ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ
1.28K subscribers
390 photos
36 videos
45 files
49 links
ይህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ ት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ደ/ብ ማዕከል የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የቀን ግቢ ጒባኤ ይፋዊ የቴሌግራም መገናኛ ነው።
Download Telegram
👨‍🎓🧑‍🎓የ2016 ዓ/ም ተመራቂዎች
                     💐💐  እንኳን ደስ አላችሁ 💐💐
ቀሪውም ጊዜያት ያማረ የሰመረ መንገድ ያድርግላችሁ በርቱ አይዟችሁ በሄዳችሁበት ሁሉ ሃያሉ ልዑል እግዚአብሔር ይከተላችሁ ከፊት ይቅደምላችሁ ❤️❤️❤️
የደ/ብ/ዩ/የቀ/ግ/ጉባኤ
# https://t.me/dbugg21group
Join us on telegram @dbugg21
And our group @dbugg21group
👍1812
<<ሰኞ ,ነሐሴ13>>>>>>>>

         †††      ስንክሳር     †††

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡

          †   እንኳን አደረሳችሁ   †

     🕊 ደብረ ታቦር🕊


አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ዐሥራ ሦስት በዚች ቀን ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅና ክቡር በዓል ነው :: በዚች ቀን መድኃኒታችን ሦስቱን ደቀ መዛሙርቶቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ላይ አወጣቸው ። መልኩም በፊታቸው ተለወጠ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ ። ስለ እነርሱም ጌታችን የሰው ልጅ በጌትነቱ ሲመጣ እስከሚያዩት ድረስ በዚህ ከቆሙት መካከል ሞትን የማይቀምሱት አሉ አለ ። ሰዎች ሁሉ እርሱ ለሙሴ ጌታውና ከሞት ያስነሣው እንደሆነ ለኤልያስም ፈጣሪው እንደሆነና ካሳረገበትም ያወረደው እርሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ እነሆ ከጌታ ከኢየሱስ ጋራ እየተነጋገሩ ሙሴና ኤልያስ ወደርሱ መጡ ። ስለዚህም ጴጥሮስ ጌታችንን እንዲህ አለው አቤቱ በዚህ ትኖር ዘንድ ትወዳለህን ሦስት ሰቀላዎችንም አንድ ላንተ፣ አንድ ለሙሴ፣ አንድ ለኤልያስ እንሠራ ዘንድ ። በዚህም ቃል የደካማነትና የትሕትና ምልክት አለበት ። ደካማነት የተባለ ጴጥሮስ ጌታችን ከሰማይ የወረደበትን ሥራ ትቶ በተራራ ላይ ይኖር ዘንድና ራሱን የሚሠውርበትን ቤት ይሠራለት ዘንድ የተናገረው ነው ። ትሕትና ያልነውም ጴጥሮስ ለራሱና ለባልንጀሮቹ ሐዋርያት ቤት ይሠራ ዘንድ ስለ አላሰበ ነው ። ራሱንና ባልንጀሮቹ ሐዋርያትን እንደ ባሮች ነቢያትን ደግሞ እንደ ጌቶች አድርጎ አስቧልና ። ሰለ ሐዋርያትም የእውቀት ማነስ አታድንቅ በዚያን ጊዜ ፍጹማን አልሆኑምና ። እንዲህም በሚልበት ጊዜ ጌታችን በሰው እጅ የተሠራ ማደሪያን የማይሻ መሆኑን ለጴጥሮስ ያሳየው ዘንድ እነሆ ደመና ጋረዳቸው ። የጌታችንን ጌትነቱን የሚገልጽ በሐዋርያትም ልቡና እምነትን የሚያጸና እንዲህ የሚል ቃል ከደመና ውስጥ መጣ ። ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱንም ስሙት ። ሙሴና ኤልያስም ከእርሱ ጋራ ሲነጋገሩ ተሰሙ ስለ ርሱ መምጣት የተናገሩትን ትንቢታቸውንም በቸርነቱ አረጋገጠ ። ወደ ተራራ ላይ በመውጣቱም ነቢያትና ሐዋርያት ደስ አላቸው ። ሁለተኛም የአብን ቃል በሰሙ ጊዜ ከእነርሱ ሥውር የነበረ የወልድ ዋሕድን በእውነት ሰው መሆን በዚያን ጊዜ ተረዱ ያን ጊዜ የጌትነቱ ክብር ተገልጦአልና ። ሐዋርያትም ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነ እርሱ ሙሴን ከመቃብር ያስነሣው ኤልያስንም ያሳረገው አውርዶም ያመጣው እርሱ እንደሆነ አወቁ ። ከእርሱ በቀር ማንም ማን የሙሴን መቃብር የሚያውቅ የለምና ከዐሳረገው ከእርሱ በቀር ማንም ማን ኤልያስ ያለበትን የሚያውቅ የለምና ። በሰማይና በምድር ሥልጣን ካለው ከሁሉ ጌታ በቀር ሙታንን አድኖ ሊአስነሣቸው ማንም አይችልም ።

ደብረ ታቦርም የቤተ ክርስቲያን አምሳል ሆነች ከብሉይና ከሐዲስ በውስጧ ሰብስባለችና ። የአብንም ቃል በሰሙ ጊዜ በግምባራቸው ፍግም ብለው በምድር ላይ ወደቁ እንደ ሙታንም ሆኑ ። ከዓለም አስቀድሞ ከእርሱ ጋራ በህልውና እንዳለ ለልጁ አብ ምስክርን ሆነ ወዲያውኑ ሙሴ ወደ መቃብሩ ኤልያስም ወደ ቦታው ተመለሱ ። ሐዋርያትንም በአነቃቸው ጊዜ ከብቻው ጌታችን በቀር ማንንም አላገኙም ። ከባሕርያችን የተዋሐደና ሥጋችንን የለበሰ ፍጹም አምላክ እንደሆነ በዚህ ሐዋርያት አስተማሩ ። እንግዲህ እናስተውል ሰው ካልሆነ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታቸንን ድንግል ማርያምን በአበሠራት ጊዜ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው እንዴት አላት ። አምላክ ካልሆነስ ለመንግሥቱ ፍጻሜ የለውም እንዴት አላት ። ሰው ካልሆነ በበረት እንዴት አስተኙት ። አምላክስ ካልሆነ መላእክት ከሰማይ ወርደው ለእግዚአብሔር በሰማያት ምስጋና በምድርም ሰላም ለሰውም ግዕዛኑ ሊሰጠው እያሉ እንዴት አመሰገኑ ። ሰው ካልሆነ ዮሐንስ በውኃ እንዴት አጠመቀው አምላክስ ካልሆነ አልዓዛርን ከመቃብር እንዴት ሊያስነሣው ቻለ ። ይህ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው እንድ ልጅ አካላዊ ቃል እግዚአብሔር እርሱ ያለ መለወጥ ያለ መለየት አንድ አካል አንድ ባሕርይ በመሆን ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው እንደሆነ እናምንበታለን ። እርሱም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ሁል ጊዜ አንድ ህላዌ ነው ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን ።

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
👍228
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!

▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
           የደ/ብ/ዩ/የቀ/ግ/ጉባኤ
# https://t.me/dbugg21group
Join us on telegram @dbugg21
And our group @dbugg21group
32👍16🕊8
...በተለይ የ 1 ቁጥር ላይ ያለውን በግል የሀብትና የመስጠት ጸጋው ያላችሁ ወይም በዚህ ባች የተመረቅን ተባብረን እንሸፍናለን የምትሉ ካላችሁ አሳውቁን?

በዚህ ወቅት ገንዘብ መጠየቅ ከባድ ቢሆንም አጣብቂኝ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ብንሆንም ግን ደግሞ እጃቸው እስኪደማ ሚስማር እየተወጋን የቀን ሥራ እየተሠራ የተሠራው አዳራሽ የሁላችንም ታሪክ የዓይን ማረፊያ መሰብሰቢያችን ነውና

ሁላችሁም አባላት ሐሳብ ስጡበት።

ከተወያየን በኋላ ነው ወደ እናንተ ያመጣነው ፕሮጀክት ክፍሉ ደምሰው ሐሳቦችን እየያዘ... አቅጣጫ እየሰጠን ገቢ አሰባሰቡን በዚህ ሳምንት ለመጀመር ነው።
👍31
ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የቀን ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ጋር ዛሬ ምሽት በቀን 15/06/2017 ዓ/ም ከአገልግሎት በኋላ የበረከት ሥራ።
5
በዚህ ዓመት የክፍላት ውድድርና ሌሎች ወጪዎች አንጠየቅም እዚህ ላይ ብቻ ነው የምንረባረበው በእውነት ካስታወሳችሁ የቀን ሥራ እየሠራን የሠራነውን አዳራሽ ዛሬ ...ደግሞ ወጥተን በትንሽ ገንዘብ ደግፈን እንጨርሰው።
ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ
ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የቀን ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ጋር ዛሬ ምሽት በቀን 15/06/2017 ዓ/ም ከአገልግሎት በኋላ የበረከት ሥራ።
አቤት ምን አይነት የግቢ ጉባኤን ፍቅር ነው የምናየው በእውነት አባታችን መካሪያችን ቀሲስ ሽፈራው ተሸክመው ስናይ ምን ይሰማን ይሆን? አባታችንን በእድሜና ይጠብቅልን አይዟችሁ በርቱ ሁላችንም የምንችለውን እናደርጋለን።
1👍1
ሰላም ወንድም እህቶች እንኮን አደረሳችው !!!የምታሳዩት እንቅስቃሴ በጣም ደስ ይላል አይዞችው በእግዚአብሔር አጋዥነት እናሳካዋለን የምስረታ በእላችንን በእዲሶ ሞንታርቦና በአዲስ አዳራሽ ወለል እናካብራለን!!!የመጽሐፍ ስማቸውን ለኛም አድርሱን ምህላ ስላለን
👍1
ሀ/ገብርኤል ከባች ክፍል
የgroup አችን ሃሳብ መስጫ ተከፍቷል ለተመራቂ እህት ወንድሞቻችን ደስታችሁን ማጋራት ትችላላችሁ 👇👇👇👇
Forwarded from Ďâňĩ Ÿé ďĩňĝĩl21❤
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን አደረሰን እንኳን አደረሳችሁ!

''ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሄድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ።
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ እግሮቻችን በአደባባይሽ ቆሙ።(መዝ 122፥1-2)

እኔሆ በጉጉት ስጠበቅ የነበረው
የደብረብርሃን ዩንቨርስቲ
የቀን ግብ ጉባኤ
18ኛ ዓመት
የምሥረታ በዓል
ደረሰ
ይሄውም
ከመጋቢት 19-21/07/ 2017 ዓ.ም
መምህራነ ወንጌል
እንድሁም ዘማሪያን
የቀድሞ የግቢ ጉባኤያችን ተመራቂ ተማሪዎች
በዩኒቨርስቲያችን የምገኙ ሠራተኞች
አሁን ላይ በግቢው የምገኙ ተማሪዎችን ጨምሮ
በአንድነት በታላቅ ድምቀት ይከበራል

ስለሆነም ከመጋቢት 19-21/07/2017 ዓ.ም
በደብረብርሃን ዩንቨርስቲ የቀን ግቢ ጉባኤ አዳራሽ በመገኘት ይህንን ታላቅ በዓል እንድታከብሩ ስትል እናት ግቢ ጉባኤ ጥሪዋን ታስተላልፋለች!

ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን !

የደብረብርሃን ዩንቨርስቲ የቀን ግቢ ጉባኤ
👍118🕊3

መፃጉዕ
የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል (፭፥፪-፱) መፃጉዕ የተባለ አንድ በሽተኛ ለሠላሳ ስምንት ዓመት በደዌ ተይዞ በአልጋ ቁራኝነት የኖረ ሰው በአምላካችን ድንቅ ተአምር እንዴት ፈውስ እንዳገኘ ይተርካል፡፡ የዐቢይ ጾም አራተኛው ሳምንትም ይህን ታሪክ በማውሳት “መፃጉዕ” ተብሎ ይጠራል፡፡ 
ጌታችንም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ በበጎች በር አጠገብ በነበረች መጠመቂያ ቦታ ስሟም በዕብራይስጥ ቋንቋ ‹‹ቤተ ሳይዳ›› ወደ ምትባል ቦታ ደርሶ በዚያ ያሉ ዕውራኖችና አንካሶች፣ ሰውነታቸውም የሰለለ ድውያን ተኝተው የውኃውን መናወጥ ሲጠባበቁ አገኛቸው፡፡ የእግዚአብሔር መልአክ ወደ መጠመቂያው ወርዶ ውኃውን በሚያናውጠው ጊዜ፥ ከውኃው መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ ወርዶ የሚጠመቅ ካለበት ደዌ ይፈወስ ነበርና፡፡ በመካከላቸውም ከበሽታው ጽናት የተነሣ ስሙ እንኳን ጠፍቶ በበሽታው ስም “መፃጉዕ” የተባለውን ሰው ጌታችን ተመከተውና ወደ እርሱም ቀርቦ ‹‹ልትድን ትወዳለህን?›› ብሎ በሽተኛውን ጠየቀው፡፡ መጠየቁ ሰውየው መዳን እንደሚፈልግ ሳያውቅ ቀርቶ ሳይሆን ‹‹በዕለተ ዓርብ ፈውሰኝ ሳልል ፈውሶኛል›› ብሎ የሚመሰክርበት ነውና አስፈቅዶ ለማዳን ጠየቀው፡፡ አንድም በድኅነት ውስጥ ሰው የራሱ ሱታፌ እንዳለው ለማስተማር ነው፡፡
ድውዩም ‹‹ጌታ ሆይ፥ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም፤ ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል›› ብሎ መለሰለት። ቸሩ አምላካችንም ‹‹ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ›› አለው። መፃዕጉም ጉልበቱ ጸንቶ ተነሣ፤ አልጋውንም ተሸክሞ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ ፈሪሳውያን ግን ‹‹በሰንበት አልጋህን ተሸክመህ መሄድ እትችልም፤ ፈውስም በሰንበት መሆን የለበትም›› ብለው ተቆጡ፡፡ (ዮሐ.፭፥ ፩-፱)
አይሁድም ‹‹አልጋህን ተሸክመህ ሂድ ያለህ ሰውዬው ማነው?›› ብለው ጠየቁት፡፡ ያ የተፈወሰው ግን ያዳነው ማን እንደ ሆነ አላወቀም፤ ጌታችን ኢየሱስ በዚያ ቦታ በነበሩት ብዙ ሰዎች መካከል ተሠውሮ ነበርና፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ያን የዳነውን ሰው በቤተ መቅደስ አገኘውና፥ ‹‹እነሆ፥ ድነሃል፤ ግን ከዚህ የባሰ እንዳያገኝህ ዳግመኛ እንዳትበድል ተጠንቀቅ›› አለው፡፡ ያም ሰው ሄዶ ያዳነው ጌታችን ኢየሱስ እንደ ሆነ ለአይሁድ ነገራቸው፡፡ ስለዚህም አይሁድ ጌታችን ኢየሱስን ያሳድዱትና ሊገድሉትም ይሹ ነበር፤ በሰንበት እንዲህ ያደርግ ነበርና፡፡ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፥ ‹‹አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል፤ እኔም እሠራለሁ›› አላቸው፡፡ ስለዚህም አይሁድ ‹‹ሰንበትን የሚሽር ነው፤ እግዚአብሔርን አባቴ ነው ይላል፤ ራሱንም ከእግዚአብሔር ጋር ያስተካክላል›› በማለት ሊገድሉት በጣም ይፈልጉ ነበር፡፡
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ ‹‹እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ወልድ ከራሱ ብቻ ምንም ሊያደርግ አይችልም፤ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ፤ ወልድም አብ የሚሠራውን ያንኑ እንዲሁ ይሠራል፡፡ አብ ልጁን ይወዳልና የሚሠራውንም ሥራ ሁሉ ያሳየዋል፤ እናንተም ታደንቁ ዘንድ ከዚህ የሚበልጥ ሥራን ያሳየዋል፡፡ አብ ሙታንን እንደሚያስነሣቸው÷ ሕይወትንም እንደሚሰጣቸው እንዲሁ ወልድም ለሚወድዳቸው ሕይወትን ይሰጣል፡፡ አብ ከቶ በማንም አይፈርድም፤ ፍርዱን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ፡፡ ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩ ወልድን ያከብሩ ዘንድ፤ ወልድን የማያከብር ግን የላከውን አብን አያከብርም፡፡›› (ዮሐ.፭፥ ፩-፳፬)
አምላካችንን እግዚአብሔር በመፍራት፣ በማከበር፣ እርሱን በማመን መኖርና ለእርሱ መታመን እንዳለብን እዚህ ላይ እንረዳለን፡፡ አለበለዚያ ግን ፈውሰ ሥጋን ካገኘን፣ ከሕመማችን ከተፈወስንና ከሥቃያችን ከተላቀቅን በኋላ እንደ መፃጉዕ መልሰን አምላካችንን መርሳት አልያም መካድ ይሆናልና በፈሪሃ እግዚአብሔር፣ በእምነት ጸንተን እንኑር!
አምላካችን እግዚአብሔር በቸርነቱ ጸሎታችንን፣ ጾማችንና ንስሐችንን ይቀበለን፤ አሜን!     
ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም ያድርሰን!
ኢትዮጵያን በጽኑ ሰላም ይጠብቅልን!!
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
 ደ/ብ/ዩ ቀን ግ/ጉ/ ት/ት እና ሐ/አ/ክ 
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
👍7
እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ!
የደብረብርሃን ዩንቨርስቲ የቀን ግቢ ጉባኤ 18ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በያዝነው ወር ማለትም መጋቢት 19-21/07/2017 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ይከበራል።
ይህንን የእናት ግቢ ጉባኤ ጥሪ ድምፅ ላልሰሙት በማሰማት የበኩልዎን ድርሻ ይወጡ!
በሰላም ለዚያች ቀን ያድርሰን!
13👍2🕊2