ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ
1.28K subscribers
390 photos
36 videos
45 files
49 links
ይህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ ት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ደ/ብ ማዕከል የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የቀን ግቢ ጒባኤ ይፋዊ የቴሌግራም መገናኛ ነው።
Download Telegram
#ሆሳዕና_ማለት_ምን_ማለት_ነው ??
#በሆሳዕና_ለምን_ቀለበት_እናስራለን ?
#በሆሳዕና_ጌታችን_ለምን_በአህያ_ላይ_ተቀመጠ.   #በሆሳዕና_ለምን_ዘንባባ_አነጠፉ ?
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ሆሳዕና ማለት ምን ማለት ነው??

🔷👉 ሆሳዕና ማለት፦ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ‹‹እባክህ አሁን አድን አሁን ባርከን ›› ማለት ነው፡፡ በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሃት ጸሎተ አስተስርዮ ስለማይፈጸም ጸሎተ ፍትሃትና አስተስርዮ የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው::

🔵👉 በሆሣዕና ዕለት በእጃችን እንደ ቀለበት ማሰራችን የምን ምሳሌ ነው??

1.ጌታ ለአዳም የሰጠው ቃል ኪዳን ለማስታወስ፡-ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድነሃለሁ ያለውን የተስፋ ቃል ለማስታወስ፡፡

2.ጌታ ለእመቤታችን የገባላትን ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው።

3.ጌታ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው።

4.ጌታ ለአዳም ከሰይጣን ግዛት ነጻ እንዳወጣው ሁሉ እኛም ከሰይጣን ግዛት ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ከክፋት ከኃጢአት አውጣን ማረን ለንስኃ ሞት አብቃን ከቤትህ አትለየን እንደ ቸርነትህ ይቅር በለን ስንል ለጌታ ዳግም ላናጠፋ ቃል የምንገባበት ነው፡፡

🔴👉 ጌታችን በዕለተ ሆሳዕና ለምን በፈረስ ላይ አልተቀመጠም??

🔵👉 ትንቢቱንና ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡ " አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።(ትንቢተ ዘካርያስ 9:9)

🔴በአህያ መቀመጡ

👉 ትህትናን ለማስተማር
👉 የሰላም ዘመን ነው ሲል
👉 አህያዎች ትሁታን ናቸው ረጋ ብለው ነው የሚሄዱት፤ በቀላሉ ትወጣበታለህ ፤በቀላሉ ትይዘዋለህ፤እንደፈለክም ታዝዋለህ።
👉 ለፈለጉኝ ሁሉ የቅርብ አምላክ ነኝ ሲል በንጽህና በየዋህነት ለሚኖሩ ምዕመናን አድሬባቸው እኖራለሁ ሲል፡፡

🔵👉 ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ዘባባ የመነጠፉ ሚስጢር የምን ምሳሌ ነው???

👉 .ዘንባባ ደርቆ እንደገና ሂይወት ይዘራል፡- የደረቀ የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡

👉.ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው፡- የሰላም አምላክ ነህ ሲሉ ነው።

👉.ዘንባባ የደስታ መግለጫ ነው፡- አንተ ደስ የምታሰኝ ሃዘናችንም የምታርቅልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡

👉.ዘንባባ እሾሃማ ነው፡- አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡

👉.ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጂ፡፡ ጌታም አንተ ባህሪህን የማይመረመር ነው ሲሉ ነው፡፡

🔴👉 ህዝቡ ከልብሳቸው ሌላ ስንት አይነት ቅጠንል አነጠፉለት ምን ምን??

🔵👉ልብሳቸውን ማንጠፋቸው ፡-

👉 ለክብሩ መግለጫ ነው፡፡ ሌሎችም ሦስት አይነት ቅጠል አነጠፉለት ዘንባባ፤የቴመር ዛፍ፤የወይራ ዛፍ አነጠፉለት፡፡

🔵👉 ጌታችን ኪሩቤል በሚሸከሙት ዙፋን የሚቀመጥ አምላክ ሲሆን ትሁት ሆኖ በአህያ ላይ ተቀመጠ፡፡ አህያዋን ከነውርንጫዋ “ፈታችሁ አምጡልኝ” ማለቱ የሰውን ልጅ ከኃጢአት እሥራት ለመፍታት የመጣ አምላክ መሆኑን ያሳየናል፡፡

🔷👉 ደቀ መዛሙርቱም አህዮቹን ፈተው ማምጣታቸው ሥልጣነ ክህነታቸውን ያመለክታል፡፡ “በምድር  የፈታችሁት በሰማይ የተፈታ ይሁን” እንዲል፡፡

🔴👉 በአህያ ላይ ልብሳቸውን ማንጠፋቸው  ደግሞ የምትመች የማትቆረቁር የወንጌልን ሕግ ሰጠኸን ሲሉ ነው፡፡

🔷👉 በአህያ የተቀመጠ ሰው በፈረስ እንደተቀመጠ ሰው ፈጥኖ አያመልጥም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከፈለጉኝ አያጡኝም ሲል በአህያ ተቀምጧል፡፡

🔴👉 ከግለሰብ ደጅ የተፈታችን አህያ “ ጌታዋ ይፈልጋታል” ብሎ ያስፈታት  በፈጣሪነቱ ወይም ስለፈጠራት ገንዘቡ ስለሆነች ነው፡፡ አህያን ያልናቀ አምላክ እኛም ከኃጢአት ርቀን ብንፈልገው  ማደሪያዎቹ ሊያደርገን ፈቃዱ ነው፡፡ የአህያዋን መፈታት የፈለገ ጌታ እኛም ወደካህናት ቀርበን ኃጢአታችንን ተናዘን ከበደል እሥራት  እንድንፈታ ይፈልጋል፡፡

🔴👉 ትልቅዋ አህያ በምን ትመሳለለች ውርን ጭለዋስ???

#ትልቅዋ_አህያ

👉1, ትልቅዋ አህያ የኦሪት ምሳሌ ነው።
ትልቅዋ አህያ ሸክም የለመደች ናት ህገ ኦሪትም የተለመደች ህግ ናትና፡፡

👉 2.የእስራኤል ምሳሌ ነው፡-ትልቅዋ አህያ ሸክም እንደለመደች ሁሉ እስራኤልም ህግ ለመፈጸም በህግ ለመራመድ የለመዱ ናቸው፡፡

👉 3.የአዳም ምሳሌ ነው፡- አዳም ሸክም የበዛበት ነበርና።

#ውርጭላዋ

👉 1.በህገ ወንጌል ትመሰላለች ፡- ምክንያቱም ወንጌል ኢየሱስ ክርስቶስ የመሰረታት የሰራት አዲስዋ ህግ ናትና፡፡

👉 2.በአህዛብ ትመሰላለች፡-ትንሽዋ አህያ ሸክም የለመደች አይደለችም እንዲሁም አህዛብም ህግህን የመቀበል የመቀበል የለመደ አይደሉም፡፡ ለህግህ አዲስ ናቸውና፡፡

👉 3.የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡- የዓለም ሸክም አቅልላለችና በእመቤታችን ትመሰለላለች፡፡ እመቤታችን ድህነተ ምክንያታችን ጌታን የተሸከመች ንጽህት እንከን የሌላት እናት ናትና፡፡

ስለ በዓሉ የመፅሐፍ ቅዱስ ማስረጃ 👇
ማቴዎስ 21
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ወደ ኢየሩሳሌምም ቀርበው ወደ ደብረ ዘይት ወደ ቤተ ፋጌ ሲደርሱ፥ ያንጊዜ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከ፥
² እንዲህም አላቸው፦ በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርስዋ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ።
³ ማንም አንዳች ቢላችሁ፦ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ፤ ወዲያውም ይሰዳቸዋል።
⁴-⁵ ለጽዮን ልጅ፦ እነሆ፥ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያ ላይና በአህያይቱ ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል በሉአት ተብሎ በነቢይ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ።
⁶ ደቀ መዛሙርቱም ሄደው ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ፥
⁷ አህያይቱንና ውርንጫዋንም አመጡለት፥ ልብሳቸውንም በእነርሱ ላይ ጫኑ፥ ተቀመጠባቸውም።
⁸ ከሕዝቡም እጅግ ብዙዎች ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፥ ሌሎችም ከዛፍ ጫፍ ጫፉን እየቈረጡ በመንገድ ላይ ያነጥፉ ነበር።
⁹ የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም፦ ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።

ከኃጢአት እሥራት ተፈተን፣ የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ማደሪያዎች እንድንሆን የእግዚአብሔር ቸርነት የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ይርዳን፡፡
👍112
text መጻፊያ ተከፍቷል
ጻፉልን!
እንኳን አደረሰን እንኳን አደረሳችሁ   ለዓመቱ በሰላም በጠና ያድርሰን
ወደ text መጻፊያ ለመሄድ 👉https://t.me/dbugg21group
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
❤️ 💛    
   🌿🌿🌿🌿"ሆሣዕና"🌿🌿🌿
💛🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲💛
  🌿🌿🌿 "እንኳን ለበዓለ ሆሣዕና አደረሳችሁ"  🕊🕊🕊
ሆሣዕና በዐቢይ ጾም ስምንተኛ ሳምንት

የሚከበር በዓል ሲሆን ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ ነው። ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መግቢያ ዋዜማ ነው።
#ሆሣዕና የሚለው “ሆሼዕናህ” ከሚለው የዕብራይስጥ ቃል የተገኘ ነው። ሆሣዕና “ #አድነን_እባክህ_አድነን_ወይም_መድኃኒትነት፣ መድኃኒት መሆን ወይም መባል” የሚል ትርጉም ይይዛል። ሆሣዕና በአርያም ሲሆን ደግሞ በሰማይ ያለ መድኀኒት ይሆናል ሆሣዕና የጸበርት(የዘንባባ እሑድም )ይባላል፡፡ በዓለ ሆሣዕና በቤተክርስቲያናችን ሊቃውንት ከዋዜማው ጀምሮ ሌሊቱን በማኅሌት እየዘመሩ የሚያመሰግኑበት ነው፡፡ ወደ ቅዳሴም ሲገባ ለየት ባለ ሁኔታ፦
-#ዲያቆኑ ወደምዕራብ በር በማምራት፦ “አርኅው ኆኃተ መኳንንት(መኳንንት ደጆችን ክፈቱ)” ሲል
-#ካህኑም በውስጥ ሆኖ በዜማ፦ “መኑ ውእቱ ዝንቱ ንጉሠ ስብሐት (የምሥጋና ንጉሥ እርሱ ማነው?)” ይላል፡፡ ይህንንም ከተቀባበሉ በኋላ
-#ዲያቆኑ፦ “እግዚአብሔር አምላከ ኃያላን ውእቱ ዝንቱ ንጉሠ ስብሐት (ይህ የምሥጋና  ንጉሥ የኃያላን አምላክ እግዚአብሔር ነው)" ሲል
-#ካህኑም “ይባእ ንጉሠ ስብሐት ይባእ አምላከ ምሕረት(የምሥጋና ንጉሥ ይግባ የምሕረት ንጉሥ ይግባ)” ይልና
-#ዲያቆናቱ ወደ ውስጥ ዘልቀው ቅዳሴ ሥርዓቱ ይቀጥላል....
በዕለቱም ስለ ሆሣዕና በጥልቀት የሚናገረው የቅዱስ ጎርጎርዮስ (ኤጲስ ቆጶስ  ዘኑሲስ) ቅዳሴ ይቀደሳል፡፡ እጅግ ልዩ በሆነውም የሆሣዕና ዑደት ከዳዊት መዝሙር ምስባክ እየተሰበከ፣ ወንጌል እየተነበበ፣ ከጾመ ድጓውም እየተዜመ ይከበራል፡፡ ለሕዝቡም ዘንባባ ይታደላል፡፡ ጸሎተ ፍትሐትም ይከናወናል፡፡
🌿ሆሣዕና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በይ። እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው። ትሑትም ሆኖ በአህያም በውርንጫይቱም ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል (ዘካ. ፱፣፱)”
ተብሎ አስቀድሞ በነቢዩ ዘካርያስ የተነገረውን ትንቢት የፈጸመበት በአህያዪቱና በውርንጫይቱ ተቀምጦ በታላቅ ክብር ወደ ኢየሩሳሌም የገባበትና ቤተ መቅደሱን ያጸዳበት ልዩ በዓል ነው። ሆሣዕና ከትንቢቱ በተጨማሪ ምሳሌውም የተገለጠበት ነው።በኦሪቱ የነበሩ ነቢያት ዘመኑ የጸብ የጦርነት ከሆነ #በፈረስ ተቀምጠው ዘገር (ጦር) ነጥቀው ይታያሉ። በተቃራኒው ደግሞ ዘመኑ የሰላም የእርቅ የሆነ እንደሆን በአህያ ተቀመጠው መነሳንስ (ጭራ) ይዘው ይታያሉ። 
የሰላም ንጉስ የሆነው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነገረው ትንቢት ተፈጽሞ የተቆጠረው ሱባኤ አልቆ የተመሰለውም ምሳሌ እውን የሚሆንበት ዘመን ደረሰ፤ ሰላም እርቅ ድኅነት ሊፈጸምላችሁ ነው ሊለን በአህያና በውርንጫይቱ ተቀምጦ በብዙ አጀብ ታጅቦ በሆታ በእልልታ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ።
ሕዝቡም ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉለት፤ ዘንባባ እና የዛፎችንም ጫፍ ጫፍ እየቆረጡ
“ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም”
እያሉ ይጮሁ ነበር፡፡ (ማቴ. 21÷1-11) ልብሳቸውን ማንጠፋቸውም ለክብሩ መግለጫ ነው፡፡ እንዲህ ባለ ክብርና ምስጋና ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ከተማዋ በዝማሬና በአመስጋኞች ጩኸት ተናወጠች፡፡
“ወይቤሎሙ ሑሩ ሀገረ ዘቅድሜክሙ፤ ወይእተ ጊዜ ትረክቡ ዕድግተ ዕሥርተ ምስለ ዕዋላ፤ ፍትሕዎን ወአምጽእዎን ሊተ፤ በፊታችሁ ወዳለችው ሀገር መንደር ሂዱያን ጊዜም የታሠረች አህያ ከውርንጫዋ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፍቱና አምጡልኝ”ማቴ    21፥ 2
ብሎ ላካቸው። እንደ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ትርጓሜም እነዚያ አህዮች #ተሠርቀው የታሠሩ ነበሩ።
እነዚህ አህዮች ባለቤታቸው ባልሆኑ ሰዎች ተሠርቀው እንደታሠሩ ሁሉ የሰው ልጆችም በምክረ ከይሲ ተታለው በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን እምነት አጉድለው ሕጉንም አፍርሰው ከተከለከሉት ዕፀ በለስ በመብላት ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን በአጋንንት ቁራኝነት ታሥረው ይኖሩ ነበር።
በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት አምነን በሐዋርያት ሥልጣን ከማዕሠረ ኃጢአት የምንፈታበት ዘመን መድረሱን ሊነግረን ሐዋርያቱን ወደ አህዮቹ ላካቸው።
ሐዋርያቱ ወንጌለ መንግሥትን አስተምረው አሳምነው በተሰጣቸው ሥልጣን በኃጢአት ማሠርያ የተያዘውን ዓለም እየፈቱ ወደ ክርስቶስ የሚያቀርቡ እውነተኞች መልእክተኞች ናቸው። አህዮቹን ፈትተው ሊያቀርቡለት ሲሞክሩም አንዳች የሚቃወማቸው ቢኖር “ወእመቦ ዘይቤለክሙ ምንተ ትገብሩ በሉ እግዚኦሙ ይፈቅዶሙ ወበጊዜሃ ይፌንወክሙ፤ ምን ታደርጋላችሁ? የሚላችሁ ቢኖርም ጌታቸው ይሻቸዋል በሉ፤ ያን ጊዜ ይሰዱአችኋል” ብሎ ነግሯቸው ነበርና እንደ ቃሉ አደረጉ። ፈተው ማምጣታቸው ሥልጣነ ክኅነታቸውን ያመላክታል።
"በምድር የምታስሩት በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የፈታችኹት በሰማይ የተፈታ ይሆናል" ማቴ 18፥18
አህያዋና ውርንጫዋ፦ አህያ በዚህ ዓለም ለሸክም የሚያገለግል የተናቀ የተጠላ እንስሳ ነው። እንዲሁም ተጭና እየተደበደበች ጌታዋን በትህትና የምታገለግል ናት አህያ።
ጌታችን በአህያ ጀርባ መምጣቱ ታዲያ በትሁታን ለማደሩ ምሳሌ ነው!!!
✍️አንድም ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ቢጠይቁት ቅርብ የመሆኑ፤ እርሱን በሃይማኖት ለሚሹት፣ በሕግ በአምልኮ ለሚከተሉት በመከራ በስቃይ ውስጥ ሆነው በጽናት ተስፋ ለሚያደርጉት የቅርብ አምላክ መሆኑን ለማጠየቅ።
✍️አንድም አህያዋ ተሰርቃ የታሰረች መሆኗ ከአቤል ጀምሮ እስከ እዚያች ዕለት የሞቱ ነፍሳት በሞት አበጋዝ እጅ በሲዖል ታስረው ነበርና ከዛ ነጻ የማውጣቱ ምሳሌ ነው።
✍️አንድም እናቲቱ ጭነት የለመደች፤ውርንጭላዋ ደግሞ ያልለመደች መሆናቸው ኦሪትን የሚያውቁት ሕጉንም የሚያከብሩ(ሕዝቦች) እና የማያውቁትን (የአሕዛብ) ምሳሌ ናቸው። በፈቃዱ በተከፈለው ዋጋ(ቤዛነት) ሕዝም አሕዛብም በርሱ አምነው ማደሪያው የመሆናቸው ምሳሌ ነው።
ከኢየሩሳሌም እስከ ቤተ መቅደስ ፲፮ ምዕራፍ ነው፡፡
፲፬ቱን በእግሩ ሄዶ ሁለቱን በአህያዋ፣ በውርንጫይቱ ደግሞ ሦስት ጊዜ ቤተ መቅደሱን ዞሯል፡፡ ይህም #የሦስትነቱ ምሳሌ፣ #አሥራ_አራቱን በእግሩ መሄዱ አሥርቱ ትእዛዛትን፣ አራቱ ደግሞ የአራቱ ኪዳናት ማለትም ኪዳነ ኖኅ፣ ክህነተ መልከ ጼዴቅ፣ ግዝረተ አብርሃም እና ጥምቀተ ዮሐንስን ያመለክተናል፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ መቅደስ ሲገባ ሕዝቡ 🌿ዘንባባ ይዘው “ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር፤ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረክ ነው።’’ (መዝ. 117፥26) በማለት ስለተቀበሉት ይህን በማሰብ ቤተ ክርስቲያናችን ዘንባባ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ታድላለች፤ በቤተ ክርስቲያን በአራቱም ማዕዘናት ከአራቱም ወንጌል ዕለቱን የሚመለከቱ ምንባባት ይነበባሉ፡፡
በአጠቃላይ ዕለቱ ቤተክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል ።ውድ ክርስቲያኖች በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ 🙏
መልካም በዓል 🙏🙏

"ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር...ይቆየን"

💚🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱💛
የደብረብርሃን ዩንቨርስቲ የቀን ግቢ ጉባኤ ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል!!!
❤️🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳❤️
👍53😭1
ስላም እንደምን ቆያችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ሰላመ እግዚአብሔር በያለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን።
በግቢ ጉባኤያችን በኩል የተላለፈ አንድ መልዕክት አለን! ይሄውም
የ2017 ዓ.ም የጌታችን ፤የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ በዓል በግቢ ጉባኤ በበዓሉ ማግስት ማለትም ሰኞ 13/07/2017 ዓ.ም አቅመ ደካሞች እና ነዳያንን በመሰብሰብ በአንድነት እንድናከብር እና በረከቱን እንድንሳተፍ ግቢ ጉባኤ ጥሪ አቅርባለች እና ሁላችንም በየ ዶርማችን የተመደቡ አካላት ይሄዳሉ እና በምገባ ተመዝግባችሁ በዓሉን በአንድነት እንድናከብር በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ምዝገባ በየ ዶርም የተመደቡ በጎ አድራጎት ወይም አካላት ይሄዱና ይመዘግባሉ

መመዝገቢያ ፦100 ብር  ጀምሮ ነው!

በአንድ መቶ ብር ብዙ በረከት እናተርፋለን አንድም 50 ብሩ ለእራሳችን ስሆን 50 ብር ደግሞ ነዳያንን ይመግባልና ሁላችንም ይሄንን ታላቅ በረከት ልንሳተፊ ይገባናል።
ይሄ ትልቅ የበረከት ሥራ አምናም እጅግ አሪፍ እንደነበር ተመልክተን ነበር!
          የደ/ብ/ዩ/ቀ/ግ/ጉ/
6👍4🕊2
ሰሙነ ሕማማት
              #ረቡዕ
በዚህች ዕለት ያስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሰጠውና ሌሎችም ይታሰባሉ። በቅዱስ ማቴዎስና በቅዱስ ማርቆስ አመዘጋገብ መሠረት በዕለተ ረቡዕ የሚከተሉት ሦስት ነገሮች ተፈጽመዋል፦
፩. #ምክረ_አይሁድ ይባላል
የካህናት አለቆች፣ የሕዝብ ሽማግሌዎችና ጸሐፍት ፈሪሳውያን በጌታችን ላይ ተማክረዋልና።

፪. #የመልካም_መዓዛ_ቀን ይባላል
ጌታችን በስምዖን ዘለምጽ ቤት ሳለ ማርያም እንተ እፍረት (የአልዓዛር እህት ማርያም) ሽቱ ቀብታዋለችና፡፡ ዮሐ.12 ፥ 3።

፫. #ከዳተኛው_ይሁዳ_ጌታችንን_አሳልፎ_ለመስጠት ከጸሐፍት ፈሪሳውያንና ከካህናት አለቆች ዘንድ ሠላሳ ብር ለመቀበል ተስማምቷል፡፡

    የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሹማንምት በጌታችን ላይ ይሙት በቃ ለመወሰን የሰበሰቡት ሸንጐ ‹#ሲኒሃ_ድርየም› ይባላል፡፡ በዚህ ሸንጐ ላይ በአብዛኛው የተሰየሙት ሰዱቃውያን ሲኾኑ ሌሎቹ ደግሞ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ነበሩ፡፡

    ሸንጎው በአጠቃላይ ሰባ ሁለት አባላት የነበሩት ሲኾን የሚመራውም በሊቀ ካህናቱ በቀያፋ ነበር፡፡ በዕለቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት ይዘው እንደሚገድሉት አይሁድ በዚህ ሸንጎ መክረዋል፡፡ ከዳተኛው ይሁዳም ጸሐፍት ፈሪሳውያንና የካህናት አለቆች በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የነበራቸውን ጥላቻ ያውቅ ስለነበር ‹‹#ምን_ልትሰጡኝ_ትወዳላችሁ? #እኔም_አሳልፌ_እሰጣችኋለሁ፤›› በማለት ጌታችንን አሳልፎ ሊሰጣቸው እንደሚችል ተስማምቷል፡፡

   ጌታችን ያስተምር በነበረበት ወቅት የአስቆሮቱ ይሁዳ ከምእመናን ለሚገባው ገንዘብ ሰብሳቢ (#ዐቃቤ_ንዋይ) ነበር፡፡ ከሚሰበሰበው ሙዳየ ምጽዋት ለግል ጥቅሙ እየቀረጠ የማስቀረት የእጅ አመል ነበረበት (ሲሰርቅ ነበር)።

   ይሁዳ ፍቅረ ንዋይ እንደሚያጠቃው ድብቅ አመሉ ጎልቶ የወጣው ጌታችን በለምጻሙ  በስምዖን ቤት ሳለ የአልአዛር እህት ማርያም እንተ እፍረት ዋጋው እጅግ ውድ የኾነ ሽቱ በቀባችው ጊዜ ነው፡፡ በዚያች ዕለት ይሁዳ የተቃውሞ ድምፅ ካሰሙት አንዱ ነበር፡፡

   ‹‹#ይህ_ሽቱ_ተሽጦ_ለድሆች_ቢሰጥ_መልካም_ነበር፤›› በማለት ያቀረበው አሳብ ‹‹#አዛኝ_መሳይ_ቅቤ_አንጓች›› እንደሚባለው ነበር፡፡ ሽቱ ሲሸጥ የሚያገኘው ጥቅም አለ፤ ሽቶው በጌታችን እግር ሥር ከፈሰሰ ለእርሱ የሚተርፈው የለም፡፡  ይሁዳ ተቆርቋሪ መስሎ ያቀረበው አሳብ ተቀባይነት በማጣቱም ማኩረፊያ ያገኘ መስሎት በቀጥታ ከካህናት አለቆች ዘንድ ሔዶ ጌታን በሠላሳ ብር ለመሸጥ ተዋዋለ፡፡ ይህ ታሪክም  በሦስቱ ወንጌላት ፤ ማቴ. ፳፮፥፫-፲፮፤ ማር. ፲፬፥፩-፲፩፤ ሉቃ. ፳፪፥፩፮፡፡ ተመዝግቦ እናገኛለን።

     የአስቆሮቱ ይሁዳ እንደ ሌሎች ሐዋርያት ከጌታችን ተምሯል፡፡ በረከተ ኅብስቱን ተመግቧል፡፡ ልዩ ልዩ ተአምራት በጌታችን እጅ ሲደረጉ ሁሉ ተመልክቷል፡፡
ጌታችንም ከሌሎች ሐዋርያት ሳይለየው እግሩን አጥቦታል፡፡ ከዳተኛው ይሁዳ ግን ለሐዋርያነት የጠራውን፣ ተንበርክኮ እግሩን ያጠበውን ጌታ ለሞት አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ ‹‹የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሔዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት!›› ተብሎ እንደ ተጻፈ (ማቴ. ፳፮፥፳፬)፡፡ ሌሎች ሐዋርያት ከጌታችን ዘንድ ፍቅሩን ገንዘብ ሲያደርጉ ይሁዳ ግን እርግማንን ነው ያተረፈው፡፡

‹‹#ገንዘብ_የኃጢአት_ሥር_ነው፤›› ተብሎ አንደ ተነገረ የኃጢአት ሥር የተባለው ገንዘብ የክርስቲያኖችን ሕይወት ያዳክማልና ፤ ምእመናን እንደ ይሁዳ በገንዘብ ፍቅር እንዳንወድቅ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ሰው ‹‹ይህን ዓለም ቢያተርፍ ነፍሱን ከጐዳ ምን ይጠቅመዋል?›› ተብሎ የተነገረውን ቃል ልብ ማለት ጠቃሚ ነው፡፡ ክርስቲያን ነን በማለት የክርስትናውን ስም በመያዝ እምነታቸውን፣ የቆሙበትን ዓላማ በገንዘብ የሚለውጡ ሰዎች ዛሬም እንደ ይሁዳ ጌታችንን እየሸጡት እንደ ሆነ ሊገነዘቡት ይገባል፡፡

   ለድሆች መመጽወት ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው፡፡ ዳሩ ግን በድሆች ስም የሰውን ገንዘብ ለግል ጥቅም ማዋል እጅግ የከፋ ኃጢአት ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ለገንዘብ ብለው ድሆችን ለረኃብ ለችግር ባልንጀራቸውን ለመከራ እና ለሞት አሳልፈው ሲሰጡ ምንም አይጸጽታቸውም፡፡ እውነተኛ ክርስቲያኖች ግን ሕይወታችንን ለገንዘብ ፍቅር ሳይሆን ለእምነታችንና ለባልንጀራችን አሳልፈን መስጠት ይኖርብናል፡፡ በፍቅረ ንዋይ ተጠምደን ሰዎችን አሳልፎ በመስጠት ለአይሁዳዊ ሸንጐ ምቹ ሆነን መገኘት እንደሌለብን መገንዘብ አለብን፡፡
   እግዚአብሔር ከይሁዳ መንገድ ይሠውረን! አሜን።

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም አሜን!

ያለ ደዌና ያለ ሕማም ያለ ፃማና ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን እንደ ዛሬ ቀን በደስታና በፍቅር በአንድነት ያድርሰን ያድርሳችሁ አሜን!
5👍2
Forwarded from Ďâňĩ Ÿé ďĩňĝĩl21❤
<<እንበለ ደዌ ወህማም፣እንበለ ፃማ ወድካም፣አመ ከመ ዮም ፣ያብጽሀነ ያብፅህክሙ፣ለብርሃነ ትንሣኤ በፍስሀ ወበሰላም።
እንደምን አላችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች?
እንደምታወቀው ሰሞኑን የተጀመረ ትልቅ የበረከት ሥራ አለ ይሄውም የጌታችን፤የመድኀኒታችንና የፈጣሪያችን የኢየሱስ ክርስቶስን የትንሣኤ መታሰቢያ በዓል ከአቅሜ ደካሞች ጋር አብረን በአንድነት ለማክበር ታቅዶ የበረከት ሥራ ላይ እንገኛለን።ስለሆነም ሁላችንም የግቢ ጉባኤ ልጆች ይህንን ታላቅ የበረከት በዓል በመሳተፍ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንደምባል እኛ በሥጋችንም በነፍሳችን ተጠቅመን፤የምስራቹን ቃለ ወንጌል ሰምተን ያዘኑትንም አጽናንተን በዓሉን እንድናሳልፍ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ማሳሰቢያ:- ለዚህ ሥራ የተመደቡ አካላት በተመደቡበት ቦታ እየሄዱ ብር ይሰበስባሉ እና ግቢ ምታሳልፉ የተባለውን በማድረግ እንድትተባበሩ ወደ ቤተሰብ የምትሄዱ ደግሞ በረከቱ ለእናንተም እንድደርሳችሁ ያላችሁን እንድታበረክቱ እና በጎዳና ወድቀው የሰዎችን እጅ የምጠባበቁትን ለቀናቶች መመገብ ባንችልም እንኳን ለሰዓታት ከእኛ ጋር በትንሣኤው ብርሃን አብረውን እንድደሰቱ ስንል እናሳስባለን!

እየሰጣችሁ  ያላችሁም እግዚአብሔር ይስጥልን እናመሰግናለን🤲!
የደ/ብ/ዩ/ቀ/ግ/ጉ
3
Forwarded from Ďâňĩ Ÿé ďĩňĝĩl21❤
Forwarded from Ďâňĩ Ÿé ďĩňĝĩl21❤
ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ
Photo
🍂 +  ሕያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጉታላችሁ?  #ተነስቷል_እንጂ_በዚህ_የለም   + 🍂

†††   ክርስቶስ ተንስአ እሙታን!
¤      በዐቢይ ኃይል ወስልጣን!
†††  አሠሮ ለሰይጣን!
¤      አግዐዞ ለአዳም!
†††   ሰላም!
¤      እምይእዜሰ!
†††   ኮነ!
¤       ፍሥሐ ወሰላም


  የሰው ልጅ በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥ እና ሊሰቀል #በሦስተኛውም_ቀን_ሊነሣ ግድ ነው እያለ ገና በገሊላ ሳለ ለእናንተ እንደተናገረ አስቡ።
                    ( ሉቃ 24 ፥ 5 , 6 )

    🍀 " ትላንት ይሁዳ ሰረቀ
ዛሬ ደግሞ ጥበቃዎች መማለጃ (ጉቦ) ተቀበሉ ፤
የእውነት ጠላቶች ኪሶቻቸውን በጉቦ አቆሸሹ ፤
ግን እውነቱን መደበቅ አልተቻላቸውም ፤
ኃያሉ ጌታ ራሱን አሳልፎ ሰጠ ፤ደካማ ሰዎች ዙሪያውን ከበቡት  ነጻ ወጥቶ በእነርሱ ላይ በቀልን እንዳያደርግባቸው
ተቀምጠው ይጠብቁት ነበር ፤ በመቃብር አድሮ ሳለ እንኳን ጠላቶቹን ማንቀጥቀጥ የሚችለው እርሱ ባያስፈራቸው ኖሮ ፤ ስለምን መቃብሩን ይጠብቁት ነበር።"
      ( ድርሳን ዘቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ በእንተ ትንሣኤ )

             +    +    +

🌻 "ይእዜኒ ንትለዋ ለሰላም እስመ ተንስዓ ክርስቶስ ዮም በዛቲ ዕለት አክሊሎሙ ለሰማዕት ክብሮሙ ለመላዕክት ወልድ ተንስሥአ ቤዛነ ሥዒሮ ሞተ ወከይዶ ሲኦለ ንግበር በዓለ በትፍሥሕት ተዝካረ ትንሣኤሁ ለመድኃኒነ።"
    
🌹  ዛሬ በዚህች ቀን ክርስቶስ ከሙታን ተነስቷልና ፤
ከዛሬ ጀምሮ ሰላምን እንከተላት ፤
የሰማዕታት አክሊላቸው ፣
የመላእክት ክብራቸው
ቤዛችን ወልድ ሞትን ሽሮ ሲኦልን ረግጦ ከሞት ተነሣ ፤ የመድኃኒታችን የትንሣኤውን መታሰቢያ
በደስታ በዓልን እናድርግ።
          ( ድጓ ዘፋሲካ )

💥 አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት
#በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነስቷል።
ሞት በሰው በኩል ስለመጣ
ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኗል።💥
     
          ( 1ኛ ቆሮ 15 ፥20 - 22 )

                      🙏

ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፤

ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን፤ የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቋልና።

ነገር ግን ከክርስቶስ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንድንኖር እናምናለን፤

ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቶ ወደ ፊት እንዳይሞት ሞትም ወደ ፊት እንዳይገዛው እናውቃለንና።

መሞትን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ለኃጢአት ሞቶአልና፤ በሕይወት መኖርን ግን ለእግዚአብሔር ይኖራል።

እንዲሁም እናንተ ደግሞ ለኃጢአት እንደ ሞታችሁ፥ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደ ሆናችሁ ራሳችሁን ቁጠሩ።

/ ሮሜ 6 - 5 -11 /

     🍂

    የትንሣኤውን ብርሃን እንድናይ ያደለን፤
ከሞት ወደ ሕይወት ፣ ከባርነት ወደ ነጻነት ፣ ከሲኦል ወደ ገነት                 #በፍቅሩ_ያሻገረን
ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ
                 ምስጋና ይሁን
                         🙏

+🍂 እንኳን  #ለብርሀነ_ትንሣኤው
በሰላም አደረሳችሁ 🍂
          
    +    +      +    +    +   +   +

  የደ/ብ/ዩ/ቀ/ግ/ጉ/
1👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ክርስቶስ ተንስአ እሙታን

በአብይ ሐይለ ወስልጣን           
አሰሮ ለሰይጣን

አጋእዞ ለአዳም                        
ሰላም

እምይዜሰ   

ኮነ

ፍስሐ ወሰላም

መልካም በዓል
የድንግል ማርያም ልጅ እየሱስ ክርስቶስ የበረከት የሰላም የጤና የአንድነት የአብሮነት በዓል ያድርግልን ።

እንኳን ለጌታችን፥ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
የደብረብርሃን ዩንቨርሲቲ የቀን ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች አብዛኛው ቅዳሴ ቀሪዎቹ ደግሞ ካፌ ላይ የጾም መፍቻ የበረከት ሥራ ላይ ።
ፍቅር+ ጾም + መተሳሰብ + መከባበር +የበረከት ሥራ =ለትንሣኤ በዓል
እንኳን አደረሳችሁ
credited by dani
11👍4🕊1
ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሰሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም''

''ክርስቶስ በታላቅ በኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ''

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም  በጤና አደረሳችሁ አደረሰን በዓሉ የሰላም የፍቅር የአንድነት ያርግልን።

text መጻፊያው ተከፍቷል መልካሙን ሰላምታ ተለዋወጡ!
👍21
ወደ ሀሳብ መስጫ ለመሄድ ይሄንን ይጠቀሙ
👉https://t.me/dbugg21group
1
ዛሬ የጥዋት መርሐ ግብር በግቢ ጉባኤ ዋና አዳራሽ
10👍2🏆2👏1🕊1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ክርስቶስ ተንስአ እሙታን

በአብይ ሐይለ ወስልጣን           
አሰሮ ለሰይጣን

አጋእዞ ለአዳም                        
ሰላም

እምይዜሰ   

ኮነ

ፍስሐ ወሰላም

መልካም በዓል
የድንግል ማርያም ልጅ እየሱስ ክርስቶስ የበረከት የሰላም የጤና የአንድነት የአብሮነት በዓል ያድርግልን ።

እንኳን ለጌታችን፥ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን🤲🤲🤲

የጥዋት መርሐ ግብ በአጭሩ
1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
''ፈርተውም ፊታቸውን ወደ ምድር አቀርቅረው ሳሉ፥ እንዲህ አሉአቸው፦ ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።(ሉቃስ24፥5)
ክርስቶስ ተንስአ እሙታን

በአብይ ሐይለ ወስልጣን           
አሰሮ ለሰይጣን

አጋእዞ ለአዳም                        
ሰላም

እምይዜሰ   

ኮነ

ፍስሐ ወሰላም

የከሰዓት የምሳ program ካፌ
👍3