Dilla Don Bosco Catholic Secondary School
1.67K subscribers
2.01K photos
29 videos
20 files
273 links
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
የአልጎሪዝም ወጥመድ !

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ - Tikvah Ethiopia)

በኢትዮጵያችን አንገብጋቢ አጀንዳዎቻችን ፖለቲካ፣ ሰብዓዊ መብት፣ በህይወት የመኖር ደህንነት፣  የኑሮ ውድነት፣ ኢኮኖሚ፣ ሰላም እና ሌሎች... ጉዳዮች ናቸው።

እውነት ነው እነዚህ ወሳኝ ጉዳዮች መሆናቸው አይካድም።

ነገር ግን ከነዚህ እኩል ሀገርን እና ትውልድን ከውስጥ እየበላ ስላለውና ትልቅ አደጋ ስለደቀነው የማህበራዊ ሚዲያ (በተለይም ቲክቶክ) ሱስ መነጋገር ይበጃል።

1. ትምህርት የሀገር ግንባታ ዋናው መሰረት ነው። ዛሬ ዛሬ ላይ የማህበራዊ ሚዲያው /ቲክቶክ " ሳይማሩ መታወቅን " እና " ሳይለፉ መክበርን " እንደ ስልጣኔ እያቀረበ ታዳጊዎቻችንን ከመጽሐፍ እያራቃቸው ነው። አንዳንዱ የትውልዱ አካል ማንበብን እንደ ኋላ ቀርነት፣ ስክሪን ላይ ፈዞ መዋል ደግሞ እንደ "ፈታ ማለት " እያየው ነው።

2. በተለይም ከማህበራዊ ሚዲያዎች መካከል ቲክቶክ አእምሮን በቀላሉና ያለ ድካም በሚገኝ ደስታ እንዲለምድ እያደረገው ነው። ትምህርት ደግሞ ትዕግስት፣ ጥረትና ትኩረት ይጠይቃል። በዚህ ምክንያት ልጆቻችን መጽሐፍ ማንበብ " አሰልቺ "፣ ቲክቶክ ማየት ግን " አስደሳች " እየሆነባቸው ነው።

3. ጠንክሮ ሰርቶ፤ ተመራምሮ ፤ አጥንቶ ሀገርን መለወጥ ቀርቶ በስክሪን ፊት ቆሞ በመሰዳደብ፣ ለረጅም ሰዓት ቁጭ ብሎ በማውራት ፣ የቤተሰብን የግልን የሰዎችን ገመና አደባባይ በማስጣት ፣ ሲበሉ ሲጠጡ ሲዞሩ በመዋል ፣ በመጨፈር ወይም ሰውን በመሳደብ የሚገኝ " ቀላል ገንዘብ " የልጆቻችን ህልም ሆኗል። ይህ ለሀገር አደጋ ነው።

4. የኛ ማህበረሰብ የሚታወቅበት ጨዋነት፣ መከባበርና እሴት በ"ቪው" እና "ላይክ" እየተቸረቸረ ነው። ዝና ለማግኘት የማይደረግ ነውር የለም።

5. የነገ ሀገር ተረካቢ ልጆቻችን በዲጂታል ሱስ አእምሯቸው እየታወረ ነው።

6. ልጆቻችን ስልክ ውስጥ ጠፍተዋል። ከቤት ሳይወጡ ግን ከእኛ ርቀዋል። ቲክቶክ የልጆቻችንን ስነ-ልቦና እና የትምህርት ፍላጎት እየገደለ ነው። የወደፊት ተስፋቸው በ60 ሰከንድ ቪዲዮ እየተቀበረ ነው።

7. ልጆቻችን " ለመክበር፣ ገንዘብ ለማግኘት ፣ ለመታወቅ፣ ጥሩ ህይወት ለመኖር ምንም መማር አያስፈልግም " የሚል የተሳሳተ መልዕክት እየተጋቱ ነው። ሳይማሩና ሳይለፉ በቲክቶክ ብቻ ገንዘብና ዝና ያገኙ ሰዎችን እንደ አርአያ (Role Model) ማየት ጀምረዋል።

8. መጽሐፍ ገልጦ ለማንበብ የሚሰለቻቸው ልጆች ለሰዓታት ስክሪን ላይ አይናቸው ሳይዝል መቆየት ይችላሉ። ይህ በትምህርታቸው ላይ ትልቅ ቀውስ እየፈጠረ ነው።

9. ልጆቻችን ስልክ ሲነኩባቸው የሚቆጡ፣ ስልክ ሲቀሙ የሚበሳጩና በትንሽ ነገር የሚጨቃጨቁ እየሆኑብን ነው።

10. ልጆቻችን የወላጆችን ጨዋነትና ስነ-ምግባር ሳይሆን የማህበራዊ ሚዲያ ዝነኞችን ጩኸትና ነውር ፣ ስድብ ፣ ጋጠወጥነት እንደ ስልጣኔ እየቆጠሩት ነው።

ወላጆች ሆይ ! ይህ እንዲሁ በቀላሉ የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም። ሁላችሁም በየቤታችሁ ተነጋገሩበት።

ግን ከምንም ነገር በፊት እኛ ወላጆች የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማችን እንዴት ነው ? ይህን ከመለስን በኋላ፦
- በየቤታችን ልጆች እንዴት እያደጉ ነው ?
- ትምህርታቸው እንዴት ነው ? ምን አይነት ችግር እያያችሁ ነው ?
- ለችግሮቹ ምን አይነት መፍትሄ እየወሰዳችሁ ነው ?


ስሜታችሁን በDM / @tikvahethiopiaBOT አጋሩ።

በፌስቡክ ኮሜንት https://www.facebook.com/61588053582297/posts/122104023063268452/?app=fbl

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia
🕊21
‎ስኬታማ የሆነች ተማሪያችን

‌‎ሰላም እንዴት ቆያችሁ የገጻችን ተከታዮች?
‎በዛሬው ፅሁፌ ላስተዋውቃችሁ የምፈልገው የቀድሞ የትምህርት ቤታችን ተማሪ የሆነችውን #ቤተልሔም_ተሻለን ይሆናል፡፡

‎ትምህርቷን ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል የተከታተለችው በዲላ ዶንቦስኮ ትምህርት ቤቶች ነው፡፡

የዛሬ 8 ዓመት በ2010 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በመፈተን አጥጋቢ ውጤት በማስመዝገብ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን በ2011 ዓ.ም ተቀላቅላለች።

‎በ2014 ዓ.ም ከአንጋፉው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በጋዜጠኝነት እና ተግባቦት በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀች ሲሆን በመቀጠል ከዚሁ ዩኒቨርስቲ በፒአር ስትራቴጂ ኮምዩኒኬሽን በማስተርስ ዲግሪ ተመርቃለች።

‎በአሁን ሰዓት በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ በቲቪ ሪፖርተርነት እያገለገለች ትገኛለች።

‎በት/ቤታችን ቆይታዎ በትምህርቷም ይሁን በስነ ምግቧሯ ምስጉን ተማሪ ነበረች።
‎በተለያዩ የመድረክ እና ሚኒሚዲያ ክበባት የነቃ ተሳትፎ የነበራት ሲሆን በ2010 ዓ.ም በት/ቤታችን የ12ኛ ክፍል የሰራተኞች ቀን በሚከበርበት ወቅት እንደ ጋዜጠኛ በሙሉ ዲሲፕሊን እና የስራ ትጋት ስታገለግል ነበር።

‎አሁን ለደረሰችበት ቦታ የዲላ ዶን ቦስኮ ት/ቤቶች አስተዳደሩ፣ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች ትልቅ እገዛ እንዳደረጉላት ትገልፃለች።

‎እኛም መልካሙን ሁሉ እንመኝልሻለን። ኮርተንብሻል በርቺ።

‎የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል

‎ለተጨማሪ መረጃ የትምህርት ቤታችንን የማህበራዊ ድህረ ገፆች ይጠቀሙ:

#ፌስቡክ:
https://m.facebook.com/groups/715959666071910/?ref=share&mibextid=NSMWBT

#ዩቱብ:
https://www.youtube.com/@DBICTC

14🕊2🏆2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
From the archives – 2015 E.C

Mr. Mikyas, Manager of Camara Education Ethiopia, delivering an inspiring Good Morning speech to our students.
2
‎የ2018 ዓ.ም የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛደረጃት/ቤት የእግርኳስ ውድድር ፍፃሜውን አገኘ።

‎ዲላ፣ መጋቢት 3፣ 2018 ዓ.ም  (ዶን ቦስኮ ኢ.ቴ.ማ)

‎ግማሽ ዓመት በላይ ተመልካችን እያዝናና ሲደረግ የነበረው የዶንቦስኮ ቶርናመንት በዛሬው እለት በዶንቦስኮ ሜዳ ፍፃሜውን ማግኘት ችሏል፡፡

‎በመሆኑም ለፍፃሜ ደርሰው የነበሩት ሁለቱ ቡድኖች ማለትም 12 social እና 10ኛ ክፍል የዋንጫ ጨዋታቸውን ፉክክር በተሞላበት መንገድ ያደረጉ ሲሆን፤ ጨዋታውን አስረኞች 4 ለ 3 በማሸነፍ የዋንጫው ባለቤት መሆን ችለዋል፡፡

‎ የዶንቦስኮ ቶርናመንት በየዓመቱ የተለያዩ ስፖርቶችን በማካተት ተማሪዎች ከትምህርታቸው ባሻገር በእረፍት ሰዓታቸው ስፖርታዊ ውድድሮችን እያደረጉ ራሳቸውን እንዲያዝናኑ እድል ይፈጥራል፡፡

‎ በዚህም ውድድር ብዙ ተማሪዎች በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች ማለትም በቅርጫት ኳስ፣ በመረብና በእግር ኳስ እንደየ ችሎታቸውና ፍላጎታቸው ሚሳተፉ ይሆናል፡፡

‎ ይህ ዲፓርትመንት በመ/ር ታጋይ ወጋሶ ዋና መሪነት እና በስፖርቱ ኮሚቴዎች አማካኝነት ብዙ ስራዎች እየተሰሩበት ይገኛል፡፡ ለቀጣዩም ዓመት ከዚ በተሻለ ሁኔታ ቶርናመንቱ እንደሚቀጥል የዲፓርትመንቱ ሀላፊ መ/ር ታጋይ ገልፆዋል፡፡

‎ በዚሁ አጋጣሚ አሸናፊ ቡድኖች እንኳን ደስ አላቹ 🏆🏆🏆 ፡፡

‎ዘገባ: ተማሪ አብዱረህማን ሙሳ
‎ካሜራ: መ/ር ይሁን አጃሎ
🏆156