DevVoltz Technology company
509 subscribers
176 photos
4 videos
2 files
181 links
DEVVOLTZ TECHNOLOGY PLC is a software and technology company dedicated to building innovative digital solutions, empowering young talents, and transforming ideas into real-world products.

www.devvoltz.com
Download Telegram
1.ራስን ከሌሎች ላይ ማወዳደር


👉እያንዳንዱ developer በራሡ roadmap እንዲሁም የራሡ journey ላይ ማተኮር  አለበት።የሌሎችን እያየ መቀያየር concern አድርጎ የመሥራት አቅም ይቀንሳል።

2.Codeን ለማስታወስ መሞከር
👉እውነተኛdeveloperኦችconceptኦችን በሚገባ ይረዳሉ።እንዲሁም Docsኦችን,Noteኦችን,Googleን refer ያደርጋሉ።

concept ሣንረዳ codeን ለማስታወስ መሞከር ምንም value የለውም።

3.Documentationን አለመጠቀም


ለአንድ developer Docs የቅርብ ወዳጅ እንደማለት ነው።Docs ጊዚያችንን እንድንቆጥብ,projectኣችንን በሚገባ እንድንረዳ እንዲሁም ከሌሎች ላይ አብሮ ለመስራት ቀለል ያደርግልናል።

#DevVoltz #ProgrammingTips #CodeSmart #DevLife #SoftwareDevelopment #LearnToCode #CodingJourney #TechGrowth #DeveloperMindset #BuildInPublic
👍41
ስንቶቻችው ChatGPT 5.2 መለቀቁን ሠምታችዋል?

Open AI GPT-5.2 የተሰኘውን ሞዴሉን ያስተዋወቀ ሲሆን ይህም ሞዴል እንደ Coding እና ሒሳብ ባሉ ዘርፎችም ላይ መሻሻሉም ተገልጿል።

በዚህም GPT‑5.2 Instant, Thinking እና Pro የተባሉ ሞዴሎችን አስተዋውቋል። GPT‑5.2 Thinking ለprofessional እና Real world ለሆኑ ፕሮጀክቶች ጥቅም ላይ እንደሚውል ተገልጿል።

Check ማድረግ ከፈለጋችሁ የchatGPT አፕሊኬሽን ክፈቱና የ+ ምልክቱን ነክታችሁ model ውስጥ auto, Instant እና Thinking የሚሉ አማራጮች አሉላችሁ። check አድርጉት።

#DevVoltz #ChatGPT5.2 #AI #TechInsights #MachineLearning #Innovation #Coding #DeveloperLife #FutureTech #AIRevolution
2
Microsoft Office በዲጅታሉ አለም ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ከፈጠሩ ሶፍትዌሮች መካከል ግንባር ቀደሙ ነው።

Microsoft wordን በ1983፣ excelን በ1985 ለየብቻ የሰራ ሲሆን፣ PowerPointን ግን በ 14 ሚሊዮን ዶላር ከ Robert Gaskins እና Dennis Austin በመግዛት፣ በ Bill Gates ሃሳብ አመንጪነትና በ Charles Simonyi (“father of Microsoft Office”) የProduction ማናጀርነት “Microsoft Office” በማለት ብዙ ሶፍትዌሮችን በ 1 ሰብስቦ በ 1990 release ተደረገ።

መጀመርያ ከተለቀቀበት 1990 እ.ኤ.አ. ጀምሮ፣ እንደ Word, Excel, PowerPoint, Outlook, Access እና በኋላም Teams የመሳሰሉ መተግበሪያዎችን በውስጡ በማካተት፣ ላለፉት 35 አመታት ለስራ ቅልጥፍናና ምርታማነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳጅ የሆነና ለውጥ የፈጠረ software ነው።

ይህ የሶፍትዌር ስብስብ ሰዎች ሰነዶችን የሚጽፉበትን፣ የንግድ ተቋማት መረጃን የሚይዙበትና የሚያስተዳድሩበትን፣ እንዲሁም ድርጅቶች በመግባባትና በጋራ የሚሰሩበትን መንገድ ፈጥሯል።

አሁን ደግሞ ከኢንተርኔት መስፋፋት ጋር ተያይዞ፣ Microsoft“Microsoft 365” አማካኝነት ኦፊስን ወደ ክላውድ (cloud) ያዛወረ ሲሆን፣ ይህም real-time collaboration በመፍጠር፣ በተለያዩ መሳሪያዎች በቀላሉ ፋይል share ማድረግን፣ በ AI የታገዘ ስራ ለመስራት አስችሏል።

1990 ጀምሮ እስካሁን Microsoft በአማካኝ 55–60 ቢሊዮን ዶላር በአመት ከ Office ብቻ ያገኛል ተብሎ ይገመታል።
2🔥2
Windows File Explorer በምትከፍቱበት ጊዜ ቀጥታ “Quick access” ጋር እየወሰዳችሁ ከሆነና፣ ስትከፍቱት ወደ “This PC” እንዲወስዳችሁ ከፈለጋችሁ በቀላሉ በዚህ መልኩ ማስተካከል ትችላላችሁ።

🖥 Windows 10 ከሆነ
Windows File Explorer ከከፈታችሁ በኋላ ጥግ አካባቢ ያለውን “View” የሚለውን ትነካላችሁ፣ ከዚያም “Options” የሚለውን መንካት እና ከ General tab ላይ ያለውን “Open File Explorer to:” ከሚለው አጠገብ ያለውን ወደ “This PC” መቀየር።

🖥 Windows 11 ከሆነ
Windows File Explorer ከከፈታችሁ በኋላ የላይኛውን “ሶስት ነጥብ (⋯)” በመንካት “Option” የሚለውን መንካት እና ከ General tab ላይ ያለውን “Open File Explorer to:” ከሚለው አጠገብ ያለውን ወደ “This PC” መቀየር።

ከዚያ በኋላ File Explorer ሲከፈት ሁሌም በ This PC ይጀምራል።

#tech_tip #devvoltz #windows #windows10 #windows11 #computer_tips
Upwork ላይ
1, የመጀመሪያ ስራ
2, የመጀመሪያ 5
3, የመጀመሪያ Review
4, 5$
ከፈለጉ

ዋጋ: 3700 ብር

For Additional info
👉በTelegram:- @devvoltz_support_team
👉በስልክ :+251940192676
👉website🌐
   www.devvoltz.com/freelance
ላይ ይላኩልን!
5
ዛሬ ድህረ-ገጽ መኖር አማራጭ አይደለም።
👉 አስፈላጊ ነው!

ድህረ-ገጽ (Website) ማለት፦
በኢንተርኔት ላይ የሚገኝ፣ መረጃ፣ አገልግሎት ወይም ምርት ለሰዎች የሚያቀርብ የዲጂታል መድረክ ነው።
እንደ ኩባንያ,ት/ቤት ,ተቋማት ስራቸውን ማሣያ ወይም ራሣቸውን መግለጫ ይጠቀሙበታል።

ድህረ-ገጽ (Website)ከሚሠጠን ጥቅሞች መካከል

📢 መረጃን ለሰዎች በፍጥነት ያስተላልፋል
🕒 ንግድን 24/7 ሁልጊዜ ክፍት ያደርጋል
🤝 ንግድን ከደንበኞች ጋር በቀላሉ ያገናኛል
💰 የማስታወቂያ እና የስራ ወጪን ይቀንሳል

ድህረ-ገጽኦን በDevvoltz ያሠሩ።ድህረ-ገጽኣችን ላይ https://devvoltz.com/software በመግባት የተሠሩ ድህረ-ገጽኦን,systemኦችን እንዲሁም ርሶ እንዲሠራሎት የሚፈልጉትን ፎርም በመሙላት ድረ ገጻን ያስገንቡ።

👉 የተሻለ ድህረ-ገጽ ለፈጣን እና ውጤታማ ስራ
👍2
የገና መልእክት – ለ Devvoltz Telegram Community
👉 ውድ የDevvoltz Telegram ቤተሰብ,
ዛሬ ገናን ስናከብር 🙏
በቀላሉ በዓል እያከበርን አይደለም፤
ከትንሽ መጀመሪያ ወደ ታላቅ ለውጥ የሚያመራ መልእክት እናስታውሳለን።
👉 ጌታ ኢየሱስ በምን ጀመረ?
በቤተ መንግሥት አይደለም፣
በቀላል መኖሪያ፣ በትህትና፣
ነገር ግን ዓለምን የቀየረ ታላቅ ራዕይ ነበረው።
ይህ ለእኛ ግልጽ መልእክት ነው፦
👉 ሰው ከምንም ሊጀምር ይችላል፣
ነገር ግን ዓለምን ሊቀይር ይችላል።
Devvoltz ይህን እውነት ያምናል።
እዚህ ያሉ ብዙዎቻችሁ
👉 coding አታውቁም ነበር፣
👉 design አታውቁም ነበር፣
👉 freelancing አልጀመራችሁም ነበር።
ነገር ግን ዛሬ…
እየተማራችሁ ነው፣
እየሰራችሁ ነው፣
እየገነባችሁ ነው።
👉 Devvoltz ቦታ ብቻ አይደለም፤
መጀመር የሚፈቀድበት ማህበረሰብ ነው።
እዚህ ትማራላችሁ፣
skill ታገኛላችሁ፣
freelancer ትሆናላችሁ፣
እና ነገ የራሳችሁን ኩባንያ ትጀምራላችሁ።
👉 እያንዳንዳችሁ የምታደርጉት
— አንድ lesson፣ አንድ project፣ አንድ client —
ምናልባት ትንሽ ይመስላል፣
ነገር ግን የወደፊታችሁን አቅጣጫ እየቀየረ ነው።
👉 ገና የሚያስተምረን፦
• ከትንሽ መጀመር አትፍራ
• መማር አቁም አትበል
• በራስህ እመን
👉 Devvoltz የተፈጠረው
ሰዎች ከምንም ጀምረው
skill እንዲኖራቸው፣
ነፃ እንዲሰሩ (freelance)፣
እና የራሳቸውን ኩባንያ እንዲገነቡ ነው።
መጨረሻ፣
ዛሬ ተማሪ ከሆንክ — ነገ ባለሞያ ትሆናለህ።
ዛሬ freelancer ከሆንክ — ነገ CEO ትሆናለህ።
መልካም ገና ለ Devvoltz Community 🎄
ከምንም መጀመሪያ → ወደ ዓለም ለውጥ 🚀
🔥3👏21👍1
የፈተና እና የትዕግሥት መልእክት – Devvoltz Community
ፈተና ሊገጥምህ ይችላል?
👉 በፍጹም! "ሊገጥምህ ይችላል" ሳይሆን "ይገጥምሃል" ነው የሚባለው።
​ምክንያቱም አንተ ሰው ነህ፤ በጉዞ ላይ ነህ፤ ታላቅ ራዕይም አለህ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን—ሁሉን የሚችልና ታላቅ ኃይል ያለው ሆኖ ሳለ—መከራን ተቀብሏል። ተከሷል፣ ተበድሏል፣ ተሰቃይቷል።
👉 ለመሆኑ ከእርሱ በላይ ማን ተበድሎ ያውቃል?
​(ጥቂት ቆም በልና አስብ...)
​ነገር ግን አንድ ነገር ተመልከት፦ በወደቀ ቁጥር፣ በቆሰለና በተገፋ ቁጥር ወደ ታላቁ ተልዕኮው እየተቃረበ ነበር። ለምን መሰለህ? ያኔ በመስቀል ላይ የሰቀሉት እርሱ፣ ዛሬ ዓለምን በእጁ የያዘ ኃያል ሆኗል።
👉 ከዚህ በላይ ምን ማስረጃ ትፈልጋለህ?
​እኛ መከራን ተቀብሎ የሚያስተምር፣ በሥቃይ ውስጥ ማለፍን የሚያውቅ ጌታ አለን። እኛ ግን ብዙ ጊዜ ፈሪዎች እንሆናለን። ዓለም ብታሰቃየውም እርሱ አላማረረም፤ ይልቁንም ለዓለም መድኃኒት ሆነላት።
ይህ ለእኛ ትልቅ ትምህርት ነው፦
ፈተናህ የመሸነፍህ ምልክት አይደለም፤
👉 ይልቁንም የማደግህና የመጠንከርህ ማረጋገጫ ነው!
ለDevvoltz Community አባላት በሙሉ፦
👉​Skill ሲከብድህ...
👉​Freelance ሥራዎች ሲከሽፉብህ...
​መንገዱ ዳገት ሲሆንብህ... 👉 "በቃኝ" አትበል!
​ከመከራ በኋላ ጥንካሬ ይመጣል። ከትዕግሥት በኋላ ስኬት ይከተላል። ከመስቀል በኋላ ደግሞ ብሩህ ትንሳኤ አለ!
Devvoltz Community!
ፈተናው አያቆምህም—ለታላቅ ክብር ያዘጋጅሃል እንጂ! 🚀
4🔥1👏1