Development Bank of Ethiopia (DBE)
22.3K subscribers
2.48K photos
107 videos
4 files
704 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, ApplicableThursday, September 17,2026
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡-
ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
#DBE #ExchangeRate
❤3
የአፍሪካ ልማት ባንክ እና የደቡብ ኮሪያ አጋርነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ሊሸጋገር ነው።

አጋርነቱ በዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና በግል ሴክተር ኢንቨስትመንት ዙሪያ በስፋት ለመሥራት ስምምነት ላይ ደርሷል።

ልዩ የተባለው ይህ ስምምነት የደቡብ ኮሪያን ቴክኖሎጂ፣ ፋይናንስ እና የኢንዱስትሪ ልማት በስፋት ለመጠቀም ዕድል የሚሰጥ ነው።

የደቡብ ኮሪያ ፈንድ (KOAFEC Trust Fund) የአፍሪካ ልማት ባንክ የረዥም ጊዜ አጋር ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. ከ2006 ጀምሮ 132.82 ሚሊየን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ አድርጓል።

8ኛው የኮሪያ-አፍሪካ የኢኮኖሚ ትብብር የሚኒስትሮች ጉባኤ በደቡብ ኮሪያ ሰሞኑን መካሄዱ ይታወሳል።

#DBE #KOAFEC #ADB
👍4❤3
Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Friday, September 18,2026
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡-
ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
#DBE #ExchangeRate
👍1
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለብድር አመላለስ በዋስትና የያዛቸውን የመያዣ ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በሐራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ለበለጠ መረጃ
ሐሙስ ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ/ም የወጣውን አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ሙሉ መረጃውን ማግኜት ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የካፒታል ዕቃዎች ተከላና ኮሚሽኒንግ አጋሮች የፍላጎት መግለጫ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ (DBE) በሊዝ ፋይናንስ የተገዙ የካፒታል ዕቃዎችን ለመትከል (Installation) እና ሥራ ለማስጀመር (Commissioning) ብቁ የኤሌክትሮ መካኒካል ኩባንያዎችን በግልጽ የፍላጎት መግለጫ (EOI) እንዲያመለከቱ ይጋብዛል፡፡
ለበለጠ መረጃ
ሐሙስ መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ/ም የወጣውን አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ሙሉ መረጃውን ማግኘት ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ

#DBE #commission #installation
❤1
መልካም የሥራ ሳምንት!
.......
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
የኢትዮጵያ ልማት ባንክትክክለኛ የማሕበራዊ ትስስር ገጾች
ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et (http://www.dbe.com.et/?
ለተጨማሪ መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
❤4
Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Monday, September 21,2026
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡-
ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
#DBE #ExchangeRate
❤3
Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Tuesday, September 22,2026
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡-
ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
#DBE #ExchangeRate
👍1
የአፍሪካ ልማት ባንክ እና ብራዚል በማሊ ግብርናንና የግሉን ዘርፍ ለማጠናከር ተስማሙ፡፡
ስምምነቱ በግብርና፣ በምግብ ዋስትና፣ በግል ዘርፍ ልማት እና በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ላይ ያተኮረ ነው።
የብራዚልን የቴክኒክ ልምድ እና የአፍሪካ ልማት ባንክን የልማት አቅም በማቀናጀት የደቡብ-ደቡብ ትብብርን ማጠናከር የስምምነቱ ዋና ግብ ነው።
በትብብሩ መሠረት በግብርና፣ በምግብ ሥርዓት፣ በኃይል ሽግግር፣ በሙያና ክህሎት ማሳደግ እንዲሁም በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ በስፋት ይሰራል።
እንደ አፍሪካ ልማት ባንክ መረጃ፣ ስምምነቱ የማሊን «ቪዥን 2063» እና የዘላቂ ልማት ስትራቴጂ ዕቅድ ጋር የተጣጣመ ነው።
ባንኩ በማሊ በግብርና፣ በትራንስፖርት፣ በኃይል መሠረተ ልማት እና በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ዙሪያ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል።
❤2👍1
Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Wednesday, September 23,2026
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡-
ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
#DBE #ExchangeRate
👍2
ሀምሳ እንደ አንድ - አንድ እንደ ሀምሳ
 
ወጣቶች ናቸው፤ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን። የዓመታት ጥረታቸው ወደ ሥራ ዓለም ያመራ ይዟል።
 
ሆኖም ሥራ በዋዛ የሚገኝ አልነበረም። ይህም ከ10 ዩኒቨርሲቲዎች በ11 የትምህርት መስኮች ለተመረቁት ወጣቶች ግራ የሚያጋባ ነበር።
 
የሆነ ጊዜ ወጣቶቹ ቢሾፍቱ በሚገኝ አንድ የሕክምና መድኃኒት ፋብሪካ ውስጥ ራሳቸውን አገኙ።
የሥራ ፍለጋው ጊዜ አከተመ፤ ደስታም ሆነ።
 
ፈንጠዝያው ግን ዕድሜው ድንክ ነበር፤ ወር ሙሉ ተሠርቶ የሚገኘው 2,800 ብር ደመወዝ ከእጅ ወደ አፍ ለመባል እንኳን አቅም ያጣ ሆነ። ከፍተኛ የሥራ ጫና፣ ተቀጣሪ ሆኖ መሥራት የሚያስከትለው የመንፈስና የኢኮኖሚ ነፃነት እጦት ለወጣቶቹ የማይታረቁ ጥያቄዎች እንደሆኑ ቀጠሉ።
 
"ችግር ብልሃትን ታስተምራለች" እንዲሉ፣ በሥራ ምክንያት የተዋወቁት 50 ወጣቶች በዚህ ጉዳይ ላይ መምከር ጀመሩ።
 
መተዋወቅ ያዳበረው ወዳጅነት "እንዴት?"፣ "ለምን?" እና "እስከ መቼ?" የሚሉ ወሳኝ ነጥቦችን ለማንሳት ደፈረ።
 
ወጣትና ጀማሪ ሠራተኞች እንደ መሆናቸው መጠን ቅርብ አዳሪ መሳይ መላ መቱ… "ዕቁብ ብንጥል?" አይነት ፤ "እድር ይሻለናል" ብለውም ነበር።
 
ውይይቱ ሲዳብርና ሃሳብ ሃሳብን ሲወልድ፣ የአስኳላ ቤት ትምህርታቸውን በአግባቡ ለመጠቀም ተስማሙ።
 
የኢኮኖሚ ነፃነታቸውን የሚያውጅና ለሀገራቸውም አስተዋጽኦ የሚያደርግ የልማት ማህበር ብንመሠርት የሚለው ነጥብ በሃሳብ ባሕር ላይ መልሕቁን ጣለ።
 
ሁለት ኮሚቴዎችን አደራጁ፤ አንደኛው የልማት ማህበሩ እንዴት ይመሠረት የሚለውን ሲያጠና፣ ቀሪው ደግሞ በምን መስክ እንሰማራ የሚለውን ያዘ።
 
"ብልጥ ልጅ የያዘውን ይዞ ነውና " ወጣቶቹ ይህን ሁሉ የሚያደርጉት መደበኛ ሥራቸውን ሳይበድሉ በብልሃት ነበር።
 
የኋላ ኋላ የልማት ማህበሩ 50 አባላትን ይዞ "ቶኩማዋ ኦዳ ነቤ" የሚል መጠሪያ በመያዝ በ2010 ዓ.ም. ተመሠረተ።
 
ከስምንት  ዓመት በፊት እንደ ሀገር 95 በመቶ የሚሆነው የምግብ ዘይት ከውጭ ይገባ ነበር። ይህም ሀገሪቱን ለከፍተኛ ወጪ ፣ ለጥራትና ለጤና እክሎች ዳርጓት ነበር።
የጥናት ቡድኑ ይህንን የገበያ ክፍተት አስልቶ አቀረበ። የቢዝነስ ሃሳቡ ለወጣቶቹ የሚበጅ፣ ለሀገርም የሚያኮራ ሆኖ ጸደቀ።
 
ወጣቶቹ በአማካሪዎቻቸው አማካኝነት ይህንን ግዙፍ ሃሳብ ፋይናንስ የሚያደርግላቸው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እንደሆነ ተነገራቸው፤ ወደ ቢሾፍቱ ቅርንጫፍም አመሩ። ተገቢው የቢዝነስ ሰነድ ተመርምሮ በሊዝ ፋይናንሲንግ ተጠቃሚ ሆኑ።
 
የሊዝ ፋይናንሲንግ ማለት የቢዝነስ ሃሳብ ወይም ዝግጅት እያለ ነገር ግን ማሽነሪ የመግዛት አቅም ሳይኖር ሲቀር፣ ባንኩ ማሽነሪውን በራሱ ወጪ ገዝቶና ተክሎ ለአልሚዎች የሚያስረክብበት አሠራር ነው።
 አልሚዎች ማሽነሪውን ሥራ ላይ በማዋል ከሚያገኙት ገቢ ላይ የሊዝ ክፍያውን (ኪራዩን) በየጊዜው ለባንኩ ይከፍላሉ።
በዚህ መሰረት የኢትጵያ ልማት ባንክ የ36.6 ሚሊየን ብር የዘይት መጨምቂያ ማሽነሪዎች  ገዝቶ፣ ተክሎ እና ተገቢውን ፍተሻ አድርጎ ለወጣቶቹ አስረከ፡፡
 
አሁን ላይ "ቶን" የሚል መጠሪያ ያለው የምግብ ዘይት በቢሾፍቱና አካባቢው ገበያ ተለምዷል።
 
የሀገራችንን አኩሪ አተር በዋና ግብዓትነት የሚጠቀመው ይህ የምግብ ዘይት ፋብሪካ በቀን 15 ሺህ ሊትር ዘይት ያመርታል። ከአካባቢ  ብክለት የፀዳው የፋጉሎ ተረፈ ምርት ለእንስሳት መኖ ይውላል፡፡
ፍብሪካው  በቀጥታ ለ36፣ በተዘዋዋሪ ደግሞ ለ200 ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል፤ አሁን ላይ  የማህበሩ አጠቃላይ ሀብት 300 ሚሊዮን ብር ደርሷል።
 
አሁን የነ ታሪኩ አበራ፣ ጫላ መለሰ፣ ተክሉ ብራ፣ ተስፋ ፀጋዬና ጓደኞቻቸው የኢኮኖሚ ነፃነት ጥያቄ ተመልሷል፤ ለሀገራቸውም በጥቂቱ አስተዋጽኦ ማበርከት ጀምረዋል።
 
"ሀምሳ ሎሚ ለሀምሳ ሰው ጌጡ፣ ለአንዱ ግን ሸክሙ" እንዲሉ… ወጣቶቹ ሀምሳ ሆነው እንደ አንድ፣ አንድ ሆነው እንደ ሀምሳ ሰው ሠርተው ለፍሬ በቅተዋል። የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደግሞ የወጣቶቹ ሕልም መሬት ይነካ ዘንድ ቀኝ እጅ ሆኗቸዋል።
 
ስኬቱ ታሪኩ በተጻፈበት መንገድ በአጭሩ የተገኝ ባይሆንም፣ እንደ ልማት ባንክ ዓይነት የልማት ቀንዲል ተቋምና ባለራዕይ ዜጎች እስካሉ ድረስ ልማትና ውጤት አይቀሬ ነው።
❤3