ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ
1.28K subscribers
390 photos
36 videos
45 files
49 links
ይህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ ት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ደ/ብ ማዕከል የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የቀን ግቢ ጒባኤ ይፋዊ የቴሌግራም መገናኛ ነው።
Download Telegram
ዛሬ ማለትም ዕለተ ሰንበተ ክርስቲያን ቅድስት 21/07/2017 ዓ.ም የደ/ብ/ዩ/ቀ/ግ/ጉ/ አስራ ስምንተኛ (18ኛ) ዓመት የግቢ ጉባኤ የምሥረታ በዓል ዛሬ ሦስተኛውን ቀን የያዘ ሲሆን ፤በዚህ ታላቅ ክብረ በዓል ላይ ተጋባዥ መምህራን እና ዘማሪያን፤የደብረብርሃን ማዕከል ማህበረ ቅዱሳን ሥራ አስፈጻሚዎች ተገኝተዋል።
በዚህ መርሐ ግብር ላይ እንዲሁም በተደረገው ቅስቀሳ መሠረት ከአንድ መቶ ሐምሳ ሦስት በላይ (153) የቀድሞ የግቢ ጉባኤያችን ተመራቂዎችም  ተገኝተዋል።
ዛሬ ላይ የነበሩን መርሐ ግብራቶች :
1,በጸሎት መክፈት
2,ዝማሬ
3,ስነ ጽሑፍ
4,በየክፍላቶች ከቀድሞ ተመራቂ ተማሪዎች ጋር የልምድ ልውውጥ እና ምክክር
5,ማጠቃለያ በማህበረ ቅዱሳን ሥራ አስፈፃሚ እና የግቢ ጉባኤያት አስተባባሪ በሆኑት በዲ/ን ዘውዱ ተሰጥቶ
በመጨረሻም በጸሎት ተዘግቶ የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል ።
አነሳስቶ ያስጀመረን አስጀምሮም ያስፈጸመን የአባቶቻችን አምላክ አምላከ ቅዱሳን ቅዱስ እግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለሙ የተመሰገነ ይሁን።
       ለከርሞ እንዲሁ በቸርነቱ ጠብቆ ቸር ያገናኘን።
11👍6🕊1🏆1
text መጻፊያ ተከፍቷል መልካም ምኞታችሁን ተለዋወጡ ለዓመቱ በሰላም በጠና ያድርሰን
ወደ text መጻፊያ ለመሄድ 👉https://t.me/dbugg21group
3🏆1
Forwarded from Ďâňĩ Ÿé ďĩňĝĩl21❤
"ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፤ የህያውን አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው። በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤

ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፥ በመኳንንት የሚፈርደውንም በእርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የሾህ ዘውድ አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የገርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት፤ ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ አሥሮ ፊቱን ጸፋው፤ የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ የሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡

ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው? ይህን ያህል ትእግስት እንደምን ያለ ትእግስት ነው? ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው? ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው? ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው በደል የሌለበትን እንደበደለኛ ሰቀሉት፡፡ ህይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋር ቆጠሩት፤ አዳምን የሠሩ እጆች በመስቀል ቀኖዎት ተቸነከሩ፤  ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ተቸነከሩ፡፡

ወዮ በአዳም ፊት የህይወት እስትንፋስን እፍ ያለ አፍ ከሃሞት ጋር የተቀላቀለ የኮመጠጠ መፃፃን ጠጣ፤... ወዮ የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምንስ አንደበት ነው? የፍቁሩ የጌታ ህማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል፤ ህሊናም ይመታል፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች፤ ሥጋም ይደክማል የማይሞተው ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ። የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡"

/ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/
👍111🕊1
ጥንተ ስቅለት
     🌳🌳    መጋቢት 27 ቀን 33 ዓ.ም የዓለም መድኅን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም በነሣው ሥጋ በቀራንዮ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሕይወቱን ለዓለም ቤዛ አድርጎ የሰጠበት ቀን እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ይህ ቀን ስለ ክርስቶስ ሕማም፣ ስለመከራ መስቀሉና ስለሞቱ የተነገሩት ትንቢቶችና ምሳሌዎች ሁሉ የተፈጸሙበት፤ ሰማያዊ አምላክ ስለ ሰው ልጆች ፍቅር ሲል ልዩ ልዩ ጸዋትወ መከራዎችን የተቀበለበትና በሞቱ ሞትን ሽሮ የአዳምን ዘር ሁሉ ከሞት ሞት ያዳነበት፣ ለዓለሙ ሁሉ ፍቅሩን የገለጠበት፣ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙም ዓለምን ነፃ ያወጣበት፣ በአጠቃላይ ዐሥራ ሦስቱን ሕማማተ መስቀል በትዕግሥት ተቀብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በገዛ ፈቃዱ የለየበት የስቅለቱና የሞቱ መታሰቢያ የሚከበርበት ቀን በመሆኑ ጥንተ ስቅለት ተብሎ ይጠራል፡፡
       🌲   የጥንተ ስቅለቱ የመታሰቢያ በዓል በሚከበርበት ቀን በመጋቢት 27 ነው በዚህም ቀን ምእመናን ሁሉ በቤተክርስቲያን በመገኘት በእሱ ደም ዓለም የዳነ መሆኑን በሚገልጠው መድኃኔዓለም በተሰኘው ስሙ እየተማጸኑና ዓለምን ለማዳን የተቀበለውን መከራ መስቀል እያስታወሱ በዓሉን በድምቀት ያከብሩታል፡፡
  🌲  ዓለም የዳነውም   በመስቀሉ ላይ በአፈሰሰው ደሙና በሞቱ አማካይነት በተገኘው ጸጋ ነውና የጥንተ ስቅለቱና የመስቀሉም ምሥጢር ዓለምን የማዳን ምስጢር ስለሆነ መድኃኔዓለም የሚለው የጌታችን ስም ቃሉ ራሱ የድኅነት ወይም የመዳን ቃል እንደሆነ በምሥጢር የሚያስረዱት ቅዱሳት መጻሕፍት ብዙዎች ናቸው ለምሳሌ ያህልም  ‹‹እግዚአብሔር ዓለም ከመፈጠሩና ከተፈጠረም በኋላ ዘለዓለማዊ ንጉሥ ነው፡፡ የምድር ማዕከል በሆነች ቀራንዮም መድኃኒትን አደረገ›› የሚለው የነቢዩ ዳዊት ትንቢት አንደኛው ማስረጃ ነው መዝ.73፡14 ፡፡
     🌲 በዓሉም በዓለ መድኃኔዓለም እየተባለ በየዓመቱ በመድኃኔዓለም ስም በታነጹ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ታቦተ ሕጉ እየወጣና ዑደትም እየተደረገ በታላቅ ክብር ሲከበር የኖረ ታላቅ መንፈሳዊ በዓል መድኃኔዓለም ማለት ምን ማለት ነውካልን ክርስቶስ ማለት መሲህ ኢየሱስ ማለት መድኃኒት አማኑኤል ማለትም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ተብሎ እንደሚተረጎም ሁሉ መድኃኔዓለም ማለትም ዓለምን ሁሉ የሚያድን የዓለም መድኃኒት ማለት እንደሆነ ከቅዱሳት መጻሕፍት እንማራለን፡፡
     🌲 መጋቢት ፳፯ ቀን የሚከበረውን የመድኃኔዓለምን በዓል ጥንተ ስቅለቱ ነው ብለን ስንናገርና የስቅለቱን መታሰቢያ በዓል ስናከብር በዚሁ ቀን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የተፈፀሙትን ጸዋትወ መከራዎችና እሱ በመስቀል ላይ እያለ በሰማይና በምድር የተፈጸሙትን ተአምራት አብረን ልናስባቸውና ልብም ልንላቸው ይገባል፡፡
🌲ጥንተ ስቅለቱ መጋቢት 27 ቀን በየዓመቱ እየታሰበ በዓለ ስቅለቱ ደግሞ ከሰሙነ ሕማማቱ ጋር በዓመት አንድ ጊዜ በዕለተ ዓርብ በጾምና በጸሎት እንዲሁም በአክፍሎትና በስግደት እንዲከበር በማድረግ ሕግና ሥርዓት ስለሠሩ በዚሁ መሠረት ሲፈጸም ኖሯል፡፡ ወደፊትም ይቀጥላል፡፡


▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
  ደብረብርሀን ዩንቨርስቲ የቀን ግቢ
      ጉባኤ ት/ት እና ሐ/ አ/ ክ
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
👍65
Forwarded from Ďâňĩ Ÿé ďĩňĝĩl21❤
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ዕለተ ሰንበት ቀን 28/07/2017 ዓ.ም

የሳምንቱ መርሐ ግብር

እሁድ

ከ3:00-5:00 የትምህርት እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል አባታዊ ምክር ቦታ ቆርቆሮ በቆርቆሮ
ከ4:00-6:00 ኦሮምኛ ኮርስ ቦታ ቤዝመንት
ከ10-12 ሰዓት ለ2ኛ ዓመት ክርስቲያናዊ ህይወት እና ስነምግባር ኮርስ ቦታ አዳራሽ ።
ከ8-10 ሰዓት ለ4ኛ እና 5ኛ ዓመት ነገረ ቤተክርስቲያን ኮርስ ቦታ ቤዝመንት።
ከ8-10ሰዓት ለ1ኛ ዓመት ሀይማኖት እና ሳይንስ ኮርስ ቦታ አዳራሽ ።
ከ10-12ሰዓት ለ3ኛ ዓመት የቤተክርስቲያን ታሪክ ኮርስ ቦታ ቤዝመንት።

ሰኞ

ከ12:00-1:30 መዝሙር ጥናት ።
ከሰዓት ከ11-12 ሰዓት ከአባል ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ የምሰጥበት ቀን ነው።
ማክሰኞ

ጠዋት ከ12:00-1:30 መዝሙር ጥናት ።
ረብዕ

ጠዋት ከ12:00-1:30 ወረብ ጥናት
ከሰዓት ከ11-12 ሰዓት የህይወት ትምህርት ።

ሐሙስ

ጠዋዉ ከ12:15-1:30 ቅዳሴ ተሰጥኦ ።
ከሰዓት ከ10:45-12:00 ቲያትር የምታይበት ቀን ።
ዓርብ

ጠዋት ከ12:00-1:30 ቅዳሴ ተሰጥኦ ።
ከሰዓት ከ10:30-12:30 የዓርብ ጸሎት።

አብነት ትምህርት በነበረበት ይቀጥላል ከቅዳሜ ውጭ!
     
ወስብሐት ለእግዚአብሔር።
👍64
🪴 ኒቆዳሞስ
ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው “ኒቆዲሞስ” ብሎ በሰየመው ክፍል መምህረ አይሁድ ኒቆዲሞስ ክርስቶስን ፍለጋ ሊቅ ሆይ እያለ እንደሄደ እንዲህ ብሎ አስቀምጦልናል።
"ኒቆዲሞስ ስሙ ዘሖረ ኀቤሁ ቀዲሙ ሌሊተ ወይቤሎ በጽሚት ረቢ ነአምን ብከ ከመ እምኀበ አብ መጻእከ ሖረ ኀቤሁ ዘስሙ ኒቆዲሞስ ወይቤሎ ለኢየሱስ ረቢ ሊቅ ንሕነ ነአምን ብከ ከመ እምኀበ አብ መጻእከ ከመ ትኩን መምህረ ወበምጽአትከ አብራህከ ለነ ወሰላመ ጸጎከነ አንሥእ ኃይለከ ወነዓ አድኅነነ"
አስቀድሞ በሌሊት ወደርሱ ይሔድ የነበረ ስሙ ኒቆዲሞስ የሚባል ሰው
  “ሊቅ ሆይ ከአብ ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን ፤ ኒቆዲሞስም ወደ እርሱ ሔደ፤ ረቢ ኢየሱስንም  ሊቅ (አዋቂ) እንደሆንክ ለማስተማር ከአብ ዘንድም እንደመጣህ እኛ እናውቃለን፤ በምጽአትህም አበራህልን፤ ሰላምንም ሰጠኸን፤ ኃይልህን አንሳ፤ መጥተህም አድነን አለው” ይለናል። (ጾመ ድጓ)
ከእርሱ የሚበልጥ ሁሉን የሚያውቅ መምህር፣ ከሣቴ ምሥጢር ነውና ኒቆዲሞስ ረቢ ሆይ እያለ ሊማር እግሮቹን ወደ ኢየሱስ አነሳ።
ጠቢቡ ሰሎሞን “ሌሊት በምንጣፌ ላይ ነፍሴ የወደደችውን ፈለግሁት” እንዳለ የመዳኗን ተስፋ ያደረገች የኒቆዲሞስ ነፍስ የሚያድናትን መድኃኒት ፍለጋ ሌሊት በጨለማ ጸብአ አጋንንቱን፣ ግርማ ሌሊቱን ሳትፈራ ፍለጋዋን ገሰገሰች። (መኃ.፫፥፩)
አባቶቻችንም ዛሬ ጉባኤ ቤት ተክለው፣ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ትምህርትን በሌሊት የሚያስተምሩት ይህን ሊቅ አብነት አድርገው ነው፤ በሌሊት ኅሊና ይሰበሰባል፤ በቀላሉም የመጻሕፍትን ምሥጢር ለመረዳት ሐሳብ መሰብሰብ ያስፈልጋል።
የኒቆዲሞስ በሌሊት ገስግሶ መምጣት በቅዳሴው በኪዳኑ በሰዓታቱ በማኅሌቱ መገኘትና መሳተፍ ረቂቅ የሆነው ሰማያዊ ምሥጢር ፍንትው ብሎ አንዲገለጥልን ምክንያት ነውና በምሥጢራት በመሳተፍ ራስን ዝቅ በማድረግ ለታላቅ ክብር እንድንበቃ የእርሱ መልካም ፈቃድ ይሁንልን፡፡

🌳ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!🌳
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
    ደብረብርሀን ዩንቨርስቲ የቀን ግቢ ጉባኤ
ትምህርት እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
🏆5👍1
D/n Adimasu:
✞በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ። አሜን!✞
  
✍️ስለ ምስጢረ ቁርባን-አጭር       ማብራሪያ
•ቁርባን የሚለው ቃል የሱርስት ሲሆን ትርጉሙ በቁሙ መንፈሳዊ አምኃ፣ መስዋዕት፣ መባዕ፣ ለአምላክ የሚቀርብ ገንዘብ ማለት ነው።
•ምስጢረ ቁርባን ከአምስቱ አዕማደ ምስጢር አንዱ ነው፡፡ በእግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት (ምስጢረ ሥላሴ) አምነው በክርስቶስ ደም የተዋጁና በአብ በወልድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ስም የተጠመቁ ምእመናን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም በመቀበል ምስጢረ ቁርባንን ይፈጽማሉ፡፡
•ቁርባን ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት ፣ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ የምንሆንበት ምሥጢር ነው ።
«እውነት እውነት እላችኋለሁ የወልደ እጓለ እመሕያው ክርስቶስን ሥጋውን ካልበላችሁ ደሙን ካልጠጣችሁ የዘለዓለም ሕይወት የላችሁም ። ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው ። ሥጋዬና ደሜ ሕይወትነት ያለው እውነተኛ ምግብ ነውና ። ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ጋር ይኖራል ። እኔም በእርሱ እኖራለሁ» (ዮሐ. 6፡53-57)
ተብሎ ተጽፎአልና ።
@ስለ ምሥጢረ ቁርባን አስቀድሞ የተነገሩ ትንቢቶችና የተገለጡ ምሳሌዎች አሉ :-
☞ትንቢቶች
«በልባችን ደስታን ጨመርህ ከስንዴ ፍሬና ከወይን ፣ ከዘይትም ይልቅ በዛ» (መዝ 4፡7)
"ጥበብ ቤቷን ሠራች፥ ሰባቱንም ምሰሶዎቿን አቆመች። ፍሪዳዋን ዐረደች፥ የወይን ጠጇንም ደባለቀች፥ ማእዷንም አዘጋጀች ባሪያዎቿን ልካ በከተማዪቱ ከፍተኛ ስፍራ ላይ ጠራች ፦☞ አላዋቂ የሆነ ወደዚህ ፈቀቅ ይበል፤ አእምሮ የጐደላቸውንም እንዲህ ፡ አለች ፦ ኑ ፥ እንጀራዬን ብሉ፥ የደባለቅሁትንም የወይን ጠጅ ጠጡ። አላዋቂነትን ትታችሁ በሕይወት ኑሩ፥ በማስተዋልም መንገድ ሂዱ።"(ምሳሌ 9፡1-6)
የሰው የሕይወቱ መጀመሪያ እህልና ውሃ ወይንና ስንዴ ነው። (ሲራ 39:26)
እነዚህም ትንቢቶች በመስቀል ላይ የተሠዋው #በግዐ_ፋሲካ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋውን ደሙን በስንዴ ኅብስትና በወይን እንደሚሰጥ የተነገሩ ናቸው ።
☞ምሳሌዎች
• እስራኤላውያን ከግብጽ ከመውጣታቸው በፊት ከሞተ በኩር ይድኑ ዘንድ የተመገቡት በግ የቁርባን ምሳሌ ነበር። ይህም
«እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ» (ዮሐ. 1፡29)
ተብሎ በተጻፈው ታውቋል።
እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ለእስራኤል ልጆች ትእዛዝ ሰጣቸው ነውር የሌለበት የአንድ ዓመት ጠቦት እንዲያዘጋጁ እስከ አስራ አራተኛው ቀንም እንዲጠብቁት ሲመሽም እንዲያርዱት፣ ከደሙም ወስደው በሚበሉበት ቤት ሁለቱን መቃንና ጉበኑን እንዲቀቡት በእሳት የተጠበሰውን ሥጋውንና ቋንጣውን እንጀራ በዚያች ሌሊት እንዲበሉ፣ የተረፈውንም በእሳት እንዲያቃጥሉት . . .(ዘጸ 12)
•በታዘዙት መሠረት ሁሉን አድርገው ከሞተ በኩር ድነዋል። ይህም ሊመጣ ላለው ምሳሌ ነበር፦
✓ነውር የሌለበት የአንድ ዓመት ጠቦት ኃጢአት የሌለበት የንጹሀ_ባህርይ አምላክ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው።
✓በጉን በወሩ በአስራ አራተኛው ቀን እንዲሰውት እንዲታዘዙ ሁሉ የጌታም ምክረቱ በመጋቢት አስር ተጀምሮ በአስራ አራተኛው ቀን ተፈጽሟል።
✓የበጉ ደም በተቀባበት ቤት ሞተ በኩር እንዳልደረሰ እንዲሁም ዛሬም በመስቀል ላይ ደሙን ባፈሰሰው አምላክ አምኖ ሥጋውንና ደሙን የተቀበለ ሰው የዘላለም ሞት አያገኘውም።
✓በቤቱ ውስጥ የነበሩት ሁሉ የተጠበሰውን የበጉን ሥጋ እንዲበሉ ታዘው ነበር ጥሬውና ቅቅሉን ግን እንዳይመገቡም
እንዲሁ #በእሳት_የተመሰለ_መለኮት የተዋሐደውን ሥጋ ለምንቀበል ለኛ አብነት ለመሆን። የምንበላውና የምንጠጣው ሥጋና ደም #ነፍስ_የተለየው #መለኮት_የተዋሐደው ነው።
• ለወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ የሆነው ካህን መልከ ጼዴቅም
በዘመነ ኦሪት ከቀደምት አበው ሁሉ ለየት ባለ መልኩ በቀራንዮ ኮረብታ ላይ ከእርሱ በፊትም ሆነ ከእርሱ በኋላ እንደሚያቀርቡት የደም መሥዋዕት ሳይሆን በኅብስትና በወይን ያስታኩት (ያመሰግን)ነበር (ዘፍ 14፡18-20) አብርሃም አምስቱ ነገሥተ ኮሌዶጎሞርን ወግቶ ሲመለስ መልከጼዴቅ ኅብስትና ወይን ይዞ ተቀብሎታል፡፡
በዚህ መሠረት፦
የመልከ ጼዴቅ ኅብስት አኮቴት ጽዋዐ በረከት #የሥጋ_ወደሙ_ምሳሌ ሲሆን
መልከጼዴቅ #የጌታ
አብርሃም #የምዕመናን
ምሳሌ ነው፡፡ ዕብ 56
☞እነዚህን ትንቢቶችና ምሳሌዎች ለመፈጸምና አማናዊ ለማድረግ
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሴተ ሐሙስ በተዘጋጀው የፋሲካ ዕራት ኅብስቱን አንስቶ አመስግኖ ባርኮ ቆርሶ ለደቀ መዛሙርቱ «ይህ ሥጋዬ ነው ፣ እንኩ ብሉ» ብሎ ሰጣቸው ጽዋውንም አንሥቶ አመስግኖ ባርኮ «እንኩ ሁላችሁ ከዚህ ጠጡ ፣ ለሐዲስ ኪዳን ኃጢአትን ለማስተሠረይ ስለ ብዙ ሰዎች የሚፈስ ደሜ ይህ ነው» ብሎ ሰጣቸው ። (ማቴ 26፡28። ማር. 14፡22። ሉቃ. 22፡19)።
☞ይህ ምሥጢር አሁንም ዕለት ዕለት በቤተክርስቲያናችን ይፈጸማል ።
ቄሱ በቅዳሴ ጊዜ ኅብስቱን በፃሕል ወይኑን በጽዋዕ አድርጎ እየባረከ ጸሎተ ቅዳሴውን ሲያደርስበት ኅብስቱ ተለውጦ አማናዊ ሥጋ ወልደ እግዚአብሔር ፣ ወይኑ ተለውጦ አማናዊ ደመ ወልደ እግዚአብሔር ይሆናል ።
ይህንም ሊቁ ቅዱስ አትናቴዎስ፦ «ካህኑ፦ ሳይባርከውና ሳያከብረው ኅብስትና ወይን እንደሆነ ካህኑ በባረከውና ባከበረው ጊዜ ግን ኅብስቱ ከኅብስትነት #የአምላክ_ሥጋ ወደ መሆን ፣ ወይኑም ከወይንነት #የወልደ_እግዚአብሔር_ደም ወደ መሆን እንደሚለወጥ እናምናለን» ብሎአል ። (አትናቴዎስ ሃይ አበው ምዕ. 28· ክፍ. 14- ቁ-22 )
☞ስለዚህ
✓በምሴተ ኀሙስ ሐዋርያት የተቀበሉት
✓በዕለተ ዐርብ በመስቀል ላይ የተሠዋው
✓ዛሬም በአራቱ መዓዝነ ዓለም እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ የሚሠዋው መሥዋዕት #አንድ ነው ። ይኸውም፦
«#አማናዊ_ሥጋ_ወልደ_እግዚአብሔር #አማናዊ_ደመ_ወልደ_እግዚአብሔር ነው እንጂ #ምሳሌ_ወይም_መታሰቢያ አ.ይ.ደ.ለ.ም!» ብላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን(ቤተ ክርስቲያናችን) #ታምናለች #ታሳምናለች
«ዛሬ በየጊዜው ካህናት የሚያቀርቡአት ንጽሕት መሥዋዕት ያን ጊዜ በቀራንዮ በመልዕልተ መስቀል የተሠዋችው ናት» ። (ዮሐ. አፈ. ቅዳሴ፡85)።
🍁ክርስቶስ ሥጋውንና የደሙን ለምን በሚባላና በሚጠጣ አደረገው?
“ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።”
  — ዮሐንስ 6፥54
ይህ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ለምን በሚበላና በሚጠጣ ነገር ተሰጠን ካልን ምግብና መጠጥ ከሰውነታችን እንደሚዋሐድ ሥጋውንና ደሙን ስንቀበል በእውነት እንደሚዋሐደን ለማስረዳት፤  ሥጋውና ደሙን በሚበላና በሚጠጣ አደረገው፡፡
                👉አንድም
“አባቶቻችሁ በምድረ በዳ መና በሉ ሞቱም፤” — ዮሐንስ 6፥49
በመብል የጠፋው ዓለም በመብል እንዲድን፤ አዳምና ሄዋን በምግብ የእግዚአብሔር ልጅነታቸውን እንዳስወሰዱ ፤ በቅዱስ ሥጋውና በክቡር ደሙ ልጅነታችንን ሊመልስልን ሥጋውና ደሙን በሚበላና በሚጠጣ አደረገው።
   👉 ይቀጥላል....
👍41
☝️☝️ከላኛው የቀጠለ..
“ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ።”— ዘፍጥረት 3፥6
                👉አንድም
መብልና መጠጥ ያፋቅራል፤ ስጋና ደሙ ያፋቅራልና፤ ቅዱስ ቁርባንም የክርስቶስን ፍቅር በልቦና ያሳድራልና ነው።
               👉አንድም
እርሱ ለእኛ ያለውን ፍቅር ሲገልጥልን ሥጋውና ደሙን በሚበላና በሚጠጣ አደረገው፡፡
               👉አንድም
ምግብ ለሥጋችን ኃይል እንደሚሆነን ሥጋውና ደሙም ለነፍሳችን መንፈሳዊ ኃይል እንዲሰጠን ሥጋውና ደሙን በሚበላና በሚጠጣ አደረገው፡፡
               👉አንድም
ከዚህም በላይ የተራበና የተጠማ ሰው  ብር፣ ወርቅ ከሚሰጡት ይልቅ መብልና መጠጥ የሰጠውን እንደሚወድ ጌታም ፍቅሩን ሲገልጥልን የነፍስ ርሃባችንን ሊያስወግድልን ሥጋና ደሙን በምግብና በመጠጥ አደረገው፡፡
                👉አንድም
ምግብና መጠጥ በቀላሉ ከሰውነታችን እንደሚዋሐድ እንዲሁ ጌታም በቀናች ሃይማኖት በመልካም ምግባር ሆነን ሥጋውን ብንበላ ደሙንም ብንጠጣ ከጌታችን ሕያውነት የተነሳ ለዘለዓለም ሕያው ሆነን በክብር እንደምንኖር ጌታችን አስተምሮናል፡፡
“ከሰማይ የወረደ እንጀራ ይህ ነው፤ አባቶቻችሁ መና በልተው እንደ ሞቱ አይደለም፤ ይህን እንጀራ የሚበላ ለዘላለም ይኖራል።”— ዮሐንስ 6፥58
ካዲያ ይህ በሚበላና በሚጠጣ ክርስቶስ የሰጠን ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ከምን ይዘጋጃል?
በቤተ ክርስትያን የምንቀበለው ቅዱስ ስጋው የሚዘጋጀው ከአዝዕርት ወገን ከሆነው ከስንዴ ነው።ቅዱስ ደሙ ደግሞ ከፍራፍሬ ወገን ከሆነው ከወይን ነው።
"የሰው የፈቃዱ መጀመሪያ ውኃ እሳት ብረት ጨው እህል ስንዴ ማር ወተት የወይን ዘለላ ደም ዘይት ልብስ ነው።""-ሲራክ 39÷26
በዚህም ከአዝዕርት ስንዴ ከፍራፍሬ ደግሞ ወይን መመረጡ የራሱ የሆነ ምስጢር እና ትንቢት አለው።በብሉይ ለኢየሱስ ክርስቶስ ክህነት ምሳሌ ሆኖ የተጠቀሰው መልከፀዴቅ ከስንዴ እና ከወይን መስዋዕትን ይሰዋ ነበር።
“የሳሌም ንጉሥ መልከ ጼዴቅም እንጀራንና የወይን ጠጅን አወጣ፤ እርሱም የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነበረ።”— ዘፍጥረት 14፥18
በተጨማሪ ደግሞ ነቢዩ ዳዊት በመዝሙሩ ላይ እንዲህ ሲል ይናገራል።
“በልቤ ደስታን ጨመርህ፤ ከስንዴ ፍሬና ከወይን ከዘይትም ይልቅ በዛ።”
  — መዝሙር 4፥7
እነዚህን እና ሌሎችም በብሉይ ኪዳን የተነገሩ ትንቢቶች እና ምሣሌዎች በዕለተ ሐሙስ በክርስቶስ ሥጋና ደም አማናዊ ሆነው ተሰጥተውናል።እንደዚሁም ደግሞ ከተፈጥሯቸው ስንነሳ ስንዴ ስብን ይመስላል ወይን ደግሞ ትኩስ ደምን ይመስላልና ነው።
👉ቅዱስ ቁርባን አንዴ ከተቀበልን አይበቃም? ለምን ይደጋገማል?
  ከቅዱስ ቁርባን ጋር በተገናኘ ብዙዎች ከሚያነሱት ጥያቄዎች መካከል ቅዱስ ቁርባንን ለምን ደጋግመን እንቀበላለን የሚል ጥያቄ ነው በተወሰነ መልኩ ለማየት እንሞክራለን ።
እንደሚታወቀዉ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያን ከምታስተምራቸዉ እና ከምታምነዉ ከሰባቱ ምስጥራተ ቤተክርስቲያን አንዱ ምስጥረ ቁርባን ነው ። እነዚህ ሰባቱ ምስጥራተ ቤተክርስቲያን በተለያየ መልኩ እና በተለያየ መንገድ በተለያዩ ክፍሎች ይከፈላሉ። ለዚህ ትምህርት ከርዕሳችን ጋር እንዲሄድልን እነዚህ ሰባቱ ምስጥራተ ቤተክርስቲያን ከሚከፈሉበት ክፍሎች መካከል አንዱ የሚደገሙ እና የማይደገሙ ምስጥራት ተብሎ በሁለት ይከፈላሉ ። ከእነዚህ መካከል ምስጥረ ቁርባን ወይም ቅዱስ ቁርባን ከሚደገሙት ምስጥራተ ቤተክርስቲያን አንዱ ነው ብላ ቅዱስት ቤተክርስቲያናችን ታምናለች ታስተምራለችም።
   👉 ስለዚህ ምስጥረ ቁርባን ወይም ቅዱስ ቁርባን ይደገማል አንዴ ብቻ ተቀብለን የምንተዉ ሳይሆን በህይወተ ሥጋ እስካለን ድረስ እየደጋገምን መፈጸም ያለብን ምስጥር ነው ቅዱስ ቁርባን።
➡️ቅዱስ ቁርባን ደጋግሞ መቀበል ለምን አስፈለገ ምክንያቱ ምንድነው ?
ለዚህ ብዙ ምክንያቶችን ማንሳት ይቻላል ነገር ግን በዋነኝነት አራት ምክንያቶችን ማንሳት ይኖርብናል ።
፩,  ቅዱስ ሥጋው መብል ክቡር ደሙ ደግሞ መጠጥ ስለሆነ፤
ቅዱስ ሥጋው መብል ክቡር ደሙ ደግሞ መጠጥ ስለመሆኑ የተወሰነዉ ነጥቦችን እናንሳ 👇
''እውነት እውነት እላችኋለሁ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችኹ ደሙንም ካልጠጣችኹ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም።'' ዮሐ 6፥53
የብሕንሳዉ ኤጲስ ቆጶስ አባ ሕርያቆስ እንዲህ በማለት ተናግርዋል👇👇👇
"ማርያም ሆይ ስለዚህ እንወድሻለን ከፍ ከፍም እናደርግሻለን እውነተኛ የጽድቅ መብልንና እውነተኛ ሕይወት መጠጥን ወልደሽልናልና።" ቅዳሴ ማርያም
ከላይ ከተጠቀሱት ሐሳቦች ቅዱስ ሥጋው መብል ክቡር ደሙ መጠጥ እንደሆነ መረዳት ይቻላል  ።
👉 እሽ አሁን አንድ ጥያቄ ላንሳላችሁ ውድ አንባቢያን:- ትላንት ምግብ በልተናል ዉሃ ጠጥተናል ብላችሁ ዛሬ ምግብ ሳትበሉ  ሳትጠጡ ትዉላላችዉን??? ቆይ ከዚህ የተሻለ ሌላዉ ይቅርና ምሳ በልተናልና እራት አንበላም ይባላልን? አይባልም!
🔔 ስለዚህ የክርስቶስ ሥጋውና ደሙ ዘላዓለማዊ ህይወት የሚያሰጥ  መብልና መጠጥ ስለሆነ ደጋግመን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን እንቀበላለን። ልክ ለሥጋችን በየጊዜዉ ምግብና መጠጥ እንደሚያስፈልገን ደግሞ ለነፍሳችንም በየጊዜዉ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙ ያስፈልገናል። ለዚህ ነው ቅዱስ ቁርባንን ደጋግመን የሚንቀበለዉ።
፪ በኃጢያት ስለምንወድቅ፤
እኛ የሰዉ ልጆች አዳማዊ ጠባይ ነው ያለን በኃጢያት እንወድቃለን እግዚአብሔርን እንበድለዋለን ሕጉንም እንተላለፋለን ስለዚህ ይህ የሰዉ ልጅ ጠባይ በየግዜዉ እየደጋገምን ከቅዱስ ምስጢር እንድንቀበል ያደርገናል ።
ውድ አንባቢያን ግልጽ ለማድረግ አንድ ምሳሌ እናንሳ አንድ የቅዱስ ቁርባን ሕይወት ያለዉ ሰዉ በኃጢያት ቢወድቅ ከቅዱስ ቁርባን ሕይወት ይርቃል ነገር ግን ለሠራዉ ኃጢያት ንስሐ ገብቶ በምክረ ካህን ታግዞ ዳግም ወደ ቅዱስ ቁርባን ሕይወት ይመለሳል ። ንስሐ ገብቶ ሲመለስ በፊት የቅዱስ ቁርባን ሕይወት ነበረህና  አሁን ንስሐ ብቻ ከገባክ ይበቃል የሚባል ነገር የለም ይልቁንም አሁን ዳግም ወደ ኃጢያት እንዳይመለስ ወደ ቅዱስ ቁርባን ሕይወት እንዲመለስ ይደረጋል።
ኃጢአታችን እንዲሰረይልን
የቆሸሸን ልብስ ውሃና ሳሙና እንደሚያነጹት በኃጢአት የጎሰቆለው ሰውነታችን በንስሐ ጸንቶ የክርስቶስን ሥጋና ደም በመቀበል ከኃጢአት የምንነጻ መሆኑን ጌታ  በቅዱስ ወንጌል እንዲህ በማለት ተናግሯል
"ስለብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው" ። ማቴ26፡27
፫, በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን አንዴ ብቻ ነው መቀበል ያለባችዉ  ወይም  መፈጸም ያለባችዉ የሚል ነገር ስለሌለ፤
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሰባቱ
ምስጥራተ ቤተክርስቲያን አንዱ የሆነው ምስጥረ ጥምቀት መፈጸም ያለበት አንዴ ብቻ  እንድሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል 👇👇👇ይቀጥላል....
👍21
☝️☝️ከላኛው የቀጠለ...
''አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት'' ኤፌ 4፥5
  ነገር ግን ከቅዱስ ቁርባን በተገናኘ እንደ ጥምቀት አንዴ ብቻ መቀበል አለባችሁ ወይም መፈጸም አለባችሁ የሚል የለም ይልቁኑም ምክንያት አንድ 👆 ላይ ባነሳነዉ ሐሳብ ደጋግመን መቀበል እንዳለብን ነው መጽሐፍ ቅዱስ የሚነግረን።
👉   የዕለት እንጀራችንን ስጠን
ሁል ጊዜ ይህንን ቃል በጸሎታችን መካከል ደጋግመን እንላለን ለምን እንደምንል የተወሰነ ነገር እናንሳ፤
አንደኛ የዕለት እንጀራችንን ስጠን ብለን የሚንለምነዉ ቃለ እግዚአብሔር ነው
👉  አንድም ደግሞ የዕለተ እንጀራችንን ስጠን ስንል ቅዱስ ሥጋህን ክብር ደምህን ስጠን ማለታችን ነው እንድንቀበል ። ለምን ከተባለ ክብር ይግባውና ክርስቶስ አምላካችን በመዋዕለ ስብከቱ እንዲህ ስላለን👇👇👇👇👇👇
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦የሕይወት እንጀራእኔ ነኝ ዮሐ 6 ፥35
፬, የክርስቶስን መከራ ሁልጊዜ እንድናስብ
"ይህን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ሁሉ ይህንም ጽዋ በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና" 1ቆሮ 11፡26
በማለት ቅዱስ ጳውሎስ አስረድቷል።
🍁ቅዱስ ቁርባንን ደጋግመን መቀበል አለብን ብለናል ለመሆኑ መቼ መቼ ነው መቀበል ያለብን ?
እንደ አጠቃለይ ዝግጁ ሆነን ከተገኘን እሑድ እሑድ መቀበል እንዳለብን ሊቃዉንተ ቤተክርስቲያን ያስተምራሉ ይህ ባይሆንልን በዓበይት በዓላት ለምሳሌ ለሆሳዕና, በሕማማት ውስጥ ባለችዉ ዕለተ ሐሙስ, በዕለተ ትንሳኤ, ለልደት, ለደብረ ታቦር,ለጥምቀት, በእመቤታችን ዕርገት ቀን(ነሐሴ 16) ወዘተ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን መቀበል ይኖርብናል።
👉 እንዲህ ማለታችን በዘረዘርናቸዉ ዕለት ብቻ ነው የሚንቀበለዉ ማለታችን እንዳልሆነ ልብ ማለት ያስፈልጋል።
 🔔ውድ የግብ ጉባኤያችን ተማሪዎች ቅዱስ ቁርባን መቀበል ያለብን በዓመት አንዴ ጊዜ ጠብቀን ያዉም በግብ ጉባኤ ተቀስቅሰን የምንቀበል ብቻ መሆን የለብንም።
በንስሐ ህይወት እና በቅዱስ ቁርባን ሕይወት ላለነዉ እግዚአብሔር አምላክ በሕይወቱ ያጽናን በእነዚህ ሕይወት ውስጥ የሌለነዉን ለዛ ለተቀደሰዉ ሕይወት እግዚአብሔር ያብቃን ❗️    
👉ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጋቢት 26 በምሴተ ሐሙስ ( በሐሙስ ምሽት ) በአልአዛር ቤት የሐዋርያቱን እግር ዝቅ ብሎ ካጠበ በኋላ በኪሩቤል ላይ አድሮ የሚኖር እርሱ ለእራት ከእነርሱ ጋር ተቀመጠ  ይህንንም ሰማያዊ ምስጢር ለሐዋርያት አሳያቸው። ይህንንም ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው
ረፈቀ ምስሌሆሙ በድራር ዘዲበ ኪሩቤል ይነብር ወሎሙ አርአየ ሥርዓተ ምስጢር ዘቁርባን ።
🌳ጾመ ድጓ ዘጸሎተ ሐሙስ። 
ሲል ገልጾታል።  ጌታ ለሰው ልጅ ከሰጠው ነገሮች ሁሉ ስጋውን እና ደሙን የሚተካከል የለም ። መስጠቱም ስለምንድነው ቢሉ በመብል የጠፋውን የሰው ልጅ በመብል ይመልሰው ዘንድ ነው ።  
🍁ቅዱስ ቁርባን የሚያስፈልገው ለማን ነው??
በቅድሚያ ይህን ጥያቄ በጥያቄ ልጠይቃችሁ ። 
🍁መድኃኒት የሚያስፈልገው ለማን ነው?
መቼም ለጤነኛ ሰው ነው አትሉም። ቅዱስ ቁርባን መድኃኒት ነው ። ምክንያቱም የመድኃኔዓለም ቅዱስ ስጋ እና ክቡር ደም ስለሆነ ነው ። አባ ጽጌ ድንግል
ዘይቤ ኢመጻእኩ እጸውዕ ጻድቃነ አላ ለንስሐ ኃጥአነ ይላል።
እውነት ነው ክርስቶስ ወደዚህች ዓለም የመጣው በኃጢያት ደዌ ክፉኛ የተመታን የሰው ልጅ ለማከም ነው። በሽተኛ ሆኖ መድኃኒት አያስፈልገኝም የሚል እንደሌለ  ኃጢያተኛ ሆኖ ስጋ ወደሙ አያስፈልገኝም የሚል መኖር የለበትም ኃጢያት የነፍስ በሽታ ነውና። 
ታዲያ ቅዱስ ቁርባን የሚያስፈልገው ለሁሉም የሰው ልጅ ነው። 
🍁ቅዱስ ቁርባን የሚገባው እንዴት ሆኖ ለተገኝ ሰው ??
1. ላመኑ ሰዎች
  ይህ ማለት በ40 በ 80 ቀን የመንፈስ ቅዱስ ልጅነትን ያገኙ ወይም በሌላ እምነት ኖረው ተገቢውን ትምህርት ተምረው ከቤተ ክርስቲያን ልጅነትን ያገኙ ሰዎች ናቸው።  ዳግመኛም በዚህም ሳሉ ደግሞ በእውነት ኅብስቱ ተለውጦ ስጋ አምላክ፤ ወይኑ ተለውጦ ደመ አምላክ እንደሚሆን ያመኑ ናቸው ። ለዚህም  አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው
ወዮ ካንቺ የተገኝ ኅብስት በማመን ከርሱ ለሚቀበሉ ሕይወትንና ድኅነትን የሚሰጥ ነው ። በማመን ከርሱ ለማይቀበሉ ሰዎች የማይላመጥ ጽኑ ነው።
 🍁 ቅዳሴ ማርያም ቁ 91 
 2. ንጹሕ ሆነው ለተገኙ
    በታላቁ ጸሎት በሥርዓተ ቅዳሴ ሠራዒው ካህን ወደ ፍሬ ቅዳሴ ከመግባቱ አስቀድሞ    ። 
" ንጹሕ የሆነ ከቁርባኑ ይቀበል ንጹሕ ያልሆነ ግን አይቀበል።"
ብሎ አዋጅ ያሰማል። ይህ እንደ ምክንያት ሆኖላቸው ለምን አትቆርቡም ሲባሉ ይህን ጠቅሰው የሚከላከሉ በርካቶች ናቸው ።  
እንደዚህ አይነት ምላሽ የሚሰጡ ሰዎች ሁለት አይነት ናቸው  ። አንደኞቹ የአዋጁን ትርጉም ወይም ማስተላለፍ የተፈለገውን መልእክት ካለመረዳት ሲሆን ሁለተኞቹ ደግሞ የኃጢያት ትራስ ተመችቶአቸው የሚኖሩ ናቸው።
ንጹሕ ሆኖ የተገኝ ማለት በሰራው ኃጢያት ተጸጽቶ ራሱን ለካህን አሳይቶ የተሰጠውን ቀኖና የጨረሰ ሰው ማለት እንጂ ዳግመኛ ኃጢያትን የማይሰራ ማለት እንዳልሆነ አንባቢ ያስተውል ። 
3. ቅዱስ ሆነው ለተገኙ
  🍁 በሥርዓተ ቅዳሴ ካህኑ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ከማለቱ በፊት ዲያቆኑ "ነጽር" ( ተመልከት ) እያለ ያዜማል ይህም ማለት ስጋ ወደሙ የምትሰጣቸው ሰዎች የተገቡ መሆን አለባቸውና አስተውል ብሎ ያሳስባል ካህኑም "ቅድሳት ለቅዱሳን" (ቅዱሳን ለሆኑ ምዕመናን እንጂ ለሌላው አይገባም ይላል ።  በዚህ ጊዜ "አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ " ቅድስናስ የባህርዩ የሆነ ሥላሴ ብቻ ነው ብለን እንመልሳለን።  ቅዱስ ማለት ቀደሰ ካለው የግዕዝ ግስ የተወሰደ ሲሆን አመሰገነ ለየ ማለት ነው ። በዚህ ዓውድ ቅዱስ ማለት ደግሞ ልዩ ማለት ነው ። ስለዚህ ካህኑ እያለ ያለው በዚያች ሰዓት ከኃጢያት ለተለዩ ንስሐ ለገቡ ማለቱ እንደሆነ ማስተዋል ያስፈልጋል። 
በአጠቃላይ ለቅዱስ ቁርባን የተጠራን ሁላችን ስንሆን የሚገባን ግን ንስሐ ገብተን ለምንኖር ሰዎች ነው። ይህ ሲባል ግን ለዚህ ክብር የምንበቃው በኛ ችሎታ ሳይሆን በእግዚአብሔር ቸርነት እንደሆነ ማሰብ ያስፈልጋል። ምክንያቱም ኃጢያትን ሳይሰራ መዋል የሚቻለው የለምና ከቆረብን በኋላ ኃጢያት ብንሰራስ ለምንል ደግሞ አንድ ሚለየን ጊዜ ኃጢየት ብንሰራ አንድ ሚለየን አንድ ጊዜ ንስሐ መግባት እንደምንችል እናስብ።  የእግዚአብሔር ምህረት ባሕር የእኛ የእድሜ ልክ ኃጢያት አንዲት የቀለም ጠብታ ናትና። የባሕሩ ቀለም በአንዲት ጠብታ እንደማይለወጥ የእግዚአብሔር ምሕረትም እንዲሁ በሰው ኃጢያት አይለወጥም ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና። 
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር  ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!
🪴🪴🪴🪴🌳🪴🪴🌳🌳🪴🪴🪴
ደብረብርሀን ዩንቨርስቲ የቀን
ግቢ ጉባኤ ትምህርት እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል
🍁🍁🍁👉👉👉🍁🍁🍁🍁👉🍁
7👍5
ስላም እንደምን ቆያችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ሰላመ እግዚአብሔር በያለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን።
በግቢ ጉባኤያችን በኩል የተላለፈ አንድ መልዕክት አለን! ይሄውም
የ2017 ዓ.ም የጌታችን ፤የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ በዓል በግቢ ጉባኤ በበዓሉ ማግስት ማለትም ሰኞ 13/07/2017 ዓ.ም አቅመ ደካሞች እና ነዳያንን በመሰብሰብ በአንድነት እንድናከብር እና በረከቱን እንድንሳተፍ ግቢ ጉባኤ ጥሪ አቅርባለች እና ሁላችንም በየ ዶርማችን የተመደቡ አካላት ይሄዳሉ እና በምገባ ተመዝግባችሁ በዓሉን በአንድነት እንድናከብር በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ምዝገባ በየ ዶርም የተመደቡ በጎ አድራጎት ወይም አካላት ይሄዱና ይመዘግባሉ

መመዝገቢያ ፦100 ብር  ጀምሮ ነው!

በአንድ መቶ ብር ብዙ በረከት እናተርፋለን አንድም 50 ብሩ ለእራሳችን ስሆን 50 ብር ደግሞ ነዳያንን ይመግባልና ሁላችንም ይሄንን ታላቅ በረከት ልንሳተፊ ይገባናል።
ይሄ ትልቅ የበረከት ሥራ አምናም እጅግ አሪፍ እንደነበር ተመልክተን ነበር!
👍2
ቅዱስ ቁርባንን በጋራ መቀበልና ከንቱ ውዳሴ???🔥
💥ጌታችን በቃሉ እንዳስተማረን ቅዱስ ቁርባን ደካማ ሥጋችን በእግዚአብሔር ጸጋ ከብሮ የሚኖርበት ድንቅ ምሥጢር ነው፡፡
በኃጢአት የደከመ ሰውነታችን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ለመሆን፣ የክርስቶስን ሥጋና ደም ለመቀበል
በንስሐ መታጠብ አለበት።
ንስሐውም እንደ ሮማዊው መቶ አለቃ ፍጹም ራስን ዝቅ በማድረግ፣ በትሕትና የሚፈጸም መሆን አለበት፡፡
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
በመሆኑም ቅዱስ ቁርባንን በጋራ መቀበል በቤተክርስቲያናችን እንዴት ይታያል ከንቱ ውዳሴስ ሊሆን ይችላል?
ከንቱ ውዳሴ የሚለው ቃል ሁለት ቃላትን የያዘ ሲሆን ወዳሴ እና ከንቱ የሚሉ ናቸው።
   🌷 የመጀመሪያው (ውዳሴ) ማለት በቁሙ ምስጋና ማለት ሲሆን ከንቱ የሚለው ደግሞ የማይረባ የማይጠቅም ተራ ተርታ ማለት ነው። በአንድነት ውዳሴ ከንቱ የሚለው ቃል የማይረባ የማይጠቅም ውዳሴ የሚል ትርጓሜ ያለው ሲሆን ውዳሴ ብጡል (የተናቀ፤ተርታ) ውዳሴ ተብሎም ይጠራል፡፡የቃሉ ትርጉም  በዚህ መልኩ የሚፈታ  ይሁን እንጂ “ የማይጠቅም “ ከመሆን አልፎ  ሰውን ሊጎዳ የሚችል ነገር በመሆኑ የቤተክርስቲያናችን መጻሕፍት  አጥብቀን ልንሸሸው እንዲሚገባ ያስተምራሉ፡፡
ጉዳቱ እንደምነው? ቢሉ አንዴ ከንቱ ወዳሴንና አድናቆትን የመሻት ችግር (ሱስ) ውስጥ ከገባን
👉 በመጀመሪያ ደረጃ የምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ በሰው ለመመስገንና ለመደነቅ ስለሚሆኑ የአገልግሎታችን(የማስተማራችን፣ የመዘመራችን፣ የመጸለያችን፣ የመጾማችን፣ የመስገዳችን፣ የመመጽወታችንና የመሳሰሉት መልካም ምግባራት ሁሉ) አላማቸውን ስለሚስቱ፤ ማለትም ከክርስቶስ ይልቅ እራሳችንን አጉልተን በማሳየት አቡሃ ለሐሰት በመባሉ የሚታወቀው ሳጥናኤልና በኋላም በዲያብሎስ ምክር አባታችን አዳም የፈጸሙት አምላክነትን የመሻት ትልቅ ኃጢአት ስለምንፈጽም በአገልግሎቱ መንግስቱን በመውረስ ፈንታ መርገምን ልንቀበል እንችላለን።
👉በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ሰው አላመሰገነንም ወይም አልተደነቅንም ብለን በማሰብ ደገኛ ከሆነችው አገልግሎት በመራቅ የተሰጠንን መክሊት ቀብረን ክፉ አገልጋይ ሊያስብለን የሚችል ከፉ ልምድም ጭምር ነው። ለምሳሌ ያክል እነዚህን አነሳን እንጂ በጣም ብዙ ጉዳቶችን እንደሚያስከትል አይተውና ሰምተው ያረጋገጡ አባቶቻችን በብዙ መልኩ ሲጽፉና ሲያስተምሩ ይስተዋላል።
ነገር ግን በአሁኑ ዘመን የከንቱ ውዳሴን ምንነት ካለማወቅ የተነሳ ከንቱ ውዳሴ ያይደሉ፤ ብዙዎቻችን ግን እርሱን ከመፍራት የተነሳ የማናደርጋቸው ማድረግ የሚገቡን ተግባራት አሉ።
🌷ለምሳሌ እኛ ስናገለግል ሰዎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሚያመሰግኑን ወይም የሚያደንቁን ከሆኑና የኛ አላማ ግን መመስገን ሳይሆን ዝቅ ብሎ ማገልገል ከሆነ እንዲሁም ሰዎች ያንን በሚያደርጉበት ጊዜ እኛ የማንቀበላቸውና ሲያበዙት ደግሞ የምንቃወማቸው ከሆነ በኛ ዘንድ ከንቱ ወዳሴ አይሆንም ሊሆንም አይችልም።
🌷ሌላኛው ከንቱ ወዳሴ ሳይሆን ከንቱ ወዳሴ እየተባለ የሚፈራው ነገር
ክርስቲያናዊ ግዴታችንን በግልጽና በሰው ፊት ማድረግን ነው።
ከነዚህም አንደኛው በተለያዩ ቦታዎችና አጋጣሚዎች ማማተብና ምግብ በምንመገብበት ጊዜ ስንጀምር መባረክና ስንጨርስ ደግሞ ስብሐት ብሎ ማመስገን ነው።
🌷እንደዚህ ማድረጉ ሃይማኖታዊ ግዴታችንን ከመወጣት ውጪ ከንቱ ውዳሴ ሊባል አይገባም ሊሆንም አይችልም።
ሌላው በተሳሳተ ዕይታ የሚታየውና በብዙዎች ዘንድ የምንመለከተው ስህተት ደግሞ በታወቁ የአዋጅ ጾም ጊዜያት ጾመኛ መሆናችንን መግለጥና ሌላውም እንዲጾም ማበረታታት፣ የ7ቱ ጊዜያት ጸሎት እንደምንጸልይና መጸለይ እንደሚገባ መናገር ፤
🌷ቅዳሴ ማስቀደስና ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙን በሕዝብ ፊት መቀበል እንዲሁም መቀበል ግዴታችን እንደሆነ ማስተማርና መግለጥ እና የመሳሰሉት ምግባራት ይገኙበታል እነዚህን ማድረግ ደግሞ ክርስቲያናዊ ግዴታዎች በመሆናቸው ሁሉም ክርስቲያን የሚያደርጋቸውና እኛም አርአያ በመሆን ሌሎች እንዲያደርጓቸው የምናበረታታቸው ናቸው። መናገራችንንና በግልጽ ማድረጋችን ሰዎች አንዲያደንቁንና እንዲያመሰግኑን እስካልሆነና አላማችንም ሰዎችን ማስተማር እስከሆነ ድረስ ከንቱ ውዳሴ ሊሆን አይችልም።
🌷ከነዚህ በተለየ መልኩ በሥርዓት ከታዘዙት ትዕዛዛት በተጨማሪ አንድ ክርስቲያን ትርፍ (በጸጋ ላይ ጸጋ በክብር ላይ ክብር በበረከት ላይ በረከት) ለማግኘት ብሎ የሚፈጽማቸውን ተግባራት እና በንስሓ ጊዜ የተሰጠውን ቀኖና ቢናገር ግን ከንቱ ውዳሴ ሆኖበት በትሩፋቱ የሚገኘውን ጥቅም ሊያሳጣው ይችላል።
የሚደረግ መልካም ነገር ሁሉ ግን ከንቱ ውዳሴ ነው ማለት አይደለምና ቅዱስ ጳውሎስእንደሚለንበአገልግሎታችን(በቃልና በኑሮ) ሁሉ እንትጋ እንጂ ምክንያት እየፈጠርን ከእውነተኛው መንገድ የምንርቅ ደካሞች ልንሆን አይገባም!
🏝️🏝️🏝️🏝️🏝️🏝️🏝️🏝️🏝️🏝️🏝️🏝️
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ደ/ብ/ዩ ቀን ግቢ ጉባኤ ትምህርት እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
👍111