Dilla Don Bosco Catholic Secondary School
1.67K subscribers
2.01K photos
29 videos
20 files
273 links
Download Telegram
‎በ2017 ዓ.ም 7ኛ ዙር የክረምት የኮዲንግ ስልጠና ለሰለጠኑ ተማሪዎች የምረቃ ሰነ ስርዓት ተዘጋጀላቸው።


‎ዲላ፣ መስከረም 24፣ 2018 ዓ.ም
(ዶን ቦስኮ ኢ.ቴ.ማ)

‎በ2017 ዓ.ም ክረምት ወራት የክፍል ደረጃቸው ከ6ኛ እስከ 9ኛ የሆኑ 40 ተማሪዎች መሰረታዊ የኮዲንግ ስልጠና ለ6 ሳምንታት መከታተላቸው ይታወሳል።

‎በዛሬው እለት የተማሪዎች ወላጆች እና ተማሪዎች በተገኙበት የምረቃ ስነ ስርዓት ተዘጋጅቷል።

‎ዝግጅቱ በፀሎት የተጀመረ ሲሆን በመቀጠል ላለፉት አራት አመታት በ7ዙር የኮዲንግ ስልጠናውን የሚዳስስ ዘጋቢ ቪዲዮ ቀርቧል።

‎በሰልጣኝ ተማሪዎች የተሰሩ ሁለት ድረ ገፆች ለታሚዎች ቀርበዋል። ድረ ገፆቹም ስለ ደራሮ የዘመን መለወጫ የሚዳስስ እና ስለ ጌደኦ ቡናን የሚያስተዋውቅ ናቸው።

‎በስልጠናው ጥሩ ውጤት ላስመዘገቡ ሽልማት፣ስልጠናውን በአግባቡ ላጠናቀቁ ሰርተፍኬት እና በ5ሚሊዮን ኮደርስ የኦንላይን ስልጠና ተከታትለው ሰርተፍኬት ላገኙ 20 ሰልጣኞች ሰርተፍኬት ተሰጥቷቸዋል።

‎በመጨረሻም ወላጆች ስለ ስልጠናው አስተያየት የሰጡ ሲሆን ፕሮግራሙ በጋራ የማስታወሻ ፎቶ በመነሳት ተጠናቋል።

‎የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል ።
13
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
የሪሜዲያል መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ።

ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን በተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት መስኮች ከ49.5% በታች ያስመዘገቡ ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የRemedial ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆናቸውን አሳውቋል።

1.  በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 33% ከመቶ እና ከዚያ የተቆረጠ መሆኑን።

2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥቡን ያሟሉ ብቻ ይሆናሉ።

የመቁረጫ ነጥብ ፦

➡️ የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 216

➡️ የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 204

➡️ ታዳጊ ክልል እና አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 198

➡️ የማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 198

➡️ ማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ዓይነስውራን ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 165

#MoE

@tikvahethiopia
1🎉1
የፊዚክስ የኖቤል ሽልማት ለሦስት የኮምፒውተር ሳይንቲስቶች ተበረከተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2025 የፊዚክስ የኖቤል ሽልማት ለሦስት የኮምፒውተር ሳይንትስቶች ተበርክቷል።

ጆን ክላርክ፣ ሚኬል ኤች ዲቮሬት እና ጆን ኤም ማርቲንስ የኖቤል ሽልማቱን ያሸነፉ የኮምፒውተር ምህንድስና ባለሙያዎች ሲሆኑ÷ ሽልማቱን ያገኙት ለቀጣዩ ትውልድ የሚመጥን ጠንካራ ኮምፒውተሮችን በመፍጠር ሂደት በሰሩት ስራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኖቤል ኮሚቴ በአሁኑ ዘመን ሞባይልን ጨምሮ ካሜራ የመሳሰሉ ቴክኖሎጂዎች የዚህ ዘርፍ ጥገኛ መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡

የዘርፉ የኖቤል አሸናፊዎች በስዊዲን ሮያል የሳይንስ አካዳሚ ይፋ የተደረገ ሲሆን÷ በካምብሪጅ ዩናይትድ ኪንግደም የተወለዱት የሽልማቱ አሸናፊ ጆን ክላርክ (ፕ/ር) የህይወቴ ትልቁ ሽልማት ነው ብለዋል፡፡

ለሦስቱ አሸናፊዎች 872 ሺህ ፓውንድ የገንዘብ ሽልማት እንደሚበረከትላቸውም ተጠቁሟል።

የተመራማሪዎቹ ግኝት ለዘርፉ ትልቅ ፋይዳ ያለውና ምርምሩ ከፈረንጆቹ 1980 በኋላ ትልቁ እንደሆነ የቢቢሲ መረጃ አመላክቷል፡፡

ምርምሩ የኮምፒውተር ቴክኖሎጂን አሁን ከደረሰበት ደረጃ ከፍ በማድረግ እጅግ ረቂቅ እና ዘመናዊ እንዲሆን እንደሚያስችልም ተገልጿል፡፡

ምንጭ: ፍና
👏4👌1
ማስታወቂያ
የዩኒቨርስቲ ምደባ እየተጠባበቃችሁ ላላችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤
የዩኒቨርስቲ ምደባችሁን በእነዚህ ሊንኮች ማየት የምትችሉ መሆኑነ እንገልጻለን።
Website: https://student.ethernet.edu.et
Telegram bot: @moestudentbot
👍2
Forwarded from Tikvah-University
ይጠንቀቁ!

የዩኒቨርሲቲ ምደባን በተመለከተ ጉዳይ እናስፈፅማለን፣ እንዲቀያየሩ እናደርጋለን ከሚሉ ግለሰቦች ይጠንቀቁ፡፡

“ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ እናቀያይራለን“፣ “ቅሬታዎ ተቀባይነት እንዲያገኝ“ እናስደርጋለን ከሚሉ የማኅበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች እንዲጠነቀቁ እናሳስባለን፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ከዩኒቨርሲቲ ምደባ ጋር የተያያዘ ማንኛውም ጥያቄም ሆነ ቅሬታ ላላቸው ተማሪዎች ምላሽ እየሰጠ መሆኑን ለቲክቫህ አረጋግጧል፡፡ 

በመሆኑም ከምደባው ጋር የተያያዘ ማንኛውም ጥያቄም ሆነ ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች በቀጣይ ቀናትም ትምህርት ሚኒስቴር #በአካል በመሔድ ቅሬታዎን ያቅርቡ፡፡

@tikvahuniversity
1👍1
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
" በሚቀጥሉት ዓመታት የተማሪዎች ምደባ ይቆማል " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥሉት ዓመታት የተማሪዎች ምደባ እንደሚያቆም ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ አስታወቁ።

ይህ ያሳወቁት የትምህርት ሚኒስቴር ከመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ጋር የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የቁልፍ ተግባራት የፊርማ ስነስርዓት ባከናወነበት ወቅት ነው።

በዚሁ ወቅት ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ጠንካራ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እንደገለፁት፤ በሚቀጥሉት ዓመታት የትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን ምደባ እንደሚያቆምና የማለፊያ ነጥብ የሚያስመዘግቡ ተማሪዎች በሚፈልጓቸው ዩኒቨርሲቲዎችና የትምህርት መስኮች እንዲያመለክቱ ይደረጋል፡፡

" የዩኒቨርሲቲ ትምህርት እንደከዚህ ቀደሙ በትምህርት ሚኒስቴር ምደባ ሳይሆን በተማሪዎቹ ምርጫ ይሆናል " ብለዋል።

" ተማሪዎች የሚማሩበትን ዩኒቨርሲቲ ሲመርጡም ምክንያታዊ በመሆን በዬትኛው ዩኒቨርሲቲ የተሻለ የትምህርት መስክ፣ እውቀትና የስራ እድል ላገኝ እችላለሁ በማለት ይመርዝታሉ " ሲሉ ገልጸዋል። #ኢፕድ

@tikvahethiopia
🎉102
#እንኳን_አደረሰን_አደረሳችሁ
#እናመሰግናለን🙏

‎የዶን ቦስኮ ሳሊዛውያን ማህበር ኢትዮጵያ ውስጥ ስራ ከጀመረ 5ዐ ዓመት ሆነው።

‎ማህበሩ በ1968 ዓ.ም የመጀመሪያ ቤቱን የከፈተው #በመቖለ ሲሆን ሁለተኛ ቤቱን ደግሞ #ዲላ ላይ ነው።

‎ማህበሩ ከሚሰራቸው ስራዎች ለአብነት
▶️ ትምህርት
▶️ ግብርና
▶️ የጋራዥ አገልግሎት
▶️ የመጠጥ ውሃ
▶️ የወጣቶች ማዕከል (ኦራቶሪዮ)
▶️ ህክምና ተጠቃሾች ናቸው

‎በነዚህ ስራዎች ላይ ከተለያዩ ሀገራት ወደ ከተማችን በመምጣት ባህላችን እና ቋንቋችን ሳያግዳቸው እንደ ቤተሰብ በፍቅር ሲደግፉን እና ሲረዱን የቆዩ በርከት ያሉ የማህበሩ አባላት ነበሩ አሁንም አሉ።

‎ከነዚህም መካከል
አባ መላኩ
አባ ፍራንኮ
አባ ሮቤርቶ
አባ ኤርማኖ
አባ ጆርጆ
አባ አርስትዴ
አባ ኢዚ
ሴቤስቲያኖ ከቤተሰቦቹ ጋር
ራሚሮ
ጃንካሎ
ሴርጆ ጥቂቶቹ ናቸው።

‎በትምህርቱ ስራ ከአፀደ ህፃናት እስከ ቴክኒክና ሙያ
‎ት/ቤቶችን በመክፈት ተማሪዎችን በእውቀት እና ስነ ምግባር እያነፁ ይገኛሉ።

‎ዲላ ባለው ማዕከል በተለያዩ የስፖርት አይነቶች አብዛኛው የዲላ ከተማ ወጣት ተጫውቷል። በአሁን ሰዓት በተለያዩ ክበባት እና ብሔራዊ ቡድን ተጫዎቾች የዚህ ማዕከል ፎሬዎች ናቸው።

‎እስኪ የዲላ ዶን ቦስኮ ት/ቤቶች የተማራችሁ እና መጨዋቻ ሜዳ እና ሌሎች ትዝታ ያላችሁ ሀሳባችሁን አካፍሉን።

‎በድርጅቱ ውስጥ ያገለገሉ እና እያገለገሉ ያሉ በጎ ፈቃደኞችን እናመስግናቸው።

‎የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል ።
21🏆2