Development Bank of Ethiopia (DBE)
22.8K subscribers
2.26K photos
84 videos
4 files
645 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Wednesday , July 22, 2026

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/dbethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

#exchangerate #DBE #Ethiopia
👍21
የጀርመን ልማት ባንክ (KfW) ከአረንጓዴ ቦንዶች ሽያጭ 12.6 ቢሊየን ዩሮ ገቢ አገኘ።
ባንኩ ገቢውን ያገኘው በስድስት የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች ከሸጣቸው አስራ አንድ አረንጓዴ ቦንዶች ነው።
እያንዳንዳቸው 5 ቢሊየን ዩሮ መጠን ያላቸው ሁለት ትልልቅ ቦንዶች ለገቢው ማደግ ተጠቃሽ ናቸው።
ባንኩ የፋይናንስ ማሰባሰብ ገቢውን በዓመቱ ሁለተኛ መንፈቅ እስከ 27 ቢሊየን ዩሮ ለማሳደግ ያቀደ ሲሆን፣ ዩሮ እና የአሜሪካ ዶላር ደግሞ ዋናውን ድርሻ ይይዛሉ።
የጀርመን ልማት ባንክ የአረንጓዴ ቦንድ ስትራቴጂያዊ ማዕቀፉን እ.ኤ.አ. ከ2024 ጀምሮ አሻሽሎ ሥራ ላይ ያዋለ ሲሆን፣ ከገቢ ባለፈ ለአረንጓዴ ሀብቶች አጠቃቀም ሰፊ ዕድል እንደፈጠረ በድረ-ገጹ አስነብቧል።
አረንጓዴ ቦንድ (Green Bond) ለአካባቢ ጥበቃ እና ለአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ለሚውሉ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የሚሆን ገንዘብ ከባለሀብቶች ወይም ከኢንቨስተሮች ለመሰብሰብ የሚወጣ የብድር ሰነድ ነው።
ቦንዱ በመንግሥታት፣ በልማት ባንኮች እና በግል ኩባንያዎች በኩል ሊቀርብ ይችላል።
አረንጓዴ ቦንድ ዓላማው እንጂ ልዩ አሰራሩ እንደ መደበኛ ቦንድ ነው። ኢንቨስተሮች ቦንዱን ሲገዙ ለተወሰነ ጊዜ ገንዘብ ያበድራሉ፤ ሰጪው አካል ደግሞ በየጊዜው የተወሰነ የወለድ መጠን እየከፈለ የቦንዱ ጊዜ ሲጠናቀቅ ዋናው ገንዘብ የሚመለስ ይሆናል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አረንጓዴ ቦንድን ለመጀመር በዝግጅት ላይ ይገኛል። ቦንዱ ሥራ ሲጀምር ሀገር ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ እና ለታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶች ተጨማሪ የገንዘብ ምንጭ እንድታገኝ የሚያስችል ነው፡፡
8👍3👏1
ሚሽን 300
ዓለም ላይ 655 ሚሊየን ሰዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ አይደሉም። ከዚህ ውስጥ 560 ሚሊየኑ በአፍሪካ፣ በተለይም ከሰሃራ በታች ባለው ክፍል ይገኛሉ።
የምድሪቱ 86 ከመቶ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እጦት መዳረሻው አፍሪካ ነው ይላል ከወር በፊት በዓለም ባንክ ገፀ-ድር ላይ የተነበበው ጥናታዊ አኃዝ ፡፡
የችግሩ ስፋት እና የመሠረተ ልማቱ ውድ መሆን ለመፍትሔው ተጨማሪ የፋይናንስ ምንጭ እንዲኖር የሚያስገድድ ነው።
ከቁጥር በላይ የሆነው ይህ ችግር ለአንድ ውጥን መነሻ ሆኗል፤ የአፍሪካ ልማት ባንክ እና የዓለም ባንክ ደግሞ ባለቤቶቹ ናቸው።
ባንኮቹ ከሁለት ዓመት በፊት መንግሥታት ይህን ችግር ለመቅረፍ ሲሠሩ "ፋይናንስ እናቅርብ" የሚል ሐሳብ ይዘው ብቅ አሉ፤ እቅዱ እ.ኤ.አ. እስከ 2030 ከሰሃራ በታች የሚኖሩ 300 ሚሊዮን ሰዎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ማድረግ ነው።
ለዚህም የዓለም ባንክ 250 ሚሊዮን፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ ደግሞ 50 ሚሊዮን ዶላር በማዋጣት ለ300 ሚሊየን ሰው ብርሃን የሚሆን በጀት ያዙ።
የበጀቱም ሆነ የተጠቃሚው ቁጥር ስለገጠመ የፕሮጀክቱ ስያሜ «ሚሽን 300» ሆነ። በአፍሪካ ውስጥ ያለውን የኃይል አቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ እና ለአነስተኛና መካከለኛ ቢዝነሶች፣ ትምህርት ቤቶች፣ እና ጤና ጣቢያዎች አስተማማኝ የመብራት አቅርቦት ማድረስ የፕሮግራሙ ዝርዝር ግብ ነው።
የመብራት መስመር ዝርጋታ (Grid Expansion) እና የታዳሽ ኃይል አማራጮችን (እንደ የፀሐይ፣ የንፋስ እና አነስተኛ የኃይል ማመንጫዎች) ማካተት ደግሞ ቴክኒካዊ ሥራው ነው።
በጀቱ ቅይጥ ፋይናንስ (Blended Financing) ዓይነት ሲሆን እርዳታን፣ ቀላል ብድርን እና የግል ኢንቨስትመንትን ያጣመረ ነው።
የአፍሪካ ልማት ባንክ በዚህ ረገድ በዘላቂ ኃይል ፈንድ በኩል ለአፍሪካ አገራት የአረንጓዴ ሃይድሮጅን ፕሮጀክቶች ቅድመ-ኢንቨስትመንት ድጋፍ የሚውል 20 ሚሊዮን ዶላር የፋይናንስ ጥሪ አስተላልፏል። ለግብፅ ደግሞ ከፀሐይ ኃይል ማመንጫ እና ባትሪ ማከማቻ የሚሆን የ66 ሚሊዮን ዶላር ብድር አጽድቋል።
ባንኩ ከሰሞኑ ለኢትዮጵያ የ110 ሚሊዮን ዶላር ብድር አጽድቋል። ገንዘቡ በግል እና በመንግሥት አጋርነት ማዕቀፍ ለሚገነባው ለአይሻ-1 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የሚውል ነው።
ይህም በግሉ ዘርፍ የሚመራ የታዳሽ ኃይል ኢንቨስትመንት በመሆኑ በአይነቱ ቀዳሚ ያደርገዋል። ፕሮጀክቱ 300 ሜጋ ዋት ኃይል የሚያመነጭ ሲሆን፣ በ25 ዓመታት የአገልግሎት ዘመኑ 1.39 ሚሊዮን ቶን የሚጠጋ የካርቦን ልቀትን ይከላከላል ተብሎ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ በውኃ፣ በፀሐይ፣ በንፋስ እና በጂኦተርማል የታዳሽ ኃይል ልማት መስክ ሰፊ ኢንቨስትመንት እያካሄደች ያለች ሀገር ነች።
ሀገራችን ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ፕሮግራም ያላት ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ2030 ሁሉን አቀፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ግብ ይዛ እየሠራች ነው።
የአፍሪካ ልማት ባንክ የ110 ሚሊዮን ዶላር የብድር አቅርቦት ይህን ግብ ከማሳካት አኳያ ለመንግሥት ተጨማሪ አቅም ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደግሞ ተጨማሪ አቅም ይዞ እየመጣ ነው። ባንኩ በሪፎርም ከያዛቸው አዳዲስ የፋይናንስ እሳቤዎች አንዱ ግሪን ፋይናንስ (Green Finance) ነው።
ግሪን ፋይናንስ ለአካባቢ ጥበቃ፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እና አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት የሚደረግ የፋይናንስ አቅርቦት ነው። ታዳሽ ኃይል፣ አረንጓዴ ትራንስፖርት፣ ዘላቂ የደን ልማትና እንክብካቤ እንዲሁም የኃይል ቆጣቢነት ላይ ትኩረት ያደርጋል።
ግሪን ፋይናንስ በአረንጓዴ ቦንዶች (Green Bonds) ፣ በአረንጓዴ ብድሮች (Green Loans) እና በካርቦን ገበያ (Carbon Markets) በተሰኙ ሦስት ዋና ዋና መንገዶች የፋይናንስ አቅርቦት ያደርጋል። ይህም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም፣ የተፈጥሮ ሀብትን ለመጠበቅ እና በአረንጓዴ ቴክኖሎጂዎችና ኢንዱስትሪዎች ዙሪያ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር ሰፊ ዕድል የሚፈጥር የፋይናንስ አሰራር ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ «የልማትዎ አጋር!» የሚለውን መሪ ቃል ሁልጊዜም በልኩ እና በደርዙ ይፈጽማል የሚባለው ለዚህ ነው።
እንደ ጊዜው እና እንደ ቴክኖሎጂው እድገት ባንኩ ሪፎርም ያደርጋል። ለሀገር የሚገቡ አዳዲስ አሰራሮችና ቴክኖሎጂዎችን ያመጣል፣ ያላምዳል፤ የንግድ ባንኮች በማይደፍሯቸው የልማት መስኮች የስጋት አደጋዎችን ተቋቁሞ የረጅም ጊዜ የፋይናንስ ምንጭ ይሆናል። አሁንም ሀገር ለምትከተለው የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ግሪን ፋይናንስን ይዞ እየመጣ ነው።
#DBE #greenenergy# #africandevelopentbank #bankloan #GreenBond
6👍4👏1
Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Thursday , July 23, 2026

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/dbethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

#exchangerate #DBE #Ethiopia
2👍2
የድርድር ሽያጭ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ለኬኛ ጠቅላላ የንግድ ሥራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና ለአቲ አንዳልካቸው ንጋቱ ለሰጠው ብድር አመላለስ በመያዣነት  የያዛቸውን እና ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለፁትን ፕሮጀክቶች እና የመያዣ ንብረቶቹን በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሸሻለው 216/92 እና 1147/2011 መሰረት ባሉበት ሁኔታ በድርድር ሽያጭ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
1
የዝግ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ለአቶ ሽመልስ ካሱ ገረሱ ለሰጠው ብድር አመላለስ በመያዣነት የያዛቸውን እና ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለፁትን የመያዣ ንረቶቹን በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሻሻለው 216/92 እና 1147/2011 መሰረት ባሉበት ሁኔታ በህግ ጨረታ አወዳድር በጥሬ ገንዘብ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
👍6
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የካፒታል ዕቃ ኪራይ አገልግሎት (ሊዝ ፋይናንሲንግ) ከሚያቀርብባቸው የግብርና ንዑስ መስኮች ውስጥ የቅባት እህሎች ማምረቻ ተጠቃሽ ነው፡፡
👍7
እውነትም ሀብታሙ…
ሐሳብ አለው፤ ሰርቶ የመለወጥ ሐሳብ! ሕይወትን በሥራ የማሸነፍ ትልም፣ ለወገን የመድረስ ውጥን፣ ለሐረር ጣፋጭ የማቅረብ ሐሳብ!
ሆኖም «መቼ?» የሚለው ጥያቄ መልስ አልነበረውም። ይህ ጥያቄ፣ ጀምበር እንደ ፈንዲሻ ፈክታ፤ ሀሩር ሆና ስታዘቀዝቅ እንኳን፣ ግለቱ የማይበርድ ጥያቄ ነበር።
ከዕለታት በአንዱ ቀን በሐረር የፈካችው ጀምበር፣ በልዩነት ለወጣቱ ብቻ የወጣች ትመስል ነበር።
ለረጅም ጊዜ ያሰላሰለው የቢዝነስ ውጥን የሚጀመርበት ጊዜ «አሁን ነው» ዓይነት ነገር ሹክ ያለችው አይነት።
ይሄኔ ወጣቱ ሥራ ለመጀመር የሚያስችል ሁኔታን አየ። «ቀስ በቀስ» እንዲሉ ፣ ባለው ማዝገምን መረጠ።
በአነስተኛ ቤት፣ በነዳጅ በምትሠራ ትንሽየ የባለ ስድስት ፓትራ የመጋገሪያ ማሽን ታላቁ ሕልም ተጀመረ፡፡
በሥራ ራስን የማሸነፍ ሕልም፣ ለወገን የመትርፍ ትልም፣ ለሐረር ጣፋጭ ኬክና ዳቦ የማቅረብ የቢዝነስ ሐሳብ መሬት ነካ። ይህ የሥራ ፈጣሪው የሀብታሙ ደስታ አጭር የመነሻ ታሪክ ነው።
አሁን ሐሳብ ግዘፍ ነስቶ ሥራ ተጀምሯል፤ ሌላ ጭንቀት ግን ጎራ አለ። የገበያ ተቀባይነት ጉዳይ ። ሆኖም ጭንቀት በጥረትና በብርቱ ድካም ተተካ ገብያውም ደራ፡፡
የጣፋጭ ኬኮችና የዳቦ ገበያው እያደገ ሲመጣ ግን ሌላ ጤነኛ ጭንቀት ብቅ ማለቱ አልቀረም።
ፍላጎት አደገ፤ እሱን ለማስተናገድ ዘመናዊ የዳቦ መጋገሪያ ማሽን መግዛትና ቢዝነሱን ማስተዳደር በራሱ ፈተና ሆነ።
ይሔኔ ሀብታሙ፣ የልማት ውጥኖችን እውን በማድረግ 117 ዓመታትን በስኬት ወደዘለቀው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጎራ አለ።
ባንኩ የቢዝነስ ጅምሩን በአግባቡ ተመልክቶ፣ ሀብታሙ ደስታ የሚያስፈልጉትን ሁለት መሠረታዊ ጥያቄዎች መፍታት ጀመረ።
ቀዳሚው አቅም ግንባታ ነበር። በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ዙሪያ በተዘጋጀው ሥልጠና ሀብታሙ ታቀፈ። ቢዝነስ በእውቀት እንዴት እንደሚመራ ከሳይንሱ ጋር ተዋወቀ። ሀብታሙ ደስታ ሥልጠናውን ሲያስታውስ፦"ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ያገኘሁት ሥልጠና ሥራዬን በእውቀትና በፍላጎት እንድመራ አድርጎኛል። ድርጅቴንም በተሻለ ብቃት እንዳስተዳድር ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጓል" ይላል።
ሁለተኛው የብድር ጥያቄ ነበር። ሀብታሙ ለተጨማሪ ወጪ የዳረገውንና በነዳጅ የሚሰራ የዳቦ መጋገሪያ ማሽን ማዘመን ነበረበት። የልማት ባንክ በሊዝ ፋይናንሲንግ ዘርፍ ዘመናዊ የዳቦ መጋገሪያ ማሽን (ኦቭን) በአራት ወር ጊዜ ውስጥ ገዛለት።
ይህ ማሽን ታሪክ ቀያሪ ሆነ፤ ሀብታሙ በቀን ከ2,000 ወደ 12,000 ዳቦ ወደ ማምረት አቅም ተሸጋገረ። ምርት ሲያድግ አገልግሎት ይጨምራል፤ ሀብታሙ ለ36 ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጠረ።
አሁን ጊዜው ከተገኘው ትርፍ ላይ ማኅበራዊ ኃላፊነትን የመወጣት ነው! ሀብታሙ ደስታ፤ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው እንዲቆዩ ቀኝእጅ ሲሆን፣ የሕክምና ወጪ መሸፈን ላዳገታቸው ዜጎች ደግሞ «አለሁ» ማለት ከጀመረ ሰነባብቷል።
የዳቦ እና ኬክ ሥራው እያደገ በመምጣቱ ሀብታሙ ደስታ እንደገና ወደ ልማት ባንክ ጎራ ሊል አስቧል፤ የዱቄት ፋብሪካ የመትከል ዕቅድ አለውና።
"ሁልጊዜም ወደ ባንኩ ስሄድ የባለሙያዎች አቀባበል፣ ክትትልና ሙያዊ ድጋፍ ይገርመኛል" የሚለው ሀብታሙ፣ ድርጅቱ ውጤታማ እንዲሆን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ድርሻ የላቀ ነው ባይ ነው፡፡
በግል ጥረት በ50 ሺህ ብር የተጀመረው የዳቦና ኬክ ቤት ቢዝነስ ፣ አሁን በባንኩ ድጋፍበሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ 5 ሚሊዮን ብር ካፒታል አስመዝግቧል። ወደ ዱቄት ፋብሪካ የማደግ እቅድ ላይ ደርሷል፡፡
ጅምሩን አይቶ መዳረሻውን ያሰበ ሰው ይህን ታሪክ ሲያነብ «እውነትም ሀብታሙ» ማለቱ አይቀርም!
5👍2
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያልተፈቀዱ የምናባዊ ንብረት ግብይቶችን ከለከለ።

ምናባዊ ንብረት ማለት በአካል የማይገኝ፣ በተለያዩ ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ታግዞ ተመን የወጣለት እንዲሁም ግብይትና ዝውውር የሚፈጸምበት የገበያ ዓይነት ነው።

የባንኩ መግለጫ እንደሚያመለክተው፣ የውጭ ምንዛሪን ጨምሮ የምናባዊ ንብረት ግብይት፣ ዝውውርና መሰል አገልግሎቶችን ማቅረብ የሚችሉት ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አካላት ብቻ ናቸው።

ክልከላው የዲጂታል ግብይት ሥርዓቶች መጠለፍንና የገንዘብ ማጭበርበርን ለመከላከል የሚያስችል ነው፡፡

በመሆኑም ያልተፈቀደ መሰል ግብይት ላይ የሚሳተፉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ብሔራዊ ባንክ አሳስቧል።
3
Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Friday , July 24, 2026

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/dbethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

#exchangerate #DBE #Ethiopia
መልካም የሥራ ሳምንት!
.......
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
የኢትዮጵያ ልማት ባንክትክክለኛ የማሕበራዊ ትስስር ገጾች
ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et (http://www.dbe.com.et/?
ለተጨማሪ መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
6👍1
Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Monday , July 27, 2026

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/dbethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

#exchangerate #DBE #Ethiopia
3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጥናቶች እንዳረጋገጡት ኢትዮጵያ በዓመት ከ 500 ሺህ ቶን በላይ ማር የማምረት አቅም አላት።

ይህም በአቅም ደረጃ ከዓለም ከቀዳሚዎቹ ሀገራት ተርታ ሲሆን፣ በአፍሪካ ደግሞ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

በመስኩ በተካሄዱ ጥናቶች ኢትዮጵያ ከሰባት ሚሊዮን በላይ የንብ መንጋዎች (ኮሎኒዎች) ባለቤት ነች።

ይህም ከማር ምርት ጋር በተያያዘ ሰፊ ሀብት እንደሆነ ይታመናል።

እንደ ሀገር የማር ምርትን ለማሳደግ በፖሊሲ ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶታል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደግሞ ዘርፉን ፋይናንስ በማድረግ ይታወቃል።

ባንኩ ንብ ማነብን በግብርና ንዑስ የኢኮኖሚ መስክ በሊዝ ፋይናንስ ያደርጋል።
3