DDU-SU President Office
3.15K subscribers
721 photos
12 videos
6 files
72 links
Download Telegram
ማስታወቂያ !!!

ለሴት ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ

በድ/ዳ/ዮ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካትቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ክፍል ለመውጫ ፈተና ይረዳቹ ዘንድ የኮምፒዩተር እና ስነልቦና ስልጠና ከ16/04/2018 -17/04/2018 ባሉት ቀናት 10:00 ላይ የሚጀመር ስልጠና ስለተዘጋጀላችሁ አስተዳደር ህንጻ አንደኛ ፎቅ ቁጥር 8 አጠገብ ባለው አዳራሽ መጥታችሁ ስልጠናውን እንድትወስዱ ስንል እናሳስባለን::
በተጨማሪም ድጋፍ ተጠቃሚ የሆናችሁ ሴት ተማሪዎች የመጨረሻ የጥር ወር የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ የሚሰጣችሁ ይሆናል::

https://t.me/DDUSUWA121
6
ውድ የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በሙሉ
በዩኒቨርስቲው ውስጥ የተሰሩ የመሰረተ ልማት ምርቃት በነገው እለት ይካሄዳል  ይህንንም ምክንያት በማድረግ ለሁሉም ተማሪዎች የ non cafe ተማሪዎችን ጨምሮ  የምሳ ግብዣ ጥሪ ስለተደረገላቹ ሁላችሁም በግቢው ካፌ እንድትገኙ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

kabajamtoota Barattoota Yuuniversitii Dire Dawa hundaaf,
Booru guyya ebba Bu'uraale misooma Yuuniversitii keessatti hojetamanidha.Kanaafuu, barattoota moora keenya hunda keessanifu warreen  caffee fayadamtani fi non caffe tatan illee guyya booru  yaaminsa affeerra laaqana isiniif godhame jira,kanaafu kabajaan akka dhuftan isiin beeysifna.

Dear all students of Dire Dawa University, The inauguration of the infrastructure projects built in the university will be held tomorrow. For this reason, we would like to extend our message to all students, including non-cafe students, to attend a luncheon at the campus cafe.
23👏8😁7👍3🥱3🤔2👀2🤗2🤨1
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ 7 ታላላቅ ፕሮጀክቶችን አስመረቀ

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲውን ገፅታ የሚቀይሩ፣ ምቹ የስራ አካባቢን የሚፈጥሩ፣ የፀጥታ እና ደህንነት ስራዎችን በእጅጉ የሚያግዙ፣ ለተማሪ የሚሰጥ አገልግሎትን የሚያሻሽሉ፣ የአካባቢውን ማህበረሰብ ችግሮች የሚቀርፉ እንዲሁም ዘመናዊ የህክምና አገልግሎትን መስጠት የሚያስችሉ ስራዎችን በብዛት አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል፡፡

በፕሮጀክት ማስመረቂያ መርሃ ግብሩ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃር፣ ክብርት ዶ/ር ፍፁም አሰፋ የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር እና የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራረ ቦርድ ሰብሳቢ፣ ክቡር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በኢፌዲሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ ክብርት ዶ/ር ኡባህ አደም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣ የፌደራል መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የዩኒቨርሲቲው ቦርድ አባላት፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ተገኝተው መርቀዋል፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከዲር ጁሃር በዚሁ የምረቃ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት “የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለመምህራን ምቹ የስራ አከባቢን ከመፍጠር ባሻገር የመምህራንን ፍልሰት ለመቀነሰ የሚያስችል ዘመናዊ የመኖሪያ ቤት መገንባቱ ለመምህራኑ የቤት ችግር እፎይታን ከማጎናፀፉም በላይ በአስተዳደራችን ያለውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመቀነስ የሚረዳ ነው” ብለዋል፡፡
1
የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር እንዲሁም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ፍፁም አሰፋ በበኩላቸው “ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የመምህራኑን የቤት ችግር ለመቅረፍ ብዙ ሰርቷል፡ የዩኒቨርሲቲውን ገፅታ ለመቀየር በርካታ ጥረቶች እየተደረጉ ነው፣ ዩኒቨርሲቲው በምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎት፣ ዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር ስራዎች፣ የዲጂታላይዜሽን ስራዎች እምርታን እያሳየ ይገኛል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ዩኒቨርቲው በፀጥታ ችግር እና ውስብስብ አስተዳደራዊ ችግሮች ሳቢያ በሚፈለገው ልክ ማደግ አለመቻሉን አስታውሰው ‘’አሁን ያለው አመራር ወደ ሃላፊነት ከመጣ በኃላ የመማር ማስተማር ስራዎች ያለችግር እንዲከወኑ አሰራሮችን በመዘርጋት፣ ባለፈ ለአመታት ሲንከባለሉ የከረሙ የመምህራን መኖሪያ ቤት፣ የተማሪ አገልገሎቶች እና መሰል የመሰረተ ልማት ስራዎችን መስራት ችሏል ከዚህም በኋላ የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ የልማት ስራዎችን ለመስራት በትጋት የሰራል’’ ብለዋል፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው እለት ያስመረቃቸው ፕሮጀክቶች

👉 267 ቤቶችን፣ የህጻናት፣ ማቆያ፣ የጋራ መገልገያ ስፈራን የካተተ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር
👉 የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ ግንባታ እና የምድረገጽ ስራ
👉 የሪፈራል ሆስፒታል የኤሌክትሮሜካኒካል ቀሪ ስራዎች ማጠናቀቂያ ግንባታ
👉 5 የተማሪ መኖሪያ ህንጻዎች የማጠናቀቂያ ግንባታ
👉 25 የተማሪ መኖሪያ ህንጻዎች የመጸዳጃ ቤቶች እና የፍሳሽ መስመር እድሳት
👉 የማህበረሰብ ታክሲ ተርሚናል እና
👉 የአጥር እና የጥበቃ ማማዎች ግንባታ ስራዎች እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡
😁8🥱76🙉4🙈3👍1
The Role of Youth in Peace

While every sector of society has a role in achieving sustainable peace, youth are at the heart of peacebuilding efforts.

Young people are not only future leaders — they are today’s peacemakers. Across communities and regions, youth are driving peacebuilding and conflict prevention, advancing environmental security, supporting peacekeeping efforts, and leading the rehabilitation of conflict-affected communities. Their impact is powerful and undeniable.

By empowering young people, we strengthen social cohesion, foster innovation, and build resilient societies capable of sustaining peace for generations to come.

🌍✌️ Invest in youth. Support peace. Shape a stable future.

Dire Forum 2026 is mobilizing youth across the Horn of Africa to lead the way for sustainable peace and climate action.

📍Dire Forum High-Level Horn of Africa Youth Forum
January 30 - February 01/2026 Dire dawa, Ethiopia

##PeaceInAction
2👍2
የጋዜጠኝነትና ስነ-ተግባቦት ትምህርት ክፍል ተማሪዎችን በአስተዳደሩ ከሚገኙ የሚዲያና የኮምኒኬሽን ተቋማት ጋር የማስተሳሰር ስራ በስፋት እንደሚሰራ ተገለፀ።

****
ታህሳስ 18 ቀን 2018 ዓ.ም

የጋዜጠኝነትና ስነ-ተግባቦት ትምህርት ክፍል ለተመራቂ ተማሪዎች የሽኝት እንዲሁም ት/ክፍሉን በአዲስ ለተቀላቀሉ ተማሪዎች ደግሞ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ፕሮግራም አካሂዷል።

በፕሮግራሙ ላይ የዩኒቨርስቲው የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር በረከት ተስፋዬ፣የተማሪዎች አገልግሎት ዲን አቶ እንዳለ ሞገስ፣የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን አቶ ሰብስቤ ጌታሁን እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

በዚህም ዶ/ር በረከት ተስፋዬ የተማሪዎች እርስ በእርስ ቅርርብና ስነ-ተግባቦት በተማሪዎች መካከል አብሮነትን ለማጠናከር አስፈላጊ በመሆኑ ጠቅሰው እንደዛሬው አይነት መሰል ፕሮግራሞች በስፋት መከናወን እንደሚገባቸው ገልፀዋል።
5🔥1
የተማሪዎች አገልግሎት ዲን አቶ እንዳለ ሞገስ በበኩላቸው የትምህርት ክፍሉ ተማሪዎች በስነ-ምግባራቸው ምስጉን በትምህርታቸውም ውጤታማና ታታሪ ከመሆናቸው በተጨማሪ በዩኒቨርስቲው በሚገኙ ክበባትና ሚዲያዎች ግንባር ቀደም ተሳታፊዎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን አቶ ሰብስቤ ጌታሁን የጋዜጠኝነትና ስነ ተግባቦት ትምህርት ክፍል ተማሪዎች በፅንሰ ሀሳብ የሚማሩትን ትምህርት በጊቢው ውስጥ ብሎም ከጊቢ ውጪ ባሉ ሚዲያዎች ላይ በተግባር የመቀየር ስራዎችን እየሰሩ እንደሚገኙና ይህም ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው አመላክተዋል።

የትምህርት ክፍሉ በተማሪዎች የመውጫ ፈተና በርካታ ተማሪዎችን በማሳለፍ በተደጋጋሚ ተሸላሚ የሆነ መሆኑንም አቶ ሰብስቤ ጠቅሰዋል።

የትምህርት ከፍሉ ኃላፊ የሆኑት ረ/ፕሮፌሰር እዮብ ነጋ በበኩላቸው የዛሬው መርሃ-ግብር በዋነኝነት ተመራቂ ተማሪዎችን ለመሸኘት እንዲሁም ደግሞ በአዲስ ወደ ትምህርት ክፍሉ የተቀላቀሉ ተማሪዎች እንኳን ደህና መጣችሁ ለማለት በተጨማሪም በትምርት ክፍሉ የሚገኙ ተማሪዎችን በማቀራረብ በቆይታቸው እንዲተጋገዙ ለማስቻል መሆኑን አብራርተዋል።

ረ/ፕሮፌሰር እዮብ አያይዘውም የትምርት ክፍሉ ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆነውም በስነ-ምግባር የታነፁና በዕውቀት የበለፀጉ ጋዜጠኞችን ለሀገራችን ብሎም ለአስተዳደሩ የሚዲያ ተቋማት እያበረከተ መሆኑን ጠቁመው፤ በቀጣይም የጋዜጠኝነትና ስነ-ተግባቦት ትምህርት ክፍል ተማሪዎችን በአስተዳደሩ ከሚገኙ የሚዲያና የኮምኒኬሽን ተቋማት ጋር የማስተሳሰር ስራ በስፋት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ተማሪ ጎሳ ከበደ የጋዜጠኝነትና ስነ-ተግባቦት ትምህርት ክፍል ተማሪዎች የቀለም ትምህርታቸውን ከመማር ጎን ለጎን በተለያዩ ክበባትና ሚዲያዎች ላይ እንዲሁም በጊቢው የሚዘጋጁ ሁነቶች ላይ ንቁ ተሳትፎን እያደረጉ የሚገኙ መሆናቸውን ጠቁመው ይህም በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው መልዕክት አስተላልፈዋል።

በቀጣይ የጋዜጠኛና የስነ-ተግባቦት ት/ክፍል ተማሪዎች ክለብ እንደሚቋቋም ከመድረኩ የተገለፀ ሲሆን በክለቡ ከዚህ ቀደም በትምህርት ክፍሉ ተምረው የተመረቁ ተማሪዎችና አሁን ላይ በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት የሚሰሩ ጋዜጠኞች አባል ሆነው የራሳቸውን አስተዋፆ የሚያበረክቱበት መሆኑም ጠቁመዋል።

በፕሮግራሙ የተማሪዎች የልምድ ልውውጥ ቶክ-ሾና የጥበብ ስራዎችም ቀርበዋል።
1