Dilla Don Bosco Catholic Secondary School
1.67K subscribers
2.01K photos
29 videos
20 files
273 links
Download Telegram
‎በ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼትቭ ፕሮግራም ስልጠና ላጠናቀቁ የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች የሰርተፍኬት መስጫ ፕሮግራም ተዘጋጀ።

‎ዲላ፣ ታህሳስ 18፣ 2018 ዓ.ም  (ዶን ቦስኮ ኢ.ቴ.ማ) የ2018 ዓ.ም 11ኛ ክፍል ለሆኑ 66 ወንዶች  እና 54 ሴቶች በድምሩ  120   ተማሪዎች ተጋባዥ እንግዶች ባሉበት በዛሬው እለት የሰርተፍኬት የመስጠት ስነ ስርዓት ተዘጋጅቷል።

‎መድረኩን በንግግር የከፈቱት የዲላ ከተማ አስተዳደር  የኢኑቬሽን እና ቴከኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ፀሐይ ቦጋለ ሲሆኑ በመቀጠል የጌዴኦ ዞን ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደረጀ ሾንጣ ስለ ስልጠናው አስፈላጊነት እና ስለ ፉይዳ መታወቂያ ገለፃ ሰጥተዋል።

‎በቦስኮ ኮዲንግ አባላት የተዘጋጀ ስለ#ደራሮ ሰፊ ገለፃ የሚሰጥ ድረ ገፅ የቀረበ ሲሆን በ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ስለ አርቴፍሻል ኢንተለጀንስ ምንነት፣ አይነቶች እና በየትኛው ዘርፉች ላይ እንደምንጠቀምበት ፕረዘንቴሽን አቅርበዋል።


‎በተጋባዥ እንግዶች ሰርተፍኬት ለሰልጣኞች የተሰጠ ሲሆን አቶ እውዩ ሀይሉ የዲላ ከተማ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የመዝጊያ ንግግር አድርገዋል። እንግዶች ከተማሪዎች ጋር የማስታወሻ ፍቶ በመነሳት የፕሮግራሙ ፍፃሜ ሆንዋል።



‎በት/ቤቱ ከ2017 ዓ.ም ጥቅምት ወር ጀምሮ እስከ ታህሳስ 2018 ዓ.ም

👨‍🎓 ወንዶች: 173
👩‍🎓 ሴቶች: 159
👥 አጠቃላይl: 332 ተማሪዎች

‎ስልጠናውን አጠናቀው የሰርተፍኬት ባለቤት ሆነዋል።

‎የዲላ ዶን ቦስኮ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል
14💯2
የቴክኖሎጂው ዓለም መነጋገሪያ ስለሆነው Quantum Computer ብዙ እንሰማለን። ግን ከእጃችን ላይ ካለው ስልክ ወይም ላፕቶፕ በምን ይለያል?

1️⃣ Classical Computing (መደበኛ ኮምፒውተር)

ይህ አሁን እኔ እና እናንተ የምንጠቀምበት ቴክኖሎጂ ነው። ስልኮቻችን፣ ላፕቶፖቻችን እና ሰርቨሮች በሙሉ በዚህ ውስጥ ይመደባሉ።

📌 መረጃን የሚያነበው "Bits" በሚባሉ ትናንሽ ክፍሎች (በ 0 እና 1) አማካኝነት ነው። ልክ እንደ መብራት ማብሪያ ማጥፊያ፣ ወይ በርቷል (1) አለበለዚያ ጠፍቷል (0) ብሎ ነው የሚሰራው።

2️⃣ Quantum Computing (ኳንተም ኮምፒውተር)

ይህ እጅግ ኃይለኛ እና የረቀቀ የፊዚክስ ህግን (Quantum Mechanics) የሚጠቀም የወደፊቱ ኮምፒውተር ነው ።

📌 የሚጠቀመው "Qubits" ነው። ይህ ማለት መረጃው በአንዴ 0ም 1ም፣ ወይም ሁለቱም ሆኖ መገኘት ይችላል። (ልክ እየተሽከረከረ እንዳለ ሳንቲም ማለት ነው!)

ልዩነታቸው በምሳሌ ሲታይ...

አንድ ቤተ-መጽሐፍት ውስጥ አንድ የተደበቀ መጽሐፍ መፈለግ ቢኖርባችሁ፡-

📌 Classical Computer ፦ እያንዳንዱን መደርደሪያ ከላይ እስከ ታች አንድ በአንድ እየዞረ ይፈልጋል። (ይሄ ብዙ ሰዓት ይፈጃል)

📌 Quantum Computer ፦ ቤተ-መጽሐፍቱን በአንዴ ስካን (Scan) አድርጎ መጽሐፉ የት እንዳለ ይጠቁማል። (ይሄ በሰከንዶች ያልቃል!)

ለምን ይጠቅመናል ?

📌 መደበኛ ኮምፒውተሮች 10,000 ዓመት የሚፈጅባቸውን ውስብስብ ስራ፣ ኳንተም ኮምፒውተሮች በደቂቃዎች ውስጥ መስራት ስለሚችሉ ነው!

📌 በህክምና (Medicine) ፦ አዳዲስ መድኃኒቶችን ለመቀመምና የቫይረሶችን ባህሪ ለማጥናት፣ መደበኛ ኮምፒውተሮች ዓመታት የሚፈጅባቸውን ስራ ይህ ኮምፒውተር በደቂቃዎች ይሰራልናል ።

📌ሳይበር ሴኩሪቲ (Cybersecurity) ፦ አሁን ያለንበትን የይለፍ ቃል (Password) አሰራር በሙሉ እንድናሻሽል ያስገድደናል፤ ምክንያቱም Quantum ኮምፒውተሮች ማንኛውንም ፓስወርድ የመስበር አቅም ይኖራቸዋል!

📌 ባትሪ እና ኢነርጂ፦ ለኤሌክትሪክ መኪኖች (EV) የሚሆኑ እጅግ ዘመናዊ እና ረጅም ጊዜ የሚቆዩ ባትሪዎችን ለመፍጠር የሚደረገውን ምርምር ያፋጥናል።

📌 የአየር ንብረት ፦ የአየር ንብረት ለውጥን በከፍተኛ ጥራት (Precision) ለመተንበይ ያስችላል ።

እንዲሁም ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጥቅም አለው !
5
The best month of the year started for the Salesians of the heart ❤️
January gives us the joy of remembering and celebrating Don Bosco, father, teacher and friend of young people. A month to return to the origin, renew hope and reaffirm that educating is an act of love and faith. 😃
Because Don Bosco lives, and his charisma continues to beat in every Salesian heart.
5🏆1
የ2018 ዓ.ም 8ኛ ዙር የህፃናት ኮዲንግ ስልጠና በምስል
5👌3
Don Bosco-Dilla

Fr. Ignacio, the Provincial of AET, paid a visit to Don Bosco Dilla and addressed the students during the Good Morning talk.
1