ደራሽ የቤት ለቤት ህክምና
119 subscribers
33 photos
1 video
1 file
4 links
የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
-የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ማማከር እና መስጠት
-የቅድመ ወሊድ ወይም የእርግዝና ክትትል መስጠት
-የህፃናት ህክምና እና የእድገት ክትትል
-የአዋቂዎች ህክምና
Download Telegram
Forwarded from ደራሽ የቤት ለቤት ህክምና (gech Invaluable)
ደራሽ የቤት ለቤት ህክምና

የምንሰራው በተለያየ ምክንያት ሆስፒታል መሄድ ያልቻሉ ታማሚዎችን ቤታቸው ድረስ እየመጣን አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ ነው።

ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል
👉የደም ግፊት እና የስኳር መጠን መለካት
👉በሀኪም የታዘዙ ተመላላሽ መርፌዎችን መስጠት
👉አካባቢዎ ላይ የሌሉ መዳኒቶችን አፈላልጎ ማምጣት
👉አረጋውያንን እና አቅመ ደካሞችን መንከባከብ
👉የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ማማከር እና መስጠት
👉የቅድመ ወሊድ ወይም የእርግዝና ክትትል መስጠት
👉የህፃናት ህክምና እና የእድገት ክትትል
👉የአዋቂዎች ህክምና
እና ሌሎችም

ጓደኞቻችሁን add በማድረግ እንዲቀላቀሉን በማድረግ ተባበሩን
እናመሰግናለን!!!

join  @derash
        @derash
Group @derasheg
            @derasheg
ለሚስጥራዋ ጥያቄ እና አስተያየት
       @tesfayemagna
       @tesfayemagna
#ፎሮፎር

#ፎሮፎር እጅግ በጣም የተለመደ የፀጉር ቆዳ ችግር ነው፡፡ በፀጉር ቆዳ ላይ የሚታይ ነጭ የተፋቀ የሞተ ቆዳ ፎሮፎር ሲሆን አልፎ አልፎም የማሳከክ ሁኔታ ሊኖረው ይችላል፡፡
#ፎሮፎርን #የሚያስከትሉ #ሁኔታዎች
👉 ደረቅ ቆዳ፡- በቆዳ መድረቅ ምክንያት የሚመጣ ከፀጉር ቆዳ በተጨማሪ በእጅ እና በእግር ቆዳዎች ላይም ይታያል፡፡
👉 ቅባታማ የቆዳ መቆጣት ፡- የቆዳ መቅላት፣ቅባታማ ቆዳ በነጭ እና ቢጫ ቅርፊት መሳይም ነገርም በፀጉር ቆዳ ላይ ይታያል፡፡ ይህ ዓይነቱ የፎሮፎር ዓይነት በቅንድብ እና በጆሮ ጀርባ ላይም ይገኛል፡፡
👉የፀጉር ንፅሕና ማጣት፡- ፀጉርዎን በመደበኛ ሁኔታ የማይታጠቡ ከሆነ ለፎሮፎር ተጋላጭ ይሆናሉ፡፡
👉ፈንገስ ፡- በፈንገስ ምክንያት የሚመጣ የፎሮፎር ዓይነትም ያለ ሲሆን አንዳንዶች ለቆዳቸው ተስማሚ ያልሆኑ የፀጉር መዋቢያዎችን በመጠቀም ምክንያት ይከሰትባቸዋል፡፡
#ለፎሮፎር #ተጋላጭነት #የሚጨምሩ #ሁኔታዎች
👉ዕድሜ፡-በአብዛኛው በልጆችና በወጣቶች ላይ ይታያል፡፡
👉ፆታ፡- አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ በወንዶች ላይ በብዛት የሚከሰት ባህርይ አለው፡፡
👉 ተጓዳኝ በሽታዎች መኖር ናቸዉ፡፡
#ፎሮፎርን #ለመከላከል
👉 በመደበኛ ሁኔታ የፀጉር ንፅሕና መጠበቅ
👉ለፀጉርዎ የሚጠቀሙትን መዋቢያዎች መቀነስ
👉ፎሮፎር በአብዛኛው ንፅሕናን በመጠበቅ እና አመጋገብን በማስተከካል የሚድን ሲሆን ችግሩ ለሳምንታት የሚቆይ፣የሚያሳክክ እና በፀረ ፎሮፎር የማይታገስ ከሆነ ወደ ሐኪም በመሄድ ሕክምና ማግኘት ተገቢ ነው፡፡ ሕክምናውንም በሐኪምዎ ትዕዛዝ መሠረት በመጠቀም ከፎሮፎር ነፃ መሆን ይችላሉ፡፡

Join @derash
@derash
#Herpes #zoster (አልማዝ-ባለጭራ)

በግማሽ የሰውነት ክፍል ላይ በድንገት የሚወጣ ሽፍታ ሲሆን ብዙዉን ጊዜ ሽፍታው መስመር ይዞ ውሀ ቋጥሮ በጣም ህመም ያለው ነው፡፡ በየትኛዉም የሰዉነት ክፍል ላይ ሊወጣ ይችላል አብዛኛውን ጊዜ ግን
👉በጀርባበማጅራት
👉በደረት ወይም
👉በፊት ላይ ሊወጣ ይችላል፡፡
በአገራችን በተለምዶ #አልማዝ #ባለጭራ እየተባለ ይጠራል::
👉 #የአልማዝ #ባለጭራ #በሽታ #ዋና #መንስኤ ጉድፍን የሚያስከትለው ቫሪሴላ ዞስተር ቫይረስ (Varicella Zoster Virus) ነው ህመሙ ምንም እንኳን ለህልፈተ ህይወት ባይዳርግም ከፍተኛ ስቃይ/ህመም ሊያመጣ ይችላል፡፡
#የህመሙ #ምልክቶች
ብዙዉን ጊዜ በአንዱ የሰዉነት ክፍል በኩል/በቀኝ ወይም በግራ በኩል/ የሚታይ ነዉ፡፡
👉የማቃጠል
👉ማሳከክ
👉የመደንዘዝ
👉መጠቅጠቅ ህመም
👉የጡንቻ ህመም (ድካም)
👉ህመሙ ከተከሰተ ከጢቂት ቀናት በኃላ በቫይረሱ የተጠቃዉ አካባቢ ቀይ ሽፍታ መከሰት/መጀመር
👉ትኩሳት
👉የራስ ምታት የመሳሰሉት ናቸው
#ተጋላጭነትን #የሚጨምሩ #ነገሮች
👉ከዚህ በፊት ጉድፍ የነበረባቸውን ሰዎች
👉የተወሰኑ የህመም አይነቶች እንደ #ካንሰር #ኤች #አይቪ #ስኳርና ሌሎች የሰዉነትን የበሽታ መከላከል አቅም የሚቀንሱ ህመሞች ካሉ
👉እድሜ ከ50 ዓመትና ከዚያ በላይ ሲሆን
#ህክምናዉ
👉ወደ ቆዳና አባለዘር ሐኪም መሄድ
👉ሕክምናው ከሐኪም ጋር በመነጋገር የሚካሄድ ሲሆን የተለያዩ አማራጮች ያሉት ነው፤የአልማዝ ባለጭራ (ኸርፐስ) በቫይረስ አማካኝነት የሚከሰት እንደመሆኑ ጨርሶ ከሰዉነት ዉስጥ የሚያስወጣ መድሃኒት የለም ቢሆንም አንዳንድ ሁኔታውን ለማቅለል የሚታዘዙ የፀረ ቫይረስ መድኃኒቶች አሉ ፡፡ በአፍም ሆነ በቅባት መልክ የሚወሰዱ መድኃኒቶች ቁስሉ ወዲያው እንደጀመረ ቶሎ መወሰድ አለባቸው፤ በፍጥነት ለማገገም ይረዳሉ፡፡
በተጨማሪም - ህመምና ሽፍታ በአይን ዙሪያ ከወጣ ይህ አይነት እንፌክሽን ካልታከመ የማይመለስ ጉዳት በአይን ላይ ሊያመጣ ይችላል፡፡

Join @derash
@derash
#ኪንታሮት - (Hemorrhoids)

#ኪንታሮት በፊንጢጣ ውስጥ እና በታችኛው ትልቁ አንጀት አካባቢ በህብረት
የሚገኙ የደም መልስ የደም ቧንቧዎች/ ስሮች ሲያብጡና ሲቆጡ የሚፈጠር
እብጠት ነው።
---
ለዚህ እብጠት(ኪንታሮት) መፈጠር መንስኤ ከሚሆኑት ውስጥ:-
👉ሠገራን በምናስወግድበት ወቅት አብዝተን ወይም ለረጅም ግዜ ማማጥ።
👉 ለረጅም ግዜ የቆየ ሳል።
👉ከመጠን በላይ የሆነ ውፍረት።
👉 ለረጅም ግዜ የቆየ የሆድ ድርቀት ወይም ተቅማጥ።
👉 እንዲሁም ሌሎች ሆድ ውስጥ ያለ ግፊት እንዲጨምር የሚያድርጉ ፣
(ለምሳሌ ለሆድ እብጠት የሚጋልጡ የጉበት በሽታዎች)።
👉በተጨማሪ በእርግዝና ግዜና እድሜያቸው ከ40 አመት በላይ የሆኑ ጎልማሶች ለይ በስፋት ይታያል።
#የኪንታሮት #ምልክቶችና #ሊያስከትላቸው #የሚችላቸው #ተዛማጅ #ችግሮች:-
👉 በፊንጣጣ ላይና ከፊንጢጣ ውስጥ የሚታይ እብጠት።
ኪንታሮት የውጪ/ውጫዊ ኪንታሮት (External Hemorrhoid)
እና የውስጥ ውስጣዊ ኪንታሮት(Internal Hemorrhoid) በመባል በሁለት ይከፈላል ። #የውስጥ#ውስጣዊ
👉የሚባለው ኪንታሮት(Internal Hemorrhoid) አራት ደረጃዎች ያሉት ሆኖ፣
የመጀመሪያ ደረጃ የሚባለው ላይ እብጠቱ ወደ ውጪ ወጥቶ አይታይም።
እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃ ላይም ሰገራ በሚወገድበት ወቅት ላይ ብቻ ነው
እብጠቱ ሊታይ የሚችለው።
👉 ሰገራ በምናስወገድበት ሰዓት ህመም መሰማት፣ ማሳከክ ወይ አለመመቸት።
👉ህመም ሳይኖር በሰገራ ላይ ወይንም በምናፀዳበት ወረቀት ላይ ደም መኖር።
👉አንዳንዴ ደግሞ ያለቁጥጥራችን የሰገራ መውጣት።
👉አልፎ አልፎ ደግሞ በደንብ ሊደማ ስለሚችል ወይም ቀስ በቀስ የሚደማው
ደም ለደም ማነስ ሊያጋልጠን ይችላል።
👉አንዳንዴ እብጠቱ በመታጠፍ ወይም እብጠቱ ውስጥ ያሉ ደም ስሮች በረጋ
ደም በመዘጋት ከፍተኛ ህመም ሊሰማን ይችላል። ይህኔ ፈጥነን በአቅራቢያችን
ሚገኝ ሆስፒታል መሄድ ይኖርብናል።
---
---
#ከታች #የተዘረዘሩትን #ዘዴዎች #በመጠቀም #የኪንታሮት #ህመም #ስሜት #እና #መጠኑ
#እንዲቀንስ #ማድረግ #ይቻላል:-
👉ለብ ባለ ውሃ ውስጥ ሁለት/ሶስት ማንኪያ ጨው በመጨመር ከ15-20 ደቂቃ
በቀን ሁለት/ሶስት ግዜ በመቀመጫ/በፊንጣጣ መዘፍዘፍ።
👉 የሎሚ ጭማቂ መቀባት።
👉 በፋይበር የበለፀጉ አትክልትና ፍራፍሬዎችን መመገብ።
👉እብጠቱ ላይ በረዶን መያዝ ፣ በቀን ብዙ ግዜ እንደዚያ ማድረግ እብጠቱ
እንዲቀንስ ያደርጋል።
👉በቂ ውሃ መጠጣት።
👉ሰገራ በመጣ ግዜ ማስገወድ። አብዝተን አለማማጥ።
👉እንዲሁም ሀኪም ቤት በመሄድ የሚሰጠውን ምክርና የህክምና አገልግሎት በአግባቡ መከታተል።
Join @derash
@derash
#የጥርስ #መቦርቦር

#የጥርስ #መቦርቦር የሚከሰተው በአፋችን ውስጥ የሚገኙ ጀርሞች (ባክቴሪያ) ጥርሳችንን የሚያበሰብሱ አሲዶችን በሚያመነጩበት ጊዜ ነው ይህም በጥርሳችን ላይ የተቦረቦሩ ቀዳዳዎችን እንዲፈጠሩ ያደርጋል የተቦረቦሩ ጥርሶች ህመም ከማስከተል ባለፈ ለኢንፌክሽን ያጋልጣሉ።

#የጥርስ #መቦርቦር #እንዴት #ይከሰታል?

👉በጥርስ ላይ ተለጥፈው የሚቀሩ ምግቦች ካልተፀዱ ይከማቹና የባክቴሪያዎች መራቢያ እና ምግብ ይሆናሉ #ባክቴሪያዎች በሚመገቡ ጊዜ ከውስጣቸው አሲድን ይረጫሉ፣ ይህም ጥርሳችን እንዲቦረቦርና እንዲበሰብስ ያደርጋል

#ለጥርስ #መቦርቦር #የሚያጋልጡ #ሁኔታዎች

👉ጥርስን በሚገባና በመደበኛ ሁኔታ አለማፅዳት
👉ጣፋጭነት የበዛባቸው ምግቦች ማዘውተር
👉የፍሎራይድ እጥረት መኖር
👉የስኳር ህመም ተጠቂ መሆን
👉በህመም ወይንም በተለያዩ መድሀኒቶች ምክንያት የአፍ ድርቀት ሲኖር
👉ሲጋራን ማጤስ ናቸው

#የጥርስ #መቦርቦር #የሚያስከትላቸው #ምልክቶች

👉የጥርስ ህመም ስሜት
👉 በተጎዳው ጥርስ አካባቢ የድድ ማበጥ
👉 መጥፎ የሆነ የአፍ ጠረን መኖር
👉በጥርስ ላይ ነጭ ግራጫ ቡኒ ወይንም ጥቁር ቀለማት የያዙ የተቦረቦሩ ቦታዎች መኖር ናቸው

#የጥርስ #መቦርቦርን #እንዴት #መከላከል #ይቻላል ?

👉ጥርስዎን በቀን ውስጥ ቢያንስ ሁለት ጊዜ (ከቁርስ በኃላ እና ከመተኛትዎ በፊት) የፍሎራይድ ኬሚካል ባለው የጥርስ ሳሙና መታጠብ
👉በማንኛው ግዜ ምግብ ከተመገቡ በኃላ አፍዎን በንፁህ ውሀ በሚገባ መጉመጥመጥ
👉ከእንቅልፍ በፊት ጥርስዎን ከታጠቡ በኃላ ምንም አይነት ምግብ አለመመገብ
👉ጣፋጭ የበዛባቸው ምግቦችን ከምግብ ፕሮግራም ውስጥ ማስወገድ
👉 ልጆች ለጥርስ መቦርቦር ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ስለሆነ ሁሌም ስለ ጥርስ ፅዳት አጠባበቅ ማስተማር
👉 የጥርስ ሀኪምዎ ጋር በዓመት አንድ ጊዜ በመሄድ ጥርስዎን በባለሞያ ማሳጠብና ማስመርመር

#ማሳስቢያ❗️❗️

የጥርስ ህመም ሲሰማዎ ጊዜ ሳይሰጡ ወደ ሀኪም መሄድን አይዘንጉ ምክንያቱም የህመም ስሜቱ ከጥቂት ጊዜ በኃላ በራሱ ሊጠፋ ቢችልም የጥርስ መቦርቦር ግን ያለ ህመም ሊቀጥል ይችላል። በአፋጣኝ ህክምና ካልተደረገ ጥርስዎን እስከማጣት ሊያደርስዎ ይችላል

Join @derash
@derash
#በወር #አበባ #ጊዜ #የሚከሰት #ሕመም

ሴቶች የወር አበባ በሚያዩበት ጊዜ የሕመም ስሜት ሊከሰትባቸው ይችላል፡፡ አብዛኛዎቹ ሴቶች ከወር አበባ መምጣት ጋር ተያይዞ የሆድ ቁርጠት ሕመም ይኖራቸዋል፡፡
የሕመሙ መጠን ከሰው ሰው የሚለያይ ሲሆን አንዳንዴም የእለት ኑሮን እስከማቃወስ ይደርሳል፡፡

#በወር #አበባ #ጊዜ #የሕመም #ስሜት #እንዲሰማ #ተጋላጭነትን #የሚጨምሩ #ሁኔታዎች

👉ዕድሜ ከ30 ዓመት በላይ
👉ጊዜውን ጠብቆ የማይመጣ ከሆነ
👉ልጅ ያልወለዱ ከሆነ
👉በወር አበባ ጊዜ ከፍተኛ ሕመም የሚሰማው የቤተሰብ አባል ካለዎት
👉ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ ናቸዉ፡፡
በወር አበባ ጊዜ የሚከሰቱ የሕመም ምልክቶች?
👉የሆድ ቁርጠት
👉የማያቋርጥ ከዕምብርት በታች ያለ የሕመም ስሜት
👉ወደ ጀርባ ወደምጥ የሚሄድ ዓይነት ስሜት
ከዚህ በተጨማሪ አንዳንድ ሴቶች
👉 የማቅለሽለሽ
👉ተቅማጥ
👉የራስ ምታት
👉ማዞር የመሳሰሉት ሊኖራቸው ይችላል፡፡

#በወር #አበባ #ጊዜ #የሚከሰትን #ሕመም #ለማስታገስ

👉የሞቀ ውኃ ያለበትን የውኃ መያዣ ላስቲክ
በሆድዎ አካባቢ ማስቀመጥ የሚሰማዎን ሕመም ያስታግሳል
👉የአልኮል መጠጦችንና ሲጋራ ማጨስን መስወገድ
👉ጭንቀትን በተቻለ መጠን መቀነስ
👉 ለሕመም ማስታገሻነት የሚጠቅሙ መድኃኒቶችንም መጠቀም ናቸው፡፡
የህመም ስሜቱ የበዛና በማስታገሻዎች ሊታገስ ካልቻለ ወደ ህክምና መሄዱ ተመራጭ ነው

Join @derash
@derash
#ቃር (Heartburn)

#ቃር የምንለው ወይንም በህክምና አጠራሩ ሀርትበርን (Heartburn) በመባል የሚታወቀው የህመም አይነት ሲሆን አብዛኞችን የሚያጠቃ እና እጅግ የተለመደም ችግር ነው።
በደረት አካባቢ የማቃጠል ስሜት መሰማት በአብዛኛው ከምግብ በኃላ እና እንቅልፍ ስንተኛ የሚብስ ነው። ይህም የሚከሰተው የጨጓራ ውስጥ አሲድ ወደ ላይኛው የምግብ አስተላላፊ ቱቦ ሲገባ ነው።

#ለቃር #ተጋላጭነትን #የሚጨምሩ #ሁኔታዎች

👉ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን መመገብ
👉ሽንኩርት
👉ሲትረስ ያላቸው ምግቦች
👉ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች
👉ቸኮሌት
👉የአልኮል መጠጦችን መውሰድ
👉ካፊን ያላቸውን መጠጦች መውሰድ
👉ከጥጋብ በላይ መመገብ
👉ከመጠን ያለፈ ውፍረት
👉ነፍሰጡርነት ናቸው።

#ምልክቶች

👉ደረት አካባቢ የማቃጠል ስሜት በተለይ ምግብ ከተመገብን በኋላ እንዲሁም ምሽት ላይ
👉በጀርባ በምንቸኛበት ወቅት የማቃጠል ስሜቱ መጨመር
👉አፋችን ላይ የመምረር ስሜት።

#ሃኪምዎን #ማማከር #የሚገባው #መቼ #ነው

#ቃር በአብዛኛው አመጋገብን በማስተካከል እና ቀስቃሽ ሁኔታዎችን በማስወገድ የሚድን ሲሆን ከፍተኛ የሆነ የደረት ማቃጠል፣ ውጋት፣መጨምደድ ስሜት እና ወደ ትከሻ የሚሰራጭ የህመም ስሜት ከትንፋሽ ማጠር ጋር ከተከሰተ በአፋጣኝ ሃኪም ማማከር ተገቢ ነው ምክንያቱም የድንገተኛ ልብ ህመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል ነው።
#ከዚህ #በተጨማሪ
👉 በሳምንት ውስጥ ከሁለት ጊዜ በላይ የሚያቅርዎ ከሆነ
👉 ለመዋጥ የሚችገሩ ከሆነ
👉 ማቅለሽለሽና ማስመለስ ካልዎት
👉 የምግብ ፍላጎት በማጣት ወይንም ለመመገብ በመቸገር ምክንያት የሰውነት ክብደትዎ ከቀነሰ ሃኪምዎን ማማከር ይኖርብዎታል።

#ቃርን #ለማስታገስ #መደረግ #ያለባቸው #የአኗኗር #ዘይቤ #ለውጦች

👉የሰውነት ክብደትዎን ማስተካከል
👉ቃርን የሚይያስነሱ ምግቦችን አለመመገብ
👉የአልኮል መጠጦችን አለመውሰድ
👉ሲጋራን አለማጤስ
👉በመኝታ ጊዜ ጭንቅላትዎን ከፍ ባለ ትራስ ላይ ማሳረፍ ናቸው።

Join @derash
@derash
#ፕሮጄሪያ (Progeria)

በሌላ ስሙ (HGPS) በመባል የሚታወቀው የአንድን ልጅ ሰውነት በፍጥነት እንዲያረጅ የሚያደርገው የዘር ውርስ ነው አብዛኛዎቹ ይሄ በሽታ ያለባቸው ህፃናት ከ 13 ዓመት በላይ በህይወት መቆየት አይችሉም በሽታው ሁለቱም ፆታዎች እና ሁሉንም ዘር እኩል ያጠቃል በዓለም ዙሪያ ከ4 ሚልዮን ሕፃናት ውስጥ አንድ ሰው በዚህ በሽታ ይጠቃል

በሰዉ አፈጣጠር ወቅት በአንድ ትክክለኛ ሴል ውስጥ አንድ ስህተት ያልተለመደ ፕሮቲን እንዲፈጥር ያደርገዋል ሴሎቹም Progerin ተብሎ የሚጠራውን ይህን ፕሮቲን ሲጠቀሙ, በቀላሉ ይበሰብሳሉ. የፕሮጀርያ ሕጻናት በሚኖሩባቸው በርካታ ሴሎች ውስጥ progerin ከእድሚያቸዉ ፈጥነዉ በአስቸኳይ እንዲያድጉ ያደርጋቸዋል

#ምልክቶቹ
አብዛኞቹ ልጆች በሚወለዱበት ወቅት ጤናማ ይመስላሉ ነገር ግን በመጀመሪያ ዓመታቸዉ ውስጥ የበሽታ ምልክት ማሳየት ይጀምራሉ. Progeria ያለባቸው ሕፃናት እድገታቸዉ በጣም ዉስን ነው እንዲሁም ክብደት አይጨምሩም

#የአካል #አቀማመጣቸውም #የሚከተሉትን #ይመስላል
👉ትልቅ ጭንቅላት
👉ትልልቅ ዓይኖች
👉ትንሽ ዝቅተኛ አገጭ
👉ከጫፉ ቀጠን ያለ ቀጭን አፍንጫ
👉ትላልቅ ጆሮዎች
👉የሰዉነታቸው ደም ስሮች በግልፅ ይታያሉ
👉ያልተለመደ የጥርስ አበቃቀል
👉በሚናገሩበት ወቅት ቀጭንና ከፍተኛ ድምፅ ያወጣሉ
👉ሰውነትታቸዉ የቅባት እና የጡንቻ ማጣት ይኖራቸዋል
👉የፀጉር መርገፍ, የዐይን ሽፈሽፍት እና ቅንድብን ጨምሮ
ከ progeria ጋር የሚኖሩ ህፃናት ቶሎ ነው የሚያረጁት ከ 50 አመት በላይ ሊይዙን ይችላሉ በሚባሉ በሽታዎች ይያዛሉ እንደ #የአጥንት መሳሳት #የደም ስሮች በሽታ #የልብ በሽታ
#የኩላሊት በሽታን ጨምሮ በተለያዩ በሽታዎች ይጠቃሉ የ Progeria ህመም ያለባቸው ልጆች ብዙውን ጊዜ በልብ ድካም ወይም በኩላሊት በሽታ ይሞታሉ
በዚህ በሽታ የተጠቁ ልጆችን የማሰብ ችሎታ ወይም የአእምሮ እድገታቸዉ አይጎዳም ችግሩ ያለበት ልጅ ከሌሎች ልጆች ይልቅ በቸለያዩ በሽታዎች የመያዝ ዕድሉ ከፍተኛ ነው.

#Progeria #ምርመራ

የበሽታው ምልክቶቹ በደንብ የሚታዩ ስለሆነ በተለመደው የክትትል ወቅት የልጅዎ የህፃናት ሐኪም ሊያያቸው ይችላል.

በ Progeria ህመም የተያዙ የሚመስሉ ልጆችን የተለያዩ ለውጦችን ከተመለከቱ ከርስዎ ከሀፃናት ሀኪም ጋር መነጋገር የተለያዩ አካላዊ ምርመራ ይደረግላቸዋል, የእይታ ብቃታቸዉ የልብ ምታቸውንና የደም ግፊትን ይለኩእና የልጅዎን ቁመት እና ክብደት እኩዮቹ ተመሳሳይ ዕድሜ ጋር ያወዳድራሉ ከዚያ በኋላ የሕፃናት ሐኪምዎ አሳሳቢ ከሆነ በደም ምርመራ አማካኝነት የምርመራውን ትክክለኛነት የሚያረጋግጡ የሕክምና ባለሙያዎችን ሊያናግር ይችላል.

#ሕክምናዎች

አሁን ባለንበት ግዜ ለ Progeria በሽታ መድኃኒት አልተገኘለትም, ነገር ግን ተመራማሪዎች አንዱን
ለየካንሰር ህመም መድሐኒት የሆነውን በመጠቀምFTI (farnesyltransferase inhibitors), የተጎዱ ሕዋሶችን ሊያስተካክሉ ይችላሉ. #መድሃኒቶች ብዙውን ጊዜ የበሽታውን ምልክቶች ሊያዘገዩ ይችላሉ.
#መድሃኒት የልጅዎ ሀኪም መድሃኒቶች ሊያዝዙ ይችላሉ ዝቅተኛ የኮሌስትሮል መጠን እንዲኖር ወይም የደም መፍሰስን ለመከላከል አነስተኛ መጠን ያለዉ በየቀኑ
#አስፕሪን የልብ ሕመምን ለመከላከል ይረዳል. #የእድገት ሆርሞኖች ይሰጣሉ ቁመት እና ክብደት ለመገንባት ይረዳሉ
#የሰውነት እንቅስቃሴ (ቴራፒ) ህመም ለልጅዎ ጠንካራና የማይተጣጠፍ መገጣጠምያ እንዳይኖረዉ ይረዳዋል
#ቀዶ #ጥገና የአንዳንድ ልጆችን የልብ ሕመምን ለማዘግየት ለመቀነስ የልብ ቀዶ ጥገና ይደረግላቸዋል
#በቤት #ውስጥ #የምናደርግላቸዉ በProgeria በሽታ የተያዙ ልጆች የሰዉነታቸዉ የዉሀ መጠን በጣም ስለሚቀንስ ስለሆነም ብዙ #ውሃ #መጠጣት አለባቸው.
#ምግቦችን በሰአቱ እንዲበሉ ማበረታታት
ልጅዎ ንቁ ሆኖ እንዲንቀሳቀስ ማበረታታት

Join @derash
@derash
መጥፎ የጫማ ሽታን ለማስወገድ የሚረዱ መንገዶች

መጥፎ የጫማ ሽታ ለብዙዎች አሳሳቢ ነው እናም የስነልቦና እና ማህበራዊ ችግሮች መንስኤ ሆኗል ፡፡ ምንም እንኳን ይህንን ሁኔታ መፈወስ የሚችሉ ብዙ የመድኃኒት ምርቶች ቢኖሩም ብዙ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ይዘው ይመጣሉ ፡፡ ስለዚህ የቤት ውስጥ መድሃኒቶችን እንዲጠቀሙ ይመከራል።

👉ሄና፦ መጥፎ የጫማ ሽታዎችን ለማስወገድ ዋና ምርጫ የሚያደርገው የፀረ-ተህዋሲያን ንብረቶች አሉት ፡፡ አንድ የሾርባ ማንኪያ ሄናን ከአንድ ብርጭቆ ውሃ ጋር ይቀላቅሉ እና ጣቶቹ መካከል ባለው ቦታ ላይ ይተግብሩ ፡፡ በቀን እስከ ሶስት ጊዜ ይህንን ያድርጉ ፡፡

👉ሽንኩርት ፦ ቀይ ሽንኩርት ፀረ-ባክቴሪያ ባህሪዎች አሉት ፡፡ ጥቂት ቀይ ሽንኩርት ይፍጩ እና በቀን ሁለት ጊዜ በእግሮች ላይ ይተግብሩ ፡፡

👉አርድ፦ መጥፎ የጫማ ጠረንን የሚያስወግዱ ጸረ-ፈንገስ ባህሪዎች አሉት ፡፡ አንድ የሾርባ ማንኪያ በአንድ ብርጭቆ ውሃ ይቀላቅሉ እና በቀን ሦስት ጊዜ በእግሮች ላይ ይተግብሩ ፡፡

ከላይ ያሉት መፍትሔዎች በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ የሚሰሩ አይደሉም ፡፡ ቁርጠኝነትን እና ወጥነትን ይፈልጋሉ ፡፡

👇
ከእነዚህ በተጨማሪ

👉የእንግሊዝ ጨው፦የእንግሊዝ ጨው ግማሽ ኩባያ ከ 1 ሊትር ውሃ ጋር ይቀላቅሉ ፡፡ እግርን ለ 30 ደቂቃዎች ይዘፍዝፋ ፡፡ ይህንን በየቀኑ ያድርጉ።

👉ሎሚ፦ሎሚ ፈንገሶችን እና መጥፎ ሽታዎችን በሚዋጋ ሲትሪክ አሲድ የበለፀገ ነው ፡፡ 1 ሎሚ በ 1 ሊትር ውሃ ውስጥ ይጨምሩት እና እግሮቹን ለ 30 ደቂቃዎች ድብልቅ ውስጥ ይዘፍዝፉ ፡፡ ይህንን በየቀኑ ያድርጉ።

👉ኮምጣጤ: - አንድ ኩባያ ኮምጣጤን በ 1 ሊትር ውሃ ይቀላቅሉ እና ለ 30 ደቂቃዎች ይዘፍዝፉ ፡፡ ይህንን በየቀኑ ያድርጉ።

Join @derash
Join @derash
ይህንን ለ20 ለጎደኞቻቹ በመላክ ፕሮፋይሎን ማን አንዳየው አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ
https://t.me/who_save_my_profile_bot?start=r0745370015