Dn Abel Kassahun Mekuria
18.6K subscribers
660 photos
61 videos
1 file
973 links
ይህ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የተለያዩ ትምህርቶችን የሚያገኙበት በባለቤቱ የተከፈተ ቻነል ነው።

ይወዳጁን

ለፌስቡክ ገጽ
https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12?mibextid=ZbWKwL

ለyoutube
https://youtu.be/s6Cn-jMYjrk?si=Tw7lXr62xkGQtL9_

ለInstagram
https://www.instagram.com/abelkassahunm?igsh=OW
Download Telegram
ቅዱስ ጳውሎስ መጽሐፍን ከኢትዮጵያ ውጭ የት ያገኙታል?
❤86👍12
“መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር ያድኃነነ እምጸር” - “መስቀል ከሁሉ ነገር በላይ ነው፤ ከጠላትም ያድነናል”

ቅዱስ ያሬድ

እንኳን አደረሳችሁ!
❤114🙏6🥰4
ቅዱስ ጳውሎስ፣ ገጽ 100

ነገረ መስቀሉን ለዘላለም በኅሊናችን ያትምልን!

እንኳን አደረሳችሁ!
❤189🙏16👍6😢4❤‍🔥3💔3🔥2🥰2
"በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ የተመረጥሽ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ አሁንም ልጅሽን እለዋለሁ...
ለቤተ መቅደስህ ተክል ያደረግኸኝ አቤቱ ሆይ፤ የውጭ ተክል አታድርገኝ... የመጻሕፍት መጀመሪያ የምትሆን ኦሪት ደመና የምትጋርደኝ፣ ከቅዱስ ወንጌል ፈሳሽ የምጠጣ ከጎንህ ከፈሰሰው ደም የምረካ ልሁን፡፡ በእናትህ በድንግል ጸሎት የሃይማኖት አበባ ላብብ፣ የጽድቅ ፍሬን ላፍራ። ከቅዱሳንህ ሐዋርያትም ከቃላቸው ፍሬ የተነሣ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ የተባረከ የወይን ቦታ ልባል። የጽድቅን ፍሬ የሚያስቀረውንም የኃጢአት እሾህ ጠምዝዘው፤ ከደጁም አሜከላውን አረሙንም ሙጃውንም ንቀለው፡፡ አቤቱ ከእኔም አርቀው"

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

የውጭው ተክል አርዮስን ለማውገዝ ሃይማኖታቸው የቀና ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንቱ ሊቃውንት ለተሰበሰቡበት "የብዙኃን ማርያም" በዓል እንኳን በሰላም አደረሰን!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://t.me/Dnabel
❤190🙏19🥰3👏2
እግዚአብሔር አዋቂዎች የሆኑ እና በሐሳብ የሚራቀቁ ሰዎች ብቻ የሚያውቁት ልዑል አምላክ አይደለም። እርሱ በሕፃናትም ልክ የሚነገርለት እና ልጆችም አውቀው እንዲያመልኩት ለእነርሱ ኅሊና ራሱን ቅርብ የሚያደርግ ትሑት፣ አምላከ ሕፃናትም ጭምር ነው። በወንጌል ክርስቶስ እንዲዳስሳቸው እና እጁን ጭኖ እንዲባርካቸው ሕፃናቶቻቸውን ወደ ጌታችን የሚያመጡ ወላጆች እንደ ነበሩ ተጽፏል።(ሉቃ 18፥15)

“ሕፃናት ጌታን ይፈልጉታል። እነርሱም ለጌታ ያስፈልጉታል”

የሕፃናት እድገት ስፔሻሊስቷ መሳይት ውበት ልጆቻችንን ለእግዚአብሔር ቅርብ የምናደርግበት እና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የምናስተዋውቅበትን ሥራ “ይድረስ ለእግዚአብሔር” ብላ ይዛ መጥታለች። “ይድረስ ለእግዚአብሔር” የተደራስያኑን እድሜያቸውን እና የአእምሮ እድገታቸውን ባገናዘበ መንገድ የተሰናዳ ሕፃናቱን እያጫወተ የሚያስተምር ጥሩ መጽሐፍ ነው። በአዲሱ ዓመት ልጅዎን ለእግዚአብሔር የማድረግ እቅድ ካልዎ /የለኝም ማለት አይቻልም :) / ይህ የመሳይት መጽሐፍ ለዚህ ተግባር ትልቅ አስተዋጽዎ አለው።
❤90👍27🥰8🙏4
እግዚአብሔር ሁልጊዜ ወደ መከራ እንዳትገባ አያደርግም። አንዳንድ ጊዜ በወጀብ ውስጥ መንገድ ያዘጋጅልሃል። ግፊው በሚበዛበት ዐውሎ ነፋስ እያለፍህ ተፍገምግመህ እንዳትወድቅ ጉልበትህን ያጸናል፤ ኃይልን ያስታጥቅሃል። እንዲህ እያደረገ በመንፈስ ያጎለምስሃል።

እግዚአብሔር ዳንኤልን በአናባስት ጉድጓድ ከመጣል፣ ሠለስቱ ደቂቅን ወደ እቶን እሳት ከመግባት፣ ጳውሎስና ሲላስን ወደ ወኅኒ ከመውረድ ሊያድናቸው ይችል ነበር። ይሁን እንጂ እንዲህ አላደረገም። አምላካችን ፈተና ካለባቸው ቦታዎች ሁሉ ሊያወጣን ቃል አልገባምና። ነገር ግን በመከራ ጊዜያችን ሁሉ ከእኛ እንደማይለይና በእውነት ይዘነውም እንደ ሆነ በድል ነሺነት እናጠናቅቅ ዘንድ እንደሚረዳን ቃሉን ሰጥቶናል።

የጌታ እናት እመቤታችን የተወደደ ልጇን ይዛ በግብጽ በረሃ እንደ ወፍ ከተንከራተተች በኋላ ሕፃኑን የሚፈልገው ክፉ ሄሮድስ ሲሞት ተመልሳ ወደ ገሊላ ገብታለች። እንደ ድንግል ጌታን በመሐል እጅህ ብትታቀፍ እንኳን ግብጽ መውረድ አይቀርልህም። ይሁን እንጂ የመጣብህን መከራ ድል ነሥተህ ወደ ገሊላ መመለስህም እርግጥ ነው።

"ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል"
1ኛ ቆሮ 10፥13

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com
አዲስ አበባ

https://t.me/Dnabel
❤140🙏12👍7❤‍🔥1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ወድቆ መነሣት - ብዙ ጠባሳ እንዳለበት ወታደር መሆን ነው!
❤119🙏15👍1🔥1
ጡቶችዋ የድንግልናን ወተት ማመንጨት በጀመሩ ጊዜ በክንዷ ደግፋ የምታጠባው ሕፃን፣ ፀሐይን እያወጣ ዝናምን እያዘነበ ፍጥረቱን የሚመግብ አምላክ መሆኑን ታውቅ ነበር። በእርሷ ማኅጸን በዝምታ ያደረው ጽንስ፣ በሰማይ ኃይላት "ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ" እየተባለ የመድረኩ መሠረት እስኪናወጽ ድረስ በታላቅ ድምፅ የሚመሰገን መሆኑ አልተሰወራትም።(ኢሳ 6፥4) ስለዚህም ራሷን ወደ ሆዷ ዘንበል በማድረግ የመላእክቱን ቅዳሴ ታደምጥ ነበር።

ድንግል ወደ እርሷ ማኅጸን የገባው "የሚሳነው ነገር የሌለ የልዑል ልጅ" እንደ ሆነ ብታውቅም ሁሉን አልጋ በአልጋ እንዲያደርግላት ግን አልተማጸነችውም። የልጇን ሁሉን ቻይነት ወልደው በሚያሳድጉ ሁሉ ከሚደርሰው የእናትነት ጭንቅ ማምለጫ አላደረገችውም። ከጡቶቿ ወተት ፈልጎ እንደ ሕፃናት ሲያለቅስ "አምላክ አይደል አይርበውም" ብላ ቸል አላለችም። ክፉው ሄሮድስ ሊገድለው በፈለገ ጊዜ "የአሸናፊ የእግዚአብሔር እናቱ" እመቤታችን ድል ነሺነቱ ወዴት አለ? አላለችም። ስለ ሄሮድስ ሠራዊት አስጨናቂነት ጉንጮቿ እስኪቃጠሉ ድረስ አነባች፣ የበኩር ልጇንም አንዴ በጀባዋ አንዴ በጎንዋ እያዘለች የግብጽን ተራሮች እንደ ወፍ ዞረች እንጂ።

በእነዚያ የረሃብ ጊዜያት ድንግል ከሃሊ ልጇ ከሰማይ መና እንዲያዘንምላት ወይም ድንጋዩን ዳቦ እንዲያደርግላት ጠይቃ አልተፈታተነችውም። እስራኤላውያን በበረሃ ጉዟቸው ወቅት የሚከተላቸው (ይዘው የሚጓዙት) ዓለት ነበራቸው። እነርሱም በተጠሙ ጊዜ የሚጠጣ የሚያገኙት ከዚያ ዓለት ከሚፈልቀው ውኃ ነበር። ቅዱስ ጳውሎስም ይህን ታሪክ በማስታወስ በበረሃ ውኃ ያፈልቅላቸው የነበረው ዓለት በምሥጢር የክርስቶስ ምሳሌ መሆኑን ሲናገር "ያም ዓለት ክርስቶስ ነበረ" ይላል።(1ኛ ቆሮ 10፥3) እመቤታችን የማይቋረጥ የሕይወት ውኃ የሚፈልቅበትን ይህን መንፈሳዊ ዓለት ይዛ ስትሰደድ አንድ ቀን ስለ ጥሟ አላማረረችውም። ራሱን በፈቃዱ ባዶ ላደረገው አምላኳ ከሁሉ ይልቅ በሥጋ ባዶ መሆንን በደስታ ለመቀበል የተዘጋጀ ቆራጥ ኅሊና ነበራት። ስለዚህም በልጇ ምክንያት ከደረሰባት መከራ በአንዱ እንኳን አላማረረችም።

+++ ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ +++

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
❤114🥰37🙏5🔥1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ማርያም ለጴጥሮስ ወለጳውሎስ ጽላሎቱ ሰበን
ወሐዋርያት መላእክተ በሰማይ ኮነኑ

"ስለዚህም ጴጥሮስ ሲያልፍ ጥላውም ቢሆን ከእነርሱ አንዱን ይጋርድ ዘንድ ድውያንን ወደ አደባባይ አውጥተው በአልጋና በወሰካ ያኖሩአቸው ነበር" ሐዋ 5፥15

"እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር፤ ስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውዮች ይወስዱ ነበር" ሐዋ 19፥11
❤164🥰10🙏8
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
“ኢየሱስ ክርስቶስ ሐናንያን ሳውል ወዳለበት የይሁዳ ቤት ከመላኩ በፊት መጀመሪያ ስለ ተጠማቂው ማንነት በራእይ ተገልጦ በዝርዝር አስረድቶታል፡፡ እንዲያውም ክርስቶስ ማሳደዱን እንዲተው ከሳውል ጋር ካደረገው ንግግር ይልቅ የተመለሰውን ሳውል አጥምቀው ለማለት ከሐናንያ ጋር የነበረው ምልልስ ይረዝማል፡፡ አንዳንዴ እግዚአብሔር ክፉ አድራጊዎችን ከመመለስ በላይ እንደ ተለወጡ በቤተ ክርስቲያን ላለነው ለእኛ ማሳመኑ ብዙ ጊዜ ሊወስድበት ይችላል፡፡ እረኛችን መድኃኔዓለም የጠፉ ልጆቹን እስኪያገኛቸው መፈለግ ብቻ ሳይሆን፣ ከመጡ በኋላ ደግሞ እስክንቀበላቸው ድረስ ውስጥ ያለነውን ማግባባትም የዘወትር ሥራው ነው፡፡”

ቅዱስ ጳውሎስ፣ ገጽ 134

ምስል @kidist_feseha @maraki_girma
❤176🙏15🥰9🔥4
ሰላም የችግሮች አለመኖር ሳይሆን በፈተናዎች ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር የመሆን ውጤት ነው።

እግዚአብሔር የሚሰጠውን ሰላም የትኛውም ኃይል ሊወስደው አይችልም!
❤276🙏20👍15🥰2😁1😭1
“ቅዱስ ጳውሎስ” ወደ ድሬ መንገድ ጀምሯል። የፊታችን እሑድ 9:00 ሰዓት ላይ በሳ/ደ/ኃ/ ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት አዳራሽ እንገናኝ።

ኑ የጳውሎስ የፍቅሩ ማኅበርተኞች እንሁን!
❤124🥰21🤷‍♂1😁1🌚1
+++ ‹‹በእግዚአብሔር ፈንታ›› +++

የአእምሮ ሕመም ሕክምና ይሰጥባቸው ከነበሩ ማዕከላት በአንዱ እንዲህ ሆነ፡፡ ነርሷ ሕመምተኛውን ‹‹አንተ ማን ነህ?›› ስትል ትጠይቀዋለች፡፡ እርሱም ‹‹ናፖሌዎን›› ነኝ ብሎ ይመልሳል፡፡ ‹‹ናፖሌዎን መሆንህን ማን ነገረህ?›› ብትለው ‹‹እግዚአብሔር ነዋ›› ሲል ፈርጠም ብሎ መለሰ፡፡ ይህን ጊዜ ከአጠገባቸው ሆኖ ምልልሱን ይሰማ የነበረ ሌላ ታካሚ ድንገት ጣልቃ ገብቶ ‹‹ኸረ እኔ አልነገርኩት›› አለ፡፡

ይህን ታሪክ ስትሰማ ፈገግ አላልህም? ‹ሰው ራሱን ‹‹እንደ እግዚአብሔር›› አድርጎ የሚቆጥረው አእምሮውን ሲታመም ብቻ ነው› ብለህስ አላሰብህም፡፡ እውነታው ግን ሌላ ነው፡፡ ጤነኛ አእምሮ እንዳለን የምናስብ ብዙዎቻችን ኑሯችን እና እንቅስቃሴያችንን ብንፈትሽ ነገረ ሥራችን ሁሉ ‹‹በአምላክ ፋንታ›› ነው፡፡ አፍ አውጥተን ‹‹እኔ እግዚአብሔር ነኝ›› አንበል እንጂ እንዲህ ከማለት የማይተናነስ ሥራ ግን እንሠራለን፡፡

ፍርድ የእግዚአብሔር ነው፡፡ እኛ ግን ወንድሞቻችን ላይ በመጨከን ስንት ጊዜ በክርስቶስ የፍርዱ ዙፋን ላይ ተቀመጥን፡፡ የሰውን ድካም ሳንረዳ ፈጥነን በመፍረድ ስንት ጊዜ ራሳችንን በእግዚአብሔር ቦታ አስገባን? እስኪ ዮሴፍን እናስበው፡፡ ወደ ግብጽ ባሪያ አድርገው በግፍ የሸጡት ወንድሞቹ ከአባታቸው ሞት በኋላ እርሱ ወደ ተሾመበት ግብጽ መምጣት በፈለጉ ጊዜ፣ የክፋታችንን ብድራት ያስከፍለናል ብለው ስለፈሩ ‹‹በደላችንን ተውልን›› ሲሉ መልእክተኛ ልከውበት ነበር፡፡ የዋሁ ዮሴፍም ይህንን ሲሰማ እያለቀሰ እንዲህ አላቸው ‹‹አትፍሩ፤ እኔ በእግዚአብሔር ፋንታ ነኝን?››፤ አይደለም ሳታውቀው ዐውቀኸው እንኳን በበደለህ ወገንህ ላይ ለመፍረድ ልብህ በከጀለህ ጊዜ ለራስህ የዮሴፍን ጥያቄ ጠይቀው፡፡ ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፋንታ ነኝን?›› (ዘፍ 50፡19)

ራሱን መምራት ያልቻለ ደካማ ሌላው ላይ በፍርድ ለመሠልጠን ሲሞክር ከማየት በላይ እግዚአብሔርን ምን የሚያሳዝን ነገር አለ?

ሁሉን የሚያውቅ እግዚአብሔር ነው፡፡ ነገር ግን የሁሉ ጥበብ መፍለቂያዎች እንደ ሆንን፣ ከእኛ የተሠወረ አንዳች እንደሌለ እያሰብን ‹‹አምላክ አምላክ የምንጫወት›› ጥቂቶች አይደለንም፡፡ የእኛ ጣት ያልገባበት ሁሉ የማይጥመንና ትክክል የማይመስለን፣ እኛ ካልመራን፣ የእኛ ቡራኬ ከሌለበት የምናራክስ፣ ‹‹አላውቅምን›› የማናውቅ፣ ብዙኃኑን እንደ ጨዋ (ምንም የማያውቅ) የምንቆጥር አያሌ ነን፡፡ የሚያሳዝነው ግን ዓለም በአንድ ወይም በጥቂት ሰው ፈቃድ ስላልተገነባች በአንድ ወይም በጥቂቶች ፈቃድ ብቻ ልትመራ አትችልም፡፡ ሁሉን በሁሉ ማድረግ የሚችለው ሁሉን የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡

‹‹ዕረፉ፤ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ ዕወቁ›› መዝ 46፡10

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com
ጥቅምት 15/ 2015 ዓ.ም.
❤166🥰8🔥5👍4👏2😢2
+++ "ጠባቡ በር" +++

ብዙ ቅዱሳን እጅግ አጥብቀው ይፈልጓታል። እርሷንም ለማግኘት ብዙ ዋጋ ይከፍላሉ። እስከ ደም ጠብታ ደርሰው ይጋደላሉ። ባገኙዋትም ጊዜ ውስጣቸው በጸጥታ ይሞላል። ሕዋሳቶቻቸውም እንደ አመዳይ የነጹ እንደ ባዘቶም የጠሩ ይሆናሉ። ይህች ቅዱሳኑ ብዙ የሚደክሙላትና ደጅ የሚጠኗት ጸጋ ማን ትሆን? በአጭር ቃል "ዝምታ" ትሰኛለች።

አንዳንድ ሰው "ንግግር ዋጋ ያለው እና የሚጠቅም ነገር ሆኖ ሳለ፣ ታዲያ ለምን ዝምታ ጥሩ እና የበጎ ሥራዎች ሁሉ ቁንጮ ተደርጎ ይወሰዳል?" ሲል ሊጠይቅ ይችላል። ለዚህ መልሱ ቀላል ነው። የሰው ልጅ በጣም በቀላሉና ብዙ ጊዜ የሚበድልበት ሕዋሱ አንደበቱ ነው። የትም ሳይጓዝ፣ ምንም ሳያይ፣ በጣምም ሳይደክም ባለበት ብቻ ጥቂት ተንቀሳቅሶ ትልቅ ጥፋት ሊያደርስ የሚችል በሰው ውስጥ ያለ ትንሽ ነገር ቢኖር ምላስ ነው። ይህ ስለሆነም አንደበት "ዝምታ" የሚባል ንቁ ጠባቂ፣ ጠንካራ ልጓም ያስፈልገዋል።

ሳይንሱ ሰው የንግግር ችሎታውን ማዳበር እንዲችል ብዙ እንዲናገር ያበረታታል። ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ርቱዕ ተናጋሪ ለመሆን ዝምታ ዓይነተኛ መንገድ መሆኑን ታስተምራለች። ቅዱስ ባስልዮስ ዘየዐቢ "በማይቋረጥ የዝምታ ልምምድ ውስጥ ካልተገባ በቀር መልካም ንግግር (ተናጋሪነት) አይገኝም" ይለናል። ቅዱስ ይሩማሲስም "የኋላ ንግግራችንን ማቅናት እንችል ዘንድ ከሁሉ በፊት ዝምታን እንማር" ሲል ይመክረናል። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙም ይህን ይለናል "ንግግራችን የዝምታ ያህል ጥቅም ያለው ይሆን ዘንድ እመኛለሁ... እንድናገር ግድ በተባልኩ ጊዜ የሚሰሙትን ወደ ጸጥታ በንግግር እና በዝምታም ጭምር እመራቸው ዘንድ ስለ "ዝምታ" ካልሆነ በቀር ስለ ሌላ ነገር አላወራሁም። ይህም ስለ ዝምታ ያለኝ የእኔ እይታ፣ ስለ ንግግርም ያለኝ የእኔ ፍልስፍና ነው"። በሥጋዊ ጥበብ የዐዋቂነት መገለጫው መናገርና ጥሩ ተሟጋች መሆን ሊሆን ይችላል። በመንፈሳዊው ዓለም ያሉ ጠበብት ግን ብዙ ሲያውቁ ብዙ የማይናገሩ በመሆን ይታወቃሉ። በጣም ሲራቀቁ ደግሞ ዝምታና ተመስጦ መገለጫቸው ይሆናል።

አንደበትን መግዛት ማለት የሥነልቡና ባለሙያዎች "Suppression" እንደሚሉት ዓይነት ስሜትን መጨቆን ወይም ማፈን አይደለም። አንደበትን በመቆጣጠርና ስሜትን በማፈን መካከል በጣም ሰፊ ልዩነት አለ። በውስጥ የሚቀጣጠለውን ፍትወት ከፍርሐት የተነሣ በንግግር ወይም በድርጊት መግለጥ ሳይቻል ሲቀር ስሜትን ማመቅ (Suppression) ይባላል። አንደበትን መግዛት ግን ምላስን ለበጎ ንግግር መለየት፣ ማንጻት ነው። በአጭሩ ያኛው Suppression ይህኛው ደግሞ purification ነው።

ዝምታ ራሳችንን የምናይበት ጥሩ መጽሔት(መስታወት) ነው። አብዛኛውን ሰዓት በወሬ ተጠምዶ የሚውል ሰው ራሱን የሚመለከትበት እድል አይኖረውም። በሌሎች ኃጢአት ሲፈርድ፣ ሲተችና ሲያማ ስለሚውል የራሱን ስህተትና ውድቀት ለማወቅ ይቸገራል። ቀኑን ሙሉ እንዲሁ ሲያወራ የሚውል ሰው የሚያሳዝነው ዝም አለማለቱ ብቻ ሳይሆን የሚጠቅም ነገር የማይናገር መሆኑም ጭምር ነው። ነገር ግን ማር ይስሐቅ እንደሚለው "አንድ ሰው ከሰዎች ጋር ብዙ ማውራት ባቆመ ጊዜ ወደ ራሱ ይመለሳል። በእግዚአብሔርም ፊት ምግባሩን ማቅናት ይጀምራል"።

የሥጋ አንደበታችንን መቆጣጠርና ዝም ማስባል ስንችል የነፍስ ጆሮአችን ንቁህ መሆን ይጀምራል። ስለዚህም ነፍሳችን ሳይሰለች ከልባችን ደጅ ቆሞ የሚያንኳኳውን የመልካሙን እረኛ ድምጽ ትሰማለች። ደጇንም ከፍታ ታስገባዋለች። ከእርሱም ጋር ለእራት ትሰየማለች።(ራእይ 3፥20) በእውነት ይህ እንደ ምን ያለ መታደል ነው? ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር "የዝምተኛ ሰው ጆሮ የእግዚአብሔርን ድንቆች ትሰማለች" ያለው ለዚህ ይሆን?!

ታዲያ ለብዙ ዘመናት ከልባችን ደጅ ቆሞ የሚንኳኳውን ትጉህ እረኛ ድምጹን ሰምተን ለማስገባት ለምን ዝም አላልንም? ራሳችንንስ ከሁከት እና ከከንቱ መለፍለፍ ስለ ምን አልጠበቅንም? አንደበትን መግታት ቀላል አይደለማ! በአንድ ወቅት ቅዱስ እንጦንስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብሎ ነበር :- "ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጠባቡ በር እንገባ ዘንድ አዝዞናል።አንደበትን ከኃጢአት መጠበቅ ካልሆነ በቀር ይህ ጠባብ በር ምንድር ነው? እንግዲያውስ ደካማ እና ክፉ የሆነውን ቃል እንዳያወጣ እየተጋደልን ለአንደበታችን ብርቱ ዘብ እናቁም"

በጠባቡ በር እንግባ!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
❤134🙏8👏4👍1🥰1
“ቅዱስ ጳውሎስ” እሑድ ጥቅምት 16 2018 ዓ. ም. በድሬደዋ ከተማ እጅግ ባማረ ሁኔታ ተመረቀ። በመርኃ ግብሩ ላይ መምህር ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ የመጽሐፍ ዳሰሳውን ያቀረቡ ሲሆን፣ ዘማሪት ሰላማዊት መላኩ ደግሞ በዝማሬው አገልግሎት አብራን ነበረች።

ይህን ምርቃት አስቦ በማቀድ እና ውብ አድርጎ በማሰናዳት የድሬ ቅርጫፍ የኢጃት ቤተሰቦች እንዲሁም የሳ/ደ/ኃ/ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ፍሬ ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ያልተሰሰተ ጉልበታቸውን ስላፈሰሱ እጅግ አድርገን እናመሰግናቸዋለን።

“ቅዱስ ጳውሎስን የጠራኸው ጥዑመ ስም ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ እኛንም በሰማያት በሚሆነው ሰርግህ ላይ ጥራን”

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
❤187🙏12🥰4👏3👍1