Dilla Don Bosco Catholic Secondary School
1.67K subscribers
2.01K photos
29 videos
20 files
273 links
Download Telegram
የማጠናከሪያ ትምህር በዕቅድና በትኩረት እንዲመራ ትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ
-------------------- // --------------------

‎(ጥቅምት 09/2018 ዓ.ም) የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት አየለች እሸቴ ከክልልና ከከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በበይነ መረብ ውይይት ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት በአጠቃላይ ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ በተለይም ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርትን በዕቅድና በትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል።

የተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ መምህራን፣ የትምህርት ቤት አመራሮች፣ ወላጆች እንዲሁም የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተማሪዎች ጊዚያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ ከወዲሁ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው ክብርት ወ/ሮ አየለች አስገንዝበዋል።

‎የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በበኩላቸው የማጠናከሪያ ትምህርት ለተማሪዎች ውጤት መሻሻል ጠቀሜታው የላቀ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።


‎የትምህርት ፕሮግራሞች ጥራትና መሻሻል መሪ ስራ አስፈጻሚ ዩሀንስ ወጋሶ(ዶ/ር) የማጠናከሪያ ትምህርትን በተመለከተ መነሻ ስትራቴጂ እቅድ ያቀረቡ ሲሆን የተያዘው ግብ እንዲሳካ ከወዲሁ የዕቅድ ክትትልና ድጋፍ ሥራዎች ሊጠናከሩ ይገባል ብለዋል።


‎በበይነ-መረብ በተደረገው በዚሁ ውይይት ላይ የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችን ፣ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) እና ሌሎችም የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
3🤝1
‎Celebrating 50 Years of Salesian Presence

‎The Salesian Family in Ethiopia has proudly marked the Golden Jubilee of its presence in the country, celebrating 50 years of dedicated service to young people through education, evangelization, and social development.

10👍1
Forwarded from Tikvah-University
የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከ9-12ኛ ክፍል ይሸፍናል፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በተመለከት ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች እንዲሁም ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ትናንት ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም ደብዳቤ ልኳል፡፡

ቲክቫህ የደብዳቤውን ትክክለኛነት አረጋግጧል።

በሚኒስቴሩ የስርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ መሪ ሥራ አስፈጻማ ቴዎድሮስ ሽዋርገጥ (ዶ/ር) የተፈረመው ደብዳቤው፤ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከ9-12ኛ ክፍል እንደሚሸፍንና ተማሪዎች የተማሩትን ይዘቶች የሚፈተኑ መሆኑን ይገልጻል፡፡

ብሔራዊ ፈተናው ከ10ኛ እስከ 12ኛ ክፍሎች የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ይዘቶችን መሠረት ያደረገ እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡

በ2015 ዓ.ም የሙከራ ትምህርት ቤቶች 9ኛ ክፍልን በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት፤ ሌሎቹ ደግሞ በቀድሞው ስርዓተ ትምህርት የተማሩ በመሆኑ ፈተናው ከሁለቱ ስርዓተ ትምህርቶች የጋራ የሆኑ ይዘቶች ተጣጥሞ የሚወጣ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በአጠቃላይ ትምህርት ስርዓተ ትምህርት ሪፎርም መሠረት የሁለተኛ ደረጃ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በ2015 ዓ.ም የሙከራ ትግበራ በማካሔድ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሙሉ ትግበራ መገባቱ ይታወቃል፡፡

@tikvahuniversity
4
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#National_ID

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ላይ ለመቀመጥ ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ቅድመ ሁኔታ ተደረገ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት " ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ለፈተና ለመቀመጥ ቅድመ ሁኔታ ነው " ብሏል።

" ማንኛውም የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ከፈተና ምዝገባ ቀድሞ ማውጣትና በእጁ መያዝ ይገባዋል " ሲል አሳውቋል።

" ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) የሌለው ተማሪ ለፈተና መመዝገብ ሆነ በማንኛውም ሁኔታ መፈተን አይችልም " ሲል አስገንዝቧል።

ተማሪዎች የብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ይዘው እንዲገኙ ፦
- የተማሪ ቤተሰብ
- መምህራን
- የትምህርት አመራሮች
- የሚዲያ አካላት ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

#National_ID

@tikvahethiopia
4
የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ይዘቶች ይፋ ሆኑ፡፡

ተማሪዎች፣ የተማሪ ቤተሰቦች፣ መምህራንና የትምህርት አመራር ለፈተና ዝግጅት በሚያደርጉበት ወቅት ፈተና የሚሸፍናቸውን የይዘት አካባቢዎች ማወቅ አስፈላጊ መሆኑ ይታመናል። በመሆኑም የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ከፍል ፈተና ዝግጅትና አስተዳደር የሚከተሉትን ያካትታል፡፡

1.የትምህርት ዓይነቶችን በተመለከተ ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች እንግሊዘኛ፣ ሒሳብ፣ እስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዝክስና ባዮሎጂ እንዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች እንግሊዘኛ፣ ሒሳብ፣ እስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣ ታሪክ፣ ጂኦግራፊና ኢኮኖሚክስ ናቸው።
2.ፈተናው ከ9ኛ እስከ 12ኛ ከፍል ደረጃዎችን እና በተማሪው መጽሐፍ ላይ ያሉትን ሁሉንም ምዕራፎች ይሸፍናል፡፡
3.ከ10ኛ – 12ኛ ክፍል ሁሉም የትምህርት ዓይነት ፈተና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት እየተዘጋጀ ያለ ሲሆን የ9ኛ ክፍል ደግሞ የሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ፈተናዎች ከቀድሞውና ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርቶች የጋራ ይዘቶችን ብቻ አካቶ እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡
4.ፈተናው ማንኛውም ተፈታኝ ተማሪ ከተማረው ሥርዓተ ትምህርትና ከተማሪው መጽሐፍ ላይ ብቻ ተመስርቶ እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡
5.የፈተናው አስተዳደር በበይነ መረብና በወረቀት ጎን ለጎን የሚሰጥ ሲሆን አብዛኛው ተፈታኝ በበይነ መረብ እንዲፈተን እየተሠራ ያለ በመሆኑ ተፈታኞች እራሳቸውን በበይነ መረብ ለመፈተን ሊያዘጋጁ ይገባል፡፡

የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን በጋራ እንከላከል!

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

ስለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት የትምህርት ምዘናን ማህበራዊ ሚዲያዎችን ይከታተሉ፡፡
8🤝3👍1
‎የቦስኮ ኮዲንግ ክበብ አባላት የተሰጣቸውን የድረ ገፅ ግንባታ ፕሮጀክት ስራ በማጠናቀቃቸው የገንዘብ እና ሰርተፍኬት ሽልማት ተሰጣቸው።

‎ዲላ፣ ጠቅምት 20፣ 2018 ዓ.ም  (ዶን ቦስኮ ኢ.ቴ.ማ)
‎በት/ቤቱ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ የኮዲንግ ስልጠና የወሰዱ ተማሪዎችን እና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ እና ተጓዳኝ የትምህርት መስኮች ለማጥናት ፍላጎት ያላቸውን ለመደገፍ በማሰብ የተቋቋመው #ቦስኮ_ኮዲንግ ክበብ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

‎በክበቡ ውስጥ 30 አባላት የክፍል ደረጃቸው ከ9-12የሆኑ ተማሪዎች ይገኛሉ።

‎በ2017 ዓ.ም በድረ ገፅ ግንባታ በቡድን ሆነው እንዲሰለጥኑ በማድረግ አራት ፕሮጀክቶችን በአራት ቡድኖች እንዲሰሩ ተደርጓል።

‎በቡድን ጥሩ አፈፃፀም ያላቸው እና የተሰጣቸውን ፕሮጀክት ስራ በጥሩ ሁኔታ ለሰሩ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃ ላገኙ የክበቡ ቡድን አባላት በዛሬው እለት የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት እና አንደኛ ደረጃ ለወጣው ቡድን ሰርተፍኬት በተጨማሪነት ተሰጥቷል።

‎አስር ሺህ ብር ገንዘቡን ድጋፍ ለክበቡ ያደረገው የቀድሞ የትምህርት ቤታችን ተማሪ የነበረው #ነብዩ_ኤልያስ ነው።

‎ላደረገልን ድጋፍ በክበቡ አባላት ስም ከልብ አመሰግናለሁ።


‎የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል ።
8👌2👏1