ማስታወቂያ
ለት/ቤታችን መምህራን እና ተማሪዎች
መደበኛ የመማር ማስተማር ስራ ነገ እሮብ ህዳር 24/2818 ዓ.ም የሚኖር መሆኑን እየገለፅን ለትምህርት አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ በተለመደው ሰዓት ት/ቤት እንድትገኙ እንገልፃለን።
የት/ቤቱ አስተዳደር

😐16👌7🕊5🤝2❤1
Forwarded from DON BOSCO ICT CENTER
List of Our School Telegram Channels👇
❤1🙏1
ዜና እረፍት
የቀድሞ የትምህርት ቤታችን ተማሪ የነበረው #ያብስራ_ጌትነት በድንገተኛ የመኪና አደጋ ከዚህ አለም በሞት ተለይቶናል።
ፈጣሪ ነፍሱን ይማርልን ለቤተሰቦቹ እና ጓደኞቹ መፅናናትን እንመኛለን።

🕊88🙏33👌1
Forwarded from Ministry of Education Ethiopia
የምስራቅና የመካከለኛ ሀገራት የፖን አፍሪካ የተማሪዎች እግር ኳስ ውድድር በዩጋንዳ ካምፖላ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል።
በኡጋንዳ አስተናጋጅነት የአፍሪካ የትምህርት ቤቶች እግር ኳስ ውድድር ላይ እየተሳተፈች የምትገኘው ሀገራችን ኢትዮጵያ ባካሄደችው ጨዋታ ከምድቧ ፍፁም የበላይነቷን አረጋግጣ በሁለቱም ጾታዎች ለዋንጫ አልፋለች ።
በውድድሩ በአጠቃላይ ከምድቧ 1ኛ ሆና ያለፈችው ኢትዮጵያ ዛሬ ማክሰኞ በሁለቱም ፆታዎች ለዋንጫ የምትጫወት ይሆናል።
ሀገራችን የወከሉ ታዳጊ ተማሪዎችም መልካም እድል እንዲሆንላቸው እንመኛለን።
ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
ዩቱዩብ- https://www.youtube.com/@ministry-of-education-ethiopia
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ

❤5🏆2
ማስታወቂያ
ለትምህርት ቤታችን ተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች፣
ከትምህርት ቢሮ በተላለፈልን መመሪያ መሰረት አጠቃላይ የተማሪዎቸን መረጃ በEducational Management Information System (EMIS) እንድናስገባ ተጠይቀናል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘጋጀውን የጎጉል ፎርም በጥንቃቄ ሞልታችሁ እስከ ሰኞ ታህሳስ 6/2018 ዓ.ም ብቻ ገቢ እንድታደርጉ እንገልፃለን፡፡
የትምህርት ቤቱ አስተዳደር
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScUpVbndTyKfaY0xPdzLw6byNnZZBzZEVsM5vE2spjIqg6j3A/viewform?usp=header

Google Docs
Dilla Don Bosco Catholic Secondary School Student Information Collection Form
Dear Parent/Guardian, this form is used for Educational Management Information System (EMIS) for managing educational data and resources in Ethiopia.
Please fill in this form carefully with accurate information about your child.
Fields marked with * are…

❤5💯1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በ2017 ዓ.ም 6ኛው ዙር የህፃናት ኮዲንግ ሰልጣኝ የነበሩ ተማሪዎች የሰሩት #የኢትዮጵያ_ባህላዊ_ሙዚቃ_መሳሪያን ለተማሪዎች የሚያስተዋውቅ አፕሊኬሽን አሰራር በኢትቪ የልጆች አለም ቲቪ ቻናል #ተማሪ_የማሪያም አቅርባለች። ሙሉውን ቃለ መጠይቅ ተጋበዙልን።
ስራውን በቡድን የሰሩት
1. ተማሪ ቃልኪዳን አማረ
2. ተማሪ የማሪያም ም/ፀሐይ
3. ተማሪ ኤልዳና ጌትነት
4. ተማሪ ዳግማዊ አማረ ናቸው
ስራውን በቡድን የሰሩት
1. ተማሪ ቃልኪዳን አማረ
2. ተማሪ የማሪያም ም/ፀሐይ
3. ተማሪ ኤልዳና ጌትነት
4. ተማሪ ዳግማዊ አማረ ናቸው
👌13❤4🏆1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#የመምህር_ዱባለ_ቱሉ እና ተማሪዎቹ የልፉት ውጤት በኢትቪ የልጆች አለም ቻናል ቀርቧል ክፍል አንድን ተጋበዙልን።
ዲላ ዶን ቦስኮ መ/ኢ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
ዲላ ዶን ቦስኮ መ/ኢ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
❤6👌3👍2
የዲላ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ ኃላፊ ለተማሪዎች መልዕክት አስተላለፉ።
ዲላ፣ ታህሳስ 16፣ 2018 ዓ.ም (ዶን ቦስኮ ኢ.ቴ.ማ)
የዲላ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ ኃላፊ የሆኑት #አቶ_ዮሴፍ_ሆርዶፉ በዛሬው እለት በት/ቤታችን በመገኘት ለተማሪዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።
ተማሪዎች በስነ ምግባር እና በእውቀት የተሻሉ እንዲሆኑ ጠንክረው መስራት ፤መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞችን ማክበር እንዳለባቸው ገልፀዋል።
ት/ቤቱ በከተማው ካሉ ት/ቤቶች በየአመቱ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የተሻለ ውጤት የሚመዘገብበት መሆኑን ጠቅሰዋል።
በ2018 ዓ.ም የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ ተማሪዎች ጊዜያቸውን በመጠቀም ጠንክረው እንዲሰሩ መክረዋል።
በት/ቤቱ ለሚመዘገበው ውጤት የት/ቤቱን አስተዳደር መምህራን ወላጆች እና ተማሪዎች ከልብ አመስግነዋል።
የዲላ ዶን ቦስኮ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል

❤9🤝2
በዚህ ዓመት በሁሉም ት/ቤቶች እየተተገበረ የሚገኘው የትምህርት የመረጃ አስተዳደር ሥርዓት (EMIS) ምንድን ነው?
EMIS (Education Management Information System) ማለት የትምህርት መረጃ አስተዳደር ሥርዓት ማለት ነው። ይህ ሥርዓት ትምህርት ሚኒስቴር የሚያስተዳድረው ሲሆን የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል፦
👉 ከተማሪዎች፣ ከመምህራን እና ከትምህርት ቤቶች መረጃዎችን ይሰበስባል።
👉 የትምህርት ጥራትን እና ተደራሽነትን ለመገምገም ይረዳል።
👉ለመንግስት የፖሊሲ ውሳኔዎች ትክክለኛ መረጃ ያቀርባል።
የEMIS ዋና ዋና ክፍሎች👇
💊የተማሪዎች መረጃ፡ ምዝገባ፣ ውጤት እና የተማሪዎች ዝውውር።
💊የመምህራን መረጃ፡ የትምህርት ደረጃ፣ የሥራ ልምድ እና ስርጭት ወዘተ።
💊የመሠረተ-ልማት መረጃ፡- የክፍሎች ብዛት፣ ላብራቶሪዎች እና የመጽሐፍት አቅርቦት ወዘተ ያካትታል ።
💊የፋይናንስ መረጃ፡ ለትምህርት ቤቶች የሚመደብ በጀት እና ወጪ ወዘተ ያካትታል።
@ሥርዓቱ እንዴትይሠራል?
መረጃዎች ከየመዋቅሩ (ከትምህርት ቤት እስከ ሚኒስቴር) ይሰበሰባሉ፣ ይተነተናሉ፣ ከዚያም ለሪፖርት ዝግጁ ይሆናሉ።
👉ስለ EMIS (የትምህርት መረጃ አስተዳደር ሥርዓት) ሶፍትዌር አጠቃቀም እና የመረጃ አያያዝ ሂደት ዋና ዋና ነጥቦች:
1. መረጃ ማስገባት (Data Entry)
#ተማሪዎች፦ በየዓመቱ አዳዲስ ተማሪዎችን መመዝገብ እና ነባር ተማሪዎችን ወደ ቀጣይ ክፍል ማሸጋገር።
#መምህራን፦ አዳዲስ ተቀጣሪዎችን መመዝገብ እና ስልጠና ወይም የደረጃ እድገት ሲያገኙ መረጃቸውን ማሻሻል።
@#ትምህርት_ቤቶች፦ የግንባታ ሁኔታን እና የሚገኙ ቁሳቁሶችን (ጠረጴዛ፣ መጽሐፍ) መመዝገብ።
2. የመረጃ ጥራት (Data Quality)
መረጃው ትክክለኛ እንዲሆን የሚከተሉትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፦
💉መረጃዎችን በወቅቱ ማስገባት፣
💉የተደገሙ መረጃዎች (Duplicates) አለመኖራቸውን ማረጋገጥ፣
💉ቁጥሮች እና ስሞች ከትክክለኛው ሰነድ ጋር መመሳሰላቸውን ማየት፣
3. ሪፖርት ማውጣት (Reporting)
ሥርዓቱ መረጃዎችን በሰንጠረዥ እና በግራፍ መልክ ያቀርባል። ይህም ትምህርት ቤቱ ምን እንደጎደለው እና ምን መሻሻል እንዳለበት ለማወቅ ይረዳል።
👉መረጃን እንዴት መሙላት እና ሪፖርት ማዘጋጀት እንደሚቻል በዝርዝር እንመልከት👇
3.1 መረጃ እንዴት ይሞላል? (Data Entry Process)
👉 የመረጃ ቅጾች (Forms): በመጀመሪያ መረጃው በወረቀት ቅጾች ላይ ይሰበሰባል። እነዚህ ቅጾች የተማሪ፣ የመምህር እና የትምህርት ቤት መረጃዎችን ለይተው የያዙ ናቸው።
👉 ወደ ሲስተም ማስገባት: የተሰበሰበው መረጃ በ EMIS ሶፍትዌር ውስጥ በየዘርፉ ይገባል። እያንዳንዱ ተማሪ ወይም መምህር መለያ ቁጥር (ID) ሊኖረው ይገባል።
👉 ማረጋገጥ (Validation): መረጃው ከገባ በኋላ ስህተቶች ካሉ ይታረማሉ። ለምሳሌ፣ የተማሪ ዕድሜ ከክፍል ደረጃው ጋር መጣጣሙ ይረጋገጣል።
3.2 የሪፖርት አዘገጃጀት (Reporting)
✍️ ማጠቃለያ (Aggregation): ሲስተሙ የግል መረጃዎችን በመሰብሰብ ወደ አሃዛዊ መረጃ ይቀይራቸዋል።
✍️ ቁልፍ አመልካቾች (KPIs): እንደ የተማሪ-መምህር ጥምርታ፣ የሴት ተማሪዎች ተሳትፎ እና የትምህርት ማቋረጥ መጠን ያሉ ሪፖርቶች ይዘጋጃሉ።
✍️ ውሳኔ መስጠት: ሪፖርቶቹ ለትምህርት ባለድርሻ አካላት ይላካሉ። ይህም #መጽሐፍት ወይም #መምህራን በብዛት ወደሚያስፈልጋቸው ትምህርት ቤቶች ለማሰራጨትና ለመመደብ ይረዳል።
ሌሎች ግንዛቤ እንዲኖራቸው #Share ይደረግ❗️

❤9👍1👌1
የቴሌግራም አካውንትዎ በመረጃ መንታፊዎች እጅ ከገባ ወይም ሌላ ሰው እየተጠቀመበት እንደሆነ ከጠረጠሩ ምን ያደርጋሉ?
በኢትዮጵያ የቴሌግራም አካውንት መጠለፍ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስፋት እየተለመደ የመጣ የሳይበር ጥቃት ነው። ብዙዎች የሚያጋጥማቸው መጠለፍ በቴክኒክ ብቃት ሳይሆን በሰዎች የጥንቃቄ ጉድለት የሚፈጠር ነው።
የቴሌግራም አካውንትዎ በመረጃ መንታፊዎች (Hackers) እጅ ከገባ ወይም ሌላ ሰው እየተጠቀመበት እንደሆነ ከጠረጠሩ፣ በፍጥነት የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ ይኖርብዎታል፡-
1. ሌሎች መሣሪያዎችን ማቋረጥ (Terminate Sessions)
ይህ በጣም አስፈላጊው እርምጃ ነው። መንታፊው የከፈተውን ግንኙነት ለመዝጋት፦
• ወደ Settings ይግቡ።
• Devices (ወይም በአንዳንድ ስልኮች Privacy and Security > Active Sessions) የሚለውን ይጫኑ።
• ከእርስዎ ስልክ ውጭ ያሉትን ሁሉንም መሣሪያዎች "Terminate all other sessions" በማለት ያስወግዱ።
2. ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (Two-Step Verification) ማብራት
መንታፊው ተመልሶ እንዳይገባ ፓስዎርድ ማዘጋጀት አለብዎት፦
Settings > Privacy and Security > Two-Step Verification ውስጥ ይግቡ።
ጠንካራ ፓስዎርድ እና የማገገሚያ ኢ-ሜይል (Recovery Email) ያስገቡ።
ማሳሰቢያ፦ መንታፊው ቀድሞ ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫን ካበራው፣ አካውንቱን "Reset" ለማድረግ 7 ቀን ሊጠብቁ ይችላሉ።
3. የስልክ ቁጥርዎን ደህንነት ማረጋገጥ
ቴሌግራም የሚላከው የማረጋገጫ ኮድ (SMS) በመንታፊው እጅ እንዳይገባ፦
የሲም ካርድዎ ኮፒ መውጣቱን ወይም ስልክዎ መጠለፉን ያረጋግጡ።
ለቴሌግራም የሚላኩ የኤስኤምኤስ (SMS) ኮዶችን ለማንም በፍጹም አያጋሩ።
4. በቀጥታ ከቴሌግራም ድርጅት በ(support@telegram.org) ወይም @SMStelegram_bot (https://t.me/SMStelegram_bot) ድጋፍን ያግኙ። እርዳታ ሲጠይቁ የእርስዎን ቴሌግራም ቁጥርዎንና መታወቂያዎን ያካትቱ።
5. አካውንቱን ማጥፋት (እንደ የመጨረሻ አማራጭ)
አካውንቱን መቆጣጠር ሙሉ በሙሉ ካቃተዎት እና ጠቃሚ መረጃዎች ካሉበት፣ አካውንቱን ማጥፋት (Delete) ማድረግ ሊኖርብዎት ይችላል።

❤6👌1
በ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼትቭ ፕሮግራም ስልጠና ላጠናቀቁ የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች የሰርተፍኬት መስጫ ፕሮግራም ተዘጋጀ።
ዲላ፣ ታህሳስ 18፣ 2018 ዓ.ም (ዶን ቦስኮ ኢ.ቴ.ማ) የ2018 ዓ.ም 11ኛ ክፍል ለሆኑ 66 ወንዶች እና 54 ሴቶች በድምሩ 120 ተማሪዎች ተጋባዥ እንግዶች ባሉበት በዛሬው እለት የሰርተፍኬት የመስጠት ስነ ስርዓት ተዘጋጅቷል።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የዲላ ከተማ አስተዳደር የኢኑቬሽን እና ቴከኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ፀሐይ ቦጋለ ሲሆኑ በመቀጠል የጌዴኦ ዞን ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደረጀ ሾንጣ ስለ ስልጠናው አስፈላጊነት እና ስለ ፉይዳ መታወቂያ ገለፃ ሰጥተዋል።
በቦስኮ ኮዲንግ አባላት የተዘጋጀ ስለ#ደራሮ ሰፊ ገለፃ የሚሰጥ ድረ ገፅ የቀረበ ሲሆን በ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ስለ አርቴፍሻል ኢንተለጀንስ ምንነት፣ አይነቶች እና በየትኛው ዘርፉች ላይ እንደምንጠቀምበት ፕረዘንቴሽን አቅርበዋል።
በተጋባዥ እንግዶች ሰርተፍኬት ለሰልጣኞች የተሰጠ ሲሆን አቶ እውዩ ሀይሉ የዲላ ከተማ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የመዝጊያ ንግግር አድርገዋል። እንግዶች ከተማሪዎች ጋር የማስታወሻ ፍቶ በመነሳት የፕሮግራሙ ፍፃሜ ሆንዋል።
በት/ቤቱ ከ2017 ዓ.ም ጥቅምት ወር ጀምሮ እስከ ታህሳስ 2018 ዓ.ም
👨🎓 ወንዶች: 173
👩🎓 ሴቶች: 159
👥 አጠቃላይl: 332 ተማሪዎች
ስልጠናውን አጠናቀው የሰርተፍኬት ባለቤት ሆነዋል።

❤14💯2