Dilla Don Bosco Catholic Secondary School
1.67K subscribers
2K photos
29 videos
20 files
272 links
Download Telegram
WHAT MAKES A GOOD STUDENT.
📌1. Discipline
✏️Shows up on time, stays focused, and avoids distractions.

📌2. Curiosity
✏️Always eager to learn more and ask questions.

📌3. Consistency
✏️Studies regularly, not only during exams.

📌4. Respectfulness
✏️Treats teachers, classmates, and school rules with respect.

📌5. Responsibility
✏️Takes ownership of their success and mistakes.

📌6. Time Management
✏️Knows how to balance school, rest, and activities.

📌7. Positive Attitude
✏️ Believes in learning, even when it’s hard.

📌8. Active Participation
✏️Contributes in class, groups, and discussions.

📌9. Self-Motivation
✏️Pushes themselves even when no one is watching.

📌10. Goal-Oriented
✏️Has a vision and works toward it step by step.
8🕊1
Forwarded from Tikvah-University
የፋይዳ መታወቂያ ያውጡ!

ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ማውጣት እንዳለባቸው ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ መስጠቱ ይታወቃል፡፡

ይህንንም ተከትሎ የመንግሥት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች የሁለተኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ ተማሪዎቻቸው በሙሉ የብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) እንዲያወጡ እያደረጉ ነው፡፡

ብሔራዊ መታወቂያው ለምዝገባ፣ ለፈተና እንዲሁም ለተለያዩ የግቢ ውስጥ አግልጋሎቶች ግዴታ እንደሚሆንም እየተገለፀ ነው፡፡

የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ለመውሰድ፣ ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ለመፈተን፣ የብቃት ምዘና ፈተና (Licensing Exam) ለመውሰድ እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና (ESSLCE) ለመውሰድ ብሔራዊ መታወቂያ ማውጣት የግድ እንደሆነ በመንግሥት መገለፁ ይታወቃል፡፡

@tikvahuniversity
1
Forwarded from Tikvah-University
የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ይሰጣል። - ትምህርት ሚኒስቴር

በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና መቶ በመቶ በበይነ መረብ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገልፀዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት የመልቀቂያ ፈተናው በወረቀት እና በበይነ መረብ ሲሰጥ እንደነበር፣ በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የግማሽ ዓመት አፈጻጸም መድረክ ላይ የተገኙት ሚኒስትሩ አስታወሰዋል፡፡

ዘንድሮ ፈተናውን ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ ለመስጠት የተለያዩ ግብዓቶች ለክልሎች ድጋፍ እየተደረገ ሲሆን፤ በፈተና ጣቢያዎች በቂ የኢንተርኔት አቅርቦት እንዲኖር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመነጋገር ይሠራል ብለዋል።

ክልሎች በቂ ኮምፒዩተር፣ ኔትዎርክ እና አማራጭ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር በትኩረት እንዲዘጋጁ ያሳሰቡት ሚኒስትሩ፤ ለተማሪዎች በቂ ስልጠና መስጠት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በዚህም የክልል እና የከተማ መስተዳድሮች ሀገር አቀፍ ፈተና ሙሉ በሙሉ በኦንላይን እንደሚሰጥ አውቀው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል።

በ2017 ዓ.ም ለመልቀቂያ ፈተናው ከተቀመጡ 585,882 ተማሪዎች መካከል 134,609 ወይም 23% ያህሉ ፈተናውን በኦንላይን የወሰዱ መሆናቸው ይታወሳል፡፡

@tikvahuniversity
3
‎ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎችና  በሙሉ

‎የ12ኛ ክፍል ለአገር አቀፍ ፈተና በበየነ መረብ ምዝገባ(online registration) ከነገ ማክሰኞ የካቲት 17 እስከ ዓርብ የካቲት 20/2018ዓ. ም የሚከናወን በመሆኑ ከታች በተቀመጠው ፕሮግራም መሰረት አስፈላጊውን መረጃ በሟሟላት ለምዝገባው ዝግጁ እንድትሆኑ እናሳስባለን።

‎ምዝገባው በሚከተሉት ሰዓት እና ቀናት ይከናወናል
‎ከሰዓት ከ8:00 እስከ 10:30 ሰዓት

‎ * ማክሰኞ የካቲት 17/2018ዓ.ም 12ኛ A ክፍል
‎* ዕሮብ የካቲት18/2018ዓ.ም12ኛB ክፍል
‎* ዓርብ የካቲት 19/2018ዓ.ም 12ኛ C ክፍል

‎** በወጣው የምዝገባ ቀን ተማሪዎች ፋይዳ መታወቂያ ሲያወጡ ያስመዘገቡትን #ስልክ ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል።


‎ማሳሰቢያ
‎* በቀኑ ከተጠቀሰው ክፍል ውጪ #ስልክ ይዞ ትምህርት ቤት መምጣት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን እንገልፃለን

‎* ከት/ቤቱ እውቅና ውጪ በመቅረት በምዝገባው ሂደት ለሚፈጠር ማንኛውም ክፍተት ት/ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን እናሳውቃለን ።
‎                            

‎አስፈላጊ መረጃዎችን ከዚህ በታች ባለው ጎጉል ፎርም በጥንቃቄ ሞልታችሁ ላኩ።

‎መረጃውን በጎጉል ፎርም ያላከ ተማሪ መመዝገብ አይችልም።

‎     ት/ቤቱ

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdVmPPWrNEoKU3ArB3Xu8yKWsr_DaZIdwgTMWkr9I8LVgTkrw/viewform?usp=header
7
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
የአልጎሪዝም ወጥመድ !

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ - Tikvah Ethiopia)

በኢትዮጵያችን አንገብጋቢ አጀንዳዎቻችን ፖለቲካ፣ ሰብዓዊ መብት፣ በህይወት የመኖር ደህንነት፣  የኑሮ ውድነት፣ ኢኮኖሚ፣ ሰላም እና ሌሎች... ጉዳዮች ናቸው።

እውነት ነው እነዚህ ወሳኝ ጉዳዮች መሆናቸው አይካድም።

ነገር ግን ከነዚህ እኩል ሀገርን እና ትውልድን ከውስጥ እየበላ ስላለውና ትልቅ አደጋ ስለደቀነው የማህበራዊ ሚዲያ (በተለይም ቲክቶክ) ሱስ መነጋገር ይበጃል።

1. ትምህርት የሀገር ግንባታ ዋናው መሰረት ነው። ዛሬ ዛሬ ላይ የማህበራዊ ሚዲያው /ቲክቶክ " ሳይማሩ መታወቅን " እና " ሳይለፉ መክበርን " እንደ ስልጣኔ እያቀረበ ታዳጊዎቻችንን ከመጽሐፍ እያራቃቸው ነው። አንዳንዱ የትውልዱ አካል ማንበብን እንደ ኋላ ቀርነት፣ ስክሪን ላይ ፈዞ መዋል ደግሞ እንደ "ፈታ ማለት " እያየው ነው።

2. በተለይም ከማህበራዊ ሚዲያዎች መካከል ቲክቶክ አእምሮን በቀላሉና ያለ ድካም በሚገኝ ደስታ እንዲለምድ እያደረገው ነው። ትምህርት ደግሞ ትዕግስት፣ ጥረትና ትኩረት ይጠይቃል። በዚህ ምክንያት ልጆቻችን መጽሐፍ ማንበብ " አሰልቺ "፣ ቲክቶክ ማየት ግን " አስደሳች " እየሆነባቸው ነው።

3. ጠንክሮ ሰርቶ፤ ተመራምሮ ፤ አጥንቶ ሀገርን መለወጥ ቀርቶ በስክሪን ፊት ቆሞ በመሰዳደብ፣ ለረጅም ሰዓት ቁጭ ብሎ በማውራት ፣ የቤተሰብን የግልን የሰዎችን ገመና አደባባይ በማስጣት ፣ ሲበሉ ሲጠጡ ሲዞሩ በመዋል ፣ በመጨፈር ወይም ሰውን በመሳደብ የሚገኝ " ቀላል ገንዘብ " የልጆቻችን ህልም ሆኗል። ይህ ለሀገር አደጋ ነው።

4. የኛ ማህበረሰብ የሚታወቅበት ጨዋነት፣ መከባበርና እሴት በ"ቪው" እና "ላይክ" እየተቸረቸረ ነው። ዝና ለማግኘት የማይደረግ ነውር የለም።

5. የነገ ሀገር ተረካቢ ልጆቻችን በዲጂታል ሱስ አእምሯቸው እየታወረ ነው።

6. ልጆቻችን ስልክ ውስጥ ጠፍተዋል። ከቤት ሳይወጡ ግን ከእኛ ርቀዋል። ቲክቶክ የልጆቻችንን ስነ-ልቦና እና የትምህርት ፍላጎት እየገደለ ነው። የወደፊት ተስፋቸው በ60 ሰከንድ ቪዲዮ እየተቀበረ ነው።

7. ልጆቻችን " ለመክበር፣ ገንዘብ ለማግኘት ፣ ለመታወቅ፣ ጥሩ ህይወት ለመኖር ምንም መማር አያስፈልግም " የሚል የተሳሳተ መልዕክት እየተጋቱ ነው። ሳይማሩና ሳይለፉ በቲክቶክ ብቻ ገንዘብና ዝና ያገኙ ሰዎችን እንደ አርአያ (Role Model) ማየት ጀምረዋል።

8. መጽሐፍ ገልጦ ለማንበብ የሚሰለቻቸው ልጆች ለሰዓታት ስክሪን ላይ አይናቸው ሳይዝል መቆየት ይችላሉ። ይህ በትምህርታቸው ላይ ትልቅ ቀውስ እየፈጠረ ነው።

9. ልጆቻችን ስልክ ሲነኩባቸው የሚቆጡ፣ ስልክ ሲቀሙ የሚበሳጩና በትንሽ ነገር የሚጨቃጨቁ እየሆኑብን ነው።

10. ልጆቻችን የወላጆችን ጨዋነትና ስነ-ምግባር ሳይሆን የማህበራዊ ሚዲያ ዝነኞችን ጩኸትና ነውር ፣ ስድብ ፣ ጋጠወጥነት እንደ ስልጣኔ እየቆጠሩት ነው።

ወላጆች ሆይ ! ይህ እንዲሁ በቀላሉ የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም። ሁላችሁም በየቤታችሁ ተነጋገሩበት።

ግን ከምንም ነገር በፊት እኛ ወላጆች የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማችን እንዴት ነው ? ይህን ከመለስን በኋላ፦
- በየቤታችን ልጆች እንዴት እያደጉ ነው ?
- ትምህርታቸው እንዴት ነው ? ምን አይነት ችግር እያያችሁ ነው ?
- ለችግሮቹ ምን አይነት መፍትሄ እየወሰዳችሁ ነው ?


ስሜታችሁን በDM / @tikvahethiopiaBOT አጋሩ።

በፌስቡክ ኮሜንት https://www.facebook.com/61588053582297/posts/122104023063268452/?app=fbl

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia
🕊21
‎ስኬታማ የሆነች ተማሪያችን

‌‎ሰላም እንዴት ቆያችሁ የገጻችን ተከታዮች?
‎በዛሬው ፅሁፌ ላስተዋውቃችሁ የምፈልገው የቀድሞ የትምህርት ቤታችን ተማሪ የሆነችውን #ቤተልሔም_ተሻለን ይሆናል፡፡

‎ትምህርቷን ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል የተከታተለችው በዲላ ዶንቦስኮ ትምህርት ቤቶች ነው፡፡

የዛሬ 8 ዓመት በ2010 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በመፈተን አጥጋቢ ውጤት በማስመዝገብ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን በ2011 ዓ.ም ተቀላቅላለች።

‎በ2014 ዓ.ም ከአንጋፉው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በጋዜጠኝነት እና ተግባቦት በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀች ሲሆን በመቀጠል ከዚሁ ዩኒቨርስቲ በፒአር ስትራቴጂ ኮምዩኒኬሽን በማስተርስ ዲግሪ ተመርቃለች።

‎በአሁን ሰዓት በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ በቲቪ ሪፖርተርነት እያገለገለች ትገኛለች።

‎በት/ቤታችን ቆይታዎ በትምህርቷም ይሁን በስነ ምግቧሯ ምስጉን ተማሪ ነበረች።
‎በተለያዩ የመድረክ እና ሚኒሚዲያ ክበባት የነቃ ተሳትፎ የነበራት ሲሆን በ2010 ዓ.ም በት/ቤታችን የ12ኛ ክፍል የሰራተኞች ቀን በሚከበርበት ወቅት እንደ ጋዜጠኛ በሙሉ ዲሲፕሊን እና የስራ ትጋት ስታገለግል ነበር።

‎አሁን ለደረሰችበት ቦታ የዲላ ዶን ቦስኮ ት/ቤቶች አስተዳደሩ፣ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች ትልቅ እገዛ እንዳደረጉላት ትገልፃለች።

‎እኛም መልካሙን ሁሉ እንመኝልሻለን። ኮርተንብሻል በርቺ።

‎የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል

‎ለተጨማሪ መረጃ የትምህርት ቤታችንን የማህበራዊ ድህረ ገፆች ይጠቀሙ:

#ፌስቡክ:
https://m.facebook.com/groups/715959666071910/?ref=share&mibextid=NSMWBT

#ዩቱብ:
https://www.youtube.com/@DBICTC

14🕊2🏆2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
From the archives – 2015 E.C

Mr. Mikyas, Manager of Camara Education Ethiopia, delivering an inspiring Good Morning speech to our students.
2
‎የ2018 ዓ.ም የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛደረጃት/ቤት የእግርኳስ ውድድር ፍፃሜውን አገኘ።

‎ዲላ፣ መጋቢት 3፣ 2018 ዓ.ም  (ዶን ቦስኮ ኢ.ቴ.ማ)

‎ግማሽ ዓመት በላይ ተመልካችን እያዝናና ሲደረግ የነበረው የዶንቦስኮ ቶርናመንት በዛሬው እለት በዶንቦስኮ ሜዳ ፍፃሜውን ማግኘት ችሏል፡፡

‎በመሆኑም ለፍፃሜ ደርሰው የነበሩት ሁለቱ ቡድኖች ማለትም 12 social እና 10ኛ ክፍል የዋንጫ ጨዋታቸውን ፉክክር በተሞላበት መንገድ ያደረጉ ሲሆን፤ ጨዋታውን አስረኞች 4 ለ 3 በማሸነፍ የዋንጫው ባለቤት መሆን ችለዋል፡፡

‎ የዶንቦስኮ ቶርናመንት በየዓመቱ የተለያዩ ስፖርቶችን በማካተት ተማሪዎች ከትምህርታቸው ባሻገር በእረፍት ሰዓታቸው ስፖርታዊ ውድድሮችን እያደረጉ ራሳቸውን እንዲያዝናኑ እድል ይፈጥራል፡፡

‎ በዚህም ውድድር ብዙ ተማሪዎች በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች ማለትም በቅርጫት ኳስ፣ በመረብና በእግር ኳስ እንደየ ችሎታቸውና ፍላጎታቸው ሚሳተፉ ይሆናል፡፡

‎ ይህ ዲፓርትመንት በመ/ር ታጋይ ወጋሶ ዋና መሪነት እና በስፖርቱ ኮሚቴዎች አማካኝነት ብዙ ስራዎች እየተሰሩበት ይገኛል፡፡ ለቀጣዩም ዓመት ከዚ በተሻለ ሁኔታ ቶርናመንቱ እንደሚቀጥል የዲፓርትመንቱ ሀላፊ መ/ር ታጋይ ገልፆዋል፡፡

‎ በዚሁ አጋጣሚ አሸናፊ ቡድኖች እንኳን ደስ አላቹ 🏆🏆🏆 ፡፡

‎ዘገባ: ተማሪ አብዱረህማን ሙሳ
‎ካሜራ: መ/ር ይሁን አጃሎ
🏆156