ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ
1.28K subscribers
390 photos
36 videos
45 files
49 links
ይህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ ት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ደ/ብ ማዕከል የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የቀን ግቢ ጒባኤ ይፋዊ የቴሌግራም መገናኛ ነው።
Download Telegram
ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ
Photo
#በዐለ_ጰራቅሊጦስ_በዐለ_ሃምሣ

ድንገትም እንደ አዉሎ ንፋስ ድምፅ ያለ ከሰማይ ድምፅ
መጣ የነበሩበትን ቤት ሞላው እንደ እሳት የተከፋፈሉ
የእሳት ላንቃዎች ታዩአቸዉ በሁሉም ላይ ተቀመጡባቸው
ሁሉም #መንፈስ_ቅዱስን ተሞሉ ሐዋ.2፥2-4

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ አብይ ፆምን አስፈፅሞ #ለብርሐነ_ትንሣኤዉ እና #ለብርሐነ_እርገቱ በሠላም አድርሶን እንሆ #በዐለ_ሐምሣ (ለመጨረሻዉ ፋሲካ) ደርሰናል ክብርን ሁሉ መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ይዉሰድ ከጌታ አበይት በዐላት አንዱ ለሆነዉ ለበዐለ #መንፈስ_ቅዱስ አመታዊ ክብረ በዐል እንኳን አደረሰን

👉 #ጰራቅሊጦስ ማለት በልሳነ ጽርዕ #መፅናንዒ ማለት ነው ትርጕሙም በጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ ናዛዚ (የሚናዝዝ)፣ መጽንዒ (የሚያጸና)፣ መስተፍሥሒ (የሚያስደስት) ማለት ነው

👉ከሶስቱ አካላት አንዱ ለሆነው #የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ ስም ነው በዓለ ጰራቅሊጦስ #በዓለ_ጰንጠቆስጤም እየተባለ ይጠራል ይኸውም በግሪክ ቋንቋ #በዓለ_ሃምሳ የፋሲካ ሃምሳኛ ዕለት፣ በዓለ ሠዊት (የእሸት የመከር በዓል) ማለት ነው (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ገፅ.፱፻፮- ፱፻፯)

👉በዓለ #ጰራቅሊጦስ ወይም በዓለ #ጰንጠቆስጤ ከዘጠኙ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዐበይት በዓላት አንዱ ሲሆን #መንፈስ_ቅዱስ_ለሐዋርያት_የወረደበትን ቀን የምናስብበት በዓል ነው

👉ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ_ካረገ በኋላ እመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያም፣12ቱ ደቀ መዛሙርት፣ 72ቱ አርድእት 36ቱ ቅዱሳት አንስት በኢየሩሳሌም ከተማ በአንድነት ሆነው ለጸሎት ይተጉ ነበር በሚያርግበት ጊዜም እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ #በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ ሲል ለሐዋርያቱ በገባላቸው ቃል መሠረት ባረገ በአስረኛው ቀን #መንፈስ_ቅዱስን ልኮላቸዋል ሉቃ.24፥49

👉በሐዋርያት ሥራ እንደ ተፃፈው #በበዓለ_ጰራቅሊጦስ ማለዳ ሁሉም በአንድ ቦታ ተሰብስበው ሳሉ እንደ #ዐውሎ_ነፋስ ያለ ድምፅ ድንገት ከሰማይ መጥቶ የነበሩበትን ቤት ሞላው

👉በመቀጠልም #እንደ_እሳት_የተከፋፈሉ_የእሳት_ላንቃዎች በሁሉም ላይ ሞላባቸው በዚህ ጊዜ ሁላቸውም መንፈስ ቅዱስን ከተሞሉ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ባደላቸው መጠን በየአገሩ ቋንቋዎች ሁሉ መናገር ጀመሩ ሐዋ.2፥1-4 ጌታችን መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት የላከበት ይህ ዐቢይ በዓል #ጰራቅሊጦስ ተብሎ ይጠራል

👉ጰራቅሊጦስ ምስጢር እዉቀት ገላጭ ነዉ ሐዋርያት በበዐለ #ጰራቅሊጦስ መንፈስ ቅዱስ ፀጋዉን ካደላቸዉ በኋላ 72 ቋንቋ ተገልፆላቸዋል በዚህም የቅዱሳን መፃህፍት ምስጢር ተገልፆላቸዋል የመድኃኒታችን #የኢየሱስ_ክርስቶስ ትምህርትን ለማስተዋል ችለዋል

👉በፅርሐ ፅዮን በሐዋርያት ላይ የወረደው #መንፈስ_ቅዱስ ያናገረው ቋንቋ የሚሰማ የሚደመጥ የሚታወቅ የሚተረጎም ነበረ ዛሬ የጌታ ተከታይ ነን የሐዋርያት መንፈስ የወረደው ለኛ ነዉ በአዲስ ቋንቋ በልሣን እንናገራለን የሚሉን ሰዎች ንግግራቸው የማይደመጥ የማይተረጎም የተናገሩትን እንኳን መልሳችሁ ተናገሩ ቢባሉ እንኳን የማይደግሙት እንደሆነ እንረዳለን #መንፈስን_ሁሉ_አትመኑ ተብሎ ተፅፏልና እንመርምር

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በቅዱስ መንፈሱ ያፅናን ሀይልና ብርታትን ይስጠን የቅዱሳን አባቶቻችን የቅዱሳን ሐዋርያት ፀሎትና ልመና አይለየን የተባረከ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
👍21
ሰላም እንደምን አደራችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ሰላመ እግዚአብሔር አይለያችሁ

እንኳን ለበዓለ ጴራቂልጦስ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
ዛሬ ጀምራችሁ ከግቢ የምትወጡ ወይም ወደ ቤተሰብ የምትሄዱ ሁሉ በምትሄዱበት ሁሉ የእግዚአብሔር ጠብቆት የእመቤታችንም ምልጃ አብሯችሁ ይሆን ዘንድ እናት ግቢ ጉባኤ ትመኝላችኋለች።
ቅርብም ይሁን ርቀት ስትሄዱ መንገዳችሁን በጸሎት ጀምሩት፤አትደንግጡ አትፍሩ ወደ መጣችሁበትም ስትመለሱ ደግሞ ጥቅትም ይሁን ብዙ በተማራቹበት ጸንታችሁ ኑሩ ለላውን አስተምሩ ከክፉ ራቁ እራሳችሁንና ቤተክርስቲያንን ጠብቁ ስትል እናት ግቢ ጉባኤ ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

ለክፍላት ተጠርዎች ወይም ለምመለከተው አካላት ሁሉ:- በትላንትናው ዕለት በነበረው መርሐ ግብር ለዚህ telegram ቻናል መለቀቅ ምችል ምስል በየክፍላችሁ ወይም የነባሮቹና የቀጣይ ሥራ አስፈጻሚዎች ምስል (photo) ካለ የክፍላችሁን ስም እየጻፋችሁ ከታች ባለው ልንክ ግቡና እዛው ላኩልን ለመረጃ እና ለትውስታ እንድቀመጥ ነው።

photo መላኪያ link👉https://t.me/dbugg12

ማሳሰቢያ ከአንድ ክፍል ይሆናል ምትሉትን አንድ ሰው ብቻ ነው መላክ የምችለው።
9
መልእክት(text) መላኪያው ተከፍቷል።
550 ሰዎች online 🙄🙄🙄
መልእክት(text) መላኪያው ተከፍቷል።
🥀"ባርክናክሙ እምቤተ እግዚአብሔር "🥀
🥀ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ (መዝ 117፥26)🥀
ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት ልጆች ፤ የቅዱሳን ሁሉ ወዳጆች እንዲሁም የግቢ ጉባኤያችን አባላት በሙሉ እንኳን ለዚች ታላቅ ቀን እግዚአብሔር በሰላም በጠና አደረሳችሁ አደረሰን።🥀🌹
ዛሬ ማለትም ዕለተ ቀዳሚት ሰንበት ከቀኑ 7:30 ጀምሮ እናት ግቢ ጉባኤ ከዓለም ብቻም ሳይሆን ከእግዚአብሔርም ቤት ትመረቁ ዘንድ ኑኑኑኑ ትለናለች ስለሆነም ሁላችንም ተቀሳቅሰን በሰዓቱ በመገኘት የዚህ ታላቅ እና ልዩ የሆነውን የምርቃት መርሐ ግብር እንድንከታተል ስንል በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን!

🥀🥀🥀CONGRATULATIONS🥀🥀🥀
🕊117
"ባርክናክሙ እምቤተ እግዚአብሔር "
ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ
(መዝ 117፥26)
ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ውድ ክቡራን ተመራቂዎቻችን እንኳን ለዚህ ታላቅ ቀን አደረሳችሁ።
እግዚአብሔር አምላክ መልካም የሥራ ዘመን ያድርግላችሁ።

መልእክቱ መላኪያው ተከፍቷል መልካም ምኞታችሁን ተለዋወጡ።
9
እንኳን ፈጠሪ ረድቷችሁ ለዚህች ለምትናፍቆት እና ለምትጠብቁዋት ቀን አበቃችሁ ውድ የግቢ ጉባኤያችን እህት ወንድሞቼ ቀሪውንም ጊዜ ፈጣሪ ከፊት ከፊት ይቅደምላችሁ ❤️❤️❤️❤️
🏆104
ሰላም እንደምን አላችሁ ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ሰላመ እግዚአብሔር በያለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን ይሄ ግሩፕ የደብረብርሃን ዩንቨርስቲ የቀን ግቢ ጉባኤ ዋና ግሩፕ ነው ስለሆነም በግቢ ውስጥ ያሉ ወደዚህ ግሩፕ(ማህበር) ውስጥ ያልተቀላቀሉ ተማሪዎችን ADD እንድታደርጓቸው በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን።
በልንክ ለመጋበዝ ከፈለጉ ይሄንን መስፈንጠሪያ ይንኩ👉https://t.me/dbugg21group
9
ቅዳሜ በ4/04/018 ግቢ ጉባኤ በመዝሙርና ኪነ ጥበብ ክፍል የተዘጋጀ መንፈሳዊ ቲያትር ስለሚቀርብ ሁላችሁም የፕሮግራሙ ተጋባዥ በመሆን ለህይወታችን የሚጠቅመንን ትምህርት እንድንማር።

ሰዓት፦ 8፡30 ይጀራል።
ቦታ፦ በግቢ ጉባኤው አዳራሽ
መግቢያ ዋጋ፦ 10 ብር ብቻ


በተቻለ መጠን ባናረፍድ መልካም ነው ከጅማሬው ካላየንው ላይገባን ስለሚችል።
11👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ቅዳሜ በ4/04/018 ግቢ ጉባኤ በመዝሙርና ኪነ ጥበብ ክፍል የተዘጋጀ መንፈሳዊ ቲያትር ስለሚቀርብ ሁላችሁም የፕሮግራሙ ተጋባዥ በመሆን ለህይወታችን የሚጠቅመንን ትምህርት እንድንማር።

ሰዓት፦ 8፡30 ይጀራል።
ቦታ፦ በግቢ ጉባኤው አዳራሽ
መግቢያ ዋጋ፦ 10 ብር ብቻ


በተቻለ መጠን ባናረፍድ መልካም ነው ከጅማሬው ካላየንው ላይገባን ስለሚችል።
9🕊1😭1
በዛሬው እለት 04/04/2018 ዓ.ም በተሰራው ቲያትር ላይ በስልክ የቀረፃቸሁ ልጆች ለጥንቃቄ ሲባል ማንኛውም አይነት ማህበራዊ ሚድያ ላይ ቲክቶክ ላይም ሆነ ዩቲዩብ ላይ መልቀቅ እንደማይቻል በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን።
👍184
🕊️መንፈሳዊ የመዝሙር ግብዣ                  ከ"ቤተ ቀጢን" 🕊️
"ሰላም ለሁላችሁ ይሁን!
ቤተ ቀጢን (Bete Kettin) የዩቲዩብ ቻናላችን በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው  አዲስ ዝማሬ ዛሬ ማታ 2:30 ላይ በቀጥታ (Live Premiere) ይለቀቃል።
በወቅቱ በላይቭ ቻት (Live Chat) አብረናችሁ ስለምንቆይ፣ ሁላችሁም በጋራ እንድትሳተፉና የዝማሬው በረከት ተካፋይ እንድትሆኑ በፍቅር ተጋብዛችኋል። 🌟
የቀጥታ ስርጭቱን ለመታደም ይህንን ሊንክ ይጫኑ፦ 👇👇👇
https://youtu.be/fjRV-zJo50c
እባክዎ ዝማሬው ለብዙዎች እንዲደርስ ለወዳጅ ዘመድዎ Share በማድረግ የቤተ ቀጢን ቤተሰብ ይሁኑ።
የእግዚአብሔር ጠባቂነት የእመቤታችን አማላጅነቷ አይለየን🙏🙏🙏
22