ድምፀ ተዋሕዶ
11.4K subscribers
3.42K photos
85 videos
189 links
ይህ መንፈሳዊ ቻናል መቀመጫውን እንግሊዝ ለንደን ያደረገ ማንኛውንም ታማኝ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የቤተ ክርስቲያን መረጃዎችን እና መንፈሳዊ ክንውኖችን ለምእመኑ በፍጥነት፤ በጥራት ያቀብላል።

የእግዚአብሔር ጸጋ እና በረከት በሁላችን ላይ ይደር።

ድምፀ ተዋሕዶ ለንደን
ለታማኝ መረጃዎ
Download Telegram
ጥብቅ ማስታወቂያ ለሰባክያነ ወንጌል

በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሥር በሚገኙ
ገዳማት አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ፡

በስብከተ ወንጌል አገልግሎት ተመድባችሁ የምታገለግሉ ሰባክያን በሙሉ ከግንቦት 7 ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ጽ/ቤት በስብከተ ወንጌል ዋና ክፍል በአካል እየቀረባችሁ ያላችሁን የትምህርት ማስረጃ ዋናውን እና ኮፒውን በመያዝ እንድትመዘገቡ እናስታውቃለን ፡፡

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በቅዱስ ፍሬምናጦስ ስም የሚነግደው እና በትግራይ የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት ከተሃድሶ ቡድን ጋር በግልጽ እየሰራ የሚገኘው የሕገ ወጥ መነኮሳት ቡድን በዚህ መልኩ "ከክርስቶስ በላይ ሕዝባችን መከራ ተቀብሏል" በማለት ፍፁም ኦርቶዶክሳዊ ያለመሆን ብቻ ሳይሆን ክብር ይግባውና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሕማሙን ከፖለቲካዊና ተራ ነገሮች ጋር መመሠል ተገቢ ያልሆነ ኃጢአትና ነውርም ጭምር ነው።


በትግራይ የሚገኘው ኦርቶዶክሳዊ ሁሉ እነዚህን በሃይማኖት ስም የፖለቲካ እሳቤ የሚያራምዱ ነውጠኛ መነኮሳት ነገራቸው ሁሉ ለሕዝብና ለቤተ ክርስቲያን በማሰብ ሳይሆን ሃይማኖት ማጥፋትን እና ሥልጣንን ብቻ መርሕ አድርገው የሚጓዙ እምነት የለሽ፣ የተወገዙ እና የተለዩ መሆናቸውን አውቆ አባቶቹ በሕይወት መሥዋዕትነት ያቆዩለትን ሃይማኖቱን በእነዚህ ውጉዛን ማታለያ እንዳያጣው ሊያውቅበት ይገባል።


በቅዱሱ አባ ሰላማ ስም በያዙት ማዕረግ ለመቀጠል እንኳ ብቃቱ የሌላቸው ተራ መነኮሳት ተሰባስበው መሠረተ ሃይማኖት የሆነችውን አክሱምን በርካሽ አስተሳሰባቸው መበከላቸው ሳያንስ ኑፋቄያዊ አመለካከታቸውን በዚህ መልኩ ሲያስተላልፉ ማየት እጅግ የሚያም ድርጊት ነው።

ተ.ሚ.ማ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Channel photo updated