ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ
1.28K subscribers
390 photos
36 videos
45 files
49 links
ይህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ ት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ደ/ብ ማዕከል የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የቀን ግቢ ጒባኤ ይፋዊ የቴሌግራም መገናኛ ነው።
Download Telegram
Forwarded from Ďâňĩ Ÿé ďĩňĝĩl21❤
ክርስቶስ ተንስአ እሙታን

በአብይ ሀይለ
ወስልጣን
አሰሮ ለሰይጣን

አግአዞ ለአዳም
ሰላም

እምይዕዘሰ
ኮነ

ፍሰሀ ወሰላም

           ዕለተ ዓርብ ቀን 17/08/2017 ዓ.ም
የሳምንቱ መርሐ ግብር
ቅዳሜ

ከሰዓት ከ10:30-12:30:የክፍላት ውይይት።
እሁድ

ከ8-10ሰዓት ለ2ኛ ዓመት ክርስቲያናዊ ህይወት እና ስነምግባር ኮርስ ቦታ አዳራሽ
ከ8-10 ሰዓት ለ4ኛ እና 5ኛ ዓመት ነገረ ቤተክርስቲያን ኮርስ ቦታ ቤዝመንት።
ከ10-12ሰዓት ለ1ኛ ዓመት ሀይማኖት እና ሳይንስ ኮርስ ቦታ አዳራሽ ።
ከ10-12ሰዓት ለ3ኛ ዓመት የቤተክርስቲያን ታሪክ ኮርስ ቦታ ቤዝመንት።
ከ8-10 ሰዓት የኦሮምኛ ኮርስ  በተለመደው ቦታ
ሰኞ

ከ12:00-1:30 መዝሙር ጥናት
ከሰዓት ከ11-12 ሰዓት ከአባል ለተነሱ ጥያቄዎች
መልስ ምሰጥበት ቀን ነው።
ማክሰኞ

ጠዋት ከ12:00-1:30 መዝሙር ጥናት
ከሰዓት ከ10:30 -12:30 ወርሀዊ የእመቤታችን የጽዋ መርሐ ግብር
ረብዕ

ጠዋት ከ12:00-1:30  ወረብ ጥናት
ከሰዓት ከ11-12 ሰዓት የህይወት ትምህርት
ሐሙስ

ከሰዓት ከ10:45-12:00 የእህቶች መርሐ ግብር
ዓርብ

ጠዋት ከ12:00-1:30 ቅዳሴ ተሰጥኦ ።
ከሰዓት የዓርብ ጸሎት ከ10:30-12:30 ይሆናል።
አብነት ትምህርት በነበረበት ይቀጥላል!
     
ወስብሐት ለእግዚአብሔር



።ይቆየን🤲
please don't forget #Add yours friend to the group.
👍12🏆1
Forwarded from Ďâňĩ Ÿé ďĩňĝĩl21❤
ሰላም እንደምን ቆያችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ? እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም መታሰቢያ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
ዛሬ ማለትም 21/08/2017 ዓ.ም የእመቤታችን የጽዋ መርሐ ግብር ስላለ ሁላችንም በሰዓቱ ተቀሳቅሰን በግቢ ጉባኤው ዋና አዳራሽ እንገኝ የበረከቱ ተካፋዮችም እንሁን።

ቦታ:- በቀን ግቢ ጉባኤ ዋና አዳራሽ
ከቀኑ 10:30 ጀምሮ

መልእክቱን ላልሰሙት በማሰማት በአንድነት እንሂድ።
2
Forwarded from Ďâňĩ Ÿé ďĩňĝĩl21❤
''ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ።(2 ጴጥሮስ 1፥10)
የደብረብርሃን ዩንቨርስቲ የቀን ግቢ ጉባኤ ለ 19 ኛ ግዜ ሥራ አስፈጻሚ ምርጫ በዛሬው ዕለት አከናውናለች።ግቢ ጉባኤያችን ከተመሠረተችበት ግዜ ጀምሮ 18ኛ ዓመቷን እያጠናቀቀች ስሆን ለአድሱ ዓመት ወይም ለ2018 ዓ.ም የግቢ ጉባኤ ሥራ አስፈፃሚዎችን አሳውቃለች።ዛሬ እንደምታወቀው የእመቤታችን የጽዋ መርሐ ግብር የነበረ ስሆን በመርሐ ግብሩም:-
ቃለ እግዚአብሔር በካህናት አባቶች
ዝማሬ በመዝሙር ክፍል
እንድሁም የ2018 ዓ.ም ሥራ አስፈፃሚዎችን የማሳወቅ መርሐ ግብራቶች ተከናውነዋል ።በዛሬው ዕለት የተገኙ አባቶችም ከቃለ እግዚአብሔር ጋር አያይዘው አዲስ ለተመረጡ ሥራ አስፈጻሚዎች አስፈላጊውን አባታዊ ምክር በመስጠት ሰላምለኪ ጸሎት ተደርጎላቸዋል፤ሥራ አስፈጻሚዎች የሥራ ምድባቸውን ወይም የአገልግሎት ክፍላቸውን አሁን ሥራ ላይ ከሉት ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር እየተነጋገሩ የምያውቁ እንደሆነም ተነግሯል።አባቶችም አክለው እነዚህን የተመረጡ አካላትን  በአገልግሎት እንድበረቱና ግቢ ጉባኤያችንን በተቻላቸው አቅም ማገልገል እንድችሉ ሁላችንም በጸሎት ልናስባቸውና በየትኛውም ግዜ ከጎናቸው ልንቆም ይገባናል ብለው በመጨረሻም በጸሎት ተዘግቶ የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሁኗል።

እነሆ ግቢ ጉባኤ ሆይ :-''በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተወለዱልሽ፥ (መዝሙር 45፥16) እንድል ለአንቺም እነሆ በልጆችሽ ቦታ ልጆች ተሰተውሻልና ደስ ይበልሽ።
ወንድሞች እና እህቶች ሆይ እመብርሃን በዕለተ ቀኗ ወደዚህ ክብር ጠርታችኋለችና የአገልግሎት ዘመናችሁን ትባርክላችሁ የመረጣችሁ እግዚአብሔር ነውና ብርታቱን እና ጽናቱን ያድላችሁ።
👍4
Forwarded from Ďâňĩ Ÿé ďĩňĝĩl21❤
እንደ አንድ ክርስቲያን ዕለተ ዓርብ ስታስብ ከህሊናችን የማይጠፋ ቃላት እነዚህን የስልክ profile ከማድረጉም ባለፈ እና በዋናነት የልባችን profile ልናደርጋቸው ይገባናል።ምክንያቱም እኛ የራሳችን ሳንሆን በዋጋ የተገዛን ውድ ልጆቹ ነን።
1👍1
Forwarded from Ďâňĩ Ÿé ďĩňĝĩl21❤
🌷ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንዴት አረፈዳችሁ??

ለማስታወስ ያህል፤ ዛሬ አርብ ከሰአት 10፡30 ጀምሮ የአንድነት የአርብ ጸሎት መርሃ ግብር እና ትምህርት ስላለ ተቀሳቅሰን በመምጣት የመርሀግብሩ ተሳታፊ እንድንሆን።"እስከዛው በሰላም ቆዩ!!"
👍2
Forwarded from Ďâňĩ Ÿé ďĩňĝĩl21❤
ሰላመ እግዚአብሔር ይብዛላችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ቆያችሁ? የጌታችን፤የመድኃኒታችን፤የኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋና ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን።

ነገ ማለትም ዕለተ ረቡዕ ቀን 29/08/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 (አስራ አንድ ሰዓት ) ጀምሮ ሳምንታዊ የህይወት ትምህርት በአውደ ምህረት ላይ ስለሆነ ሁላችንም በመቀሳቀስ በሰዓቱ በመገኘት ህይወት እና ዕረፍት የሆነውን ቃለ እግዚአብሔር እንድንማር ስንል በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ቦታ:-ጠባሴ ደ/ኃ/ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አውደ ምህረት ።

ከቀኑ 11:00 ጀምሮ
እንደ ሀሳብ ይሄንን መልዕክት ለሌሎችም ወይም ላልሰሙትም አሰሟቸው።

ሰላም እንደምን አመሻችሁ ውድ የደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ የቀን ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ውድ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር የአምላካችን ሰላምና ረድኤት ጠብቆቱም ሁል ግዜ ከእኛ አይለየን አሜን።

እንደምታወቀው የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች በየግዜው ወደ ቤተ እግዚአብሔር በመሄድ በጥዋትና በማታ በቀንም የቤተክርስቲያንን ፊት ሳያዩ አይውሉም አያድሩም ይህ በእንዲህ እንዳለ አሁን አሁን ላይ በዩኒቨርስቲው አካባቢ እና በሌሎችም አካባቢዎች እንደምንሰማውና እንደምናየውም ሁሉ በተለይ ሰሞኑን ጥሩ ዜና የለንም በክፉዎች ሰዎች በደል የደረሰባቸው በግቢያችንም በሌሎችም ግቢዎች እየተበራከቱ መጥተዋል ስለሆነም እግዚአብሔር ምጠብቀን የተጠበቀ ሁኖ እኛ ስለራሳችን ደህንነት የራሳችን ሱታፌ ወይም ድርሻ ልንወጣ ይገባናል። ወደ ቤተክርስቲያን ስትሄዱ ግቢው ከ12:00 በፊት እንደማይወጣ እያለ እኛ 11:00 የምንወጣ አለን ይሁን ፈቅደው ካስወጡን እንወጣለን ስንወጣ ግን ቢቻል ከ 3 እና ከ 4 በላይ ሁነን በርከት ብለን እንውጣ እንደው እግዚአብሔር ነው ምጠብቀን እያልን በራሳችን ተላልፈን ለክፉዎች እጅ እንዳንሰጥ እንጠንቀቅ በለሎች ላይ የደረሰው ነገር ደግመው በእኛ ላይ እስኪደርስ ከምንጠብቅ አስፈላጊውን ጥንቃቄ አድርገን እንንቀሳቀስ።

ማድረግ ያለብን ጥንቃቄዎች በዋናነት

1

ነግ ላይ ወይም ጠዋት ቤተክርስቲያን ስንሄድ በህብረት ተቀሳቅሰን እንሂድ ካልሆነ እስከ 12:00 በዶርማችን የግል ጸሎት አድርገን ከ12:00 በኋላ ሂደን የቤተመቅደሱን ኪዳን እና ቅዳሴ መካፈል ።
2

በግቢ ውስጥ ከ library ስናመሽ ብቻችን ባንሆን እና የምናነብበትን ሰዓት ከጓደኞቻችን ጋር አምብበን ሰዓቱ ስሄድ ዶርም ገብተን ብናነብ።

3

ሰሞኑን ከሌሎች ዩንቨርስቲዎች እንደሰማነው አይነት ነገር ልፈጠር ስለምችል አዳድስ ሰዎች በዶርማችን አካባቢ ብመጡ እንደ ክርስቲያን መጠንቀቅ እና ሌሎችንም እንዲሁ ጥንቃቄ እንድያደርጉ መናገር።

4

በቀንም ይሁን በማታ በየትኛውም ግዜና ቦታ እራሳችንን መጠበቅ እና ስንወጣ መጸለይ ስንገባ ማመስገን ይጠበቅብናል።

ይህን ሁሉ እንግዲህ ለራሳችን ደህንነት ስባል እንድናደርግ እንገደዳለን!



ከሁሉ በላይ ግን የእግዚአብሔር ጠብቆት፤የድንግል ማርያም ምልጃና የቅዱሳን ሁሉ ተራዳኢነት ይበልጥብናልና

የእግዚአብሔር ጠብቆት፤የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃና ጸሎት ፤የቅዱሳን መላእክት የቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕታት ፈጣን ተራዳኢነት አይለየን አሜን።

          ከዲ/ን ዳንኤል ደገፉ ( ባች ክፍል)
                    የደ/ብ/ዩ/ቀ/ግ/ጉ/
9🕊6👍3👏3
ዮም ፍስሐ ኮነ
በእንተ ልደታ #ለማርያም
    

    እንኳን
አደረሰን
           አደረሳችሁ
ይህ ቀን በእውነት
ለክርስቲያን ወገኖች ሁሉ የደስታ ቀናቸው ነው።

እንኳን አደረሳችሁ ተባባሉ

ማሳሰቢያ :- ማንኛውም ሰው ምንም አይነት link ወደዚህ ግሩፕ መላክ ፈጽሞ የተከለከለ ነው።
👍9
Forwarded from Ďâňĩ Ÿé ďĩňĝĩl21❤
ይህ ቀን በእውነት የተለየ ቀን ነው በዚህ ቀን ለክርስቲያን ወገኖች ሁሉ የደስታቸው ቀን ነው።
እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን!

ዛሬ ማለትም ግንቦት 01/9/2017 ዓ.ም ዕለተ ቅዳሜ ከቀኑ 10:00 (አስር ሰዓት) ጀምሮ ሳምንታዊው የዓርብ ጸሎት እና ዓመታዊ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የልደቷ መታሰቢያ ክብረ በዓል መርሐ ግብር በግቢ ጉባኤው ይካሄዳል እና በሰዓቱ ተቀሳቅሰን እንድንገኝ በእመቤታችን ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም🤲🤲🤲
የደ/ብ/ዩ/ቀ/ግ/ጉ/
👏6👍1
Forwarded from Ďâňĩ Ÿé ďĩňĝĩl21❤
ሰላም እንደምን አደራችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ?
ሰላመ እግዚአብሔር ይብዛላችሁ ዛሬ ማለትም ዕለተ ቅዳሜ ግንቦት 02/09/2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 (አስር ሰዓት ) ጀምሮ የ ክፍላት ውይይት ስላለ ሁላችንም  በየክፍላችን ልጆችን እየቀሰቀስን በሰዓቱ  እንድንገኝ በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን ።
           የደ/ብ/ዩ/የ/ቀ/ግ/ጉ/