Dn Abel Kassahun Mekuria
18.5K subscribers
637 photos
61 videos
1 file
949 links
ይህ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የተለያዩ ትምህርቶችን የሚያገኙበት በባለቤቱ የተከፈተ ቻነል ነው።

ይወዳጁን

ለፌስቡክ ገጽ
https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12?mibextid=ZbWKwL

ለyoutube
https://youtu.be/s6Cn-jMYjrk?si=Tw7lXr62xkGQtL9_

ለInstagram
https://www.instagram.com/abelkassahunm?igsh=OW
Download Telegram
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ እና ዮሐንስ ዘደማስቆ ሐዋርያው ጴጥሮስ ጌታ በዐረገ በዓመቱ (34 ዓ.ም.) ቅዱሱን እሳት በመቃብሩ ስፍራ ማየቱን ጽፈዋል። ይህ ተአምር አሁን እስካለንበት ዘመን የቀጠለ ሲሆን፣ ሁል ጊዜም በትንሣኤ በዓል ዋዜማ ቅዳሜ ቀን ይታያል። ስለዚህ የሚያስደንቅ ተአምር ብዙ የማያምኑ ሰዎች በራሳቸው መንገድ ለማጣራት ሞክረዋል። እስኪ ከእነዚህ ውስጥ አንዱን ታሪክ ላጫውታችሁ።

በአንድ ወቅት እንዲህ ሆነ…

ዕለቱ ቅዳሜ ጠዋት 4 ሰዓት የትንሣኤ ዋዜማ ነው። የእስራኤል አይሁድ ፖሊሶች እና የከተማዋ ከንቲባ ይህ እሳት ይፈልቅበታል የተባለውን የጌታን መቃብር እውነትነት ማረጋገጥ ስለ ፈለጉ በውስጡ ለእሳቱ መነሣት ምክንያት የሚሆኑ ተቀጣጣይ ነገሮች ካሉ በሚል ለሁለት ሰዓታት ያህል ሦስት ጊዜ ጥብቅ ፍተሻ አደረጉ። ግን ምንም ሊያገኙ አልቻሉም። ቀጥሎም ሁለት መቃብሩን የሚጠብቁ ሙስሊሞችን በማምጣት ልክ የቀድሞዎቹ አይሁድ የጌታን መቃብር እንዳተሙ እነርሱም መቃብሩን ዘግተው በሰም እንዲያትሙት አደረጉ።

ይህንም ተከትሎ በቦታው የነበሩ አረብ ክርስቲያኖች ቱርክ እስራኤልን በተቆጣጠረችበት በ13ኛው ክፍለ ዘመን ከቤተ ክርስቲያን ውጭ በየትኛውም ቦታ ቢሆን እንዳይዘምሩ የተከለከሉትን ቆየት ያለ ዝማሬ በኅብረት ከፍ ባለ ድምፅ መዘመር ጀመሩ። መዝሙሩም:-

“እኛ ክርስቲያኖች ነን። ለብዙ መቶ ክፍለ ዘመናትም ክርስቲያኖች ነበርን። እስከ ዘላለምም እንዲሁ እንሆናለን፣ አሜን!” የሚል ነበር።

እኩለ ቀንም ሲሆን የግሪኩና የአርሜንያው ፓትርያርክ፣ የግብፁ ሜትሮፖሊታንት እንዲሁም ቀሳውስት እና ዲያቆናት ወደ ታተመው የክርስቶስ መቃብር መጡ። ከብዙ ጸሎት እና ምስጋናም በኋላ የታተመው የክርስቶስ መቃብር እንዲከፈት አደረጉ። ፓትርያርኩም ሞጣህቱን ብቻ አስቀርተው ከላይ የለበሱትን ልብሰ ተክህኖ በማውለቅ በክርስቶስ የዕድሜ ቁጥር ልክ ሦስት 33 ያልበሩ ሻማዎችን ይዘው ጨለማ ወደ ነበረው መቃብር ገቡ። ምእመናኑም ከውጭ ሆነው በአንድ ድምፅ ኪርዬሌይሶን (አቤቱ ይቅር በለን) እያሉ በመዘመር ይጠባበቁ ጀመር። ወደ ቅዱሱ መቃብር ገብተው የነበሩትም የግሪኩ ፓትርያርክ ያን በሰው ያልተቀጣጠለ እና የክርሰ‍ቶስን የትንሣኤ ብርሃን የሚያበሥረውን አምላካዊ እሳት ይዘው ብቅ አሉ። ይህን ጊዜ ጎልጎታ በእልልታ ተሞላች የቤተ ክርስቲያኑም ደወል በሐሴት ይደወል ጀመር።

ትንሣኤከ ለእለ አመነ
ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ

እንኳን አደረሰን!!!

https://youtu.be/OGyzCFZO0VY?si=2ptLkHV_WD5rYRvY

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com
111👍3🥰3
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፥
በአማን ተንሥአ፤
2215🙏17😢9👍2
+++ ቶማስን አድርገኝ +++

ሞት ያጠላበት ነው ኑሮዬ ዘወትር
ገና አልተከበረም ትንሣኤህ እኔ ጋር
ስቃይህን ዘንግቷል ብኩን ኅሊናዬ
ደምህ እንዳልዋጀው ነው ነገረ ሥራዬ
መነሣትህን ያዩ ተነሥቷል ቢሉኝም
እኔ ዓይነ ስውሩ ምንም አላየሁም

ይኸው ነው ሕይወቴ ምንም እንዳላየ
በትንሣኤው ብርሃን እንዳልተጎበኘ

እባክህ ጌታዬ!

ቶማስን አድርገኝ እጆችህን ልዳብስ
አምኜ ለመኖር" የእኔም ተራ ይድረስ
ጣቶቼ ይንኩና የጎን ውግታትህን
ስዘከረው ልኑር ሕማም ትንሣኤህን

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com
232❤‍🔥16🙏15😢7
ሥጋዊ ኃይልና ጉልበት በሕመም ይደክማል። ጽኑዕ ደዌ ብርቱ ክንድን ልምሾ ያደርጋል። የታጠከው የጉብዝና ኃይል በእድሜህ አመሻሽ ይፈታል። ደዌ የማያደክመው እድሜ የማያጠፋው ጉልበት "ኃይለ እግዚአብሔር" ነው። ብዙ ድንቅ ያደረጉና የዓለምን አስፈሪ ነገሮች የታገሉ ታላላቅ ቅዱሳንን ተመልከት። እንደ ቅዱስ ቂርቆስ ያሉ ሰውነታቸው ያልጸና ሕፃናትን፣ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ በራስ ምታት፣ በጎን ውጋትና በቁስል የሚሰቃዩ የደዌ ሰዎችን፣ ከአናብስት ጋር እንደ ተፋለመው ቅዱስ አግናጥዮስ ያሉ አረጋውያንን ታያለህ። የተሻለ እንዳገለግል ይህ ደዌ ቢርቅልኝ፣ ጉልበቴ ቢመለስልኝ አትበል። የሰውነትህ ድካም በአንተ የሚሠራውን የእግዚአብሔርን ኃይል ሊያስቆመው አይችልም። ዓለምን በወንጌል ያጠመቀው እና ከሁሉ ይልቅ የደከመው ሐዋርያ ታማሚው ጳውሎስ መሆኑን አትርሳ።

+++ "አቤቱ ጕልበቴ ሆይ፥ እወድድሃለሁ" መዝ 18፥1 +++

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://t.me/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
197🙏13👍6🥰5🔥1
+++ "በስሙ ጥራው" +++

ሰይጣን የሰው ልጆችን የክፋት እስረኛ ከሚያደርግበት ዘዴው አንዱ ኃጢአትን "ኃጢአት" ብለን እንዳንጠራት ማለሳለስ ነው። ከዚያ ይልቅ መልካም በሚመስልና ቢሰማም ብዙ በማይቆረቁር ስም እንድንጠራው ያደርገናል። ለምሳሌ በትዳር ሳይወሰኑ እንዲሁ ከአገኙት ጋር በዝሙት መውደቅ "ነጻ ፍቅር" ("free love")፣ በሚስት እና በባል ላይ መሄድ ደግሞ "ባለጉዳይ"ነት (affair) ተሰኝተዋል። ይህን የሚያደርጉትም ኃጢአቱን ያለ ምንም መሳቀቅ መሥራት እንዲችሉ ስሙን ያሳምሩታል።

ሰው የትኛውንም ኃጢአት ከመስራቱ በፊት ኃጢአቱን የሚጠራበት ስም ይለያል። ኃጢአትን የምንጀምረው በጎ ዓላማ እና ጥሩ ስም ያለው አስመስለን ነው። የሚሰክረው ከስካሩ በፊት ምን ልታደርግ ነው? ቢሉት "ልዝናና ነው" ይላል። የሚሳደበውና የሚራገመውም ከስድቡ በፊት ምን ልታደርግ ነው? ቢሉት "ልመክር" ወይም "እርማት ልሰጥ ነው" ይላል፤ ሌሎቹንም እንዲሁ። ጌታችን በመሰለው የጠፋው ልጅ ምሳሌ ላይ ያለውን ልጅ ከአባቱ ቤት ከመውጣቱ በፊት "ለምን ንብረት ተካፍለህ ከአባትህ ቤት ርቀህ ትሄዳለህ?" ብለን ብንጠይቀው፣ "ዓለምን ለማየት" ይላል እንጂ "ኃጢአት ስላማረኝ" እንደማይል ጥርጥር የለውም።

ከኃጢአት መራቅ ትፈልጋለህ? እንግዲያስ ልታደርግ ያሰብከውን ክፋት በስሙ ጥራው። አታድበስብስ፣ አታለስልስ፤ በቃ ኃጢአት ነው። ስለዚህ አትጀምረው። ገብተኽበትም እንደሆነ ስሙን እያሽሞነሞንክ ራስህን አትዋሸው። በደል እንደ ሆነ አምነህ በትክክለኛው ስሙ እስክትጠራውና እስክትጋፈጠው ድረስ መድኃኒት የለህም። መዝሙረኛው ዳዊት በኦርዮ ሚስት ተሰነካክሎ ከወደቀ በኋላ ዳግመኛ የተነሣው "አንተን ብቻ በደልሁ፥ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ" ብሎ መጸለይ በጀመረ ጊዜ ነው።(መዝ 51፥4)

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ሐምሌ 2፣ 2014 ዓ.ም.
ሻሸመኔ

https://t.me/Dnabel
123🙏40👍7
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፣
በአማን ተንሥአ፤

ሰላም እንዴት አረፈዳችሁ፣

የዛሬው ክፍል ሰባት ትምህርታችን ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ላይ ይጀምራል። በዛሬው ትምህርታችን ከምዕራፍ አምስት እስከ አሥር ያሉትን ንባቦች እንድንረዳ የሚያደርገንን የሊቀ ካህናትነትን ትርጉም፣ የኦሪቱን የመሥዋዕቱን ጉድለት፣ የሐዲስ ኪዳኑን መሥዋዕት ፍጹምነት በስፋት የምናነሣ ይሆናል። እንደ ተለመደው ምዕራፍ ስድስትን አንብበን እንገናኝ።

መገናኛችን:

Telegram: https://t.me/Dnabel

Tiktok: https://www.tiktok.com/@dnabelkassahun?_r=1&_t=ZS-94eT9fhoVaX


የZoom አማራጭ: https://us06web.zoom.us/j/86200559976?pwd=oIBuOuJyqdjlNTbXs8SdoVirTUw67U.1
61
Live stream scheduled for
Live stream started
Live stream finished (1 hour)
"ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል" ማቴ 28፥7

ጌታችን ሞትን ድል አድርጎ ከተነሣ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ ብዙ እና ጥቂት ሆነው ሳለ በተለያየ ጊዜ ራሱን ገልጦ አሳይቷቸዋል። አሁን ደግሞ አስቀድሞ በሴቶች በኩል "ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል" ብሎ ያስነገረውን ትንቢት ሊፈጽም፣ ዓሣ ለማጥመድ ወደ ገሊላ ባሕር ለወረዱ ለጴጥሮስና ለስድስቱ ወንድሞቹ የተገለጠበትን ሦስተኛ ታሪክ ዮሐንስ ይጽፍልናል።(ዮሐ 21፥1)

ቅዱስ ጴጥሮስ "ሰላም ለእናንተ ይሁን" የሚለውን የትንሣኤውን ጌታ ድምጽ ከሰማ ፣ የተጠራጠረው ቶማስ እጁን በጎኖቹ አግብቶ "ጌታዬ አምላኬ" ብሎ ሲያምን ከተመለከተ በኋላ "ዓሣ ላጠምድ እሄዳለሁ" ብሎ ሲናገር እናገኘዋለን።(ዮሐ 21፥3) ክርስቶስ ተላልፎ በተሰጠበት በሐሙስ ምሽት ከእሳት ዳር ተቀምጦ ያደረገውን ሊረሳውና ራሱን ይቅር ሊል ስላልቻለ፣ ጌታው ቀድሞ የሰጠውን የወንጌል መረብ ተወና የዓሣውን መረብ ጨብጦ ወደ ገሊላ ባሕር ሮጠ።(ማቴ 4፥19) በኃጢአት ምክንያት የተሰማው ኃፍረትና መሸማቀቅ ሐዋርያነቱን ትቶ በድሮ ማንነቱ ውስጥ ራሱን እንዲደብቅ አደረገው። የካደን ማን ለምስክርነት ይፈልገዋል በሚል ዓይነት ስሜት ለወንድሞቹ "ዓሣ ላጠምድ እሄዳለሁ" አላቸው።

ደስ የሚለው ነገር ግን ይህን አስቀድሞ የሚያውቅ ይቅር ባይ አምላኩ ጴጥሮስን "በገሊላ ቀድሞት ነበር"። በበደሉ ተሸማቆ የተወውን ሐዋርያነት ሥልጣን በፍቅሩ መማለጃነት መልሶ ሊሰጠው፣ አይገባኝም ብሎ ያስቀመጠውን የወንጌል መረብ ዳግመኛ ሊያሲዘው በገሊላ ባሕር ዳር ቀደመው። እኛም አንድ ኃጢአት ይኖረናል። መርሳት ያልቻልነው፣ ንስሐ እንኳን ብንገባበት ራሳችንን ይቅር ለማለት የተቸገርንበት፣ "ከዚህ በኋላማ..." እያሰኘ የድሮ መረብ አስይዞ ወደ ገሊላ የሚመልስ አንድ በደል ይኖረናል። ነገር ግን ጌታ ለቅዱስ ጴጥሮስ እንዳደረገው ለእኛም እንዲሁ ያደርጋል። ከባሕሩ ዳር ይጠብቀናል፣ "ትወደኛለህ" ብሎ ይጠይቀናል፣ ከዚያ በማይለወጥ ፍቅሩ ወልውሎ ሰንግሎ አፍረን ወደ ሸሸነው መንፈሳዊነት ይመልሰናል።

+++ ጌታችን በገሊላ ይቀድመናል! +++

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ግንቦት 6/ 2015 ዓ.ም.
አዲስ አበባ
3204🥰17🙏17👍5🔥4
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፣
በአማን ተንሥአ!

ዛሬ የዕብራውያን መልእክት ሐተታ ትምህርት አይኖረንም።

ቸር ያገናኘን።
31🙏6
Audio
ያለፈው ሳምንት ክፍል 7 ትምህርታችን እነሆ!
69👍8🥰4👏1🙏1
+++ ‹‹ወንጌሉን ተወው!›› +++

የትሕርምት ሕይወትን በሚመለከት በጻፋቸው አያሌ ድርሰቶቹ የምናውቀው ሶርያዊው አባት ማር ይስሐቅ ነነዌ በተባለችው አገር ሊቀ ጳጳስ ሆኖ ተሹሞ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በመንበረ ጵጵስናው ግን የቆየው ለአምስት ወራት ያህል ብቻ ነው፡፡ በቅዱሱ ሕይወት ዙሪያ ጥናት ያደረጉ ጥቂት የማይባሉ የነገረ አበው ሊቃውንት ‹ለምን በአጭር ጊዜ ውስጥ መንበረ ጵጵስናውን ትቶ ሄደ?› ለሚለው ጥያቄ መልስ እንዳላገኙ ይገልጻሉ፡፡

ነገር ግን ከወደ ሶርያ የሚነገር አንድ ታሪክ አለ፡፡ ይኸውም በአንድ ወቅት በብድር ምክንያት መስማማት ያልቻሉ ሁለት ክርስቲያኖች ይዳኛቸው ዘንድ ወደ ማር ይስሐቅ ይመጣሉ፡፡ ገንዘብ አበደራዊው ሰው እየተበሳጨ ተበዳሪው መክፈል ካለበት ጊዜ አሳልፎ ጭማሪ ቀናት እየጠየቀው በመሆኑ፣ አሁን የማይከፍለው ከሆነ ጉዳዩን ወደ ሸንጎ እንደሚወስደው ለቅዱሱ ተናገረ፡፡ ማር ይስሐቅም ከወንጌል ትምህርት በመጥቀስ ለወንድሙ እንዲያዝንለትና ተጨማሪ ቀናት በመስጠት እንዲታገሰው ተማጸነው፡፡ አበዳሪው ግን በሊቀ ጳጳሱ ንግግር እየተናደደ ‹አሁን ከዚህ ውስጥ ወንጌሉን አውጣው!› ሲል መለሰ፡፡ የነነዌው ሊቀ ጳጳስ ማር ይስሐቅም በዚህ ሰው መልስ በጣም በማዘን ‹‹በወንጌል የተነገረውን የጌታን ትዕዛዝ ስነግርህ ሰምተህ ካልተቀበልክ፣ ታዲያ የእኔ እዚህ መሆን ምን ይጠቅማል?!›› አለው፡፡ ከዚያ ጊዜም በኋላ የብቸኝነትና የጽሙናን ሕይወት ፍለጋ መንበረ ጵጵስናውን ትቶ ወደ አስቄጥስ በረሃ ገብቷል፡፡

ከራሳችን ሐሳብ ጋር የሚስማማውን ብቻ ሳይሆን የማይስማማውንም የወንጌል ትምህርት ሰምቶ ለመቀበል ስንቶቻችን ዝግጁዎች ነን? ልክ እንደዚህ አበዳሪ ጆሮዎቻችን ለወንጌል ትምህርት ክፍት የማይሆኑባቸው ጊዜያቶች የሉም? ‹እዚህ ላይ ወንጌሉን ተወው!›፣ ‹አሁን ወንጌልን መጥቀስ ምን አመጣው!›፣ እያልን ሳግና ቁጣ ተናንቆን የጮኽንባቸውን ሁኔታዎች አታስታውሱም?

ከራሳችን ጠባይና አኗኗር ጋር ብቻ የሚስማማውን የወንጌል ክፍል መርጠን እየተቀበልን ሌላውን ግን አትጥቀሱብኝ የምንል ከሆነ፣ ‹በቅዱስ ወንጌልህ ቃል አምናለሁ› ብለን እንዴት ልንናገር እንችላለን?! ጌታችን ወደ ጌርጌሴኖን አገር መጥቶ በመቃብር ስፍራ ይኖሩ የነበሩ ሁለት አጋንንት ያደሩባቸውን ሰዎች ፈውሶ ነበር፡፡ ከእነዚያም ሰዎች ላይ የወጡት አጋንንት ወደ እሪያዎቹ ስለ ገቡ፣ መንጋውን አጣድፈው ከውኃ ሰጥመው እንዲሞቱ አደረጓቸው፡፡ ታዲያ በከተማው የሚኖሩ ሰዎች ይህን የክርስቶስን ሥራ በሰሙ ጊዜ ወዲያው እርሱ ወዳለበት መጥተው ‹ከአገራቸው እንዲሄድላቸው ለመኑት›፡፡ በጣም ይገርማል፤ በዓለም ውስጥ ተነጻጻሪ የማይገኝላት የከበረችውን ነፍስ ከአጋንንት፡ እስራት ማላቀቁ ቢያስደንቃቸውም፣ የእሪያዎቹ መንጋው መጥፋት ግን የበለጠ ስላሳሳቸው እንዲሄድላቸው ለመኑት፡፡(ማቴ 8፡34) ፈውሱ ገንዘባቸውን ከሚነካባቸው ይልቅ የድኅነታቸውን አምላክ አባርረው ከነእስራታቸው መኖር ምርጫቸው ሆነ፡፡ ለእኛ የወንጌል መልካምነት የእኛ የሆኑት ገንዘቦቻችንን፣ ክብራችንን፣ የበላይነታችንን እስካልነካብን ድረስ ነው፡፡ ወንጌሉ ለእኛ እንዲመች እንጂ፣ የእኛ ሕይወት ለወንጌሉ የተመቸ እንዲሆን አንፈልግም፡፡ ይህ ካልሆነ ግን እንደ ጌርጌሴኖን ሰዎች ከፊታችን ዘወር እንዲያደርጉልን ‹ወንጌሉን ተዉት!› እያልን በቁጣም ይሁን በልመና መናገራችን የማይቀር ነው፡፡

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com
አዲስ አበባ
176🙏30💔10👍4🥰4🔥2👏2
ሰው እግዚአብሔርን እንጂ፣ እግዚአብሔር ሰውን አይሸሽም!
275🙏21❤‍🔥16😢13👍5💯1
የእግዚአብሔር ሰው ሰሎሞን ለአምላኩ ሕንፃ መቅደስን ሊያንጽ በተነሣ ጊዜ ፤ "በጥበብና በማስተዋል በብልሃትም የተሞላ" የናሱን ሠራተኛ ኪራምን ከጢሮስ አስመጥቶ ነበር። ከዚህም ጥበበኛ ጋር ሆኖ እጅግ አስደናቂ የሆነውን መቅደስ በታላቅ ጥንቃቄ አንጿል። በእውነት ይህን ሰሎሞን ያሳነጸውን ውብ መቅደስ ማየት ምንኛ ያጓጓ ይሆን? በእርግጥም መቅደሱንና የመሥዋዕቱን ሥርዓት የተመለከተች ንግሥተ አዜብ ማክዳ "ነፍስ አልቀረላትም" ነበር (1ኛ ነገ 10:5)።

ሆኖም ግን እግዚአብሔር በነቢዩ ኢሳይያስ አድሮ "ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ ለእኔ ምን ዓይነት ቤት ትሠራላችሁ?" ብሎ መጠየቁ አልቀረም (ኢሳ 66:48)። ለጊዜው በረድኤት የሚያድርበትን መቅደስ ንጉሥ ሰሎሞን ውብ አድርጎ ቢያንጽለትም ፤ በኋላ ግን የሰውን ልጆች ለመቤዠት በአካል የሚያድርበትን ሕያው መቅደስ ማንም ማዘጋጀት አልቻለም ነበር። ስለዚህም "ልዑል የሰው እጅ በሠራችው አይኖርም" ተብሎ ተጻፈ (ሐዋ 7:50)። በመሆኑም መቅደሱን ላነጹ ለሰሎሞን እና ለኪራም ጥበብን የሰጠው ጥበበኛ "ለራሱን ቤት ሊሠራ ፣ሰባት ምሰሶዎችንም ሊያቆም" ፈቃዱ ሆነ። የመቅደሱንም መሠረት እንቁ አደረገ። ቤቱንም እጅግ በከበሩ ድንጊያዎች አነጸ።

ይህች በአምላክ እጅ የታነጸች ፣እግዚአብሔር በረድኤት ሳይሆን በአካል የሚያድርባት ሕያው መቅደሱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። የተመሠረተችባቸውም አዕናቁ (እንቁዎች) ቅዱሳን ቤተሰቦቿ ናቸው። የታነጸችበትም የከበሩ ድንጊያዎች ንጽሕና ፣ቅድስና ናቸው።

"ይህች ዓለም አይቶ የማያውቃት በተስፋ ትጠበቅ የነበረችው ድንቅ አማናዊት መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህች ምድር ላይ የታየችው በዛሬው ቀን ነበር"

ኪራም ያነጸው የሰሎሞንን መቅደስ መጎብኘት "ነፍስ የማያስቀር" ፣ልብን በሐሴት የሚሞላ ከሆነ ፤ በእግዚአብሔር እጅ የታነጸች ፣የአምላክ ጥበብ የፈሰሰባት እውነተኛ መቅደሱን የእመቤታችንን መወለድ የማየትና የመስማት የደስታ ጥጉ ምን ያህል ይሆን?

እንኳን ደስታን ወደ ዓለም ይዞ ለመጣ ተናፋቂው ለድንግል ማርያም ልደት አደረሳችሁ!!!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com
196🙏23🥰10🔥1
ዛሬ የትዕግስት ምሳሌ የሆነ፣ ንጹሕ ሆኖ እነዚያን ሁሉ መከራዎች በመቀበሉ ያለ በደሉ የተሰቃየ የክርስቶስ ምሳሌ ለመሆን የበቃ የጻድቁ አባታችን የኢዮብ የዕረፍቱ መታሰቢያ ቀን ናት። በረከቱ በሁላችን ትደርብን!!!
320🙏60🥰18🔥1
ከመላእክት ጋር አብረን የምንዘምርበትን የዜማ ሥርዓት ለሠራልን፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ የወረደውን የምስጋና ማዕድ ለእኛ እንደሚገባ አድርጎ ላደረሰ ታማኝ መጋቢ፣ ለዘማሪው፣ ለተርጓሚው፣ ለባለ ቅኔው ለቅዱስ ያሬድ ማኅሌታይ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን።

-የአንደበት አመጽ ጸጋን አስገፍፎ እንዴት የመልአክነትን ክብር እንደሚያሳጣ በሳጥናኤል አየን!

-የአንደበት ፍሬ እንዴት እንደሚያከብር እና ምድራዊ መልአክ እንደሚያደርግ ደግሞ በቅዱስ ያሬድ ማኅሌታይ ተመለከትን!

አቤቱ የያሬድን ልሳን ስጠኝ!

ዲያቆን አቤል ካሣሁን

https://t.me/Dnabel
267🙏41🥰10👍6
"በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን" ኤፌ 2፥6-7

እንኳን ለበዓለ ዕርገት በሰላም አደረሰን!
272🙏45🥰37🔥5