የፍቅር ደብዳቤዎች
39 subscribers
2 links
Download Telegram
ለመወጣት ነበር። በጣም ነበር የምጠላህ! የእናትህ ሞት ግን ብዙዉን ነገር ቀየረዉ! ብዙ ጊዜ በአሽሙር ልነግርህ ሞክሬያለሁ። አንዴ በረንዳዉ ላይ ተቀምጠን በህይወትህ አንዴ የምትሰራዉ ስህተት ህይወትህን በሙሉ ሊያዘበራርቀዉ ይችላል ምናምን ብዬህ ነበር። አንተ ግን ራስህን ልታይበት አልቻልክም።" አለችኝ።
ሀፍረት እየወረረኝ "እና እገባሻለሁ?" አልኳት።
አምሪ አሁንም እንደፈገገች "ሀቢቤ ሰዉ ይሳሳታል! ስህተት ፍጥረታችን ነዉ። ዋናዉ ቁም ነገር ከስህተት ተመልሶ መፅዳቱ ነዉ። ዛሬ አንተ በጣም መልካም ሰዉ ነህ!" አለችኝ።
ድምፄን ሳግ እያነቀዉ "አምሪ እኔ እኮ ቆሻሻ ነኝ።" አልኳት።
አምሪ ትክዝ እንደማለት አለችና "ቆሻሻ ማለት ስህተቱ ዉስጥ የሚዘወትር ነዉ። ከስህተቱ ተፀፅቶ የተመለሰዉማ ንፅህናዉ ካልቆሸሹት ሁሉ ይበልጣል። አንተ በጣም ንፁህ ነህ።" አለችኝ።
የአምሪ ቅንነት እየገረመኝ "አምሪዬ ግን ከምንድነዉ የፈጠረሽ?" አልኳት።
እየሳቀች "ከጎንህ ነዋ!" አለችኝና "እሺ ሶስቱ ፎቶዎችስ?" አለች።
የሁሉንም ማንነት ነገርኳት። አምሪ የፌቪን ታሪክ ስነግራት አለቀሰች። እኔም ሳላስበዉ እንባዬ ከአይኔ ፈሰሰ።
አምሪ ስትረጋጋ "ከቤተሰቧ ጋር የምትስማማበትን መንገድ መፍጠር አለብን!" አለችኝና "ሀቢቤ ግን ወንዶች የማይገባችሁ ትልቁ ነገር ምን እንደሆነ ታዉቃለህ? የሴት ልጅን ሀፍረት አንዴ ከገፈፋችሁት መመለሱ በጣም ከባድ መሆኑ! ፌቨንንም አንተ ሀፍረቷን ገፈሀት ነዉ እንደዚህ ህይወቷ የተመሰቃቀለዉ! አንተ ዛሬ ሰዉ መሆን ቻልክ! እሷ ግን የስቃይ መዓት ወረደባት! ሀቢቤ ልንረዳት ይገባል!" አለችኝ።
ሀሳቧ እያረካኝ "በጣም ደስ ይለኛል አምሪዬ!" አልኳት።
አምሪ አየችኝና "ሀቢቤ ግን በህይወቴ ሶስት ቀናትን አስለቅሰኸኛል።" አለችኝ።
ግራ እየተጋባሁ "መች መች?" አልኳት።
አምሪ በረዥሙ ተነፈሰችና "ያዉ የእናትህ ሞት ብዙዉን ነገር እንደቀየረዉ ነግሬሀለሁ። ስቀርብህ ትንሽ ከእምነት ጥንካሬዬ አንሸራተትከኝ። የመጀመሪያዉ ሆስፒታል ሆነን ምግብ አምጥቼላችሁ ያጎረስከኝ ቀን ነዉ። ቤት ገብቼ ጌታዬን ይቅር እንዲለኝ አልቅሼ ለመንኩት። ሁለተኛዉ ደግሞ ከእናንተ ቤት ስወጣ እጄን የነካኸኝ ቀን እንደዚህ እንዲደፍር ያደረገዉ ሁኔታዬ ነዉ ብዬ ወደ ጌታዬ አለቀስኩ። ሶስተኛዉ እኛ ቤት መኖር ከጀመርክ በኋላ ብቻችንን ተቀምጠን ያወራን ቀን ነዉ። እንደዉም አይፈቀድም ምናምን ብዬህ ነበር። አንተ ደግሞ ካልተፈቀደ ለምን አብረሽኝ ተቀመጥሽ ስትለኝ ይለፈኝ ብዬህ ነበር። ስለምወድህ ነበር ከማንም ጋር ሆኜ የማላዉቀዉን የሆንኩት። ብቻ አላህ ይቅር ይበለኝ።" አለችኝ።
እሷን ያስለቀሳት ወንጀል እራሴን እንድመለከት አደረገኝ። እኔ ማን ልባል ነዉ? ፈገግ ለማለት እየሞከርኩ "አሁን ያስለቀሰሽ ነገር ምንዳ የሚያስገኝልሽ ሊሆን ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተዋል።" አልኳት።
አምሪ ኮስተር እንደማለት እያለች "ከዚህ በኋላ ሌላ ሴት አያለሁ ብትል ግን ሟች ነህ!" አለችኝ።
እየሳቅኩ "ያዉ እሱማ መች ይቀራል?" አልኳት።
አምሪ እየተነጫነጨች "ሞክረዉ እና ታየኛለህ!" አለችኝ።
አሁን በህይወቴ ዉስጥ ሰላም ለማግኘት የፌቨን ህይወት ተስተካክሎ ማየት አለብኝ። ማበላሸት ቀላል ነዉ። ያፈረሱትን ለመገንባት መሞከሩ ግ

የማይፋቅ ስህተት
ክፍል አስራስምንት
(ፉአድ ሙና)
.
አምሪ ሁሉንም ጉዴን ማወቋ ትንሽ እረፍት ሰጠኝ። ይቅርታዋ ልቤን አረጋጋዉ። በነጋታዉ ፌቨንን ከአምሪ ጋር አገናኘኋት። አምሪ እኔን እንደገና መስራት ችላለችና ፌቪን መስራት አይከብዳትም ብዬ አስቤያለሁ። ሀጂ ትምህርት ቤታችን ዉስጥ ልዩ ዝግጅት አዘጋጅተዉ ሊድሩን እየተሯሯጡ ነዉ።
አምሪን ከፌቪ ጋር ካስተዋወቅኳት ሳምንት አለፈ። አምሪ ከሷ ጋር ከተግባባች በኋላ የፌቪን ቤተሰቦች አናገረች። ቤተሰቦቿ መፀፀቷን ሲሰሙ በጣም ደስ ብሏቸዉ ተቀበሏት። እኔም እረፍት አገኘሁ።
.
የኔና የአምሪ ጋብቻ ጥቅምት መጨረሻ ላይ እንዲደረግ ቀኑ ተቆረጠ። ጥቅምት 26 ሀሙስ ቀን ትምህርት ቤታችን ዉስጥ በጣም ደስ የሚል ድግስ ተዘጋጀ። የመርከዙ ተማሪዎች የተለያዩ ዝግጅቶችን አቀረቡ። በኋላ ላይ ምስክሮች ባሉበት የኒካህ ስነ ስርዓቱ ተፈፀመ። አምሪ ሚስቴ ሆነች። አምሪ የኔ ዉድ!
ጋብቻችን ቢፈፀምም አብረን መኖር ለመጀመር ያሰብነዉ ግን ከአራት ወራት በኋላ ነዉ። እነሰሚራ የኛን ቤት ለቀዉ ሌላ ቤት ለመቀየር የሚያስፈልጋቸዉን ጊዜ ለመስጠትና እኛም የሚያስፈልጉንን ነገሮች ለማዘገጃጀት እንዲረዳን አስበን ነዉ።
የኒካህ ስነ ስርዓቱ ሲያልቅ ሀጂ ብድግ አሉና "ያዉ ዛሬ ሁለት ልጆቼን ድሬያለሁ። ሽኩሪያ የሰጠችኝን አደራ ተወጣሁ ማለት እችል ይሆን? አላዉቅም! ለማንኛዉም ሀቢብ አሁን ትምህርት ቤቱ ዉስጥ ከማስተማር እና ከመማር በዘለለ የተቋሙን ስራ በምክትል ስራ አስኪያጅነት ታስተዳድረዋለህ። እዉቀቱ ስላለህና ጠንካራም ስለሆንክ ትልቅ ደረጃ እንደምታደርሰዉ ተስፋ አለኝ።" አሉ።
እንባ እየተናነቀኝ አቀፍኳቸዉ። ከዝቅጠቴ የነፃሁበትን ተቋም ታላቅ ደረጃ በማድረስ ብዙዎችን ለመጥቀም ለራሴ ቃል ገባሁ።
.
አምሪያን ካገባሁ ከአንድ ወር በኋላ ዉጪ ሀገር ያሉ ሴቶች ገንዘባቸዉን እንደነሚኪ ባሉ ሰዎች እንዴት እንደሚገፈፉ በዝርዝር የሚያስረዳ ቪዲዮ አዘጋጅቼ የፌስቡክ ገፄ ላይ ለቀቅኩ። እንደ ተሚማ ያሉ ሴቶች ይማሩበት ይሆናል። ቪዲዮዉ በጣም ብዙ ተመልካች አገኘ። አንዳንዶች የደረሰባቸዉን በሙሉ ይፅፉልኝ ጀመር። ሰው በስንቱ እንደሚበዘበዝ ሳስብ ሴቶቹ አሳዘኑኝ።
ከአምሪ ጋር ባልናሚስት ከተባልን ወር ከአስራአምስት ቀን ሆነዉ። ሀሙስ ነበር። መርከዝ ቤተ መፅሀፍ ተቀምጬ እያነበብኩ ነዉ። አምሪ ደወለችልኝ።
ስልኩን አንስቼ "ወዬ የኔ ዉድ!" አልኳት።
"ሆዴ ኸበር አለ! ፌቨን ወለደች።" አለችኝ። ኸበር ማለት ዜና ማለት ነዉ።
የሆነ የደስታ ስሜት እየተናነቀኝ "መች ወለደች?" አልኳት።
"ከትናንት ወዲያ ነዉ አሉ! ዛሬ መስማቴ ነዉ!" አለችኝ።
ወደ ማታ ተገናኝተን አራስ ለመጠየቅ ለመሄድ ተቀጣጠርን።
አስራአንድ ሰዓት አካባቢ ከአምሪ ጋር ሆነን ፌቪን ለመጠየቅ ወደ ቤታቸዉ ሄድን። ቤታቸዉ ባለ ሶስት ፎቅ ነዉ። በጣም ያምራል! ከዚህ የመሰለ ቤት አዉጥቼ እንዳሰቃየኋት ሳስብ በጣም አመመኝ። ቤቱ ዉስጥ ስንገባ ሰራተኛቸዉ ፌቨን ወዳለችበት ክፍል እየመራች ወሰደችን። ፌቪ ልጇን አቅፋ ተጋድማለች። እኛ እዛዉ እንዳለን ሚኪ፣ከሪሜ እና ኤልዳና ሊጠይቋት መጡ።
"ሀቢቤ!" አለ ሚኪ እያቀፈኝ። በጣም ከሳስተዋል። በአትኩሮት እያየኋቸዉ "እንዴት ናችሁ?" አልኩ።
ሚኪ "ያዉ እንዳንተ ባንሆንም ደህና ነን!" አለ።
ከነሚኪ ጋር ብዙ ነገሮችን ተጨዋወትን። ሚኪ ባጃጅ ገዝቶ ከኤልዳና ጋር አብሮ መኖር ጀምሯል። ያዉ የፈረደባቸዉን ግጦ እንደገዛዉ አልጠፋኝም። ከሪሜ ትምህርቱን ቀጥሏል። አብነት ግን ክፍለሀገር ከሄደ በኋላ ደዉሎላቸዉ እንደማያዉቅ ነገሩኝ።ከነሚኪ ጋር ተጨዋዉተን ፌቪንም ትንሽ አጫዉተናት ተሰናብተን ወጣን። ቤተሰቦቿ በደንብ የሚንከባከቧት ይመስለኛል።
.
ጊዜዉ መቁጠሩን ቀጥሎ እነሰሚራም ቤቱን ለቀዉልን ታች ሰፈር ሌላ ቤት ተከራዩ። ሀጂም ለአንዳንድ ነገር እንዲሆነኝ ብለዉ የቤት ኪራዩን ገንዘብ ወደ ባንክ አካዉንቴ አስገቡልኝ። አጠቃላይ ሁለት መቶ ሺህ ብር አካባቢ ይሆናል። ቤቱን ካሳደስነዉ በኋላ የቤት እቃዎችን ገዝተን አሟላን። ያዉ ሴት ያለበት ቤት መድመቁ የግድ ነዉና ቤታችን በአምሪ እቅድ ተኳለ። ቤታችንን አስተካክለን ከጨረስን በኋላ በተጋባን በአምስተኛዉ ወር አብረን መኖር ጀመር
ብ!" አለኝ። ከመቀመጫዬ ብድግ አልኩና "ትናንት ፈጣሪ በጣም ግፈኛ እና ፍትህ የማያዉቅ ይመስለኝ ነበር። እናቴ ስትሞት ከፈጣሪ ጋር መደባደብ ሁሉ አምሮኝ ነበር።" ስል ሁሉም ጮክ ብለዉ ሳቁ። ሳቃቸዉን ሲጨርሱ ቀጠልኩ "ግን ፍትሀዊ አይደለም ያልኩት ፈጣሪዬ መልዓክ የሚመስሉ ሶስት ሰዎችን ልኮ ማንንም እንደማይበድል አሳየኝ። ሀጂን የመርከዛችንን ባለቤት ከአባቴ በኋላ በምድር አባቴ የሆኑ ታላቅ ሰዉ አደረገልኝ። ሚስታቸዉናልጃቸዉም ብቸኝነቴን አስረሱኝ። ይኸዉ ዛሬ ከነበርኩበት የጨለማ ህይወት ተላቀቅኩ። ለከዚህ ቀደሙ ጌታዬ እንዲምረኝ ለምኑልኝ። ፈጣሪ ሁሌም ፍትሀዊ ነዉ። ከወሰደብን ይልቅ የሰጠን የተሻለ ነዉ። ምናልባት ቤተሰቦቼ በህይወት ቢኖሩ ዛሬ የሆንኩትን አልሆን ይሆናል። ለሁሉም አልሀምዱሊላህ!" አልኩና ተቀመጥኩ። ሁሉም ጮክ ብለዉ "አላሁአክበር!" አሉ።
ሁሉም ከተናገረ በኋላ ኡስታዙ የፃፍናቸዉን ደብዳቤዎች ለቤተሰቦቻችን እንደሚያደርስ ነግሮን ዝግጅቱ ተጠናቀቀ።
በነጋታዉ አምሪ ሰላም ልትለኝ ወደ መርከዝ መጣች። በእጇ ለሀጂ የፃፍኩትን ደብዳቤ ይዛለች። እየሳቅኩ "ማን ሰጠሽ?" አልኳት።
ጥርሷን ያጠረዉ ሽቦ እስኪታይ ድረስ ፈገግ አለች። ፈገግ ስትል ሽቦዉ ቀለሙ ተለየብኝ።
እያየኋት "አስቀይረሽዉ ነዉ?" አልኳት። "አዎ" አለችና ደብዳቤዬ ላይ ሳፈጥ "አቢ ደብዳቤህን ስጦታ ሰጠኝ!" አለችኝ።
"ምን ይጠቅምሻል?" አልኳት።
"አላዉቅም!" አለችኝ። ትንሽ ካወራን በኋላ በትምህርቴ በደንብ እንድበረታ አደራ ብላኝ ሄደች።
አምሪ ሁለነገሯ ደስ ይለኛል። እዉቀቷ ፣ ብስለቷ ፣ ፈገግታዋ! ግርም ይለኛል። አንድ ሚስት ሊኖራት የሚገባዉ ሁሉ ያላት ይመስለኛል።
.
እነሚኪያስ እንደድሮዉ መርከዝ ድረስ እየመጡ መጠየቅ ትተዋል። ስለፌቪም የሚነግረኝ አላገኘሁም። አንዴ የመጡ ጊዜ ክለብ መዉጣት እና አብራቸዉ መጠጣት ህይወቷ እንደሆነ እና ከሪም ፣ አብነት እና ሚኪም ትምህርት እንዳቋረጡ ነግረዉኝ ነበር። የአረብ ሀገሩ ገንዘብ ህይወታቸዉን ሙሉ ያኖራቸዉ ይመስል በሱስ ተተብትበዉ ትምህርት ማቋረጣቸዉ አሳዝኖኛል። ሁኔታቸዉ እንዳላማረኝ ገብቷቸዉ ነዉ መሰለኝ እነሱም ወደኔ መምጣት አቆሙ።
.
ሀምሌ ሊጠናቀቅ ሲል መርከዝ በገባሁ በአስራአንደኛ ወሬ ቁርዓንን ሙሉ ለሙሉ ሸምድጄ ጨረስኩ። ሀጂ ቁርዓን ሸምድጄ እንደጨረስኩ ሲነገራቸዉ ሁለት በግ ምፅዋት እንዲሆንላቸዉ ወደ መርከዝ ላኩ። በጎቹ ታርደዉ ደስ በሚል መልኩ ተደገሰልኝ። አምሪ ወደ ማታ ብቅ ብላ በስጦታ ማሸጊያ የተሸፈነ ስጦታ ሰጠችኝ። ስከፍተዉ መፅሀፍ ነዉ። የመፅሀፉ አርዕስት ደግሞ " ትዳርን የሚያጣፍጡ 1000 መንገዶች " ይላል። ፈገግ አልኩ። በጥረቴ ላይ እንድቀጥል ምልክት እየሰጠችኝ ይሆን? አምሪን የማግባት እድል ሊኖረኝ እንደሚችል ጠረጠርኩ።
.
ቁርዓንን ሸምድጄ ጨርሼ ትንሽ እንደቆየሁ የረመዳን ፆም ደረሰ። የኛ ትምህርት ቤት ደግሞ ረመዳን ሲደርስ ድምፃቸዉ የሚያምር የሆኑና ቁርዓንን በአግባቡ ተረድተዋል ብሎ የሚያስባቸዉን ተማሪዎቹን በረመዳን ምሽት የሚሰገደዉን የተራዉሂ ስግደት በመሪነት እንዲያሰግዱ ወደ መስጂዶች ይበትናል። ረመዳን ሊገባ ነገ ወይም ከነገ ወዲያ ይገባል ተብሎ የሚጠረጠርበት ቀን ሲደርስ የተመረጥን ተማሪዎች በየመስጂዱ ተበተንን። እኔ በሀጂ ትዕዛዝ ከኛ ቤት አቅራቢያ ያለዉ መስጂድ ተመደብኩ። ለቤትም ቅርብ ስለሆነ ደስ ብሎኛል። የረመዳን ፆም ከቤተሰብ ጋር ሲፆም ደስ የሚል ይመስለኛል። ዘንድሮ እንደ ሙስሊም የምፆምበት የመጀመሪያዉ አመት ነዉ።
.
ከሀጂ ጋር ሆነን ወደ ሰፈራችን መስጂድ ሄድን። የረመዳን ፆም ወይ ነገ አሊያም ከነገ ወዲያ ይጀመራል። ጨረቃዋ ዛሬ ከታየች ነገ ስለሚፆም ተራዉሂ የሚባለዉ የምሽት ስግደት ዛሬ ይጀመራል። የለበስኩት ነጭ ጀለቢያ ሀጂ አዲስ የገዙልኝ ነዉ። ቀይ በነጭ ጥምጣም ጭንቅላቴ ላይ ጠምጥሜያለሁ። ሀጂ መኪናቸዉን ዉጪ ላይ አቁመዉ ወደ መስጂዱ ግቢ በእግር ገባን። ጫማችንን አዉልቀን ወደ መስጂዱ ስንገባ አንድ በጣም የሚያምር ሽበት ጣል ያደረገበት ፂም ያላቸዉና ብዙ ጊዜ የስግደት መሪዎች የሚለብሱትን ካባ የለበሱ ፊተ፥በሻሻ ሰዉ ከተቀመጡበት ተነስተዉ ተቀበሉን። ሀጂ ፈገግ ብለዉ "ኢማማችን ይኸዉ ዘንድሮ ያመጣንላችሁ እርሱን ነዉ።" አሉ። ሰዉየዉ የመስጂዱ ዋና አሰጋጅ ኢማም እንደሆኑ ተረዳሁ።
ኢማሙ ፈገግ እንዳሉ "ሀጂዋ አላህ ይጠብቅዎት!" አሉና ወደኔ ዞረዉ ትከሻቸዉ ላይ አስጠግተዉ እየጨመቁኝ "ሙሀመድ እባላለሁ።" አሉኝ።
"ሀቢብ" አልኩ አክብሮት አይኔን እየሰበረዉ።
"እሺ ሀቢቤ ነገ ረመዳን መሆኑ ከተረጋገጠ የዛሬዉን ስግደት ከበቀራ ምዕራፍ ጀምረን እናሰግዳለን። አንተ የመጀመሪያዎቹን አራት ረከዓዎች ታሰግዳለህ!" አሉኝ። አራቴ መቆም ፣ ማጎንበስ ፣ በግንባር መደፋት እና መቀመጥ እንደ አንድ ረከዓ ይቆጠራሉ። ኡስታዙም ያዘዙኝ ይህን አራት ጊዜ እንዳሰግድ ነዉ።እሺ ብያቸዉ የመስጂዱ የመጀመሪያዉ ሰልፍ ጋር ሄድን። ወዲያዉ አንድ ወጣት የመስጂዱን ድምፅ ማጉያ አንስቶ "የረመዳን ፆም ነገ እንደሆነ ስለተረገገጠ የተራዉሂን የምሽት ስግደት ዛሬ እንጀምራለን" አለ። ሁለት ሰዓት ላይ የሚሰገደዉ የኢሻ የግዴታ ስግደት ከተሰገደ በኋላ ትንሽ እንደቆየን ዋናዉ አሰጋጅ ፈገግ ብለዉ ወደ ማሰገጃዉ ቦታ ጋበዙኝ። ይህ የማሰገጃ ቦታ በእምነቱ ተከታዮች ሚህራብ ይባላል።
ወደ ሚህራቡ ገብቼ ኢማሙ ጀለቢያዬ ላይ ተንጠልጣይ ድምፅ ማጉያ ካሰሩልኝ በኋላ ወደ ኋላዬ ዞር ብዬ "ስተው ፣ ስተው አተዲሉ ወሱዱል ኸለል" አልኩ። በአረብኛ ሆነ እንጂ ሰልፋችሁን አስተካክሉ ተጠጋጉ ከማለት የዘለለ ትርጉም የለዉም። ሰዉ ሰልፉን ሲያስተካክል ተመለከትኩ። የመጀመሪያዉ ሰልፍ ላይ ያሉት በጣም የእስልምና እምነት አዋቂ የሚባሉ ሰዎች እና ሽማግሌዎች ናቸዉ። አንዳንድ ወጣቶችም አሉ። ከአይኖቼ የእንባ ዘለላዎች እየተሽቀዳደሙ ወረዱ። ትናንት የስንት ሴቶችን ህይወት ያበላሸሁ ዝሙተኛ የነበርኩ ሰዉ እነዚህን የተከበሩ ሰዎች እየመራሁ ላሰግድ ነዉ። ፈጣሪ ቀናትን እንዴት እንደሚያዘዋዉራቸዉ ሳስብ ደነቀኝ። ትናንት ርካሽ የነ

በሩትን ማክበር አልተሳነዉም።
.
ጌታዬን ምህረትን ጠየቅኩና የመጀመሪያዉን ስግደት ለመጀመር እጄን ወደ ጆሮዎቼ ከፍ አድርጌ "አላሁአክበር" አልኩ። ከትንሽ ዝምታ በኋላ ጮክ ብዬ ቁርዓንን ማንበብ ጀመርኩ። ድምፄ በለቅሶ ታፍኗል። "አ ል ሀም ዱ ሊ ላሂ ረቢል ዓ ለሚሚሚ ን" እያልኩ ማንበብ ጀመርኩ። የኔ ለቅሶ ባየለ ቁጥር ከጀርባዬ የሚሰግዱ ሰዎችም ይንሰቀሰቃሉ። ከረዥም ሰዓት በኋላ ስግደቱን ወደ ቀኝ እና ወደ ግራ አንገቴን ዞር እያደረግኩ "አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላህ" ብዬ ጨረስኩ። በጥምጣሜ ፊቴን ያጠበዉን እንባዬን ጠረግኩ። ወዲያዉ የመጀመሪያዉ ሰልፍ ላይ የነበሩት ትላልቅ ሰዎች ኢማሙን ጨምሮ ወደ እኔ እየመጡ ግንባሬን ሳሙኝ። "አላህ ይጨምርልህ!" እያሉም ፀሎት አደረጉልኝ። ቀሪዎቹን አራት ረከዓዎች ኢማሙ እንዲያሰግዱ ቦታዉን ለቀቅኩላቸዉ። አሰገዱ። የመጨረሻዎቹን ሶስት ረከዓዎች እንዳሰግድ ቦታዉን ለቀቁልኝ። ብዙ መስጂዶች ላይ ይህን ስግደት የሚመሩት ዋና አሰጋጆቹ ናቸዉ። አሁን ግን ኢማሙ ግባ ስላሉኝ ትንሽ ተግደርድሬ ለማሰገድ ገባሁ። ይሄ ስግደት ትንሽ ለየት የሚለዉ የመጨረሻዉ ረከዓ ላይ ተቁሞ ዱዓ ወይም ፀሎት መደረጉ ነዉ። ገብቼ ለረዥም ሰዓት እየተንሰቀሰቅኩ ፀሎት አደረግኩ።
ስግደቱ ሲጠናቀቅ ሰጋጁ በሙሉ የኔን ማንነት ለማየት ወደ ማሰገጃዉ ቦታ ግር ብሎ መጣ። ብዙዎቹ እየመጡ አቀፉኝ። ግርግሩ ሲቀን
ስ ከሀጂ ጋር ሹልክ ብለን ወጣን። ከግቢዉ እንደወጣን አምሪ እና ወ/ሮ ለይላን ከሀጂ መኪና አጠገብ ቆመዉ አገኘናቸዉ። አብረን አልመጣንም እነሱ ከኛ ትንሽ ዘግየት ብለዉ ነበር የመጡት። መኪናዉ ዉስጥ እንደገባን ወ/ሮ ለይላ የምርቃት መዓት አወረዱብኝ። አምሪ "ኢትዮዽያዊዉ ሱደይስ ብለንሀል የኛ አልቃሻ!" አለችኝ። ሱደይስ የመካ መስጂድ ዋና አሰጋጅ ኢማም ነዉ። ሲያሰግድ በጣም ያለቅሳል።
.
ቤት እንደገባን ከምሽቱ አራት ሰዓት ሆኖ ስለነበር ወደ መኝታ ሄድን። ለሊት ዘጠኝ ሰዓት ሲል እንደለመደብኝ ተነስቼ ቁርዓን ማንበብና መስገድ ጀመርኩ። አስር ከሩብ ሲል አምሪ ክፍሌን አንኳኳች። "ሀቢቤ ሰዓት ሄዷል። ስሁር እንብላ!" አለች። ስሁር ማለት የረመዳን ፆም ላይ ፆም ከመጀመሩ በፊት የሚደረገዉ የመመገብ ስነ ስርዓት ነዉ። ነብዩ ሙሀመድ(ሰዐወ) በረከት አለዉ ስላሉ ሁሉም ተነስቶ ለበረከቱ ይቀማምሳል። ምግብ በለሊት መብላት የሚከብደዉም ቢሆን አንድ ጉንጭ ዉሀ ለበረከቱ ይጎነጫል። የክፍሉን በር ከፍቼ ወደ ሳሎን ሄድኩ። እነአምሪ ምግቡን አቀራርበዉ ጨርሰዉ ነበር። ምግቡን ሳየዉ ድሮ ህፃን እያለሁ የረመዳን ፆም ሲደርስ ሙስሊም ያልሆኑ ጓደኞቼ የሚሉኝ ትዝ አለኝ። "እናንተ ግን ለሊቱን ሙሉ እየበላችሁ ቀኑን ፆምን ትላላችሁ አይደል?" ነበር የሚሉኝ። እነሱ ፆሙ ከመጀመሩ አስራአምስት ደቂቃ በፊት እንደምንቀማምስ አያዉቁም። ሲጀመር የሰዉ ልጅ ለሊቱን ሙሉ የሚበላዉ ምግብ ቢኖረዉ እንኳ መብላት አይችልም። ለነገሩ ድሮ ብቻ ሳይሆን ሚኪም በቅርብ አመታት ብሎኝ ያዉቃል። ማን ይህን አስተሳሰብ እኩል ሰፍቶ እንዳደላቸዉ እኔንጃ!
.
ስሁር በልተን ስንጨርስ ወ/ሮ ለይላ "ነገ አፍጥር እነሰሚራ ቤት ተጠርተናል። ልጅ እምቢ ብሏቸዋል ሰደቃ ሊያወጡ አስበዋል።" አሉ። አፍጥር ማለት ፆም ሲገደፍ ማታ የሚበላዉ ነዉ። ሰሚራ እስከአሁን ልጅ አልወለደችም። ይገርማል። ከልቤ ፀሎት ላደርግላት ለራሴ ቃል ገባሁ። ለነገሩ ችግሩ ከባሏም ሊሆን ይችላል።
.
ይቀጥላል...❤️❤️❤️
#like & #share እንዳይረሳ
👍❤️👍❤️👍❤️👍❤️

የማይፋቅ ስህተት
ክፍል አስራአራት
(ፉአድ ሙና)
.
የረመዳንን የመጀመሪያ ቀን ፆም የገደፍነዉ ሰሚራ በሰራችዉ ምግብ እነሰሚራ ቤት ነበር። ከልቤ ፈጣሪ ልጅ እንዲሰጣቸዉ ለመንኩ። አምሪ ሰሚራ "ምን ልጨምርልህ?" እያለች ስታስተናግደኝ ስታይ የሌለ ሳቀች። ምን ያስቅሻል እንዳይሏት በጣም ፈርቼ ነበር። ደግነቱ ብዙም ትኩረት አልሰጧትም። ሰሚራ በደንብ ነበር ያስተናገደችን። ምግቡም በጣም ይጣፍጥ ነበር። በወጉ ተስተናግደን ከነሰሚራ ቤት ወጣን። የሰሚራ ባል ስንወጣ ያዝ አድርጎኝ "አላህ ያንተን ይሰማሀል አደራ ለምንልኝ! ልጅ በጣም እወዳለሁ።" አለኝ።
"አላህ የማንን እንደሚቀበል አናዉቅም አንተም አድርግልኝ። አብሽር!" አልኩት። እንደዚህ አክብሮ የሚያወራኝ ሰዉ የሚስቱን ክብር የገፈፍኩት እኔ እንደሆንኩ ቢያዉቅ ምን ይል ይሆን? የብዙዎቻችን ጉድ አደባባይ ቢወጣ አንዳችንም ቀና ብለን መሄድ የምንችል አይመስለኝም። ፈጣሪ እያመፅነዉ እንኳ ወንጀላችንን መሸሸጉ እንድንመለስ እድል እየሰጠን እንደሆነ እና ምን ያህል ለባሮቹ አዛኝ መሆኑን የሚያሳይ ይመስለኛል።
.
የረመዳን ፆም ገብቶ የተወሰኑ ቀናት አለፉ። እኔም እንደተለመደዉ ማሰገዴን ቀጥያለሁ። የረመዳንን አስራአምስተኛ ለሊት ስግደት ጨርሼ ከመስጂዱ ስወጣ ፌቨንን ከመስጂዱ አቅራቢያ ቆማ ተመለከትኳት። ከነሀጂ ጋር ስለነበርኩ ባላየ ወደ ሀጂ መኪና ገባሁ። መኪናዉ በአጠገቧ ሲያልፍ ትኩር ብዬ አየኋት። በደንብ ዘንጣለች። ረዘም ያለ ሱሪ እና ሌዘር ጃኬት ለብሳለች።እጇ ላይ ሲጃራ አለ። ሱስ የሚባል የቀራት አይመስለኝም። ለሁሉም ተጠያቂዉ እኔ ነኝ። ሚስኪኗን የቤት ልጅ አበላሸኋት። ቆይ ግን እንዴት መስጂድ በር ላይ መጥታ ቆመች? ልደዉልላት ፈለግኩ። ደሞ ለሌላ ነገር የፈለግኳት ይመስላታል ብዬ ተዉኩት። ከዚህ ቀን በኋላ ፌቪ ሁሌ ማታ ማታ መስጂድ በር ላይ ትቆምና ትሄዳለች። ሀያኛዉ ለሊት ላይ ሰግጄ ስወጣ ከመስጂዱ ትንሽ ራቅ ብላ ቆማለች። ዛሬ ሀጂ የሉም። ከወ/ሮ ለይላ እና ከአምሪ ጋር ነዉ የመጣሁት! እነሱ ከሴቶች መስጂድ እስኪወጡ ስጠብቃቸዉ ፌቪ እየተራመደች ወደኔ መጣች። አለባበሷ ሙስሊም ሴት አስመስሏታል።ቀሚስ ነዉ የለበሰችዉ። ፀጉሯ ላይ ሻሽ ጠምጥማለች። እኔ ደግሞ ጀለቢያ እንደለበስኩ ጥምጣሜንም እንደጠመጠምኩ ነኝ። ሰዉ እየመጣ ሰላም እያለኝ ያልፋል።ፌቪ አጠገቤ ስትደርስ አቀረቀርኩ። "ሀቢቤ ሰላም ነህ?" አለችኝ።
መልስ ሳልሰጣት "እዚህ ምን ትሰሪያለሽ?" አልኳት።
"ያዉ ድምፅህ ናፍቆኝ ነበርና እዚህ ይፀልያል ሲባል ሰምቼ መጣሁ! ባይዘዌይ ድምፅህ በጣም ያምራል!" አለችኝ።
"ፌቪ ለሁሉም ይቅርታ! ከዚህ በኋላ ግን ያንቺ መሆን አልችልም! እኔን ለመርሳት ሞክሪ!" አልኳት።
ፌቪ ድምጿ በሳግ እየታፈነ "አዉቃለሁ! ጌታ መልካሙን ይስጥህ! ግን ሁሌም አፈቅርሀለሁ። ከዚህ በኋላ ሰዉ መሆን አልችልም። እስከምሞትም ሰዉ አልሆንም! ያዉ ባስጀመርከኝ የሴሰኝነት መንገድ እጓዛለሁ። አንተ እራስህን አፅዳ ግድ የለም! ቀለል አድርገህ እርሺኝ በል! ግድ የለም!" ብላ እንባዋን መጠራረግ ጀመረች። ቀና ስል እነአምሪያ ወደኛ ሲመጡ አየኋቸዉ። ፈጠን ብዬ "ፌቪ አሁን ሂጂ! ለኔ ጥሩ አይደለም!" አልኳት።
"ላንተ ጥሩ አይደለም!? አንተን ካወቅኩ በኋላ እኮ ለኔ ምንም ጥሩ ሆኖ አያዉቅም!" አለችኝ። አምሪያ እየተጠጋችን "አሰላሙአለይኩም ሀቢቤ!" አለች። በጣም ጨነቀኝ። አምሪ ፊቷን ካየቻት ታዉቃታለች። አምሪ ስትጠጋን ፌቪ ድምጿን ከፍ አድርጋ "አመሰግናለሁ ኡስታዝ! አላ ይስጥልኝ።" ብላ ወደ አምሪያ ሳትዞር ሄደች። አምሪ ፌቪ መጨረሻ ላይ ያለችዉን ስለሰማች አልጠረጠረችም። እያደነቀችኝ መስሏትም ይሆናል።
አምሪ እየሳቀች"ሀቢቤ እየፈረምክላት ነዉ? አድናቂህ በዛ አይደል?" አለችኝ። ወ/ሮ ለይላ እየሳቁ "አይ አምሪያዬ እስኪ ተይዉ መወደድ የአላህ ፀጋ ነዉ!" አሉ።
አምሪ አሁንም እየሳቀች "ኧረ እኔ እኛን እንዳይረሳን ብዬ ነዉ!" አለች።
እኔ ዉስጤ ላይ መረጋጋት የለም። ፌቪን ያደረግኳት ነገር ፀፀቱ ሰላም ነሳኝ። ያበላሸሁት ማንነት ሊስተካከል የሚችል አይነት አይደለም። ምናለ ባላወቅኳት!
.
የረመዳን ፆም ከተጠናቀቀ እና የኢድ አል ፈጥር በዓል ተከብሮ አስራአምስት ቀናት ካለፉ በኋላ ወደ መርከዝ ተመለስኩ። ወደ ዉዱ የሀይማኖት ትምህርት ቤት!
ቁርዓንን ሸምድጄ ስለጨረስኩ በተለየ መልኩ ሙሉ ሰዓቴን ሌሎች የእምነቱ ዘርፍ ትምህርቶችን በመማር አሳልፋለሁ። ከአንድ ኡስታዛችን ጋር በጋራ ሆነን ደግሞ ትምህርቶችን በድምፅ እየቀረፅን ኢንተርኔት ላይ እንለቃለን። እኔም አዲስ የፌስቡክ አካዉንት ከፍቼ ሀይማኖታዊ ፅሁፎችን መልቀቅ ጀምሬያለሁ። ከቀን ወደ ቀን አንባቢዎቼም እየበዙ እየሄዱ ነዉ። ኢንተርኔት የምንጠቀመዉ ቢሮ ባሉት ኮምፒዩተሮች ነዉ። በርግጥ ሰዓት እንዳይሻማብኝ እኔ አልጠቀምም። በወረቀት ፅፌ ለነኡስታዝ ሰጥቼያቸዉ እነሱ ናቸዉ በኮምፒዩተር ፅፈዉ ፌስቡኬ ላይ የሚለጥፉት። እኔ በሳምንት እሁድ ባየዉ ነዉ።
ህይወት በመማር እና በማስተማር ታጥራ ነጎደች። መርከዝ ከገባሁ አመት ከአራት ወር አለፈ። አምሪ በየሳምንቱ ከራቀም በአስራአምስት ቀን እየመጣች ትጠይቀኛለች። ዛሬ ወደ መርከዝ መጥታ ትንሽ ከተጨዋወትን በኋላ "ሀቢቤ አሁን ታዋቂም እየሆንክ ነዉ! አሪፍ ሚስት ታገኛለህ! እስከአሁን አግባኝ ያለ
: @dfabF
@dfabF
የማይፋቅ ስህተት
ክፍል አስራስድስት
(ፉአድ ሙና)
.
የኒካህ ዝግጅቱ ተጠናቆ ሙሽራዉ ሙሽሪቷን ይዞ ሄደ። አምሪ ለታሪክ የሚተላለፍ ጉድ ነዉ የሰራችኝ! ወደ ትምህርቴ ተመልሼ ሶስት ቀንም ሳልቆይ የረመዳን ፆም ስለደረሰ ወደ ሰፈራችን መስጂድ ለማሰገድ ተመለስኩ። አሁን ትንሽ ፌስቡክ ላይ በምፅፋቸዉ ትምህርቶች ሰው እያወቀኝ ነዉ። በርግጥ ፎቶዬን ስለማልለጥፍ በአካል አያዉቁኝም። ስሜ ግን እየገነነ መጥቷል። በረመዳኑ ከብዙ የሀይማኖት መምህራን ጋር ያለኝ ትስስር በጣም ጠበቀ። ረመዳን ተጀመሮ በሁለተኛዉ እሁድ መስጂዳችን ዉስጥ የተዘጋጀ የስብከት መድረክ ላይ ስለጓደኝነት ለአስራአምስት ደቂቃ ያህል እንዳስተምር ተጋበዝኩ። ህዝብ በተሰበሰበበት የማስተምርበት የመጀመሪያዉ መድረክ ስለሆነ በደንብ ተዘጋጅቻለሁ። የመስጂዱ ኢማም ለአንድ ሰዓት የጉረቤት መብትን በተመለከተ ካስተማሩ በኋላ መድረክ መሪዉ ስለ ጓደኝነት እንዳስተምር ጠራኝ። መድረኩ ፊት ለፊት ሶስት ካሜራዎች ተጠምደዋል። ዝግጅቱ ላይ ላልተገኙ ሰዎች እና ዉጪ ሀገር ላሉ ኢትዮጵያዉያን ለማስተላለፍ ታስቦ ይመስለኛል። መድረኩ ላይ ወጥቼ በአረብኛ አላህን ካወደስኩና በነብዩ ሙሀመድ(ሰዐወ) ላይ ሰላምታ ካወረድኩ በኋላ ንግግሬን ቀጠልኩ። "የተወደዳችሁ አማኞች፣ ከወንድም ከሴትም ያላችሁ የጌታችን ቅን ባሮች ሰላም በናንተ ላይ ይሁን! ነገ በትንሳኤ ቀን ለቅጣት ተዳርገዉ ከሚቆጩት ሰዎች መካከል አንዱ ማን እንደሆነ ታዉቃላችሁ? ጌታችን በተባረከዉ ቃሉ እንዲህ ይላል" አልኩና ድምፄን አሳምሬ የቁርዓኑን አንቀፅ አነበብኩ። ሁሉም አፉን ከፍቶ ያዳምጣል። ያነበብኩትን በአማርኛ መተርጎም ጀመርኩ። "በዚያ አስጨናቂ ቀን ለቅጣት ከሚዳረጉት ዉስጥ 'ወዮልኝ እገሌን ለምን ጓደኛ አድርጌ ያዝኩ? በርግጥ እዉነታዉን ካወቅኩ በኋላ አጠመመኝ።' የሚሉ አሉ። በምድር ላይ ከመልካምነታቸዉ በጓደኛቸዉ ግፊት የወጡ እና ቅጣት የተረጋገጠባቸዉ ሰዎች ናቸዉ። እስኪ ልጠይቃችሁ..." ስል የፌቨን ጓደኛ ፍቅር ትዝ አለችኝ። ፌቨንን አብረን እንድንተኛ ስጠይቃትና ፌቪ ሄዳ ለጓደኛዋ ለፍቅር ስትነግራት ፤ፍቅር ተይ ይቅርብሽ ብላ የፌቪን ክብር ከማትረፍ ይልቅ ክብሯን የምትነጠቅበትን የሶደሬ ጉዞ አመቻቸች። ምናልባት የፌቪ ጓደኛ ፍቅር መልካም ብትሆን ኖሮ ይቅርብሽ ብላ ባስተወቻት እና የፌቪም ህይወት እንዲህ ባልተቃወሰ ነበር።
ስብከቴን ቀጠልኩ "አዎ ልጠይቃችሁ! ጓደኛችሁ ማነዉ? መልካም ለማድረግ ስትሞክሩ የሚያዳክማችሁ ነዉ ወይስ የሚያበረታችሁ ነዉ? ንገሩኝ እስኪ መጥፎ ነገር ለማድረግ ስትሞክሩ መጥፎ ነዉ ብሎ ያስተዋችኋል ወይስ ያበረታታችኋል? ጓደኛችሁ በመልካም የሚያዛችሁና ከመጥፎ የሚከለክላችሁ ከሆነ እናንተ እድለኞች ናችሁ። በተቃራኒዉ በመጥፎ የሚያዛችሁና ከጥሩ የሚከለክላችሁ ከሆነ ግን የትንሳዔ ቀን 'ወዮልኝ ምናለ ጓደኛ አድርጌ ባልያዝኩት!' ብላችሁ ትፀፀታላችሁ። ዛሬ ስለጓደኛችሁ በደንብ አስቡ!" ብዬ ሌሎችንም የቁርዓን አናቅፅን አንብቤ ካስተማርኩ በኋላ ከመድረኩ ወረድኩ። ገና ተስተካክዬ ሳልቀመጥ ከአጠገቤ የተቀመጠዉ ኡስታዝ "ሀቢቤ ያለንበትን ተጨባጭ በደንብ የሚያስረዳ ዳዕዋ ነበር። የሚቀጥለዉ ሳምንት እኛ መስጂድም ዝግጅት ስላለ በፈለግከዉ ርዕስ ላይ ተዘጋጅተህ ብታስተምር ደስ ይለኛል።" አለኝ። ዳዕዋ ማለት ስብከት ማለት ነዉ። አመሰገንኩትና ግብዣዉን ተቀበልኩ።
.
ስድስት ሰዓት ተኩል አካባቢ የሚሰገደዉ የዝሁር ስግደት ተሰግዶ ሲያልቅ ከሀጂ ጋር ከመስጂድ ወጣን። መኪናዉ ዉስጥ እስክንገባ ድረስ ብዙዎች እየመጡ ያቅፉኝ እና ያመሰግኑኝ ጀመር። እንደምንም ሰውን አልፈን መኪናዉ ዉስጥ ገባን! አምሪ እና ወ/ሮ ለይላ ከሴቶች መስጂድ ከመጡ በኋላ ሀጂ መኪናዉን አስነስተዉ ወደ ቤት መሄድ ጀመርን። አምሪ እየሳቀች "ኡስታዝ ዛሬ በጣም ገራሚ ትምህርት ነዉ ያስተማሩን!" አለችኝ። ወ/ሮ ለይላ እየሳቁ "በቃ አምሪ ልጁ አሰግዶም አስተምሮም ሲወጣ በነገር ወጋ ካላደረግሽዉ አትረኪም አይደል?" አሏት።
ሀጂ እየሳቁ "ባይሆን አምሪ ልጠይቅሽ ጓደኛሽ ማነዉ? ከሀቢቤ ንግግር አልተማርሽም?" አሏት።
አምሪ እየሳቀች "እኔ ጓደኛዬ ሀቢብ ነዉ። እሱ ደሞ በመጥፎ አያዘኝም።" አለች። ሀጂና ወ/ሮ ለይላ ጮክ ብለዉ ሳቁ። መኪናዉ በነሚኪ ሰፈር ጋር ሲያልፍ ፌቨንን ከሚኪ ጋር ወደነሚኪ ቤት መግቢያ አካባቢ ቆማ አየኋት። በደንብ ስመለከታት ያየሁትን ማመን ከበደኝ። ፌቪ አርግዛለች! ሆዷ በጣም ገፍቷል። ሚስኪን ፌቨን! ከማን ይሆን? ትናንት ከኔ ጋር በፍቅረኛነት የጀመረችዉ ሴሰኝነት ዛሬ ለዚህ ሁሉ ኪሳራ ይዳርጋታል ብሎ ማን አሰበ? እወድሻለሁ የሚለዉ ቃሌ ከርካሽ እኔነቴ እንደወጣ መች አወቀች!? ወንድ ልጅ ያላገባትን ሴት እወድሻለሁ ካለ ይህ ንግግሩ ከስሜቱ እንጂ ከልቡ እንዳልሆነ መች ነገርኳት!? ከልቡ ከሆነ እንኳ የማህበረሰቡን እሴት ጠብቆ በፍቅር የመዛለቅ አቅም እንደማይኖረዉ መረዳት እንዴት ተሳናት? ዘላቂ ፍቅር እና መተሳሰብ ያለዉ ትዳር ዉስጥ ብቻ መሆኑን ቤተሰቦቿ ምነዉ ሳያስተምሯት? ወይኔ ፌቪ! የህይወቴ የማትፋቂ ስህተት!
.
በቀጣዩ ሳምንት በኡስታዙ ግብዣ መሰረት ዝግጅታቸዉ ላይ "ወጣቶቻችን የት ናቸዉ?" በሚል አርዕስት ተዘጋጅቼ ለመስበክ ሄድኩ። መስጂዱ ትንሽ ራቅ ያለ ነዉ። በሀጂ መኪና ከአምሪ እና ከወ/ሮ ለይላ ጋር ሆነን ሄድን። መስጂዱ ዉስጥ ስንገባ ለማስታወቂያ የሰሩትን ባነር ተመልክቼ ተገረምኩ። የኔም ስም ሰውን ለማጓጓት በሚመስል መልኩ ተፅፏል።
ዝግጅቱ ከተጀመረ በኋላ አንድ ታዋቂ ዳዒ(ሰባኪ) ወደ መድረኩ ወጥቶ ለአንድ ሰዓት ያክል አስተማረ። ከሱ ቀጥዬ እኔ ወደ መድረኩ ወጥቼ ማስተማር ጀመርኩ።
ትንሽ ካስተማርኩ በኋላ "...በእርግጠኝነት ቤት የምታከራዩ ሰዎች በመካከላችን ትኖራላችሁ አይደል? ቤታችሁን ለማን ነዉ ያከራያችሁት? ወጣቱ የሚባልግበት ቤት የናንተ ቤት ላለመሆኑ እርግጠኞች ናችሁ? ወይስ ስለ ገንዘባችሁ እንጂ ስለማህበረሰቡ ጉዳያችሁ አይደለም? በየሰፈሩ ኦፊስ ተብለዉ የሴቶቻችን ክብር የሚገፈፍባቸዉ ቤቶችን ማነዉ ለባለጌዎች የሚያከራየዉ? እናንተ አይደላችሁም? ስለዚህ ልጆቻችን ተበላሹ ከማለታችሁ በፊት ቤታችሁን አፅዱ! ለብልግና ቤታችሁን አከራይታችሁ የናንተ ልጅ ጨዋ ልትሆን አትችልም! ከልጆቻችሁ ጋር በግልፅ ተወያዩ። ልጃችሁ አንድ ሴት አይቶ ከወደደ ወይም አይታ ከወደደች በግልፅ መጥቶ እንዲነግራችሁ የሚያደርግ ማንነት ይኑራችሁ። ልጆቻችሁን ትዳርን አክብዳችሁ እያሳያችሁ ለዝሙት አታመቻቿቸዉ። ሀብታሞች ወጣቱን አጋቡ! በገንዘብ ደግፉ!..." ብዬ የማህበረሰቡ ወቅታዊ ችግር ናቸዉ ብዬ ያሰብኳቸዉን አርዕስቶች ዳሰስኩ። ከመድረኩ እንደወረድኩ ከፊት ለፊት ተቀምጠዉ የነበሩ አንድ ሽማግሌ መጥተዉ ግንባሬን ሳሙኝ። ከመስጂዱ ስንወጣ ሰው ሰላም ለማለት ከበበኝ። ሀጂ በግርምት ቆመዉ ያዩኛል። ሰላም ብዬ ስጨርስ ሌላ ሰዉ ሳይዘኝ ፈጠን እያልኩ ወደ ሀጂ መኪና ገባሁ። አሁን በጉጉት የምጠብቀዉ የአምሪን ነቆራ ነዉ። አምሪናወ/ሮ ለይላ መኪናዉ ዉስጥ እንደገቡ ሶስታችንም አምሪ ምን እንደምትል ለመስማት ወደሷ ዞርን። አምሪ ወዲያዉ "ሳታገባ አግቡ ምናምን ትላለህ አይደል?" አለች። ሁላችንም ሳቅን። ሀጂ ትንሽ እንደማሰብ አሉና "ሀቢቤ ግን ታዋቂነቱ ሲበዛ ፈተናዉ ከባድ ነዉ። ኒካህ ማሰር አለብህ። ቆይ ጥሩ ልጅ እፈልግልሀለሁ።" አሉኝ። ዝም ብዬ ሳቅኩኝ! ልጃቸዉ እያለች የምን ፍለጋ መዉጣት ነዉ!? ሀጂ አምሪን እያዩ "ምነዉ ልክ አይደለሁም
እንዴ?" አሏት። አምሪ እያየችኝ ሳ

ቋን ለቀቀችዉ። ስትስቅ አሳቀችኝ። ሀጂ "ምን ያስቃችኋል? እዉነቴን እኮ ነዉ።" አሉ። ወ/ሮ ለይላም ሀሳባቸዉን ደገፉ። እኔና አምሪ ዝምታን መረጥን።
.
ቤት ገብተን ትንሽ እንደቆየን አምሪ "ሀቢቤ ፌመስ ሆነሀል!" አለችና በስልኳ ስለኔ ፌስቡክ ላይ የተፃፉ ነገሮችን አሳየችኝ። ሳያቸዉ ዛሬ ካስተማርኩት ንግግሬን ቆርጠዉ በፎቶ መልክ ሰርተዉ ከስሩ ወጣቱ ዳዒ ሀቢብ ከማል ብለዉ ፅፈዉበታል። ዳዒ ማለት ሰባኪ ማለት ነዉ። የባለፈዉ ትምህርቴንም የለቀቁ ታዋቂ ገፆችን አምሪ አሳየችኝ። በራሴ የፌስቡክ አካዉንት ስገባ 20,000 ተከታይ አፍርቻለሁ። ገረመኝ።
.
ረመዳኑ ሊያልቅ ሲል ሀጂ ማታ ላይ በተሰበሰብንበት በግልፅ የሴት ምርጫዬን ጠየቁኝ። እየተሽኮረመምኩ "እርሶን ደስ እንዳልዎት" አልኳቸዉ። በጣም ጨነቀኝ! ሀጂ ሌላ ሴት አምጥተዉ ልዳርህ ካሉኝ ምን ሊዉጠኝ ነዉ? በነጋታዉ አምሪን "ምን ይሻላል?" አልኳት። ለሀጂ እንድንነግራቸዉ ነገረችኝ። የዛኑ ቀን ማታ ሀጂን ልናናግራቸዉ ወሰንን። ማታዉን ሁላችንም ባለንበት ፍርሀት እየተናነቀኝ "ሀጂ የሚድሩኝን ሴት እኔዉ ብጠቁሞት ምን ይመስልዎታል?" አልኳቸዉ።
ሀጂ ፈገግ ብለዉ "እንደዉም የወደድካት ካለችማ ስራም ይቀልልናል።" አሉኝ።
ልነግራቸዉ ሳመነታ ሀጂ አንዳች ነገር እንዳስታወሱ ነገር ፊታቸዉን ቀያየሩና "ቆይ ከሱ በፊት እጠይቅሀለሁ እያልኩ ረስቼዉ የነበረ አንድ ነገር አለ። ከሁለት አመት በፊት ወደ መርከዝ ስትገባ ስልክ አልያዝክም ነበር። ከዛም ዉስጥ ስልክ ይዘህ ተገኝተህ ተቀምተሀል። ማነዉ ስልክህን የሰጠህ? መችስ አትዋሸኝም።" አሉኝ። ለሀጂ አምሪያ ናት ያመጣችልኝ ማለት ይከብዳል። ለኔዉ ብላ ስልክ ባቀበለችኝ እሷን ማስጠቆር አልፈለግኩም።
"ሀጂ ይሄ ጥያቄ ይቅርብኝ!" አልኳቸዉ።
ሀጂ እንደመቆጣት እያሉ "ማነዉ እኔ እንድትስተካከል ስጥር ስልክ እየሰጠ ከትምህርትህ ያዘናጋህ? ንገረኝ!" አሉ። አምሪ ስልኩን የሰጠችኝ የለመድኩትን በአንዴ መተዉ እንደማልችል ተረድታ እንጂ ልታዘናጋኝ አይደለም።
ዝም ስላቸዉ "ሀቢብ ንገረኝ! አሊያም እንጣላ!" አሉኝ።
አምሪን አየኋት። ከአባቷ ጋር እንድትጣላማ ምክንያት አልሆንም።
የሞት ሞቴን "ሀጂ በቃ ከኔ ጋር ቢጣሉ ይሻላል ልነግርዎት አልችልም።" አልኳቸዉ።
"ከምር? እርግጠኛ ነህ አትነግረኝም?" አሉኝ።
"ሀጂ ይቅርታ! መናገር አልችልም። ለእርስዎም መልካሙ ባልነግርዎት ነዉ።" አልኩ።
ሀጂ ደግመዉ "እርግጠኛ ነህ?" አሉኝ። እራሴን አጠንክሬ "አዎን ይቅርታ ሀጂ!" አልኳቸዉ።
ሀጂ "እንግዲያዉስ ..." አሉና በረዥሙ ተንፍሰዉ በድጋሚ "እንግዲያዉስ" አሉና ዝም አሉ።
አምሪ አላስቻላትም መሰለኝ "አቢ በቃ ከዚህ በላይ አታስጨንቀዉ!" አለች።
ሀጂ ዝም ብለዉ አዩኝ! ምን ይሉኝ ይሆን? እንቆራረጥ ይሆን? በጣም ፈራሁ። ከነሱ በቀር ምድር ላይ ማን አለኝ? አይ ዱኒያ! ሁሉ ነገርሽ ፈተና! አልቅሰን ሳንጨርስ ደስታ! ስቀን ሳንጠግብ ጭንቀት! ግራ የገባሽ አለም!
.
ይቀጥላል...❤️❤️❤️
Don't forget 👇👇👇👇👇👇👇
#like & #share 👍❤️👍❤️👍❤️
@dfabF
@dfabF keep on shari

የማይፋቅ ስህተት
ክፍል አስራሰባት
(ፉአድ ሙና)
.
ሀጂ ዝም ማለታቸዉ ቤቱ ዉስጥ ትልቅ ጭንቀት ፈጠረ። አምሪያ ስልኩን ሰጥታኛለች ብዬ ብነግራቸዉ በጣም የሚወዷት አባቷ ሊያዝኑባት ነዉ። በፍፁም አልነግራቸዉም! እነሱ እንደተዋደዱ ይኑሩ! ትናንት መጥቼ ህይወታቸዉን መበጥበጥ አልፈልግም። ሀጂ ከረዥም ዝምታ በኋላ "ሀቢቤ የትምህርት ቤቱን ቆጣሪ ለሊት ላይ ላለመማር ብለህ አንድ ቀን አጥፍተህ ተኛህ! በቀጣዩ ቀን አጥፍተህ ስትተኛ በቀላሉ ተያዝክ! ማን ያጋለጠህ ይመስልሀል? የነገርከዉ ሰዉ ነበር?" አሉኝ። ዛሬ ሀጂ ትምህርት ቤት ስገባ ከመስተካከሌ በፊት የሰራኋቸዉን ጥፋቶች ለምን እንደሚያነሱ ግራ ገብቶኛል። የድሮዉ ስህተት መሆኑን አምኜ ተስተካክዬ የለ እንዴ!
አንገቴን እንደደፋሁ "ሀጂ ሁሉም አልፏል! ለምን ይቅር ብለዉኝ አናልፈዉም?" አልኳቸዉ።
ሀጂ ሳቁ! ለምን እንደሳቁ አላዉቅም። ፊታቸዉ በፈገግታ እያበራ "ዛሬ የማታዉቃቸዉን ብዙ ነገሮች እነግርሀለሁ!" አሉኝ። አምሪ እየሳቀች ታየኛለች። ምንድን ነዉ?
ሀጂ ቀጠሉ "ሀቢቤ አንተን የተስተካከለ ሰዉ ለማድረግ ወደ ሀይማኖት ትምህርት ቤት እንድትገባ ሀሳቡን ያቀረበችዉ አምሪያዬ ነበረች። ስልኩን ስትሰጥህም ለኔዉ ነግራኝ ነዉ። የነበርክበትን ጨለማ ከኔ ይልቅ አምሪያዬ በደንብ ትረዳዉ ነበር። ስልኩን የሰጠችህም የምታደርገዉን እያንዳንዱን እንቅስቃሴህን ለመከታተል እንዲረዳ ብላ ነበር። ቆጣሪ አጥፍተህ የተኛህ ጊዜ ጠዋቱን ለአምሪያዬ እንደ ጀብዱ ነገርካት። እሷ ወዲያዉ ለኡስታዞችህ ደዉላ ነገረቻቸዉ። በቀጣዩ ቀን ስታጠፋ በቀላሉ ቆጣሪዉ ተመልሶ ላንተም ማስጠንቀቂያ ተሰጠህ። ትንሽ ትምህርትህ ላይ ትኩረት ማድረግ ስትጀምር አምሪ ኡስታዞችህ ስልክህን እንዲቀሙህ አደረገች። አሁን እንዲህ ትልቅ ሰዉ ከሆንክ በኋላ ለኔ የምስጋና ደብዳቤ ስትፅፍ ለአምሪያ በስጦታ ደብዳቤህን የሰጠኋትም እዚህ ደረጃ የመድረስህ ምክንያት ከኔ ይልቅ እርሷዉ ስለሆነች ነዉ። ከፈረስክበት በድጋሚ ሰርታሀለች።" አሉና አምሪያን ዞር ብለዉ አይተዋት ፈገጉ።
የሆነ የአንስታይን ቤተሰብ እየመሰለኝ ነዉ። ሁሉም ነገር ስሌት? ሲያበሽቁ!
ሀጂ ቀጠሉ "አምሪያዬን እንደምትወዳት የነገርካት ቀን ፣ ሁኔታህ ትንሽ ስላሰጋት ነግራኝ ነበር። ሊያሳስቷችሁ ከሚችሉ ነገሮች በደንብ ተጠንቅቃ እንድታስተካክልህ ያዘዝኳት እኔዉ ነኝ። ከተስተካከልክ በኋላ ከአምሪ ጋር መኳረፍ ስትጀምሩ እሷም እንደወደደችህ ገባኝ። አምሪያዬን ማግባት ፈልገዉ ሶስት ሰዎች አናግረዉኝ ነበር። እሷን ስጠይቃት አልፈልግም አለች። ይሄ ደግሞ እንደምትዋደዱ በደንብ አስረገጠልኝ። ባለፈዉ መኪና ዉስጥ ልዳርህ ስል ያሰብኩልህ አምሪያዬን ነበር። ሁለታችሁም ተያይታችሁ ተሳሳቃችሁ! ለማንኛዉም አሁን ስልኩን ማን ሰጠህ ብዬ ያስጨነቅኩህ አሳልፈህ ትሰጣታለህ ወይስ አትሰጣትም የሚለዉን ለማየት ነበር። አንተ ግን አሳልፈህ አልሰጠሀትም። ለአባቷ አሳልፈህ ያልሰጠሀት ለማንም አሳልፈህ ትሰጣታለህ ብዬ አላስብም!" አሉ። በጣም በሸቅኩ። አምሪ ሰጥታኛለች ብዬ ብናገር ኖሮስ? ፈተናዉን ብወድቅስ? አምሪን ሊያሳጡኝ ነበር? ያበሽቃሉ። ፈተናዉን በማለፌ ልደሰት ወይስ ልብሸቅ?
አንገቴን ሰብሬ ተሽኮረመምኩ። ወ/ሮ ለይላ እየሳቁ "እንግዲህ ምን ቀረ? የኒካሁ ቀን ይቆረጥ እንጂ!" አሉ።
ሀጂ ፈገግ እንዳሉ "ኒካሁ ትምህርት ቤቱ ዉስጥ ኡስታዞቹ ባሉበት ይደረጋል።" አሉ። የሆነ ህይወቴ ዉስጥ አንድ ነገር ሲሰምር ተሰማኝ።
ሀጂ እንደመተከዝ አሉና "ሀቢቤ ሌላዉ ያልነገርኩህ ነገር ስለእናትህ ነዉ። እናትህ ከሆስፒታል ከወጣች በኋላ ሞተች። ከሆስፒታል ግን የወጣችዉ ተሽሏት ሳይሆን ዶክተሯ መፍትሄ የላትም ስላለች ነበር። ዶክተሯ ላንተ ብትነግርህ ልትረበሽ ስለምትችል እኔን ቢሮዋ አስጠርታ ነገረችኝ። እናትህ ጉበቷ ሙሉ ለሙሉ ከጥቅም ዉጪ ሆኖ ነበር።" አሉኝ።
እኔም ጥያቄ የሆነብኝ እናቴ ተሻላት ተብሎ ከወጣች በኋላ መሞቷ ነበር። ዛሬ መልሱን አገኘሁ። ሁሉም አልፏል።
.
አምሪያ በህይወቴ ዉስጥ ያላት ሚና በጣም ከፍ ያለ መሆኑን ተረዳሁ። አምሪያ መልካም አድርጋ ስለሰራችኝ እገባታለሁ። ለሷ ያለኝ ክብር ጨመረ። ግን ምድር ላይ ካሉት ሴቶች ምን ያህሉ ናቸዉ የባላቸዉን ክፍተት ሞልተዉ
ለሙሉነቱ የሚለፉት? አንዳችን ያለአንዳችን እንደማንሞላ የተረዱ፤ተረድተዉም ከመነቃቀፍ ይልቅ በመደጋገፍ ያመኑት ምን ያህል ይሆናሉ? አምሪያዬ እኮ ገና ባሏ ሳልሆን ከዘቀጥኩበት ወጥቼ ሰዉ መሆን እንድችል ለፍታልኛለች። የአምሪያ አይነት ሚስት ሁሉም ሰዉ ቢኖረዉ ተመኘሁ!
ሀጂ እንደሚድሩን ከነገሩን አስራአምስት ቀናት አለፉ። እኔም ወደ ትምህርቴ ተመልሻለሁ። የትምህርት ቤቱ ታላቅ ሸይኽ ጋር ብስለት የሚጠይቁ የሀይማኖት ህግጋትን እየተማርኩ ነዉ። ሀጂ መጥተዉ "ሀቢቤ የኒካህ ስነ ስርዓቱን ከወር በኋላ ጥቅምት ላይ ብናደርገዉስ?" አሉኝ። አምሪ የተፈቀደች የምትሆንልኝን ቀን ብናፍቅም ትምህርት ላይ ስለሆንኩ ብዙም አልተፈታተነኝም። በሀሳባቸዉ ተስማማሁ። ከሳምንት በኋላ እሁድ ቀን ትምህርት ቤታችን ልዩ የጉብኝት ዝግጅት አዘጋጅቶ ስለነበር ሆስፒታሎችን እና የቀብር ቦታዎችን በመጎብኘት ነብሳችንን ለማስተማር በጉብኝቱ ላይ ከነነስሩ ጋር ሆነን ተሳተፍን። ነስሩ ትምህርት ቤቱ ዉስጥ ኡስታዝ ሆኗል። ከኔ ጋር ከፍ ያሉ የሀይማኖት ድንጋጌዎችን እየተማርን ነዉ። እኔም በከፊል አስተምራለሁ።
የጉብኝት ስነ ስርዓቱ ቀጥሎ አንድ በሱስ የተጠቁ ግለሰቦች የሚያገግሙበትን ሆስፒታል መጎብኘት ጀመርን። ትንሽ እንደጎበኘን አንድ የማዉቀዉ የመሰለኝን ሰዉ ተመለከትኩ። የማዉቀዉ ቢመስለኝም በቀላሉ ላስታዉሰዉ አልቻልኩም። አልፌዉ ሄጄ ሌሎች ቦታዎችን እየጎበኘሁ ወዲያዉ ማንነቱን አስታወስኩ። እናቴ የታመመች ጊዜ "ሀቢቤ አሁንስ የትም ብትዘል የማታመልጠዉ አምላክ መኖሩ ገባህ?" ምናምን ብሎ አፉን የከፈተብኝ ልጅ ነዉ። የዛኔ ሁለት ሆነዉ ነበር የተናገሩኝ። ልመታቸዉ ፈልጌ ሀዘን ላይ ስለነበርኩ አልፌያቸዋለሁ። ሲገርም! ትናንት ከፈጣሪ የጀነት ማረጋገጫ የተሰጠዉ ይመስል ራሱን አፅድቶ እኛ የጀሀነም ተብለን የተፈረደብን ይመስል ሲያንኳስሰን የነበረዉ ሰዉ በሱስ ተተብትቦና ዘቅጦ ማገገሚያ ገባ?! ያንኳሰሰኝ እኔ ህዝብ የማስተምር ሰባኪ ሆንኩ! ፈጣሪ ቀናትን እንዴት እንደሚያዘዋዉራቸዉ ሳይ ተደነቅኩ። ብዙዎች መመራት ከፈጣሪ እንጂ ከሰዉ እንዳልሆነ ሳይረዱ ይቀሩና እራሳቸዉን ሲያፀዱ ተሽመድምደዉ ይወድቃሉ። እጄን ከፍ አድርጌ ጌታዬ እኔንም እሱንም እንዲምረን እና እሱንም ካለበት የሱስ በሽታ ነፃ እንዲለዉ ለመንኩ።
ጉብኝቱን ጨርሰን ስንወጣ አምሪ ስልክ ደወለችልኝ። አሁን እራሳችንን በአግባቡ መቆጣጠር እንችላለን ተብሎ ስለታሰበ እና በከፊልም ወደ ማስተማሩ ስለገባን ስልክ እንይዛለን።
ስልኩን አንስቼ "እጩ ሚስት!" አልኩ።
"እጩ ባል ገራሚ ዜና አለ።" አለችኝ።
እየሳቅኩ "ጋብቻዉ ነገ ነዉ ተባለ?" አልኳት።
"አዛ! ከሱ ሌላ!" አለችኝ።
"አንቺን ከማግባት ሌላ ዜና የሚሆን ምን አለ?" አልኳት።
"ሰሚራ አረገዘች ፤ አብዱ በደስታ ሊያብድ ነዉ! ተዓጀብ!" አለችኝ። ተዓጀብ ያለችዉ ተገረም ለማለት ነዉ።
በጣም ደስ አለኝ። አላህ ምን ይሳነዋል? ምንም! ህይወቷን አበላሸሁት ብዬ በጣም ተፀፅቼ ነበር። ልጅ ስታጣ ደግሞ በጣም አሳዝናኝ ነበር። አብዱ ልጅ በጣም ይወዳል። ምስጋና ለአላህ ይሁን!
"ሀቢቤ ማታ ቤታቸዉ ሰደቃ ጠርተዉናል። እንዳትቀር!" አለችኝ።
እንደ ህፃን እየቦረቅኩ "አልቀርም አምሪያዬ!" አልኳት።
.


ታ ወደ ቤት እየተመለስኩ ከፌቨን ጋር መንገድ ላይ ተገናኘን። ሆዷ እንደገፋ ነዉ።
ናፍቆት በወገረዉ ድምፅ "ሀቢቤ ..." አለችኝ።
ወደ ሆዷ እየጠቆምኳት "ፌቪ ምንድነዉ የማየዉ?" አልኳት።
አይኗን እንባ እየሞላዉ "አረገዝኩ እኮ!" አለችኝ።
"አዉቃለሁ የማን ልጅ ነዉ? " አልኳት።
ፌቪ አንገቷን እየሰበረች "እሱማ የአብነት ነበር!" አለችኝ።
"እንዴት? ማለቴ ከአብነት ጋር ..." አልኩና የምናገረዉ ግራ ሲገባኝ ዝም አልኩ።
"አንድ ቀን ጠጥተን ነበር እና ሚኪናኤልዳና ፊት ለፊታችን ሲተኙ አብነት አላስቻለዉም እኔን ተኛኝ! እኔ ራሴን አላዉቅም ነበር!" አለችኝ።
"ልታሳድጉት አስባችሁ ነዉ ያረገዝሽለት?" አልኳት።
"እኔ ማታ ላይ ምን እንዳደረገኝ በደንብ አላወቅኩም ነበር። ከሁለት ወር በኋላ ምልክቶች ማየት ስጀምር ኤልዳና ናት የነገረችኝ! ደንግጬ ስጠይቀዉ ተሳስቼ ነዉ እናሳድገዋለን ምናምን አለኝ። የሱን ልጅ ለማሳደግ አልፈልግም ነበር! እንዳላስወርደዉ ደግሞ ገንዘብ አጠረኝ። ዛሬ ነገ ስል ሆዴ በጣም ገፋ! ሆዴ መግፋቱን ሲያይ እሱ ወደ ክፍለሀገር ሄዶ ጠፋ! አሁን እንዳላስወርደዉ ደሞ በጣም ገፍቷል!" አለችኝ። አብነት ክፍለሀገር ቤተሰብ እንዳለዉ አዉቃለሁ። በጣም አሳዘነችኝ። ለሁሉም ስቃዮችዋ ተጠያቂዉ እኔ ነኝ።
ምላሴ እየተሳሰረ "እና ምን አሰብሽ?" አልኳት። ፌቪ ከአይኗ የእንባ ዘለላዎች እየተሽቀዳደሙ እየወረዱ "ምን አማራጭ አለኝ? መዉለድ ነዋ!" አለችኝ።
"ቤተሰቦችሽ ምን አሉ?" አልኳት።
የፌዝ ሳቅ ሳቀችና "ከቤተሰቤ ጋር ከተቆራረጥኩ እኮ ስምንት ወር አለፈኝ። ካልተስተካከልሽ ብለዉ ጨቀጨቁኝ። እኔ ደሞ አልቻልኩም። ሲመራቸዉ አይንሽን ለአፈር አሉ። ከነሱ ጋር ባልቆራረጥማ ገንዘብ መች ያጥረኝ ነበር!?" አለችኝ።
በቅርበት እሷን የማግዝበትን መንገድ ማሰብ ጀመርኩ። ለማንኛዉም ብዬ ስልኳን አጥፍቼዉ ስለነበር በድጋሚ ተቀብያት ሄድኩ። አሁን መከራ የመከራት ይመስለኛል። መልካም ሰዉ ለመሆን የሚረዳት ብታገኝ ትስተካከል ይሆናል።
.
እነሰሚራ ቤት የተዘጋጀዉን የሰደቃ ድግስ ታደምኩኝ። ሰሚራ በጣም ደስተኛ ሆናለች። አብዱ ደስታዉ እንዳይገድለዉ ያሰጋል። አምሪ እያየችኝ ትስቃለች።
ከነሰሚራ ቤት ከወጣን በኋላ አምሪ "ሀቢቤ ከመጋባታችን በፊት ላዉቃቸዉ የሚገቡ ነገሮች ካሉ ንገረኝ!" አለችኝ።
ምን ብዬ እንደምነግራት ግራ ስለገባኝ "ካንቺ እንጀምር!" አልኳት።
ሳቅ አለችና "በህይወቴ ፍቅረኛ የሚባል ነገር አላዉቅም! እወድሀለሁ! ሌላ ምን ልንገርህ?" አለችኝ።
ወዲያዉ ሶደሬ የተገናኘንበት ቀን ትዝ አለኝና "ያኔ ለምን ሶደሬ ቤተሰቦችሽ ሳያዉቁ ሄድሽ?" አልኳት።
ፈገግ አለችና "ጓደኛዬን አጉል እወድሻለሁ የሚላት ልጅ ነበር። እሷም ትንሽ ተንሸራታለት ነበር። እናልህ ፈተና ሲያልቅ አዲስ አበባ ዉስጥ ለመዝናናት አስበን በመሀል ልጁ ሶደሬ ካልሄድን ብሎ ወጠራት። ስታማክረን አንሄድም ስንላት ከሱ ጋር ለብቻዋ ለመሄድ ወሰነች። ይሄ ከሆነ ደግሞ ልጁ ያልሆነ ነገር ያደርጋታል ብለን ስለፈራን እሷኑ ለመታደግ ስንል ለመሄድ ወሰንን። እናም ቤት ሳልናገር ሄድኩ። ቤት ቢያዉቁ ቦታዉን ስለማይወዱት ከእነሱ ጋር እንጂ ለብቻዬ መሄድ አይፈቅዱልኝም ነበር። ሌላ ምን ልንገርህ?" ብላ እየተፍለቀለቀች አፈጠጠችብኝ።
የኔ ታሪክ ከሷጋር ሲወዳደር ምን ያህል የዘቀጠ እንደሆነ እያሰብኩ "እኔንጃ!" አልኳት።
"አንተስ ፍቅረኛ ኖሮህ ያዉቃል?" አለችና በጣም ሳቀች።
ሳቋን ችላ ብዬ "ከመስተካከሌ በፊት ሁሉ ነገሬ የዘቀጠ ነበር። ምን ብዬ እንደምነግርሽ አላዉቅም!" አልኩና ዝም አልኩ።
"ሀቢቤ ከሰላም ጋር ተኝተሀል አይደል?" አለችኝ።
ድንግጥ ብዬ "እንዴት አወቅሽ?" አልኳት።
ሳቀችና "የክፍላችን ልጅ ነበረች። እናትህን ስናስታምም የአራት ሴቶች ፎቶ ከቁምሳጥንህ ዉስጥ አግኝቼ የሷን ብቻ ነጥዬ ማናት ያልኩህ ስለማዉቃት ነበር። አንተ ግን የክፍል ልጅ ናት ብለህ ዋሸኸኝ። አንተ ከተዉካት በኋላ ሰላም ተፀፅታ ያደረጋችሁትን ሁሉ ነግራን ነበር! እዚህ ሰፈር የገባን ሰሞን ሆነ ብዬ እንጨት እያወጣሁ አስፈልጥህ፣ዉሀ በጀሪካን አሸክምህ የነበረዉ እንጨት አስፈልጎኝ ወይም ቧንቧችን የዉሀ መቀነሻ ሳይኖረዉ ቀርቶ ሳይሆን የሰላምን እልህ
ን። እኔ ሀጂ የሰጡኝን ሀላፊነት ከትምህርቴ ጋር ደርቤ እያስኬድኩ ነዉ። አምሪ የህክምና ትምህርቷን እየተከታተለች ነዉ። የሶስተኛ ዓመት ተማሪ ናት። ማታ ማታ ማጥናት ስትፈልግ ወተትእናቡና እያፈላሁ ማኪያቶ እሰራላታለሁ። እሷ አምሽታ የምታጠና ቀን እኔም ስፅፍ አመሻለሁ። አሁን ፌስቡክ ላይ መቶ ሺህ ተከታይ አፍርቼያለሁ። ብዙ ቦታዎች እየዞርኩ አስተምራለሁ። አንዳንዴ አምሪ ሳሎን ተቀምጣ እያነበበች እንቅልፍ ይዟት እብስ ይላል። እንደህፃን ልጅ እቅፍ አድርጌ ወደ አልጋዉ እወስዳትና አስተኛታለሁ። ከዛም ረዥም ሰዓት ቆሜ አያታለሁ። ይህቺን የመሰለች ሴት አገባለሁ ብዬ በህልሜ እንኳ አስቤ አላዉቅም። የክፍተቴ ሁሉ መሙያ! የኔ ውብ! ትዳር ግን ምን የሚሉት ዉብ ጥምረት ነዉ? በተጋባንባቸዉ ቀናት ዉስጥ ያጣጣምኳቸዉን ደስታዎች ቆጥሬ አልዘልቃቸዉም። ሀጂ እና ልጆቻቸዉ በኛ ትዳር በጣም ደስተኛዎች ናቸዉ።
.
ከአምሪ ጋር መኖር ከጀመርን አንድ ወር ሞላን። ዛሬ ማታ ሶስት ሰዓት ሲል ቤት ገባሁ። አምሪ ነገ ፈተና ስላላት እያጠናች ነዉ። እራት አቀራርባ ስለነበር እጃችንን ታጥበን በላን። አምሪን ማጉረስ በራሱ ትልቅ ደስታ አለዉ። የኔ ሁሉነገር! የሁልጊዜ ንግስቴ! የንግስናዬ መሟላት ምክንያት! ምግቡን እየተጎራረስን በልተን እንደጨረስን ወደ ማዕድቤት ሄድኩ። ይዤ የመጣሁትን ወተት ላፈላ ማንቆርቆሪያዉ ዉስጥ ስገለብጥ አምሪ መጥታ "ሁቢ ተወዉ እኔ አፈላለሁ።" አለችኝ። አይሆንም ብዬ ወደ ጥናቷ መለስኳት። ተመልሳ ንባቧን ቀጠለች። ወተቱን አፍልቼ ስጨርስ ወደ ሳሎን ወስጄ አቅርቤላት እኔም ማንበብ ጀመርኩ። በመሀል የአምሪ ስልክ ብልጭ ብሎ ጠፋ። የፅሁፍ መልዕክት ገብቶላት ነዉ። ከፈተችዉና ካነበበችዉ በኋላ ወደኔ አዙራ አሳየችኝ። "ታንክስ ፎር ኦል አምሪ! በት ፎር ሚ ኢትስ ሶ ሀርድ ቱ ሊቭ ኢን ዲስ ዎርልድ! ፋር ዌል ቱ ዩ ሲስ!" ይላል።
ግራ እየተጋባሁ "ከማን ነዉ?" አልኳት።
አምሪ እንባዋ ከአይኗ እየወረደ "ሀቢቤ ፌቨን ናት!" አለችኝ።
የሆነ ነገር ሰዉነቴን ነዘረኝ። ግራ እየተጋባሁ "ማለት ምን ልታደርግ ነዉ?" አልኳት።
አምሪ እንባዋን ለመጥረግ እየሞከረች "ሀቢቤ መልዕክቷ እኮ እዚህ ምድር ላይ መኖር ከብዶኛል ደህና ሁኚ ነዉ የሚለዉ!" አለችኝ።
"እና ይሄ ምድር ከከበዳት የት ልትሄድ ነዉ?" ካልኩ በኋላ ሳስበዉ የመልዕክቱ ትርጉም ገባኝ።
ከወንበሩ ተፈናጥሬ እየተነሳሁ "እናቷ ጋር ደዉይ አምሪ!" አልኩ።
አምሪ ደወለችና ስልኩን ስፒከር ላይ አደረገችዉ። ስልኩ አይነሳም። ፌቨን ጋር ደወለች። ስልኳ ዝግ ነዉ። በጣም ተጨነቅን። ደግሞ በጣም መሽቷል። አራት ሰዓት ተኩል ሊሆን ነዉ። የነፌቪ ቤት ከኛ ቤት ይርቃል። ስልኬን አዉጥቼ ሚኪያስ ጋር ደወልኩ። ሚኪ አንስቶት "ወዬ ሀቢቤ?" አለ።
"ፌቪን አግኝተሀታል?" አልኩት።
እንቅልፍ በያዘዉ ድምፅ "ፎንቃዋ አገረሸብህ እንዴ?" አለ።
ምርር እያለኝ "ሚኪ ፌቨን ሰላም አትመስለኝም። ማግኘት የምንችልበት መንገድ ካለ ንገረኝ!" አልኩት።
"በቃ ኤልዲ ጠዋት ሄዳ ያለዉን ነገር ትነግርሀለች።" አለኝ። እስከጠዋት እንዴት እንደምንሆን አላዉቅም።
አምሪ ማጥናት ከበዳት። እኔም ደነዘዝኩ። ከአምሪ ጋር ተያይዘን ወደ መኝታችን ሄድን።
አምሪ ትንሽ ለ

መተኛት ሞከረችና "ሀቢብ!" አለችኝ።
እጆቼን ወደ ጉንጮቿ እየወሰድኩ "ወዬ የኔ ቆንጆ!" አልኳት።
እጆቼን በእጆቿ እየያዘች "ፌቨን የሆነ ነገር ብትሆንስ?" አለችኝ።
ግንባሯን ሳምኳትና "እኔንጃ አምሪ! ተኚ በቃ።" አልኳት።
ሁለታችንም ለመተኛት ሞከርን። መተኛት ግን አልቻልንም። መጨረሻ ላይ ሁለታችንም ከመኝታችን ተነስተን ከተጣጠብን በኋላ ለፌቨን ዱዓ ማድረግ ጀመርን። መጥፎ ነገር እንዳያገኛት ተመኘን። ፀሎት እያደረግን ቆይተን ወደ መኝታችን ስንመለስ ደክሞን ስለነበር ተቃቅፈን የእንቅልፍን ታንኳ ተሳፈርን።
የንጋት ስግደት ሲደርስ ከእንቅልፌ ባነንኩ። ሌላ ጊዜ ዘጠኝ ሰዓት ነበር የምነቃዉ! ዛሬ በጣም ስላመሸን እንቅልፍ ይዞኝ ጠፋ። አምሪን ቀስቅሼያት እኔ ወደ መስጂድ ሄድኩ። ከመስጂድ ስመለስ አምሪ ቤቱን ፏ አድርጋ ጠበቀችኝ። ቤትን በጠዋቱ ንቁ ማድረግ ከቤተሰቧ የወረሰችዉ ድንቅ ዉርስ ነዉ። ቁርስ በልተን እንደጨረስን አምሪ "እስኪ ሚኪያስ ጋር ደዉልለት!" አለችኝ። ደወልኩ። ሚኪ ስልክ አያነሳም። አምሪ ጠዋት ፈተና ስለነበራት በጊዜ መዘገጃጀት ጀመረች። ሚኪ ጋር በድጋሚ ስደዉል ስልክ አያነሳም። አምሪን ተረጋግታ ፈተናዋን እንድትፈተን አደራ ብዬ ግንባሯን ሳምኳት። "እሺ!" አለችኝና ወደ ትምህርት ቤቷ ሄደች።
ሶስት ሰዓት ሲል ሚኪ ደወለልኝ። ሳነሳዉ ኤልዳና ናት "ሀቢቤ ፌቨን ሞታለች!" አለችኝ።
ግራ እየተገባሁ "ሞት ማለት?" አልኳት።
"ራሷን አሰናብታለች። አዝናለሁ።" አለችኝ።
ልቤ በጣም ተሸበረ። ትናንት እንደቀልድ ከንፈሯን የሳምኳት ሚስኪን፣ ከንፈሯ ላይ የነበረዉ ልቧ ተሸርሽሮ፤ ክብር መስሏት አብራኝ ተንከባለለች። መሳሳቴ ሲገባኝ በቃኝ ብዬ ተመለስኩ። ስመለስ ግን አብራኝ መመለስ ከበዳት። ብዙ ስቃዮችን አሳልፋ ህይወቷ ሊስተካከል ነዉ ስንል ስነ ልቦናዋ ተረጋግቶ እንደገና መቆም ከበደዉና ተሸነፈች። የሞቷ የመጀመሪያዉ ምክንያት ደግሞ እኔዉ ነኝ። ሚስኪን ፌቪ!
.
የተሰማኝን ስሜት ስም አጣሁለት። በጣም ተረበሽኩ። ቤቴ ጨነቀኝ። የግቢዉን በር ከፍቼ በር ላይ ቆምኩ። ሰዉ በመንገዱ ላይ ይተላለፋል።ወደ ሀጂ ቤት ስዞር በሩ ላይ በኩራት ተጀንኖ የቆመዉን ዛፍ ተመለከትኩት። እኔናአምሪ ነበርን የተከልነዉ። የዛኔ ሀጂ ያሉን ትዝ አለኝ። "መልካምን ከዘራችሁ ነገ የምታጭዱት መልካምን ነዉ። መጥፎን ከዘራችሁም በተመሳሳዩ!" ነበር ያሉን። ይሄ ዛፍ ዛሬ ትልቅ ሆኖ ጥላ ሆነ። ፌቪ ላይ የዘራሁት መጥፎ ስራዬ ደግሞ በደንብ አብቦ ህይወት አጠፋ! እኔ ማነኝ? መልካም ሰዉ ነኝ ወይስ መጥፎ? አላውቅም። ወደ ቤት ገብቼ ማሰብ ጀመርኩ።
አምሪ ከፈተና ስትመለስ ከቤት አልወጣሁም።
"ሁቢዬ ፈተናዉ ቀላል ነበር።" አለችና ተጠመጠመችብኝ። አቅፌያት አለቀስኩ።
እንባዬን እየጠረገችልኝ "ምነዉ ሆዴ ምን ሆንክብኝ?" አለች።
ምላሴ እየተሳሰረ "ፌቪ ሞተች!" አልኳት።
ተቃቅፈን ተላቀስን። የኔ ዉድ ስትረጋጋ አባበለችኝ። እኔ ደህና ነኝ። ያቆሸሽኩት ነብስ ግን ምድርን ለቆ ሄዷል።
ምናለ ግን አንድ ወንድ አንድን ሴት ሲቀርብ የግንኙነታቸዉ መጨረሻ ምን እንደሚሆን በቅጡ መረዳት በቻለ። የተከበረችዉ የሴት ልጅ ላይ የምንሰራዉ ስህተት በፍፁም ሊፋቅ እንደማይችል ብንረዳዉ ምን ነበር? ክብሯን ያጣች ሴት ተመልሳ ሰዉ ለመሆን በጣም እንደሚከብዳት ብንረዳ ምናለበት? ለሰዓታት የመንፈራገጥ ደስታ ብለን የምንነጥቀዉ የሴት ክብር ነገ ትዳሯን ገሀነም እንደሚያደርገዉ መረዳት ለምን ከበደን? አላዉቅም!
ወላጆች ሁሉ እንደሀጂ፣ ሴቶች ሁሉ እንደ አምሪ ቢሆኑ ምን ነበር? እኔንጃ! ቀልድ መስሎኝ በፍቅር ስም የለኮስኩት እሳት የተከበረዉን የሰዉ ልጅ ህይወት አቃጠለ። ፈጣሪዬ ምህረትህን!
.
ይቀጥላል...❤️❤️❤️
Don't forget to #like & #share 👍❤️👍❤️👍❤️
@dfabF
@dfabF
:
የማይፋቅ ስህተት
ክፍል አስራዘጠኝ
የመጨረሻዉ ክፍል
(ፉአድ ሙና)
.
የፌቪን ሞት ከሰማሁ በኋላ ሰላም የሚባል ነገር ከኔ ራቀ። ወንጀለኛ መሆኔን ህሊናዬ ሁሌ እያስታወሰ ያስጨንቀኛል። ጌታዬ ይምረኝ ይሆን? አላዉቅም።
ዛሬ ፌቪ መሞቷን ከሰማሁ ሁለት ሳምንቱ ሆነ። ቤት ሳሎን ዉስጥ ተቀምጬ ተክዣለሁ። አምሪ የሆነ ተዓምር መኝታ ቤቱ ዉስጥ እየሰራች ይመስል ሳልጠራህ እንዳትመጣ ብላኝ መኝታ ቤቱ ዉስጥ ትንጎዳጎዳለች። ሰሞኑን አምሪ እረፍት ላይ ናት። እኔ ሀሳቤ ሁሉ ፌቨን ጋር ነዉ። ሰላሜ አብሯት ሳይቀበር አይቀርም።
አምሪ ሙዝዝ እያለች "የኔ ንጉስ መምጣት ትችላለህ!" አለችኝ። መሟዘዝ ሲያምርባት! እስከአሁን መኝታ ክፍሉ ዉስጥ ምን እየሰራች እንደሆነ ለመመልከት ወደ መኝታ ክፍሉ ሄድኩ። አምሪ ክፍሉን በሚያምር ጠረን አጥናዋለች። አልጋዉ የጫጉላ አልጋ መስሏል። አምሪ ጭኗን የማይዘል፣ ቀሚስ ለማለት የሚከብድ ልብስ ለብሳለች። ደረቷ እና ወገቧ ተጋልጧል። በዛ ላይ የሽቶዉ ጠረን ብቻዉን ልብስ ያስወልቃል። አምሪ አልፎ አልፎ መኝታ ክፍላችን ዉስጥ እንዲህ ለየት ባለ መልኩ ስናሳልፍ ደስ ይላታል። አሁን ያቺ ረዥም ቀሚስ የምትለብሰዋ፣ ከአካሏ አንድንም ለባዳ የማታሳየዉ አምሪ ለባሏ እንዲህ ትዋባለች ብሎ ማን ይገምታል? ማንም! ግን አምሪ የት በምን መልኩ መልበስ እንዳለባት በደንብ ታዉቃለች። አንዳንዶች ዉጪ እየተራቆቱ ቤት ዉስጥ ለባላቸዉ ሰዉነታቸዉን ማጋለጥ አይፈልጉም። በጣም ያስቁኛል። አንዳንዶቹ ደግሞ ሰዉነታቸዉን ለባላቸዉም አታሳዩ የተባሉ ይመስል ቤት ከባላቸዉ ጋርም ሆነዉ ሰዉነታቸዉን አይገልጡም። ይሄ የግንዛቤ ማነስ ነዉ። ከባል ጋር ሲኮንማ የእርካታን ጥግ ማሰስ ነዉ እንጂ! አምሪ በደንብ ትችልበታለች። በደንብ!!
አምሪ ተጠግታ ሳመችኝ። ሙሉ ሰዉነቴን ነዘረኝ። ግን ቅዝቅዝ ማለቴ ስለገባት ደረቴ ላይ እንደተለጠፈች "የኔ ጣፋጭ ምን ሆንክብኝ?" አለችኝ። እንባዬ እየታገለኝ "ሁቢ በጌታሽ ይሁንብኝ ፌቨን ላይ የሰራሁትን ነገር ከጭንቅላቴ ማዉጣት ከብዶኛል።" አልኳት።
አምሪ ጉንጮቼን በጣቶቿ እየዳበሰች "ሀቢቤ አንተ እኮ አሁን ተፀፅተህ ተመልሰሀል። አላህ ደግሞ የተፀፀቱ ባሮቹን ሊምር ቃል ገብቷል። ወንጀልን በመላ ይምር የለ እንዴ ምን ያስጨንቅሀል?" አለችኝ።
አምሪን ደረቴ ላይ ልጥፍ አድርጌ እያቀፍኳት "አምሪ ይሄ እኮ በኔና በጌታዬ መካከል የተሰራ ወንጀል አይደለም። በኔናበፌቨን መሀል ነዉ። አላህ ደግሞ ሰዉየዉ ይቅር እስካላለ ድረስ በሰዉ መብት ጣልቃ አይገባም።" አልኳት። ሁሌም የሚቆጨኝ ልክ እንደሰሚራ ፌቨንንም ይቅር እንድትለኝ አለመማፀኔ ነዉ።
አምሪ "አብሽር አላህ አለ።" አለችና ሳላስበዉ አልጋዉ ላይ ወረወረችኝ። ተንጠራርቼ መብራቱን አጠፋሁት።
.
ለሊት ተነስተን ከአምሪ ጋር አንድ ላይ ሻወር ከወሰድን በኋላ እንደተለመደዉ ወደ ጌታችን ተዋደቅን። እኔ ነገ ጌታዬ ለፍርድ ሁሉንም በሚሰበስብበት ቀን ፌቨን ሀቢብ በድሎኛል ብላ ስትከሰኝ ከኔ ብዙም ሳልጎዳ ለሷ የምከፍለዉ መልካም ስራ እንዲኖረኝ ያደርግልኝ ዘንድ ጌታዬን ለመንኩት። የንጋት ስግደት ሲደርስ እኔ ወደ መስጂድ ሄጄ ሰግጄ መጣሁ። አምሪ ቤቱን ድምቅ አድርጋ ቁርስ አቀራርባ እየጠበቀችኝ ነበር። ቁርስ በልተን ስንጨርስ ወደ ስራዬ ለመሄድ ተነሳሁ። አምሪ ልወጣ በር ላይ ስደርስ እጄን ያዘችኝ። "ወዬ?" አልኳት።
አምሪ መንገዱን ዘግታብኝ እየቆመች "በነብያችን ላይ ሰላምታ አዉርድ!" አለችኝ። ሙስሊሞች ነብዩ ሙሀመድ ቢሞቱም እኛ ሰላም ስንላቸዉ መልዓክ ሄዶ ይነግራቸዉና እሳቸዉም ሰምተዉ ሰላምታ ይልኩልናል ብለዉ ያምናሉ።
እየሳቅኩ "አላህ ሆይ በሙሀመድ ላይ ሰላት እና ሰላምን አዉርድ!" አልኩኝ።
አምሪ ፍልቅልቅ እያለች "አሁን ነብያችን አንተ ላይ አስር ጊዜ ሰላምታ ያወርዳሉ። ስለዚህ ቀንህ የሰላም ይሆናል የኔ ፍቅር!" አለችና ከንፈሬን ሳመችኝ። የአምሪ አስተሳሰብ በጣም ድንቅ ይለኛል። በሳቅ እንደታጀብኩ ወደ ስራ ሄድኩ። እያስተማርኩ አምሪ ትዝ እያለችኝ እስቃለሁ። ዛሬ ከሰዓቱን የምማረዉም የማስተምረዉም ነገር ስላልነበር ቤት ከአምሪ ጋር ለማሳለፍ ወሰንኩ። ከቤት ስወጣ በፍቅር ስለምትሸኘኝ ተመልሼ አይኗን እስካያት እቸኩላለሁ። ሚስቶች ባላቸዉን እንዴት መያዝ እንዳለባቸዉ ከአምሪ ሰብሰብ ብለዉ ቢማሩ ቆንጆ ነበር።
ወደ ቤት እንደተመለስኩ ከአምሪ ጋር አልጋ ላይ ስንደባደብ ፣ሆዴ ላይ ተቀምጣ ፂሜን እየጎተተች ስታዝገኝ ከቆየች በኋላ ሆዴ ላይ እንደተቀመጠች "ሁቢ አሪፍ ሀሳብ መጣልኝ።" አለችኝ።
እየሳቅኩ "የኔ ቆንጆ ምን?" አልኳት።
አምሪ ደረቴን እንደቂጣ እየጠፈጠፈች "ለምን ቤተሰቦቿን ይቅርታ አትጠይቃቸዉም?" አለችኝ። ሳስበዉ አሪፍ ሀሳብ መሰለኝ።
በተራዬ ግልብጥ አድርጌያት "ልክ ነሽ አምሪዬ ቢያንስ ጭንቀቱን ያቀልልኛል!" አልኳት።
አምሪ እንደማሰብ አለችና "በቃ ወደ አስራአንድ ሰዓት እንሄዳለን።" አለችኝ። አልጋዉ ላይ ተቀምጠን እየተጨዋወትን ካረፈድን በኋላ ተጣጥቤ መስጂድ ደርሼ መጣሁ። አስራአንድ ሰዓት ሊሆን ሲል ከአምሪ ጋር ተያይዘን ወደ ፌቪ ቤተሰቦች ቤት ሄድን። ልጃቸዉ እኔ በለኮስኩት እሳት ሞታ ይቅር በሉኝ ማለት ይከብዳል። ግን ህሊናዬን ለማፅዳት ከዚህ የተሻለ አማራጭ አላገኘሁም። በር ላይ ስንደርስ ልቤ በፍርሀት ተዋጠ። እንደምንም አንኳኩተን ወደ ቤት ገባን። ሰራተኛቸዉ በሩን ከፍታልን እየሮጠች ወደ ቤት ገባች። እሷም አይናችንን ማየት ቀፈፋት ማለት ነዉ? ይገርማል። ቢያንስ ለምን መጣችሁ ማለት እንኳ የአባት እኮ ነዉ። ወደ ቤቱ ስንገባ ሰራተኛቸዉ ወደ ፎቅ እንድንወጣ ነገረችን። ፎቅ ላይ ወጥተን ሶፋዉ ላይ እንደተቀመጥን የፌቪ እናት ጥቁር የሀዘን ልብሳቸዉን እንደለበሱ መጡ። አሳዘኑኝ። እየተቀመጡ "ምነዉ ለቅሶ ለመድረስ ዘገያችሁ?" አሉን። ሰራተኛቸዉ የፌቪን ልጅ አቅፋ እያባበለች አመጣችና ለሴትየዋ አሳቀፈቻት።
ህፃኗን ሳይ እንባዬ ከአይኔ ፈሰሰ። ዉይ ስራዬ! ምንም የማታዉቀዋን ሚስኪን ህፃን በራሱ እናት አልባ አደረግኳት።
አምሪ "ያዉ ሀዘኑ ትንሽ ለኛም አስደንጋጭ ስለነበር በሰዓቱ ለቅሶ የመድረስ ወኔዉ አልነበረንም።" አለች።
ሴትየዋ ፈገግ እያሉ "አንቺ ምን ታደርጊ ልጄ? አንቺማ የተጣላችኝን ልጄን መክረሽ አምጥተሽልኝ ነበር።" አሉና ወደ እኔ ዞረዉ በቁጭት እያዩኝ "ወንዶቹ ያደረጓት ነገር ነዉ እንጂ ሰዉ እንዳትሆን ያደረጋት!" አሉ።
ከዚህ በላይ ህሊናዬ እንዲቆስል አልፈቀድኩም እንባዬን በእጆቼ እየጠረግኩ "እማማ ለፌቨን እንዲህ መሰቃየት እና መሞት የመጀመሪያዉ ጥፋተኛ እኔ ነኝ። የማይሆን ተስፋ ሰጥቼ ልቧን አሸፈትኩት። ሲከፋም ክብሯን አቆሸሽኩ። ከወንጀሌ ስፀፀት ግን እሷን መመለሱ ከበደኝ። አምሪ ከናንተ ጋር እንድታስታርቃት ያደረግኩትም ፀፀቱ ስለከበደኝ ነበር። ግን ህይወቷ ሊስተካከል ነዉ ስንል በመሀል ላትመለስ ሄደች። ምን እንደምል አላዉቅም ይቅር ይበሉኝ።" አልኳቸዉ።
ሴትየዋ እንባ እየተናነቃቸዉ "ፌቨን እኮ ለኔ ዘጠኝ ወር ተሰቃይቼ ያረገዝኳት፣ አምጬ የወለድኳት ልጄ ናት። በየቀኑ በስስት ነበር ያሳደግኳት። ታዲያ የአይኔን ማረፊያ ነጥቀኸኝ በቀላሉ ይቅር የምልህ ይመስልሀል?" አሉ። ግራ ገባኝ። ታዲያ ይቅርታዋን ለማግኘት ምን ማድረግ ይኖርብኝ ይሆን? ምናልባት መቀጮዉን ብጠይቅስ?
ቅዝቅዝ ባለ ድምፅ "መቀጣት ካለብኝ ልቀጣ እኔ ፀፀቱን አልቻልኩትም።" አልኳቸዉ።
ትንሽ ዝም አሉና "እንግዲያዉስ ልቀጣ ካልክ ያዝ የፌቨንን ልጅ" አሉና ልጅቷን እየሰጡኝ
"እኔ በስስት ያሳደግኳትን ልጅ አይ

ደል የነጠቅከኝ? አሳድጋትና አስራሰባት አመት ሲሞላት ለኔ ትመልስልኛለህ።" አሉኝ። ልጅቷን እንዳቀፍኩ አምሪን ዞር ብዬ አየኋት። ፈገግ ብላ "አብሽር እናሳድጋታለን።" አለች።
የፌቪ እናት ወዳቀፍኳት ህፃን እያዩ "ታዲያ በአንክብካቤ አሳድጓት። ስሟ የአብስራ ነዉ። ሀይማኖቷን ለማስቀየር እንዳታስቡ። እሁድ እሁድ ሁሌም ቸርች ይዛችኋት ሂዱ።" አለችን። በጣም ከባድ ቢሆንም ምንም አማራጭ ስለሌለን መስፈርቱን ለመቀበል ወሰንን። ሌላ መስፈርት ሳትጨምርብን ለመዉጣት አስቤ "በቃ እማማ እየመጣን እንጠይቅዎታለን። ደህና ይሁኑ።" ብዬ ልሰናበት ስል ከበስተጀርባችን የነበረዉ በር እየተከፈተ አንድ ሴት "ከመጠን በላይ መፀፀትህን አረጋግጫለሁ። ይቅር ብዬሀለሁ ሀቢቤ።" አለች። ድምፁን ወደ ሰማንበት ስንዞር ያየነዉን ማመን ከበደን። ህፃኗን እንዳቀፍኩ ከመቀመጫዬ ብድግ አልኩ። አምሪ ድንጋጤ ዉርር አድርጓታል። እናትየዉ እየሳቁ የለበሱትን ጥቁር ሻሽ ፈተዉ ጣሉት። ድምፁ የፌቨን ነበር። እዉነት ግን ፌቨንን እያየኋት ነዉ? ወይስ መንፈስ የሚባለዉ ነገር እዉነት ነዉ? ፌቨን ፈገግ እንዳለች አጠገቤ ቆመችና ህፃኗን እየተቀበለችኝ "እናቴ ትወና ላይ እንዴት ናት?" አለችኝ። አላምንም ፌቨን በህይወት አለች። አምሪ ከመቀመጫዋ ተነስታ ነካቻት። እዉነት መሆኑን ለማረጋገጥ ብላ መሰለኝ። አምሪ ደስታዋን መቆጣጠር ከብዷት እያለቀሰች "ፌቪዬ በህይወት አለች።" አለችና ተጠመጠመችባት።
ሰራተኛዋ እየሳቀች ገብታ ተቀመጠች። ለካ በር ከፍታልን የሮጠችዉ እናትየዉ ለድራማዉ የሚያስፈልጋትን ልብስ እንድትቀይር እና ፌቪ እንድትደበቅ ለማድረግ ነበር። የሆነች ብሽቅ! ድንዝዝ እንዳልኩ ሶፋዉ ላይ ዘፍ አልኩ። ፌቪ ስትቀመጥ "ማለት ይሀ ሁሉ ነገር ድራማ ነበር?" አልኳት።
እየሳቀች "የእማዬ ስራ ነዉ። እሷ ናት ሰዉን አፈቀርኩ ብለሽ ራስሽን አትጉጂ ብትሞቺ እንኳ ይረሱሻል እንጂ ዞር ብለዉ አያዩሽም ብላ ልታሳምነኝ አምሪያ ጋር ቴክስት እንዳደርግ ያደረገችኝ። እማዬ ጋር ስትደዉሉ መኝታ ክፍል ተቀምጠን እያየነዉ ስንስቅ ነበር። ኤልዳና ጠዋቱን ለማጣራት ስትመጣ እማዬ አራስ ነብር መስላ አባረረቻት። እሷ ደግሞ እማዬ ስታባራት ያለቻትን ለናንተ ነገረቻችሁ። እነሚኪም ለቅሶ ሊደርሱ ሲመጡ ከበር ተባረሩ። እማዬ እዉነቷን ነበር። ይቅርታ ፈልጋችሁ እንጂ እኔን ናፍቃችሁ አልመጣችሁም።" አለችኝ።
እኔ ይሄ ጌታዬ እኔን ንፁህ ለማድረግ የሰራዉ ንፁህ ተዓምር እንደሆነ እየተሰማኝ ነዉ። እናትየዉ እየሳቁ "ልጄን ገደልክብኝ ብዬ የልጅ ልጄን የምመርቅልህ ይመስልሀል?" አሉ። ምናይነት ቲያትረኛ ቤተሰብ ነዉ? ጭንቀቴ ሁሉ ትቶኝ ጠፋ።
ፈገግ እንዳልኩ "ፌቨን ለሁሉም ነገር ይቅርታ!" አልኳት። እየሳቀች "ህይወቴን ሰጥቼህ ይቅርታዬን መስጠት እንኳ አይከብደኝም። ስለተፀፀትክ ይቅር ብዬሀለሁ።" አለችና ትኩረቷን ወደ እኔናአምሪ እያደረገች "ባይሆን አንድ ነገር ታግዙኛላችሁ።" አለችኝ። በጣም ደስ እያለን እኔም አምሪም እኩል "ምን?" አልናት።
"እንደኔ የማይሆን ህይወት ዉስጥ በፍቅር ስም የተጣዱ ሴቶችን ለመርዳት ስልጠና የሚሰጥበት ትንሽዬ የእድር ፍቃድ ያላት ክበብ ነገር ለመመስረት ይህን ሁለት ሳምንት ፕሮፖዛል ስቀርፅ ነበር። እና ሀቢቤ ስልጠና ብትሰጥልኝ፣ አምሪ ደግሞ አብረን ክበቡን አሳድገን እህቶቻችንን እንድንታደግ አብረን ክበቡን ብናስተዳድረዉ ምን ይመስላችኋል?" አለችን።
በጣም ደስ እያለን ጥያቄዋን ተቀበልናት። ትንሽ ከተጨዋወትን በኋላ ተሰናብተን ልንወጣ ስንል የአብነት ጉዳይ ትዝ አለኝና "የልጅሽ አባት ነገር እንዴት ሆነ?" አልኳት።
ፌቪ የሀፍረት ሳቅ ሳቀችና "በዚህ ሳምንት ከክፍለሀገር ይመጣል። ያዉ ለልጅቷ ስል አብሬዉ ለመኖር ወስኛለሁ።" አለችኝ። ያዉ ቢያንስ ልጅቷ አባቷን ማወቋ በራሱ መልካም ነዉ።
ፌቪ ያሰበችዉ የተቀደሰ ሀሳብ ያለዉን ክበብ በመመስረቱና በማሰልጠኑ ልናግዛት ተስማምተን ወደ ቤት ተመለስን። የፌቪ ህይወት ላይ የሰራሁት ስህተት ተፍቆ እንደድሮዉ መሆን ባትችልም ይቅርታዋ ሰላሜን መለሰዉ። የሴት ልጅ ክብሯ ከተገፈፈ በኋላ ሊመለስ አይችልም። ፌቪ ብዙም የማትወደዉን ሰዉ ከሱ በመዉለዷ ምክንያት ልታገባዉ ነዉ።
ብቻ ግን የማይታፈስ ነገር ከፈሰሰ ምንም ለማፈስ ቢለፋ እንኳ ሳይታፈስ ከመሬት ከመቅረት ዉጪ ሌላ መፍትሔ የለዉም።
ፈጣሪ ልብ ይስጠን። የትዉልዱን የደነዘዘ አእምሮ በችሮታዉ ማሰብን ይግጠመዉ።
የማይፋቅ ስህተት ከመስራት ይጠብቀን! አሚን!
.
💞ተፈፀመ።💞

አስቲ እንዴት ነበር #የማይፋቅ_ስህተት ትልቅ ትምህር እንዳገኛችሁበት አልጠራጠርም ፡፡ አስቲ ስሜታችሁን በዚህ ግለፁልን @Dfabb
#like & #share እንዳይረሳ k
Forwarded from 🎞🍿ᴘαɴᴅα мσᴠɪᴇ 'ѕ🍟🎞 (åbìŋəť)
Watch "ABIYE " on YouTube
https://youtube.com/channel/UCRP9g-Jq_BUNRu9lWPc-YGg


joine bemalet beteseb yihunu
Forwarded from Deleted Account
GROUP LAY ADD MEDERAREG MIFELG KALE INBOX LAY YAWRAG KE 100 SEW BELAY... @ABI_RIHANN
የፈቲ_ባል_……_ክፍል_1_ተራኪ_ጃዕፈር_ጀማል
<unknown>
የ ፈቲ_ባል

#የፈቲ ባል ክፍል 1 ዛሬ ጀመረ

አስተያየት ካለወት☞ @ABI_RIHANN ያድርሱን

@YEFIKIR_DEBDABEWOCH ❤️❤️