Dilla Don Bosco Catholic Secondary School
1.67K subscribers
2.02K photos
29 videos
20 files
276 links
Download Telegram
‎የቦስኮ ኮዲንግ ክበብ አባላት የተሰጣቸውን የድረ ገፅ ግንባታ ፕሮጀክት ስራ በማጠናቀቃቸው የገንዘብ እና ሰርተፍኬት ሽልማት ተሰጣቸው።

‎ዲላ፣ ጠቅምት 20፣ 2018 ዓ.ም  (ዶን ቦስኮ ኢ.ቴ.ማ)
‎በት/ቤቱ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ የኮዲንግ ስልጠና የወሰዱ ተማሪዎችን እና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ እና ተጓዳኝ የትምህርት መስኮች ለማጥናት ፍላጎት ያላቸውን ለመደገፍ በማሰብ የተቋቋመው #ቦስኮ_ኮዲንግ ክበብ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

‎በክበቡ ውስጥ 30 አባላት የክፍል ደረጃቸው ከ9-12የሆኑ ተማሪዎች ይገኛሉ።

‎በ2017 ዓ.ም በድረ ገፅ ግንባታ በቡድን ሆነው እንዲሰለጥኑ በማድረግ አራት ፕሮጀክቶችን በአራት ቡድኖች እንዲሰሩ ተደርጓል።

‎በቡድን ጥሩ አፈፃፀም ያላቸው እና የተሰጣቸውን ፕሮጀክት ስራ በጥሩ ሁኔታ ለሰሩ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃ ላገኙ የክበቡ ቡድን አባላት በዛሬው እለት የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት እና አንደኛ ደረጃ ለወጣው ቡድን ሰርተፍኬት በተጨማሪነት ተሰጥቷል።

‎አስር ሺህ ብር ገንዘቡን ድጋፍ ለክበቡ ያደረገው የቀድሞ የትምህርት ቤታችን ተማሪ የነበረው #ነብዩ_ኤልያስ ነው።

‎ላደረገልን ድጋፍ በክበቡ አባላት ስም ከልብ አመሰግናለሁ።


‎የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል ።
8👌2👏1
‎ማስታወቂያ

‎ለኮዲንግ ስልጠና ፈላጊዎች

‎የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል ለ8ኛ ዙር የኮዲንግ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል።

▶️ የክፍል ደረጃ: ከ6ኛ እስከ 10 ኛ ክፍል
▶️ የምዝገባ ቀናት: ከሰኛ ጥቅምት 24 ጀምሮ
▶️ የምዝገባ ቦታ: በት/ቤቱ ኢኮቴ ማዕከል እና ኦንላይን
▶️ ስልጠናው የሚሰጠው: ዘወትር ቅዳሜ ጠዋት
▶️ ስልጠናው የሚወስደው ጊዜ :አምስት ወራት

‎ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ


‎ለበለጠ መረጃ: 0911984389
‎ቴሌግራም: @anduict
‎ኢሜል: andutsega@gmail.com

‎ስልጠናው ቅዳሜ ህዳር 6/2018 ዓ.ም ይጀምራል

‎የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል ።

‎በሚከተለው የጎጉል ፎርም በኦላይን መመዝገብ ይቻላል

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSez0eOwB7nMFVbuBmf59Olv4p5PnYxQgztdss3KRZibW0jyXw/viewform?usp=header
5🎉1👌1
ማስታወቂያ

‎ለ8ኛ ዙር የኮዲንግ ስልጠና የተመዘገባችሁ ተማሪዎች ከዚህ በፊት ቅዳሜ ሕዳር 6/2018 ዓ.ም ይጀምራል የተባለው ስልጠና በሚድ ተርም ፈተና ምክንያት ወደ ቅዳሜ ሕዳር 13/2018 ዓ.ም የተሸጋገረ መሆኑን እንገልፃለን።

‎እስከ አሁን ያልተመዘገባችሁ ተማሪዎች ውስን ቦታ ስላለ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

‎የዲላ ዶን ቦስኮ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል።

በኦንላይን ለመመዝገብ የጎጉል ፎርሙን ተጠቀሙ
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSez0eOwB7nMFVbuBmf59Olv4p5PnYxQgztdss3KRZibW0jyXw/viewform?usp=header
2👍1
‎የ2018 ዓ.ም የአንደኛ መንፈቅ አመት አንደኛ የሚድ ተርም እና የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ተጀመረ።

‌‎ዲላ፣ ህዳር 8፣ 2018 ዓ.ም (ዶን ቦስኮ ኢ.ቴ.ማ)

‎የት/ቤታችን የ2018 ዓ.ም ከ9-11ኛ ክፍል የሚድ ተርም እና የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና በዛሬው እለት ተጀምሯል።

‎በጠዋቱ መርሀ ግብር 10ኛ እና 12ኛ ክፍል እንዲሁም በከሰዓቱ መርሀ ግብር 9ኛ እና 11ኛ ክፍሎች ይፈተናሉ። የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ሲባል በ14 ክፍሎች እስከ 25 ተማሪዎች ብቻ ተደልድለው ይፈተናሉ።

‎ፈተናው ለ አምስት ቀናት ይሰጣል። በዘንድው አመት ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በ12 ክፍሎች 354 ወንዶች 362 ሴቶች በድምሩ 716 ተማሪዎች በት/ቤቱ ውስጥ ይማራሉ።

‎የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል

‎ለተጨማሪ መረጃ የትምህርት ቤታችንን የማህበራዊ ድህረ ገፆች ይጠቀሙ:

#ፌስቡክ:
https://m.facebook.com/groups/715959666071910/?ref=share&mibextid=NSMWBT

#ቴሌግራም:
https://t.me/dbict

#ዩቱብ:
https://www.youtube.com/@DBICTC

#ኢሜል:
‎donboscohsdilla@gmail.com

#ቴሌግራም_ቦት
@DonBHS_bot

#ዋትስ_አፕ
https://whatsapp.com/channel/0029Vaa2AUE6buMFIk04MO29
4👍4🤝41