ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ
1.28K subscribers
390 photos
36 videos
45 files
49 links
ይህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ ት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ደ/ብ ማዕከል የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የቀን ግቢ ጒባኤ ይፋዊ የቴሌግራም መገናኛ ነው።
Download Telegram
እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ!
የደብረብርሃን ዩንቨርስቲ የቀን ግቢ ጉባኤ 18ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በያዝነው ወር ማለትም መጋቢት 19-21/07/2017 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ይከበራል።
ይህንን የእናት ግቢ ጉባኤ ጥሪ ድምፅ ላልሰሙት በማሰማት የበኩልዎን ድርሻ ይወጡ!
በሰላም ለዚያች ቀን ያድርሰን!
13👍2🕊2
Forwarded from Ďâňĩ Ÿé ďĩňĝĩl21❤
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
11👍2
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ      ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!

      👉 5 ቀን ብቻ ቀረው👈
🌲 "መጋቢት 14 የህይወት ቀን"🌳
እንኳን ለተወደደችው እና ለተመረጠችው የሕይወት ቀን በሰላም በጤና አደረሳችሁ!
ለመሆኑ የህይወት ቀን ምንድነው????
እስኪ ሁላችንም ይችን ጽሁፍ በማስተዋል እናንብብ👇👇👇👇👇👇👇👇👇
✍️የሕይወት ቀን በግቢ ጉባኤያችን ከሚታወጀው ንስሓ ሳምንት በኋላ የክርስቶስን ስጋ እና ደም በጋራ ሆነን ነጭ ለብሰን እንደመላዕክቱ ደምቀን የምንቀበልበት ቀን ነው ።🙏🙏🙏🙏
👉ጌታችን በቅዱስ ቃሉ ‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለሁ›› በማለት እንደተናገረ በህብረት የተቀበልነው ቅዱስ ቁርባን የሕያው አምላክ የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም ነውና የዘላለም ሕይወት ባለቤት መሆናችንን ያረጋግጣል፡፡
👉ዳግመኛም ቅርንጫፍ ከግንዱ እስካልተለየ ድረስ ልምላሜ፣ ጽጌና ፍሬ ሕይወት ለዘላለም እንዲኖረው ሁሉ ክርስቲያኖችም ጉንደ ሐረገ ወይን ከሆነው ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ አለመለየታችንና በሕይወት መኖራችንን ቅዱስ ቁርባን ስንቀበል እናረጋግጣለን፡፡ (ዮሐ 6፡53፣ ሮሜ 11፡21-24) ሕያዋን የሚያደርጉንም በውስጣችን ያደረው (የተዋሐደን) ሥጋ ክርስቶስና ደመ ክርስቶስ ናቸው።
   ቊርባን  ምን ማለት ነው?

ቊርባን ማለት ቃሉ ከሱርስት የተወሰደ ሲሆን፣ መስዋዕት ማለት ነው። እንዲሁም ቊርባን ሙሉ ትርጉሙ ለአምላክ የሚቀርብ መንፈሳዊ መባዕ ፣ ስጦታ፣ አምኃ፣ ማለት ነው። አንድም ሥጋውና ደሙ የተሰጠን በነፃ ያለ ዋጋ በችሮታ ነውና ቁርባን ስጦታ ይባላል።
ምሥጢረ ቁርባን ክርስቶስ ስለ እኛ ኃጢአት በመስቀል ላይ መሥዋዕት ሆኖ በሥጋው በመሞቱ የዓለምን ኃጢአት ያስወገደበት፥ የዘላለም ሕይወትን ያስገኘበት የመዳናችን መሠረት፥ የጸጋችን ሁሉ ምንጭ የሆነውን የቅዱስ ሥጋውንና የክቡር ደሙን የማዳን ስራ የምንማርበት ታላቁ የሃይማኖታችን ትምህርት(ዶግማ) ነው "ለእኔስ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል።" መዝ፤73
🔸ምሥጢረ ቍርባን በብሉይ ኪዳን
👉ከአባታችን አዳም ጀምሮ የነበሩ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን በኃጢአታቸው ከእግዚአብሔር በተለዩ ጊዜ ሁሉ በግና ላምን የመሳሰሉ እንስሳትን በእምነት መስዋዕት አድርገው ያቀርቡ ነበር፤ እግዚአብሔርም መስዋዕታቸውን እየተቀበለ ይታረቃቸው ነበር፡፡ በሕገ ልቡናና በሕገ ኦሪት የነበሩት ሁሉ በዚህ ሥርዓት አልፈዋል፡፡ አበ ብዙሐን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን ለመሰዋት ወደ ሞሪያ ተራራ በሚወስደው ሰዓት የክርስቶስ ምሳሌ የሆነ ይስሐቅ አባቱን አብርሃምን የጠየቀው ጥያቄና በመንፈስ ቅዱስ የተቃኘው የአብርሃም ምላሽ በብሉይ ኪዳንና በሐዲስ ኪዳን መስዋዕት መካከል ያለውን መሰረታዊ ልዩነት ያስረዳናል፡፡
🔸በዘመነ ብሉይ መስዋዕቱ ምድራዊ፣ አቅራቢውም ምድራዊ ነው፡፡ ይስሐቅ እንደተለመደው የመስዋዕት በግ እንዳልተያዘ ባየ ጊዜ “አባቴ ሆይ…እሳቱና እንጨቱ ይኸው…የመሥዋዕቱ በግ ግን ወዴት አለ?” በማለት ጠይቆት ነበር፡፡ በአብርሃም ህሊና የመሥዋዕቱ በግ ይስሐቅ ነበር፡፡ ይሁንና መንፈስ ቅዱስ እንዳቀበለው “ልጄ ሆይ የመሥዋዕቱን በግ እግዚአብሔር ያዘጋጃል፡፡” በማለት መለሰለት፡፡
🔸ሚሥጢረ ቁርባን በሐዲስ ኪዳን
  👉ምስጢረ ቁርባንን የመሠረተው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ ‹‹ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራውን አንስቶ ባረከ፤ ቆርሶም ለደቀመዛሙርቱ ሰጠና እንካችሁ ብሎ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋውንም አንስቶ አመስግኖ ሰጣቸው፡፡ ሁላችሁም ከእርሱ ጠጡ፤ ስለብዙዎች የኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የሐዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው፡፡›› (ማቴ 26፡26) በማለት የምስጢረ ቁርባንን አመሠራረት ጽፎታል፡፡ አስቀድሞ በብሉይ ኪዳን ሲቀርቡ የነበሩ መስዋዕቶችን ሁሉ ምሳሌው አድርጎ በማሳለፍ የራሱን መስዋዕትነት ካቀረበ በኋላ ቀድሞ የነበሩትን ነፍሳት ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድርስ የሚመጡትን ሁሉ አንድ ጊዜ ባቀረበው መስዋዕት የሚያድን ስለሆነ ምስጢሩ ይፈጸም ዘንድ ከሞቱ አስቀድሞ አስተማረ፡፡
👉‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው››ዮሓ፤፮፤፭፬ በማለት እስከዓለም ፍጻሜ የሰው ልጅ ሌላ መስዋዕት ሳያስፈልገው በአምላካችን ሥጋና ደም ሕይወት እንደሚያገኝ አስተማረ፡፡  የምስጢረ ቁርባንን ትምህርት በወቅቱ የነበሩ አይሁድ ሰምተው ምስጢሩ ስላልገባቸው ‹‹ይህ ሰው ሥጋውን ልንበላ ይሰጠን ዘንድ እንዴት ይቻላል›› በማለት ጠይቀው ነበር፡፡ ደቀመዛሙርቱም ትምህርቱ ከብዷቸው ነበር፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከወረደ በኋላ ግን ምስጢሩን ተረድተው አለምን ዞረው ወንጌልን አስተምረዋል…።
ከምስጢረ ቁርባን መሳተፍ የሚያስገኘው ጸጋ ምንድነው??

👉ቅዱስ ቁርባን የዘላለም ሕይወት ያሰጠናል፡፡ጌታችን በማይታበል አማናዊ ቃሉ ‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለሁ›› በማለት እንደተናገረ የተቀበልነው ቅዱስ ቁርባን የሕያው አምላክ የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም ነውና የዘላለም ሕይወት ባለቤት መሆናችንን ያረጋግጣል፡፡
👉ሥርየተ ኃጢአትን ያስገኛል፡፡
አባቶቻችን ‹‹ሰው ሆኖ የማይበድል እንጨት ሆኖ የማይነድ የለም፤ ከሰው ስህተት ከብረት ዝገት አይጠፋም›› እንዲሉ ደካማና ስሑት የሚሆን ሰብአዊ ባሕርያችን ወደ ስህተት ጎዳና ሲነዳንና ኃጢአት ሲያገኘን በደላችንን ለካህን ተናዝዘን፣ ቀኖና ተቀብለንና ንስሐችንን ጨርሰን በካህኑ ፈቃጅነት ቅዱስ ቁርባንን ስንቀበል የቀደመ ኃጢአት በደላችን ሁሉ እሳት ላይ እንደወደቀ ቅቤ ቀልጦ ጠፍቶ ነጻ ያደርገናል፡፡
👉የኃጢአት ልጓም ሆኖ ያገለግለናል፡፡
ሥጋው ለኃጢአት የሚጓጓና የሚሰነካከል እንዳይሆን የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ይጠብቀዋል፡፡ በሥጋውና በደሙ የተዋሐደው አምላክ ኃጢአትን ተደፋፍሮ እንዳይሠራ ይወቅሰዋል፡፡ የኃጢአት ውጤት ሞት መሆኑን ያሳስበዋል፡፡ በአጠቃላይ ወደ ቅድስናና ጽድቅ የሚመራ መንፈሰ እግዚአብሔር ስለተዋሐደን ለጽድቅ ሥራ የምንተጋ ለኃጢአት እጅ የማንሰጥ እንሆናለን፡፡
፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣,,,፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣,,,፣፣፣፣፣፣፣፣፣
ወስብሃት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክብር...ይቆየን!!!
፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣,,,፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣,,,፣፣፣፣፣፣፣፣
     🌈 መጋቢት፡10/07/2017🪐
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
  ደ/ብ/ዩ ቀን ግ/ጉ ት/ት እና ሐ/አ/ክ
💚💛❤️▰▰▰▰▰▰❤️💛💚
👍201🏆1
እንኳን አደረሰን እንኳን  አደረሳችሁ!

''ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሄድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ።
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ እግሮቻችን በአደባባይሽ ቆሙ።(መዝ 122፥1-2)

እኔሆ በጉጉት ስጠበቅ የነበረው
የደብረብርሃን ዩንቨርስቲ
የቀን ግብ ጉባኤ
18ኛ ዓመት
የምሥረታ በዓል
ደረሰ
ይሄውም
ከመጋቢት 19-21/07/ 2017 ዓ.ም
መምህራነ ወንጌል
እንድሁም ዘማሪያን
የቀድሞ የግቢ ጉባኤያችን ተመራቂ ተማሪዎች
በዩኒቨርስቲያችን የምገኙ ሠራተኞች
አሁን ላይ በግቢው የምገኙ ተማሪዎችን ጨምሮ
በአንድነት በታላቅ ድምቀት ይከበራል

ስለሆነም ከመጋቢት 19-21/07/2017 ዓ.ም
በደብረብርሃን ዩንቨርስቲ የቀን ግቢ ጉባኤ አዳራሽ በመገኘት ይህንን ታላቅ በዓል እንድታከብሩ ስትል እናት ግቢ ጉባኤ ጥሪዋን ታስተላልፋለች!

ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን !

የደብረብርሃን ዩንቨርስቲ የቀን ግቢ ጉባኤ
👍73👏2🕊1
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!
🌲🌷🌳🌳🌷🌳🌳🌷🌷🌳🌲       
✍️ይነበብ 👇👇👇👇👇
👉ላለመቁረብ የሚቀርቡ ተገቢ ያልሆኑ         ምክንያቶችና መፍትሄዎቻቸው 👈

🍃ቀስ ብዬ እደርሳለሁ ፣ ምን አስቸኮለኝ?
ያዕ. 4 ÷ 13-15 -አሁንም። ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ፥ ተመልከቱ፥ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና። ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና። በዚህ ፈንታ። ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን ማለት ይገባችኋል።
🍂ወደፊት ብሳሳትስ፣ ብወድቅስ?
1ኛ.ዬሐ. 5 ÷3-4
💨ሀጢያተኛ ስለሆንኩ አይገባኝም
ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች።(ኢሳ 1:9) 
መድኃኒት የሚያስፈልገው ለታመመ ነው።
💥በስራ ቦታዬና በማህበራዊ ኑሮዬ ተፅዕኖ ቢያመጣብኝስ?
ቲቶ. 2 ÷ 7-8 -የሚቃወም ሰው ስለ እኛ የሚናገረውን መጥፎ ነገር ሲያጣ እንዲያፍር፥ በነገር ሁሉ መልካምን በማድረግህ ምሳሌ የሚሆን ራስህን አሳይ፤ በትምህርትህም ደኅንነትን፥ ጭምትነትን፥ ጤናማና የማይነቀፍ ንግግርን ግለጥ....
🌿የቅዱስ ቁርባን ዝግጅት🌿

ቅድመ ቊርባን
​​ከመቁረባችን በፊት ሊደረጉ የሚገባቸው ቅድመ ዝግጅቶች/ነገሮች
1) ንስሐ መግባት

🔸እራስን ለካህን ማሳየት/ ማስመርመር፣ ቀኖና ተቀብሎ በሚገባ መፈጸም ይገባናል፡፡ ንስሐ ሳይገባ በድፍረት መቀበል ግን እንደ በደል ይሆንብናልና፡፡ 1ኛ ቆሮ. 11፡27
2) ስጋዊ ንጽህና  መጠበቅ
🔸ሰውነትን መታጠብ /ከቁርባን በፊት ያለው ቀን ላይ /
🔸ካለን ነጭ ልብስ  ፤ ከሌለን ንጹሕ ልብስ መልበስ/ነጭ ልብስ የምንለብሰው በመንግስተ ሰማያት የምንኖረው ሕይወትን ለማሰብ ነው።/
🔸 ነጠላ ማጣፋት
3) ከመቁረባችን  ከሶስት ቀን በፊት ከግብረ ስጋ ግንኙነት መታቀብ /መከልከል/
4) አፋችንን እሬት እሬት እስኪለን ድረስ መጾም
🔸ለአስራ ስምንት ሰዓታት/ የክርስቶስን መከራ፣ ሕማማተ መስቀል አሰብን የሚያሰኘንም ከበረከቱ የሚያሳትፈንም ይህ ነውና/
🔸ከምግብ፣ ከውሀ፣ ገላን ከመታጠብ፣ ጥርስን ከመቦረሽ፣ ጥፍርን/በጸጉርን ከመሰራት/ከመቆረጥ፣ ልብስ ከማጠብ፣ ከማንኛውም ወደ አፍ ከሚገቡ ነገሮች መጠበቅ ያስፈልጋል።
5) አካል ላይ ከሚደርስ ማንኛውም አደጋ መጠበቅ(እንቅፋት፣ቁስል፣ነስር፣አፍ የሚገባ ትንኝ ፣ ዝንብ፣ መድማት...)
6) ለወንዶች ዝንየት/ ህልመ ለሊት ፤ ለሴቶች የወር አበባ ከታየ በዚያን ቀን ስጋ ወደሙን መቀበል ክልክል ነው፡፡
ጊዜ ቊርባን
በቁርባን ቀን እና ጊዜ ሊደረጉ የሚገባቸው ነገሮች
🔸ከኪዳን በፊት ጀምሮ ቤ/ክ መገኘት እና ቅዳሴ መፈጸም
🔸 ጸሎት
🔸አፍን በመጎናጸፊያ(በነጠላ) መሸፈን
🔸ቅዱስ ቁርባን ከተቀበሉ በላ ወዲያው ቅዳሴ ጠበል መጠጣት አይገባም ቆመው ያስቀደሱበት ቦታ በመሄድ ድርገት እስኪመለስ ድረስ መቆም ይገባል።
🔸 ከቤተ መቅደስ ሳይጋፋ በቀስታ ወጥቶ በደጀ ሰላም ዛቲ ቀምሶ አፍን ማደፍ ይገባል።
ድኅረ ቊርባን
ከቊርባን በኃላ ሊደረጉ የሚገባቸው ነገሮች
🔸ከንግግር መቆጠብ( በምግብ አፍን እስከሚያድፉ)
🔸 በእርጋታ መንቀሳቀስ
🔸በውሃ መታጠብ አይፈቀድም ስለዚህ ለንጽህና ሶፍት መጠቀም
🔸ትንፋሽን እፍ ብሎ አለማውጣት
🔸ማንኛውንም ነገር አለመትፋት(ምራቅ ፣ምግብ...)
🔸አለመራቆት-እስከ ማታ በለበሱት መፅናት ይገባል።
🔸አብዝቶ አለመመገብ፣አለመጠጣት
🔸 ነገር እና መንገድ አለማብዛት
🔸 ቢቻል በአንድነት ሆኖ መንፈሳዊውን ነገር እየተጨዋወቱ መቆየት ፤
🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃
እግዚአብሔር በቸርነቱ ለዚህ ክብር ያብቃን!!!
🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂
🌱መጋቢት 11/07/2017 ዓ.ም🌱
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰ 
ደ/ብ/ዩ ቀን ግቢ ጉባኤ ት/ት እና ሐ/አ/ክ
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
👍25
ሁሉም ክፍላቶች ከነገ ማለትም ዕለተ ዓርብ 12/07/2017 ዓ.ም ጀምረው እስከ ቀጣይ ማክሰኞ እና ረቡዕ ድረስ ለተመራቂ ተማሪዎች ወይም ቀድሞ የግቢ ጉባኤያችን አባል ለነበሩት ልጆቿ በተቻለ መጠን ለሁለተኛ ግዜ ቅስቀሳ እንዲደረግ የማስታወቂያ እና ቅስቀሳ ክፍል አሳስቧል።

በቅስቀሳውም ወቅትም በየክፍሉ በመዞር እና በመደወልም መረጃ የሚሰበስቡ አካላት እንዳሉ ጠቅሰው በመጨረሻም በተሳካ ቅስቀሳ ብዙ አባል ያስመዘገቡ ክፍላቶች ልዩ ሽልማት እንደምዘጋጅላቸውም ጠቁመዋል።
👍13🏆8
ነገ ማለትም ቅዳሜ 13/07/2017 ዓ.ም ጠዋት ከ 3:00-6:00 የበረከት ሥራ ስላለ ሁላችንም የግቢ ጉባኤ አባል ተቀሳቅሰን በመምጣት የበረከቱ ተሳታፊ እንድንሆን በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን!
👍8👏2
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ዕለተ ቅዳሜ ቀን 13/07/2017 ዓ.ም

የሳምንቱ መርሐ ግብር


ቅዳሜ

ጠዋት ከ 3:00-6:00 የበረከት ሥራ ስላለ ሁላችሁም ተቀሳቅሳችሁ እንድትመጡ ።
ከሰዓት ከ10:00-12:00 የክፍላት ውይይት።

እሁድ

ከ8-10ሰዓት ለ2ኛ ዓመት ክርስቲያናዊ ህይወት እና ስነምግባር ኮርስ ቦታ አዳራሽ ።
ከ8-10 ሰዓት ለ4ኛ እና 5ኛ ዓመት ነገረ ቤተክርስቲያን ኮርስ ቦታ ቤዝመንት።
ከ10-12ሰዓት ለ1ኛ ዓመት ሀይማኖት እና ሳይንስ ኮርስ ቦታ አዳራሽ ።
ከ10-12ሰዓት ለ3ኛ ዓመት የቤተክርስቲያን ታሪክ ኮርስ ቦታ ቤዝመንት።

ሰኞ

ከ12:15-1:30 መዝሙር ጥናት ።
ከሰዓት ከ11-12 ሰዓት ከአባል ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ ምሰጥበት ቀን ነው።
ማክሰኞ

ጠዋት ከ12:15-1:30 መዝሙር ጥናት ።
ከሰዓት ከ11:00-12:00 መዝሙር ጥናት ።
ረብዕ

ጠዋት ከ12:15-1:30 የአዳራሽ ጽዳት ስለምንኖር ሁሉም የግቢ ጉባኤው አባል እንድገኝ።
ከሰዓት ከ11-12 ሰዓት የህይወት ትምህርት ።

ሐሙስ

ጠዋዉ ከ12:15-1:30 ቅዳሴ ተሰጥኦ ።
ከሰዓት ምንም አይነት መርሐ ግብር አይኖርም።
ዓርብ

ጠዋት ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል ስለሆነ  ምንም አይነት መርሐ ግብር አይኖርም ።
ከሰዓት ከ10:00-12:00 የዓርብ ጸሎት ከምመጡ እንግዶች ጋር በአንድነት የምናደርስበት እና በተጋባዥ መምህራን ት/ት የምሰጥበት ቀን ነው።

አብነት ትምህርት በነበረበት ይቀጥላል ከቅዳሜ ውጭ!
     
ወስብሐት ለእግዚአብሔር።
👍32😭1
እነዚህ በደብረብርሃን ዩንቨርስቲ በቀን ግቢ ጉባኤ ለ18ኛ ዓመት ለግቢ ጉባኤያችን የምሥረታ በዓል ምክንያት በማድረግ የተዘጋጁ ናቸው ሁላችሁም እየገዛችሁ ይህንን ታላቅ በዓል በድምቀት ከምመጡ እንግዶቻችንም ጋር በአንድነት እናከብራለን።
በፈለጋቹት size ታገኛላችሁ
1,medium
2,large
3,xxl
አለላችሁ በየክፍል ተጠሪዎቻችሁ በኩል
ወይም ደግሞ በግቢ ጉባኤው ልማት ሱቅ አካባቢ ይገኛል።
ባሉበት ሁነው ይዘዙን እናደርሳለን :-+251924275669

ዋጋ=300 ብር ብቻ
3👍2
አራት ቀናቶች ብቻ ቀሩት!!!
የግቢ ጉባኤያችን የ18ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አራት ቀናቶ ብቻ ቀርተውታል
ሁላችንም በዓሉ የደመቀ እና የተሳካ እንድሆን የበኩላችንን ድርሻ እንድንወጣ በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን።
በተቻለ መጠን ለቀድሞ ተማሪዎቻችን መደወል ከዛም መልዕክት (text) በመላክ ማስታወስ ከእኛ የምጠበቅ ነገር ነው
በመቀጠል ይህንን ባነር ሁላችሁም የግቢ ጉባኤ ልጆች profile በማድረግ ድባቡን አድምቁት።
ይህ የእናት ግቢ ጉባኤ የጥሪ ድምፅ ነው ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን።
5👍2🕊2🏆1
2 ቀናቶች ብቻ ቀርተዋሉ!
ከወዲሁ እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ ልንላችሁ እንወዳለን ።
መርሐ ግብ ዓርብ መጋቢት 19/072017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ እንግዶቻችን በተገኙበት በጸሎት እና በቡራኬ ይጀመራል
የእግዚአብሔርን ቃል እንድትሰሙ የእግዚአብሔር ማዕድ እንድትጋሩ ኑ ኑ ኑ!!!
👍7👏2🏆1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አንድ ቀን ብቻ ቀረው!!!!!
እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን
ነገ ማለትም መጋቢት 19/07/2017 ዓ.ም መርሐ ግብራችን በይፋ ይጀመራል ሁላችንም አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅብናል።
T-shirt መግዛት የምትፈልጉ እያለቀ ስለሆነ በፍጥነት ደውሉልን።
ስልክ:-+251924275669
👍64🕊2🏆2
''ያለ ማንጐራጐር እርስ በርሳችሁ እንግድነትን ተቀባበሉ፤(1 ጴጥሮስ 4
9)
የመጀመሪያው ቀን

ዛሬ ማለትም ዕለተ ዓርብ 19/07/2017 ዓ.ም የግቢ ጉባኤያችን የምሥረታ በዓል የመጀመሪያው ቀን እንዲህ ያማረ ሁኖ በጸሎት እና በቡራኬ ተጀምሯል ።
በመርሐ ግብሩ ላይ
በቃለ ወንጌል :-መላከ ታቦር የኔታ ሀይለ ኢየሱስ ሕይወት የሆነውን ቃለ እግዚአብሔር የመገቡን ስሆን
ቀጥሎም ዝማሬ ቀርቦ በመጨረሻም ለዛሬው በጸሎት ተዘግቶ መርሐ ግብሩ አብቅቷል ።

   ነገ ማለትም መጋቢት 20/07/2017 ዓ.ም ይህ ጉባኤ ቀጥሎ የሚደረግ ይሆናል ።

ነገ ከጥዋቱ 3:00 ጀምሮ ጉባኤው ይቀጥላል።
መቅረት ይቅርና ማርፈድ ያስቆጫል !
3👍2🕊1