Dilla Don Bosco Catholic Secondary School
1.66K subscribers
2.02K photos
29 videos
20 files
276 links
Download Telegram
‎የ2018 ዓ.ም 8ኛው ዙር የኮዲንግ ስልጠና ተጀመረ

‎ዲላ፣ ህዳር 13፣ 2018 ዓ.ም  (ዶን ቦስኮ ኢ.ቴ.ማ)
‎ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 7ዙሮች ከ300 በላይ ተማሪዎችን ያሰለጠነው የቦስኮ ኮዲንግ አካዳሚ በዛሬው እለት 8ኛ ዙር ስልጠናውን በይፉ ጀምሯል።

‎በስልጠናው ለመሳተፍ 60 ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን በተለያዩ የግል ፕሮግራም ያልተገኙ ተማሪዎች እንዳሉ ሆነው በዛሬው እለት 37 ተማሪዎች ስልጠናውን ለመከታተል በማዕከሉ ተገኝተዋል።

‎ስልጠናው አምስት ወራትን የሚወስድ ሲሆን ዘወትር ቅዳሜ ጠዋት ከ2:30-5:30 ይሰጣል።

‎በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር በሁለት የኮምፒውተር ማዕከላት አምስት ኮርሱች ተካተዋል ስልጠናው ይሰጣል።


‎በዚህ ዙር በተለየ ሁኔታ 18 ሰልጣኞች በአማኑኤል ቤተክርስቲያን ዲላ አጥቢያ ድጋፍ ሰጭነት ስልጠናውን እንዲከታተሉ ተደርጓል። በዚህም ቤተክርስቲያኒቱ ተማሪዎች የዘመኑን ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆኑ ፈጣሪ እንዲሆኑ ለምታደርገው ጥረት ምስጋና ሊቸራት ይገባል።

‎ከስልጠናው ጎን ለጎን ለሰልጣኞች በቂ ግንዛቤ በመስጠት የ5ሚሊዮን ኮደርስ የኦንላይን ስልጠና እንዲወስዱ ይደረጋል።

‎የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል።
6👍1👌1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ኢቲቪ የልጆች አለም ቻናል በዲላ ዶን ቦስኮ ት/ቤቶች ያደረገው ቆይታ። ቅዳሜ ከ8:00 ጀምሮ ይተላለፉል።
👌42😐2
#ከ# 1.7 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የ 5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ስልጠናን በማጠናቀቅ የምስክር ወረቀት ወስደዋል፡፡

እርስዎም ስልጠናውን በነጻ በመውሰድ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርትፍኬት ይቀበሉ።

የስልጠና ዘርፎች፦

🌐 ዌብ ፕሮግራሚንግ
🤖 አንድሮይድ ማበልፀግ
📊 ዳታ ሳይንስ
🧠 አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ

ይመዝገቡ 👇
https://www.ethiocoders.et/

በ 8 ሳምንታት ውስጥ ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ፥ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ያገኛሉ።
3👌1
‎ማስታወቂያ

‎ለት/ቤታችን መምህራን እና ተማሪዎች

‎መደበኛ የመማር ማስተማር ስራ ነገ እሮብ ህዳር 24/2818 ዓ.ም የሚኖር መሆኑን እየገለፅን ለትምህርት አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ በተለመደው ሰዓት ት/ቤት እንድትገኙ እንገልፃለን።

‎የት/ቤቱ አስተዳደር
😐16👌7🕊5🤝21
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
50ኛ ዓመት ዶን ቦስኮ ሳሊዛውያን በኢትዮጵያ ዶክመንተሪ ቪዲዮ (ሁለተኛ ቤት ዲላ)
6👌1
‎ዜና እረፍት
‌‎የቀድሞ የትምህርት ቤታችን ተማሪ የነበረው #ያብስራ_ጌትነት በድንገተኛ የመኪና አደጋ ከዚህ አለም በሞት ተለይቶናል።

‌‎ፈጣሪ ነፍሱን ይማርልን ለቤተሰቦቹ እና ጓደኞቹ መፅናናትን እንመኛለን።

‎የት/ቤቱ አስተዳደር
🕊88🙏33👌1
የምስራቅና የመካከለኛ ሀገራት የፖን አፍሪካ የተማሪዎች እግር ኳስ ውድድር በዩጋንዳ ካምፖላ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል።
በኡጋንዳ አስተናጋጅነት የአፍሪካ የትምህርት ቤቶች እግር ኳስ ውድድር ላይ እየተሳተፈች የምትገኘው ሀገራችን ኢትዮጵያ ባካሄደችው ጨዋታ ከምድቧ ፍፁም የበላይነቷን አረጋግጣ በሁለቱም ጾታዎች ለዋንጫ አልፋለች ።

በውድድሩ በአጠቃላይ ከምድቧ 1ኛ ሆና ያለፈችው ኢትዮጵያ ዛሬ ማክሰኞ በሁለቱም ፆታዎች ለዋንጫ የምትጫወት ይሆናል።
ሀገራችን የወከሉ ታዳጊ ተማሪዎችም መልካም እድል እንዲሆንላቸው እንመኛለን።

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
ዩቱዩብ- https://www.youtube.com/@ministry-of-education-ethiopia
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ
5🏆2
ማስታወቂያ
ለትምህርት ቤታችን ተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች፣
ከትምህርት ቢሮ በተላለፈልን መመሪያ መሰረት አጠቃላይ የተማሪዎቸን መረጃ በEducational Management Information System (EMIS) እንድናስገባ ተጠይቀናል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘጋጀውን የጎጉል ፎርም በጥንቃቄ ሞልታችሁ እስከ ሰኞ ታህሳስ 6/2018 ዓ.ም ብቻ ገቢ እንድታደርጉ እንገልፃለን፡፡
የትምህርት ቤቱ አስተዳደር

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScUpVbndTyKfaY0xPdzLw6byNnZZBzZEVsM5vE2spjIqg6j3A/viewform?usp=header
5💯1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በ2017 ዓ.ም 6ኛው ዙር የህፃናት ኮዲንግ ሰልጣኝ የነበሩ ተማሪዎች የሰሩት #የኢትዮጵያ_ባህላዊ_ሙዚቃ_መሳሪያን ለተማሪዎች የሚያስተዋውቅ አፕሊኬሽን አሰራር በኢትቪ የልጆች አለም ቲቪ ቻናል #ተማሪ_የማሪያም አቅርባለች። ሙሉውን ቃለ መጠይቅ ተጋበዙልን።

ስራውን በቡድን የሰሩት

1. ተማሪ ቃልኪዳን አማረ
2. ተማሪ የማሪያም ም/ፀሐይ
3. ተማሪ ኤልዳና ጌትነት
4. ተማሪ ዳግማዊ አማረ ናቸው
👌134🏆1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#የመምህር_ዱባለ_ቱሉ እና ተማሪዎቹ የልፉት ውጤት በኢትቪ የልጆች አለም ቻናል ቀርቧል ክፍል አንድን ተጋበዙልን።
ዲላ ዶን ቦስኮ መ/ኢ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
6👌3👍2
‎የዲላ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ ኃላፊ ለተማሪዎች መልዕክት አስተላለፉ።

‎ዲላ፣ ታህሳስ 16፣ 2018 ዓ.ም  (ዶን ቦስኮ ኢ.ቴ.ማ)
‎የዲላ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ ኃላፊ የሆኑት #አቶ_ዮሴፍ_ሆርዶፉ በዛሬው እለት በት/ቤታችን በመገኘት ለተማሪዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።

‎ተማሪዎች በስነ ምግባር እና በእውቀት የተሻሉ እንዲሆኑ ጠንክረው መስራት ፤መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞችን ማክበር እንዳለባቸው ገልፀዋል።

‎ት/ቤቱ በከተማው ካሉ ት/ቤቶች በየአመቱ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የተሻለ ውጤት የሚመዘገብበት መሆኑን ጠቅሰዋል።

‎በ2018 ዓ.ም የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ ተማሪዎች ጊዜያቸውን በመጠቀም ጠንክረው እንዲሰሩ መክረዋል።

‎በት/ቤቱ ለሚመዘገበው ውጤት የት/ቤቱን አስተዳደር መምህራን ወላጆች እና ተማሪዎች ከልብ አመስግነዋል።


‎የዲላ ዶን ቦስኮ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል
9🤝2