†
🕊 💖 ቅዱስ ያሬድ 💖 🕊
[ ግንቦት ፲፩ [ 11 ] የቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ በዓል ]
♥ ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ አባቱ አብዩድ [ ይሥሐቅ ] እናቱ ክርስቲና [ ታውክልያ ] ሲባሉ የተወለደውም በ፭፻፭ ዓ.ም. በአክሱም ነው፡፡ ሰባት ዓመት ሲመላው አባቱ ስላረፈ፤ እናቱ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እንዲያስተምረው ለአባ ጌዴዎን ሰጠችው፡፡
❤ ነገር ግን ማጥናት ስላልቻለ አባ ጌዴዎን ይቈጣው ነበርና ሸሽቶ ከዱር ውስጥ ገባ ፤ ከዐዘኑም ብዛት የተነሣ በዛፍ ሥር ተጠልሎ ሳለ አንዲት ታናሽ ትል ከዛፍ እኩሌታ ደርሶ ሲወድቅ ሲነሣ በመጨረሻም በጭንቅ ከዛፉ ላይ ሲወጣ በማየቱ እግዚአብሔር በዚኽች ታናሽ ፍጥረት እንዳስተማረው በመረዳት ይቅርታ ጠይቆ ወደ መምህሩ ተመልሷል፡፡
♥ ❝ ወእምዝ ሶበ ሰአለ ኀበ እግዚአብሔር በብካይ ብዙኅ ተርኅወ ልቡናሁ ወተምህረ በሐጺር ዕለት መጻሕፍተ ብሉይ ወሐዲስ❞ ይላል ከዚኽ በኋላ ቅዱስ ያሬድ ወደ እግዚአብሔር በለመነ ጊዜ ልቡናው ብሩህ ኾኖለት በዐጭር ጊዜ ውስጥ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትን ተምሮ በመጨረስ ዲቁናን ተሾመ ፤ እስከ ርሱ ዘመን በማነብነብ እንጂ በከፍተኛ ድምፅ የመዝሙር ማሕሌት አልነበረም ፤ እግዚአብሔርም ለዚኽ አባት የመላእክትን ዝማሬ ሊያሳየው ስለወደደ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እስከ ሦስተኛው ሰማይ እንደተነጠቀ ኹሉ ሊቁም ተነጥቆ የኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይን የምስጋና ዝማሬ ሰምቶ ተመለሰ፡፡
♥ ቅዱስ ያሬድ ከአርያም ወርዶ ወደ ምድር እንደ ደረሰ ወደ አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ፦ ❝ ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ ❞
[ ለአብ ምስጋና ይገባል ፣ ለወልድም ምስጋና ይገባል ፣ ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል፡፡ ከጽዮን አስቀድሞ ሰማይን ፈጠረ ዳግመኛም ለሙሴ የድንኳኑን ሥራ እንዴት እንደሚሠራ አሳየው ] ሲል ዘምሮ ይቺኑ መዝሙር ከሰማይ መላእክት አገኘኹት ፣ በማለት "አርያም" በሚል ሥያሜ ጠርቷታል፡፡
♥ ይኽነኑ ድርሳነ ዜማ የጻድቁ ካሌብ ልጅ ንጉሥ ገብረ መስቀል በሰማ ጊዜ ጫማውን ሳይጫማ ንግሥቲቱም ደንገጡሮቿን አጃቢዎቿን ሳታስከትል መኳንንቱ ፣ ካህናቱና መምህራኑ እነሱን ተከትለው እየተጣደፉ ወደ ዐደባባዩ በመኼድ በተመስጦ ሲሰሙት ውለዋል፡፡
♥ ቅዱስ ያሬድ ዐምስት የዜማ መጻሕፍትን የደረሰ ሲኾን እነርሱም ፦
፩ኛ ] ድጓ
፪ኛ ] ጾመ ድጓ
፫ኛ ] ምዕራፍ
፬ኛ ] ዝማሬ
፭ኛ ] መዋሥዕት ናቸው፡፡
♥ እነዚኽንም ታላላቅ ድርሰቶቹን በሦስት የዜማ ስልቶች ማለት በግእዝ ፣ በዕዝል ፣ በአራራይ አዘጋጅቷቸዋል፡፡ ❝ ወአሐተ ዕለተ እንዘ ይዜምር ያሬድ ቀዊሞ ታሕተ እገሪሁ ለንጉሥ ገብረ መስቀል ወእንዘ ያጸምዕ ንጉሥ ቃሎ ለያሬድ ተከለ በትረ ኀጺን ውስተ መከየደ እግሩ ለያሬድ❞ ይላል ፤ ከዕለታት ባንዳቸው ቅዱስ ያሬድ በተመስጦ ልዑል እግዚብሔርን በዝማሬ ሲያመሰግን ንጉሥ ገብረ መስቀል ሳያውቁት ልባቸው በጣዕመ ዜማው በመመሰጡ የብረት ዘንጉን በቅዱስ ያሬድ እግር ላይ ተክለውታል፤ ከእግሩም ብዙ ደም ቢፈስስም ቅዱስ ያሬድ ግን ማሕሌቱን እስከሚፈጽም ድረስ ምንም አልሰማውም ነበር፡፡
♥ ንጉሡም የደሙን መፍሰስ አይቶ ደንግጦ ቅዱስ ያሬድን ❝ የደምኽ ዋጋ የፈለግኸውን ንገረኝ ❞ አለው ፤ ቅዱስ ያሬድም ተምኔቱ ወደ ገዳም መኼድ እንደኾነ ነገረው ፤ ያን ጊዜ ንጉሡ እያዘነ አሰናብቶታል፡፡
♥ ❝ ወእምዝ ቦአ ያሬድ ውስተ ቤተ ክርስቲያን ወቆመ ቅድመ ታቦተ ጽዮን ❞ ይላል ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ በታቦተ ጽዮን ፊት በመቆም የአንቀጸ ብርሃንን ምስጋና ከመዠመሪያው እስከ መጨረሻው በተናገረ ጊዜ በእግዚአብሔር ኀይል ክንድ ያኽል ከምድር ከፍ ከፍ አለ።
❤ ከዚኽ በኋላ ወደ ሰሜን ተራራዎች ወደ ገዳም ሲኼድ የአኲስም ጽዮን ካህናት እስከ ተከዜ ወንዝ ድረስ ሸኙት ርሱም እጅግ ባማረ ጣዕመ ዜማ ድምፁን ከፍ አድርጎ ❝ ሰላም እግዚአብሔር ኲሉ ባቲ ተሃሉ ወትረ ምስለ ኲልክሙ ❞ [ በኹሉ ላይ ጸንታ የምትኖር የእግዚአብሔር ሰላም ዘወትር ከኹላችኊ ጋር ትኑር ] ብሎ የስንብት መዝሙርን ዘመረ ፤ ካህናቱም ይኽነን ቃል ሰምተው መሪር እንባን አለቀሱና ተሰነባበቱ፡፡
♥ በትርጓሜ ቅዳሴ ማርያም መቅድም ላይ እንደምናነብበው ቅዱስ ያሬድ ማይ ኪራህ በተባለው ቦታ ተሰውሮ ጸዋትወ ዜማን ሲያስተምር እመቤታችን ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬምን የብህንሳውን አባ ሕርያቆስን በአካለ ነፍስ እንዲመጡ አድርጋ ኤፍሬም ውዳሴዬን ፤ ሕርያቆስ ቅዳሴዬን ነግራችኹት ቅዱስ ያሬድ በዜማ ይድረስልኝ ብላ ነግረውት በዜማ ደርሶታል ፤ ይኽም ሊታወቅ ሥረይ በቅዳሴ ማርያም ይበዛል፡፡
♥ ርሱም ጸዋትወ ዜማን ለደቀ መዛሙርቱ እያስተማረ መላእክት ዘወትር እየጐበኙት በጾም በጸሎት ተወስኖ በተጋድሎ ለኻያ ኹለት ዓመት ጸንቶ ኖረ፤ በመጨረሻም ጌታችንም ለቅዱስ ያሬድ ተገልጾለት ፦
❝ ኦ ፍቁርየ ቀዳሚኒ በከመ ሰመርኩ ትርአይ ሥርዐተ ስብሐተ መላእክት ዘበሰማያት ወአስተኀለፍከ ዘንተ ማሕሌተ ዲበ ምድር ... ❞
[ ወዳጄ ሆይ ቀድሞ በሰማይ ያለ የመላእክትን ሥርዐተ ማሕሌት እንድታይና ወደ ምድርም አስተላልፈኽ ይኽነኑ ዜማ እንድትመሠርት እንደ ወደድኊ ኹሉ እኔ ዳግም ተመልሼ በምመጣበት ጊዜ ከካህናተ ሰማይና ሄሮድስ ደማቸውን ካፈሰሰው ሕፃናት ጋር በደብረ ጽዮን ትዘምር ዘንድ ሰማያዊ የክብር አክሊልና የብርሃን ልብስ ተዘጋጅቶልኻል። ] ብሎት ቃል ኪዳንን ሰጥቶት ጌታ በክብር ዐረገ፡፡ የቅዱስ ያሬድ መታሰቢያውም ግንቦት ዐሥራ አንድ ነው፡፡
♥ ሊቁ አርከ ሥሉስም የቅዱስ ያሬድን ነገር በአርኬው ላይ ፦
❝ ሰላም ለያሬድ ስብሐተ መላእክት ለሕዋጼ
እንተ አዕረገ በልቡ ኅሊና መንፈስ ረዋጼ
ለትምህርተ መጽሐፍ ገብአ እምኀበ ኮነ ነፋጼ
በብዙኅ ጻማ ዘአልቦ ሑጻጼ
መልዕልተ ጒንደ ዖም ነጺሮ እንዘ የዐርግ ዕጼ❞
[ የመላእክትን ምስጋና ለመጐብኘት ከመንፈስ ቅዱስ የሚሰጥ ፈጣን ዐሳብን ወደ ልቡናው ያሳረገ ለኾነ ፤ ጒድለት በሌለበት በብዙ ድካምም ወደ ዛፍ ግንድ ጫፍ ላይ ትል ሲወጣ ተመልክቶ፤ ኰብልሎ ከኼደበት መጻሕፍትን ለመማር የተመለሰ ለኾነ ለያሬድ ሰላምታ ይገባል። ] በማለት ሊቁ ማሕሌታይን አመስግኖታል፡፡
♥ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ ማኅቶተ ቤተ ክርስቲያን ሊቁ ቅዱስ ያሬድን ሲያወድስ ፦
❝ ሰላም ለያሬድ ቀሲስ ዘጽጉብ እክለ መንፈስ ቅዱስ ፤
ዘአስተጋብአ ምድራሳተ እምኲሎሙ መጻሕፍት
ወአሰርገዋ በሐዋዝ ስብሐት ወበጥዑም ማሕሌት
ለብሔረ ኢትዮጵያ በስብሐት ሃሌ ሉያ
ዘከዐወ ቃለ መለኮት ዲቤሃ
ከመ አስራበ ወርቅ ንጹሐ፡፡ ❞
[ የመንፈስ ቅዱስን ምግብን የጠገበ ፤ ከመጻሕፍት ኹሉ ትርጓሜያተ ድርሰትን ያሰባሰበ ፤ ሃሌ ሉያ በሚል ምስጋና የኢትዮጵያ ሀገርን በጥዑም ማሕሌትና በሚያምር ምስጋና ያስጌጠ፤ የመለኮት ቃልን በላይዋ ላይ እንደ ንጹሕ የወርቅ ሻሻቴ ያፈሰሰ ለኾነ ለካህኑ ያሬድ ሰላምታ ይገባል ] ይለዋል፡፡
[ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ]
† † †
💖 🕊 💖

👍8❤1
Forwarded from Ďâňĩ Ÿé ďĩňĝĩl21❤
● ጥዑመ ልሳን
● ንሕብ
● ሊቀ ሊቃውንት
● የሱራፌል አምሳያ
●የቤተ ክርስቲያን እንዚራ
●ካህነ ስብሐት
●መዘምር ዘበድርሳን
● ማኅሌታይ
● ልዑለ ስብከት ቅዱስ ያሬድ
ነገ ግንቦት ፲፩/11 እንኳን ለታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
ይህንን በዓል ምክንያት በማድረግ በግቢ ጉባኤያችን የዝክረ ያሬድ መርሐ ግብር ስለተዘጋጀ ነገ ማለትም ዕለተ ሰኞ 11/09/2017/ ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ታላቅ የቃለ እግዚአብሔር ፤የዝማሬ እና እንዲሁም ለሎችም መርሐ ግብራቶች ተዘጋጅተዋል ። ስለሆነም ሁላችሁም በክፍላችሁ ፤ በንዑስ ክፍላችሁና በለሎችም ግሩፕ ላይ መልእክቱን በማስተላለፍ ተቀሳቅሳችሁ በሰዓቱ እንድትገኙ ስንል በቅዱስ ያሬድ ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ከቀኑ 10:00 ጀምሮ።
ቦታ:- በግቢ ጉባኤው ዋና አዳራሽ።
🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊
🌻🌻 ቅዱስ 🌻🌻️
🌻🌻 ያሬድ 🌻🌻
🌻🌻ግንቦት 11🌻🌻️
🌻️🌹🌾🌻💐🌷🌻
🕊🌻🌻🌻🌻🌻️🕊

❤1🕊1
🌹🥀🥀 ዝክረ 🌹🌿🌿
🥀🥀ቅዱስ ያሬድ 🌹🌹
🌹🌹ግንቦት :-11🌹🌿🥀
🥀የቅዱስ🌹ያሬድ🥀ዓመታዊ 🌹🌿🥀
🌹🌹 መታሰቢያ ክብረ በዓል ነው።🌹 🌿
🌹🌹እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን!🌿🌿🥀
🥀 በግቢ ጉባኤ መርሐ ግብር ስለተዘጋጀ🌹
ተቀሳቅሳችሁ በሰዓቱ እንድትገኙ
🌿🌿በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን🌱🌱
🌿🌿ቦታ:-በግቢ ጉባኤው ዋና🌿 🌿
🥀🥀አዳራሽ 🌹ከቀኑ:-10:00 ጀምሮ🌹
እስከዚያ ሰላም ዋሉ🤲
የደ/ብ/ዩ/ቀ/ግ/ጉባኤ
🥀🥀ቅዱስ ያሬድ 🌹🌹
🌹🌹ግንቦት :-11🌹🌿🥀
🥀የቅዱስ🌹ያሬድ🥀ዓመታዊ 🌹🌿🥀
🌹🌹 መታሰቢያ ክብረ በዓል ነው።🌹 🌿
🌹🌹እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን!🌿🌿🥀
🥀 በግቢ ጉባኤ መርሐ ግብር ስለተዘጋጀ🌹
ተቀሳቅሳችሁ በሰዓቱ እንድትገኙ
🌿🌿በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን🌱🌱
🌿🌿ቦታ:-በግቢ ጉባኤው ዋና🌿 🌿
🥀🥀አዳራሽ 🌹ከቀኑ:-10:00 ጀምሮ🌹
እስከዚያ ሰላም ዋሉ🤲
የደ/ብ/ዩ/ቀ/ግ/ጉባኤ
❤7👍5👏2🕊1
✨"ስራህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ ፥ ሀሳብህም ትፀናለች"ምሳ 16፥3✨
ከነገ ጀምሮ ፈተና ለምትጀምሩ ለ ሪሚዲያል ተማርዎቻችን በሙሉ መልካም ፈተና ይሁንላችሁ ።
በአነበባቹት ልክ ሥሩ እንጂ ከቶ መጨነቅን ከእናንተ አርቁ ፤ፈተና ከመጀመራችሁ በፊት ጸሎት ማድረጉን አትዘንጉ፤ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን ። መልካም ፈተና ✞✝

👍1
Forwarded from Ďâňĩ Ÿé ďĩňĝĩl21❤
ሰላም እንደምን ዋላችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ? የእግዚአብሔር ሰላም የእመቤታችንም ምልጃ የቅዱሳን ሁሉ ጸሎትና ተራዳኢነት ዘወትር አይለየን አሜን።
ነገ ማለትም ዕለተ ሰኑይ 18/09/2017 ዓ.ም ከጥዋቱ 1:45 ጀምሮ የመጨረሻ ጉዞ ወደ ሐበሻ አረጋዊያን ማዕከል ለተመራቂ ተማሪዎች ስለተዘጋጀ ሁላችንም ተቀሳቅሰን ግቢ ጉባኤ ልማት ሱቅ አካባቢ ተሰብስበን በመሄድ የበረከት ሥራዎችን እንሳተፍ።
ልክ 2:00 ስል ጉዞ ይጀመራል 5:00 ስል ወደ ግቢ የምንመለስ ይሆናል።
በየክፍላችሁ ላሉ ተመራቂ ወንድም እህቶቻችን ይደርስ ዘንድ መልእክቱን በራሳችሁ ግሩፕ ላይ share አድርጉት!
ማሳሰቢያ :- ከሐበሻ አረጋዊያን ማዕከል የበጎ አድራጎት ተሳትፎ certificate መቀበል የምትፈልጉ 50 ብር እየያዛችሁ እንድትመጡ።
ጠዋት :- 1:45
ቦታ:- ግቢ ጉባኤ ልማት ሱቅ አካባቢ
የነገ ሰዎች ይበለን ደህና እደሩ🤲❤

➕በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
💚የእግዚአብሔር ሰላም፤የቤዛዊት አለም ምልጃ፣የቅዱሳኑ ተራዳኢነት ከሁላችንም ጋር ይሁን 🤲🤲🤲🤲🤲🤲
👋ሰላም የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ??
💚🌷💚🌷🍂💚🍂🪴💚
የ2ኛ ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና እየወሰዳችሁ ላላችሁ የግቢ ጉባኤያችን ተማሪዎች በሙሉ ግቢ ጉባኤያችን መልካም ፈተና እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቷን ትገልፃለች ።
🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴
💠በፈተናችሁ ሁሉ አምላከ ቅዱሳን ቅዱስ እግዚአብሔር አይለያችሁ፣
ድንግል ማርያም ብርታት ትሁናችሁ ።
💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚
👉በፈተና ወቅት መርሳት የሌለባችሁ ነገሮች
💠 ጸሎታችሁ ሳይታጎል ይቀጥል ፣
💠 ስታነቡም ሆነ ፈተና ስትጀምሩ እና ስትጨርሱ መጸለይን አትርሱ ፣
💠 በሁሉም እግዚአብሔርን አመስገኑ ፣
💠 ሌሎች እህት ወንድሞችን በጸሎት ማሰብ እና መረዳዳት፣
🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂
“ሥራህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፥ አሳብህም ትጸናለች።”
ምሳሌ 16፥3
➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!🙏🙏
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ደ/ብ/ዩ ቀን ግ/ጉ/ት/ት እና ሐ/አ/ክ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

❤7👍5
❖ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የዕርገት በዓል በሰላም አደረሰን/አደረሳችሁ።
#ዕርገት
ቤተክርስትያናችን ከምታከብራቸው በዓላት ውስጥ አንዱ የጌታችን የመድኃኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ ዕርገት ነው።ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ከሞት ከተነሳ በ፵ኛው ቀን ማረጉን በማሰብ ቤተክርስትያናችን ዕርገትን ትንሳኤን በተከበረ በ፵ኛው ቀን ዕርገትን ታከብራለች።በዚህ ዓመትም ቤተክርስትያነችን ዕርገትን ግንቦት21 ታከብረዋለች።
ዕርገት ልክ እንደ ትንሳኤ ሁሉ ቀኑ ይለዋወጣል። ነገር ግን ምንጊዜም ዕርገት ሐሙስን አይለቅም።ልክ ትንሳኤ እሁድን ስቅለት አርብን እደማይለቅ ሁሉ እርገትም ሐሙስን አይለቅም።
ዐረገ በስብሐት
ዐረገ በስብሐት ዐረገ በእልልታ
በስብሐት በእልልታ ዐረገ በስብሐት በእልልታ
አዝ
ሞትን ደል አድርጎ የሰራዊት ጌታ
አረገ በስብሐት በእልልታ
አዝ
እየዘመሩለት መልአክት በደስታ
አረገ በስብሐት በእልልታ
❖ መልካም በዓል ይሁንልን።
የደ/ብ/ዩ/ቀ/ግ/ጉ/

❤13👍4
➕በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
💚የእግዚአብሔር ሰላም፤የቤዛዊት አለም ምልጃ፣የቅዱሳኑ ተራዳኢነት ከሁላችንም ጋር ይሁን 🤲🤲🤲🤲🤲🤲
👋ሰላም የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ??
💚🌷💚🌷🍂💚🍂🪴💚
ማጠቃለያ ፈተና እየወሰዳችሁ ላላችሁ እና ነገ ለምትጀምሩ የግቢ ጉባኤያችን ተማሪዎች በሙሉ ግቢ ጉባኤያችን መልካም ፈተና እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቷን ትገልፃለች ።
🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴
💠በፈተናችሁ ሁሉ አምላከ ቅዱሳን ቅዱስ እግዚአብሔር አይለያችሁ፣
ድንግል ማርያም ብርታት ትሁናችሁ ።
💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚
👉በፈተና ወቅት መርሳት የሌለባችሁ ነገሮች
💠 ጸሎታችሁ ሳይታጎል ይቀጥል ፣
💠 ስታነቡም ሆነ ፈተና ስትጀምሩ እና ስትጨርሱ መጸለይን አትርሱ ፣
💠 በሁሉም እግዚአብሔርን አመስገኑ ፣
💠 ሌሎች እህት ወንድሞችን በጸሎት ማሰብ እና መረዳዳት፣
🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂
“ሥራህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፥ አሳብህም ትጸናለች።”
ምሳሌ 16፥3
➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!🙏🙏
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ደ/ብ/ዩ ቀን ግ/ጉ/ት/ት እና ሐ/አ/ክ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
💚የእግዚአብሔር ሰላም፤የቤዛዊት አለም ምልጃ፣የቅዱሳኑ ተራዳኢነት ከሁላችንም ጋር ይሁን 🤲🤲🤲🤲🤲🤲
👋ሰላም የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ??
💚🌷💚🌷🍂💚🍂🪴💚
ማጠቃለያ ፈተና እየወሰዳችሁ ላላችሁ እና ነገ ለምትጀምሩ የግቢ ጉባኤያችን ተማሪዎች በሙሉ ግቢ ጉባኤያችን መልካም ፈተና እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቷን ትገልፃለች ።
🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴
💠በፈተናችሁ ሁሉ አምላከ ቅዱሳን ቅዱስ እግዚአብሔር አይለያችሁ፣
ድንግል ማርያም ብርታት ትሁናችሁ ።
💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚
👉በፈተና ወቅት መርሳት የሌለባችሁ ነገሮች
💠 ጸሎታችሁ ሳይታጎል ይቀጥል ፣
💠 ስታነቡም ሆነ ፈተና ስትጀምሩ እና ስትጨርሱ መጸለይን አትርሱ ፣
💠 በሁሉም እግዚአብሔርን አመስገኑ ፣
💠 ሌሎች እህት ወንድሞችን በጸሎት ማሰብ እና መረዳዳት፣
🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂
“ሥራህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፥ አሳብህም ትጸናለች።”
ምሳሌ 16፥3
➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!🙏🙏
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ደ/ብ/ዩ ቀን ግ/ጉ/ት/ት እና ሐ/አ/ክ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
❤24
ለተቸገረ ሰው በጎ ነገር ለማድረግ ቸል አትበል።
ምሳ 3፥27
ማኅበረ ቅዱሳን ከደም ባንክ አገልግሎት ጋር በመተባበር ሀገር አቀፍ የደም ልገሳ መርሐ ግብር ግንቦት 29 እንደሚያካሂድ አስታውቋል።
በመሆኑም በደ/ብርሃን ከተማ ማኅበረ ቅዱሳን ደብረ ብርሃን ማእከል ከደ/ብርሃን ደም ባንክ አገልግሎት ጋር በመተባበር በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 3:00 እስከ 11:00 ሰዓት ድረስ የደም ልገሳ መርሐግብር ስለሚካሄድ የማኀበሩ አባላት፣ የግቢ ጉባዔ አባላት እና የከተማው ማኅበረሰብ ወደ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን መገንጠያ ምንሊክ አደባባይ በመገኘት ለዚህ በጎ ተግባር እንድትተባበሩ ማእከሉ ጥሪውን ያስተላልፋል።
ማኅበረ ቅዱሳን ደብረ ብርሃን ማእከል

❤5
የደም አክሊል
ሰኔ 01/10/2017 ዓ.ም በቀን ግቢ ጉባኤ ዋና አዳራሽ በቪክትሪ ግቢ ጉባኤ ተዘጋጅቶ ይታያል ።
ከቀኑ 6:00 ጀምሮ
ቦታ:- በቀን ግቢ ጉባኤ ዋና አዳራሽ

❤7🕊1
Forwarded from Ďâňĩ Ÿé ďĩňĝĩl21❤
ከ exit በኋላ የት ለመሄድ አስበዋል???
እነሆ ለተመራቂ ተማሪዎች የመጨረሻ እና የማጠቃለያ ጉዞ ተዘጋጅቷል ይሄውም በግቢ ቆይታችን የነበረንን ረጅሙን የህይወት ውጣ ውረድ ጨርሰን ከexit exam በኋላ አዕምሯችንን ለማደስ፤ መንፈሳዊነታችንን ለማጠናከር፤ ወደፊት ያለንን ሩጫ በትጋት ለመሮጥ ያስችለን ዘንድ ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር፤ በመጨረሻም በህይወታችን የማይረሳ ክንውን እንድሆነን ይህ ጉዞ ተዘጋጅቷል ። ስለሆነም መነሻችን በቀን 11 ስሆን መመለሻችን ደግሞ ሰኔ 12 ይሆናል። በጉዟችንም ሦስት እና አራት የምሆኑ ቅዱሳን መካናትን የምንሳለም ይሆናል።ፈጥነው ይመስገቡ!

ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን አመሻችሁ?
የእግዚአብሔር ሰላም ፤የእመቤታችንም ምልጃና ጸሎት፤ የቅዱሳን ሁሉ ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን።
ነገ ማለትም ዕለተ ቀዳሚት ሰንበት 30/09/2017 ዓ.ም ይህ መርሐ ግብር ይካሄዳል ሪሚዲያል ተማሪዎች በቀን 2 ስለምወጡ well go ተዘጋጅቷል ሌላው ደግሞ ልዩ የሆነ የዝማሬ ምሽት ይኖራል ሁላችንም ልጆቻችንን እየቀሰቀስን እንድንመጣ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።
ማሳሰቢያ :- በመጨረሻም የ photo program ስላለ ተመራቂ ተማሪዎች በየክፍላችሁ ካሉ ልጆቻችሁ ጋር የደረሰላችሁ የመመረቂያ ልብሳችሁን ለብሳችሁ እንድትመጡ በድጋሚ በእናት ግቢ ጉባኤ ስም እናሳስባችኋለን ።
በሰላም እደሩ!

👍5❤3
ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ
Photo
#በዐለ_ጰራቅሊጦስ_በዐለ_ሃምሣ
ድንገትም እንደ አዉሎ ንፋስ ድምፅ ያለ ከሰማይ ድምፅ
መጣ የነበሩበትን ቤት ሞላው እንደ እሳት የተከፋፈሉ
የእሳት ላንቃዎች ታዩአቸዉ በሁሉም ላይ ተቀመጡባቸው
ሁሉም #መንፈስ_ቅዱስን ተሞሉ ሐዋ.2፥2-4
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ አብይ ፆምን አስፈፅሞ #ለብርሐነ_ትንሣኤዉ እና #ለብርሐነ_እርገቱ በሠላም አድርሶን እንሆ #በዐለ_ሐምሣ (ለመጨረሻዉ ፋሲካ) ደርሰናል ክብርን ሁሉ መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ይዉሰድ ከጌታ አበይት በዐላት አንዱ ለሆነዉ ለበዐለ #መንፈስ_ቅዱስ አመታዊ ክብረ በዐል እንኳን አደረሰን
👉 #ጰራቅሊጦስ ማለት በልሳነ ጽርዕ #መፅናንዒ ማለት ነው ትርጕሙም በጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ ናዛዚ (የሚናዝዝ)፣ መጽንዒ (የሚያጸና)፣ መስተፍሥሒ (የሚያስደስት) ማለት ነው
👉ከሶስቱ አካላት አንዱ ለሆነው #የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ ስም ነው በዓለ ጰራቅሊጦስ #በዓለ_ጰንጠቆስጤም እየተባለ ይጠራል ይኸውም በግሪክ ቋንቋ #በዓለ_ሃምሳ የፋሲካ ሃምሳኛ ዕለት፣ በዓለ ሠዊት (የእሸት የመከር በዓል) ማለት ነው (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ገፅ.፱፻፮- ፱፻፯)
👉በዓለ #ጰራቅሊጦስ ወይም በዓለ #ጰንጠቆስጤ ከዘጠኙ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዐበይት በዓላት አንዱ ሲሆን #መንፈስ_ቅዱስ_ለሐዋርያት_የወረደበትን ቀን የምናስብበት በዓል ነው
👉ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ_ካረገ በኋላ እመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያም፣12ቱ ደቀ መዛሙርት፣ 72ቱ አርድእት 36ቱ ቅዱሳት አንስት በኢየሩሳሌም ከተማ በአንድነት ሆነው ለጸሎት ይተጉ ነበር በሚያርግበት ጊዜም እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ #በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ ሲል ለሐዋርያቱ በገባላቸው ቃል መሠረት ባረገ በአስረኛው ቀን #መንፈስ_ቅዱስን ልኮላቸዋል ሉቃ.24፥49
👉በሐዋርያት ሥራ እንደ ተፃፈው #በበዓለ_ጰራቅሊጦስ ማለዳ ሁሉም በአንድ ቦታ ተሰብስበው ሳሉ እንደ #ዐውሎ_ነፋስ ያለ ድምፅ ድንገት ከሰማይ መጥቶ የነበሩበትን ቤት ሞላው
👉በመቀጠልም #እንደ_እሳት_የተከፋፈሉ_የእሳት_ላንቃዎች በሁሉም ላይ ሞላባቸው በዚህ ጊዜ ሁላቸውም መንፈስ ቅዱስን ከተሞሉ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ባደላቸው መጠን በየአገሩ ቋንቋዎች ሁሉ መናገር ጀመሩ ሐዋ.2፥1-4 ጌታችን መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት የላከበት ይህ ዐቢይ በዓል #ጰራቅሊጦስ ተብሎ ይጠራል
👉ጰራቅሊጦስ ምስጢር እዉቀት ገላጭ ነዉ ሐዋርያት በበዐለ #ጰራቅሊጦስ መንፈስ ቅዱስ ፀጋዉን ካደላቸዉ በኋላ 72 ቋንቋ ተገልፆላቸዋል በዚህም የቅዱሳን መፃህፍት ምስጢር ተገልፆላቸዋል የመድኃኒታችን #የኢየሱስ_ክርስቶስ ትምህርትን ለማስተዋል ችለዋል
👉በፅርሐ ፅዮን በሐዋርያት ላይ የወረደው #መንፈስ_ቅዱስ ያናገረው ቋንቋ የሚሰማ የሚደመጥ የሚታወቅ የሚተረጎም ነበረ ዛሬ የጌታ ተከታይ ነን የሐዋርያት መንፈስ የወረደው ለኛ ነዉ በአዲስ ቋንቋ በልሣን እንናገራለን የሚሉን ሰዎች ንግግራቸው የማይደመጥ የማይተረጎም የተናገሩትን እንኳን መልሳችሁ ተናገሩ ቢባሉ እንኳን የማይደግሙት እንደሆነ እንረዳለን #መንፈስን_ሁሉ_አትመኑ ተብሎ ተፅፏልና እንመርምር
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በቅዱስ መንፈሱ ያፅናን ሀይልና ብርታትን ይስጠን የቅዱሳን አባቶቻችን የቅዱሳን ሐዋርያት ፀሎትና ልመና አይለየን የተባረከ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

👍2❤1
ሰላም እንደምን አደራችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ሰላመ እግዚአብሔር አይለያችሁ
እንኳን ለበዓለ ጴራቂልጦስ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
ዛሬ ጀምራችሁ ከግቢ የምትወጡ ወይም ወደ ቤተሰብ የምትሄዱ ሁሉ በምትሄዱበት ሁሉ የእግዚአብሔር ጠብቆት የእመቤታችንም ምልጃ አብሯችሁ ይሆን ዘንድ እናት ግቢ ጉባኤ ትመኝላችኋለች።
ቅርብም ይሁን ርቀት ስትሄዱ መንገዳችሁን በጸሎት ጀምሩት፤አትደንግጡ አትፍሩ ወደ መጣችሁበትም ስትመለሱ ደግሞ ጥቅትም ይሁን ብዙ በተማራቹበት ጸንታችሁ ኑሩ ለላውን አስተምሩ ከክፉ ራቁ እራሳችሁንና ቤተክርስቲያንን ጠብቁ ስትል እናት ግቢ ጉባኤ ጥሪዋን ታስተላልፋለች።
ለክፍላት ተጠርዎች ወይም ለምመለከተው አካላት ሁሉ:- በትላንትናው ዕለት በነበረው መርሐ ግብር ለዚህ telegram ቻናል መለቀቅ ምችል ምስል በየክፍላችሁ ወይም የነባሮቹና የቀጣይ ሥራ አስፈጻሚዎች ምስል (photo) ካለ የክፍላችሁን ስም እየጻፋችሁ ከታች ባለው ልንክ ግቡና እዛው ላኩልን ለመረጃ እና ለትውስታ እንድቀመጥ ነው።
photo መላኪያ link👉https://t.me/dbugg12
ማሳሰቢያ ከአንድ ክፍል ይሆናል ምትሉትን አንድ ሰው ብቻ ነው መላክ የምችለው።

Telegram
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የቀን ግቢ ጉባዔ photo ማህደር
ይህ የቴሌግራም አውታር የደ/ብ/ዩኒቨርሲቲ የቀን ግቢ ጉባዔ የተለያዩ መደበኛ መርሐ ግብራት የሚከናወኑበት እና የግቢ ጉባኤው መልእክት የሚተላለፍበት ነው።
❤9