Development Bank of Ethiopia (DBE)
22.8K subscribers
2.26K photos
84 videos
4 files
645 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Thursday , July 23, 2026

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/dbethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

#exchangerate #DBE #Ethiopia
2👍2
የድርድር ሽያጭ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ለኬኛ ጠቅላላ የንግድ ሥራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና ለአቲ አንዳልካቸው ንጋቱ ለሰጠው ብድር አመላለስ በመያዣነት  የያዛቸውን እና ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለፁትን ፕሮጀክቶች እና የመያዣ ንብረቶቹን በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሸሻለው 216/92 እና 1147/2011 መሰረት ባሉበት ሁኔታ በድርድር ሽያጭ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
1
የዝግ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ለአቶ ሽመልስ ካሱ ገረሱ ለሰጠው ብድር አመላለስ በመያዣነት የያዛቸውን እና ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለፁትን የመያዣ ንረቶቹን በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሻሻለው 216/92 እና 1147/2011 መሰረት ባሉበት ሁኔታ በህግ ጨረታ አወዳድር በጥሬ ገንዘብ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
👍6
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የካፒታል ዕቃ ኪራይ አገልግሎት (ሊዝ ፋይናንሲንግ) ከሚያቀርብባቸው የግብርና ንዑስ መስኮች ውስጥ የቅባት እህሎች ማምረቻ ተጠቃሽ ነው፡፡
👍7
እውነትም ሀብታሙ…
ሐሳብ አለው፤ ሰርቶ የመለወጥ ሐሳብ! ሕይወትን በሥራ የማሸነፍ ትልም፣ ለወገን የመድረስ ውጥን፣ ለሐረር ጣፋጭ የማቅረብ ሐሳብ!
ሆኖም «መቼ?» የሚለው ጥያቄ መልስ አልነበረውም። ይህ ጥያቄ፣ ጀምበር እንደ ፈንዲሻ ፈክታ፤ ሀሩር ሆና ስታዘቀዝቅ እንኳን፣ ግለቱ የማይበርድ ጥያቄ ነበር።
ከዕለታት በአንዱ ቀን በሐረር የፈካችው ጀምበር፣ በልዩነት ለወጣቱ ብቻ የወጣች ትመስል ነበር።
ለረጅም ጊዜ ያሰላሰለው የቢዝነስ ውጥን የሚጀመርበት ጊዜ «አሁን ነው» ዓይነት ነገር ሹክ ያለችው አይነት።
ይሄኔ ወጣቱ ሥራ ለመጀመር የሚያስችል ሁኔታን አየ። «ቀስ በቀስ» እንዲሉ ፣ ባለው ማዝገምን መረጠ።
በአነስተኛ ቤት፣ በነዳጅ በምትሠራ ትንሽየ የባለ ስድስት ፓትራ የመጋገሪያ ማሽን ታላቁ ሕልም ተጀመረ፡፡
በሥራ ራስን የማሸነፍ ሕልም፣ ለወገን የመትርፍ ትልም፣ ለሐረር ጣፋጭ ኬክና ዳቦ የማቅረብ የቢዝነስ ሐሳብ መሬት ነካ። ይህ የሥራ ፈጣሪው የሀብታሙ ደስታ አጭር የመነሻ ታሪክ ነው።
አሁን ሐሳብ ግዘፍ ነስቶ ሥራ ተጀምሯል፤ ሌላ ጭንቀት ግን ጎራ አለ። የገበያ ተቀባይነት ጉዳይ ። ሆኖም ጭንቀት በጥረትና በብርቱ ድካም ተተካ ገብያውም ደራ፡፡
የጣፋጭ ኬኮችና የዳቦ ገበያው እያደገ ሲመጣ ግን ሌላ ጤነኛ ጭንቀት ብቅ ማለቱ አልቀረም።
ፍላጎት አደገ፤ እሱን ለማስተናገድ ዘመናዊ የዳቦ መጋገሪያ ማሽን መግዛትና ቢዝነሱን ማስተዳደር በራሱ ፈተና ሆነ።
ይሔኔ ሀብታሙ፣ የልማት ውጥኖችን እውን በማድረግ 117 ዓመታትን በስኬት ወደዘለቀው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጎራ አለ።
ባንኩ የቢዝነስ ጅምሩን በአግባቡ ተመልክቶ፣ ሀብታሙ ደስታ የሚያስፈልጉትን ሁለት መሠረታዊ ጥያቄዎች መፍታት ጀመረ።
ቀዳሚው አቅም ግንባታ ነበር። በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ዙሪያ በተዘጋጀው ሥልጠና ሀብታሙ ታቀፈ። ቢዝነስ በእውቀት እንዴት እንደሚመራ ከሳይንሱ ጋር ተዋወቀ። ሀብታሙ ደስታ ሥልጠናውን ሲያስታውስ፦"ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ያገኘሁት ሥልጠና ሥራዬን በእውቀትና በፍላጎት እንድመራ አድርጎኛል። ድርጅቴንም በተሻለ ብቃት እንዳስተዳድር ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጓል" ይላል።
ሁለተኛው የብድር ጥያቄ ነበር። ሀብታሙ ለተጨማሪ ወጪ የዳረገውንና በነዳጅ የሚሰራ የዳቦ መጋገሪያ ማሽን ማዘመን ነበረበት። የልማት ባንክ በሊዝ ፋይናንሲንግ ዘርፍ ዘመናዊ የዳቦ መጋገሪያ ማሽን (ኦቭን) በአራት ወር ጊዜ ውስጥ ገዛለት።
ይህ ማሽን ታሪክ ቀያሪ ሆነ፤ ሀብታሙ በቀን ከ2,000 ወደ 12,000 ዳቦ ወደ ማምረት አቅም ተሸጋገረ። ምርት ሲያድግ አገልግሎት ይጨምራል፤ ሀብታሙ ለ36 ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጠረ።
አሁን ጊዜው ከተገኘው ትርፍ ላይ ማኅበራዊ ኃላፊነትን የመወጣት ነው! ሀብታሙ ደስታ፤ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው እንዲቆዩ ቀኝእጅ ሲሆን፣ የሕክምና ወጪ መሸፈን ላዳገታቸው ዜጎች ደግሞ «አለሁ» ማለት ከጀመረ ሰነባብቷል።
የዳቦ እና ኬክ ሥራው እያደገ በመምጣቱ ሀብታሙ ደስታ እንደገና ወደ ልማት ባንክ ጎራ ሊል አስቧል፤ የዱቄት ፋብሪካ የመትከል ዕቅድ አለውና።
"ሁልጊዜም ወደ ባንኩ ስሄድ የባለሙያዎች አቀባበል፣ ክትትልና ሙያዊ ድጋፍ ይገርመኛል" የሚለው ሀብታሙ፣ ድርጅቱ ውጤታማ እንዲሆን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ድርሻ የላቀ ነው ባይ ነው፡፡
በግል ጥረት በ50 ሺህ ብር የተጀመረው የዳቦና ኬክ ቤት ቢዝነስ ፣ አሁን በባንኩ ድጋፍበሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ 5 ሚሊዮን ብር ካፒታል አስመዝግቧል። ወደ ዱቄት ፋብሪካ የማደግ እቅድ ላይ ደርሷል፡፡
ጅምሩን አይቶ መዳረሻውን ያሰበ ሰው ይህን ታሪክ ሲያነብ «እውነትም ሀብታሙ» ማለቱ አይቀርም!
5👍2
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያልተፈቀዱ የምናባዊ ንብረት ግብይቶችን ከለከለ።

ምናባዊ ንብረት ማለት በአካል የማይገኝ፣ በተለያዩ ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ታግዞ ተመን የወጣለት እንዲሁም ግብይትና ዝውውር የሚፈጸምበት የገበያ ዓይነት ነው።

የባንኩ መግለጫ እንደሚያመለክተው፣ የውጭ ምንዛሪን ጨምሮ የምናባዊ ንብረት ግብይት፣ ዝውውርና መሰል አገልግሎቶችን ማቅረብ የሚችሉት ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አካላት ብቻ ናቸው።

ክልከላው የዲጂታል ግብይት ሥርዓቶች መጠለፍንና የገንዘብ ማጭበርበርን ለመከላከል የሚያስችል ነው፡፡

በመሆኑም ያልተፈቀደ መሰል ግብይት ላይ የሚሳተፉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ብሔራዊ ባንክ አሳስቧል።
3
Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Friday , July 24, 2026

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/dbethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

#exchangerate #DBE #Ethiopia
መልካም የሥራ ሳምንት!
.......
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
የኢትዮጵያ ልማት ባንክትክክለኛ የማሕበራዊ ትስስር ገጾች
ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et (http://www.dbe.com.et/?
ለተጨማሪ መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
6👍1
Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Monday , July 27, 2026

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/dbethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

#exchangerate #DBE #Ethiopia
3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጥናቶች እንዳረጋገጡት ኢትዮጵያ በዓመት ከ 500 ሺህ ቶን በላይ ማር የማምረት አቅም አላት።

ይህም በአቅም ደረጃ ከዓለም ከቀዳሚዎቹ ሀገራት ተርታ ሲሆን፣ በአፍሪካ ደግሞ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

በመስኩ በተካሄዱ ጥናቶች ኢትዮጵያ ከሰባት ሚሊዮን በላይ የንብ መንጋዎች (ኮሎኒዎች) ባለቤት ነች።

ይህም ከማር ምርት ጋር በተያያዘ ሰፊ ሀብት እንደሆነ ይታመናል።

እንደ ሀገር የማር ምርትን ለማሳደግ በፖሊሲ ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶታል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደግሞ ዘርፉን ፋይናንስ በማድረግ ይታወቃል።

ባንኩ ንብ ማነብን በግብርና ንዑስ የኢኮኖሚ መስክ በሊዝ ፋይናንስ ያደርጋል።
2
የአፍሪካ ልማት ባንክ የ100 ሚሊየን ዩሮ ብድር ለሞሮኮ አፀደቀ፡፡

ገንዘቡ በሞሮኮ ለሚገነባው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ባትሪ ፋብሪካ የሚውል ነው፡፡

ባንኩ ለሊቲየም አይኦን ፎስፌት ባትሪ ጊጋፋብሪካ ግንባታ ተጨማሪ 141 ሚሊየን ዩሮ ለማሰባሰብ እቅድ ይዟል።

ፕሮጀክቱ በአፍሪካ እንዲሁም በመካከለኛው ምስራቅ እና ሰሜን አፍሪካ ክልል የተቀናጀ የባትሪ ማምረቻ ይሆናል ።

ፋብሪካው በምዕራፍ 1 ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የሚሆኑ 10 ጊጋዋት ሰዓት የባትሪ ሴሎችን እና ፓኮችን የሚያመርት ሲሆን፣ በሂደት ወደ 100 ጊጋዋት ሰዓት ያሳድጋል፡፡

የቀረበው ፋይናንስ በአፍሪካ የኢነርጂ ሽግግርን ለማስቀጠል ፤አነስተኛ ካርቦን ያለው ታዳሽ ኃይል የሚያቀርብ፣ የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ ውጥን አካል እንደሆነ የአፍሪካ ልማት ባንክ አስታውቋል፡፡

ይህ በእንዲህ እዳለ ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በቅርቡ ከሚጀምራቸው አዳዲስ አገልግሎቶች ግሪን ቦንድ አንዱ ነው።

ለአካባቢ ጥበቃ፣ የአየር ንብረትን ለመቋቋም እና ዘላቂ ልማትን ለማስፋፋት የሚሰጥ የብድር ሰነድ ግሪን ቦንድ ተብሎ ይጠራል።

ከዚህ ውስጥ ታዳሽ ኃይል ከፀሐይ፣ ከነፋስ እና ከውሃ ኃይል ማምረትን ጨምሮ፤ በንፁህ ትራንስፖርት ዘርፍ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች፣ የባቡር መስመሮች እንዲሁም የብዝሃ-ትራንስፖርት ማሻሻያዎች እና ማዘመኛዎች ተጠቃሽ ናቸው።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እያካሄደ ያለው ሪፎርም በታዳሽ ኃይል ረገድ የግሪን ቦንድ የፋይናንስ አማራጭን የሚተገብር ይሆናል። ይህም ኢትዮጵያ እየገነባችው ላለው የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
#DBE #evcars #evbattery #CleanEnergy
1👍1