን ሰጣቸው፡፡ በርግጥም አጋንንት ተባራሪ፣ ወጭ እንጂ ተሰሚ፣ መስካሪ ሊሆኑ አይገባም።

❤107🥰8👍6🙏5👏2
ሁሉም ነገር ልክ እና መጠን አለው። አሁንስ መሸሻችን ወዴት ነው? ስማችን እስኪጠፋን ድረስ አእምሯችን በሞት ወሬ ደነዘዘ። እንግዲህስ ጩኸታችን ወደ ማን ነው? “ኢ ሀሎኑ በዝ ሰማይ አምላከ ኢትዮጵያ አዶናይ” - “የኢትዮጵያ አምላክ አዶናይ በዚህ ሰማይ የለምን?!”
"አቤቱ በእኛ ላይ የደረሰብንን ሁሉ አስብ ተመልከት"
ሰቆ. ኤር. 5፥1
"አቤቱ በእኛ ላይ የደረሰብንን ሁሉ አስብ ተመልከት"
ሰቆ. ኤር. 5፥1
😭234💔84❤46🙏25😢2👍1
ሞት ምንድር ነው?
በክርስትናው ዓለም የሞት አረዳድ ምን ይመስላል?
በጣም የቅርባችሁን ሰው በሞት ስታጡ ምን ተሰማችሁ?
የሚወደውን ሰው በሞት ያጣውን ሰውስ እንዴት ነው የምናጽናናው?
በእነዚህ ጥያቄዎች ዙሪያ በHealing with Eleni podcast ከሥነ ልቡና ባለሙያዋ ወ/ሮ እሌኒ ክፍሌ ጋር ብዙ ተወያይተናል። እስኪ ገብታችሁ ታደሙ። በዚያውም ለቤቱ አዲስ የሆናችሁ ቻናሉን ተወዳጁ። ታተርፉበታላችሁ።
https://youtu.be/rJwpA_15Sx0?si=h4Z4ucQgqbFwsgxz

YouTube
"ግድየለም አትዘን ፤ አታልቅስ" አይባልም! ሀዘን ላይ ስንሆን አምላካችንን ለምን ተዉከኝ እንላለን ዲያቆን አቤል ካሳሁን | Deacon Abel Kassahun
በዚህ ክፍል ከመምህራችን ዲያቆን አቤል ካሳሁን ጋር ጥሩ ቆይታ አድርገናል። ዲያቆን አቤል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሰባኪ ወንጌል፣ የ4 መጽሐፍት ደራሲ እና የሥነ ልቦና ባለሙያ ናቸው። በቆይታችን ስለ ሞት፣ ሐዘን፣ Denial፣ ማህበረሰባችን የሚጠቀማቸው የሐዘን ማጽናኛ መንገዶች እና በእነዚህ ሁሉ ውስጥ የእግዚአብሔር መገኘት እስከ ምን እንደሆነ ከሥነ ልቦናዊና ከመንፈሳዊ እይታ ተወያይተናል።…
❤64🙏8😍2🤣2👍1
+++ እግዚአብሔር ለአንተ ፍትሐዊ ነው? +++
ጋሽ ስብሐት ለአብ ገብረ እግዚአብሔር በአንድ የሬዲዮ ጣቢያ ላይ ቃለ መጠይቅ ሲደረግለት ለጋዜጠኛው "እግዚአብሔር በአንዳንድ ነገሮች ጥሩ አላደረገም" አለው። ጋዜጠኛውም "እንዴት? እስኪ ለምሳሌ?" ቢለል፣ "ለምሳሌ ለእኔ ያደላል" ሲል መለሰለት።
እኛስ እንዲህ የምንልባቸው አጋጣሚዎች የሉም? በእርግጥ "እግዚአብሔር ለእኔ ያደላል" ስንል "ከሌላው ያስበልጠኛል" እያልን አይደለም። በዚህስ "እግዚአብሔር የሰውን ፊት አይቶ አያደላም"።(ገላ 2፥6) ነገር ግን እርሱ እያንዳዳችንን ልክ እንደ አንድና ብቸኛ ልጅ ያህል የሚወድ አምላክ ስለሆነ ከዚህ ተአምራዊ የአባትነት ፍቅሩ የተነሣ ሁላችንም ለእኛ "የሚያደላ" መስሎ ይሰማናል።
ለመሆኑ "አምላክ ለእኔ ያደላል" ስንል ምን ማለታችን ይሆን? እግዚአብሔር ያደላልኛል ስንል እኔ ምንም ሊደረግለት የማይገባ አመጸኛ ሰው ሆኜ ሳለሁ ክፋቴን ሳይሆን ደግነቱን እያሳየ ያኖረኛል ማለታችን ነው። አንዲት እናት መልካም ከሆኑ ልጆቿ መካከል አንድ አስቸጋሪ ልጅ ቢኖራት ይጎዳብኛል ብላ ለእርሱ እንደምትሳሳ፣ ፈጣሪዬ እኔ አመጸኛ ልጁን ከስንፍናዬ የተነሣ እንዳልጠፋበት በስስት ያየኛል ይጠብቀኛል እያልን ነው።
ሶርያዊው ማር ይስሐቅ እግዚአብሔር እኛ ኃጢአተኞቹ ላይ በሚያደረገው ሁሉ ፍትሑ አልታየምና እንዴት "ፍትሐዊ ነው" ብለን ልንናገር እንችላለን ይለናል። እውነት ነው፤ እስኪ አስቡት:- በአመሻሹ ገብተን በሠራናት ጥቂት ሥራ ከጠዋት ጀምረው ከደከሙት ጋር እኩል ዲናር የሚከፍለንን፣ ገንዘቡን ወስደን በማይገባ ኑሮ ስላባከንን ፈንታ ጸጸታችንን ብቻ ተመልክቶ ወደ እኛ ሲሮጥ በመምጣት አንገታችንን አቅፎ የሚስመንን እና መልሶ በገንዘቡ ሁሉ ላይ የሚያሰለጥነንን ጌታ እንዴት "ለእኔስ ፍትሐዊ ነው" ልንለው እንችላለን?
እግዚአብሔር ከሕይወት ይልቅ ሞት፣ ከበረከት ይልቅ እርግማን ለሚገባን ለእኛ በደለኞቹ አንድም የሚገባንን አላደረገብንም። ታዲያ እግዚአብሔር እኛ ላይ ባሳየው ነገር "ፍትሐዊ" ነው ትላላችሁ?

❤156🥰8❤🔥7😢6🔥3💔3👍2👏2