Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.7K subscribers
2.02K photos
76 videos
4 files
538 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ (ESX)፣ የንግድ ባንኮችና የፋይናንስ ዘርፉ ቁልፍ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የአገሪቱን አውቶሜትድ በባንኮች መካከል የሚካሄድ የውጭ ምንዛሪ ግብይት አውታር (Platform) ዛሬ በይፋ ተጀመረ።

የግብይት አውታሩ በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ላለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና ለፋይናንስ ዘርፍ ዘመናዊነት ወሳኝ ምዕራፍ ሲሆን፤ በባንኮች መካከል በሚደረገው የውጭ ምንዛሪ ገበያ ውስጥ ግልጽነትን፣ ትክክለኛ ዋጋን የማወቅ ሂደትንና የገበያ ሥርዓትን ያጠናክራል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ክቡር ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ሲናገሩ
“ዛሬ በይፋ ያስጀመርነው የግብይት አውታር የአገራችን የውጭ ምንዛሪ ገበያን መዋቅር ለማዘመን አስፈላጊ እርምጃ መራመዳችንን ያሳያል። ይህ በባንኮች መካከል የሚካሄድ የውጭ ምንዛሪ አውቶማቲክ የንግድ አውታር (Platform) ለተሳታፊ ሁሉ ግልጽ፣ ፈጣንና በመመሪያ የተመራ የገበያ አካባቢ ይፈጥራል። መድረኩ የገበያ ዲሲፕሊንን ለማጠንከር፣ የዋጋ ሂደትን ለማሻሻልና የፋይናንስ ገበያ ሪፎርምን ለመደገፍ ትልቅ ግብዓት ነው።” ብለዋል።

ክቡር ገዥው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባለሙያዎች በተጨማሪ በዚህ ሂደት ላይ የተሳተፉትን የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ (ESX) እና ሌሎች አካላትን በሙሉ አመስግነዋል። ሁሉም ባንኮች በመድረኩ ላይ በንቁ መንገድ እንዲሳተፉ እና ከመመሪያዎች ጋር የተጣጣመ ሥራ እንዲያከናውኑ አሳስባዋል።

#NBE #DBE #Ethiopia
4
Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Thursday, January 29, 2026
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡-
ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::
ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/dbethiopia
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
#ExchangeRate #DBE #Ethiopia
2
የአምራች ኢንዱስትሪ ብሔራዊ ካውንስል አቅጣጫዎች ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጥረት እንደ ወሳኝ ድጋፍ!

ኢትዮጵያ ወደ ኢንዱስትራላይዜሽን ለመሸጋገር ለምታደርገው መዋቅራዊ ለውጥ፣ የአምራች ኢንዱስትሪ ብሔራዊ ካውንስል የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን የካውንስሉ ሰብሳቢ አምባሳደር ግርማ ብሩ የበጀት ዓመቱን የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም በገመገሙበት ወቅት ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እንደ አንድ የመንግስት የፖሊሲ ባንክ ለአምራች ዘርፉ ከሚሰጠው የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ አኳያ የካውንስሉ ጥረት በዘርፉ ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት አቅም የሚሰጥ እንደሆነ ከተመዘገቡት ውጤት መገንዘብ ይቻላል፡፡

የአምራች ኢንዱስትሪ ብሔራዊ ካውንስል የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን በገመገመበት ወቅት፣ አምባሳደር ግርማ ብሩ እንደገለጹት፤ ካውንስሉ በየ15 ቀኑ በመሰብሰብ ዘርፉን የሚፈትኑ ማነቆዎችን በመለየት የመፍትሔ አቅጣጫዎችን እያስቀመጠ ይገኛል። ይህም በተለይ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ትኩረት ሰጥቶ ለሚደግፋቸው የማኑፋክቸሪግ ዘርፍ አቅምን ለማሳደግ፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ የመተካት ስራን (Import Substitution) እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ ግኝትን በማሳደግ ረገድ አበረታች ውጤቶች እንዲመዘገብ አስችሏል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በበኩላቸው አምራች ኢንዱስትሪ ብሔራዊ ካውንስል ተቋቁሞ ወደ ስራ ከገባ ጀምሮ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ያሉበትን የስራ እንቅስቃሴ በመስክ ምልከታ የድጋፍና ክትትል በመደረጉ በዘርፍ መነቃቃትን የፈጠረ፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር የተዘረጋበት እንዲሁም ዘርፉ ትኩረት እንዲያገኝ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡

በግምገማው ወቅት ለካውንስሉ የቀረቡት የጥጥ ምርት፣ የጥሬ ቆዳና ሌጦ ልማት እንዲሁም የግብይት ስርዓት ተግዳሮቶች፤ ባንካችን ቅድሚያ ሰጥቶ ፋይናንስ ከሚያደርጋቸው የግብርና ዘርፍ በቀጥታ የሚገናኙ ናቸው። የእነዚህን ንዑስ ዘርፎች ማነቆ መፈታት፣ ባንኩ ለዘርፉ የሰጠው ብድር ውጤታማ እንዲሆንና የኢንዱስትሪው የሰንሰለት ትስስር እንዲጠናከር ከፍተኛ ፋይዳ ያለው በመሆኑ በትኩረት መያዙ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው አመላካች ነው።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እንደ ፖሊሲ ባንክ፣ የካውንስሉን የፖሊሲ አቅጣጫዎች መነሻ በማድረግ ለአምራች ኢንዱስትሪው የሚሰጠውን የፋይናንስ ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል።

መረጃው ከኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገጽ የተወሰደ ነው፡፡

Ethiopian Ministry of Industry

#DBE
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#madeinethiopia
7
Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Friday, January 30, 2026

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/dbethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

#ExchangeRate #DBE #Ethiopia
6👍1
የዝግ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ! #DBE #auction #agriculture
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ!

#DBE #agriculture #manufacturing #Ethiopia
የድርድር ሽያጭ ማስታወቂያ!

#DBE #agriculture #manufacturing #Ethiopia
7
Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Monday, February 2, 2026

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/dbethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

#ExchangeRate #DBE #Ethiopia
5
Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Tuesday, February 3, 2026

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/dbethiopia 

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

#ExchangeRate #DBE #Ethiopia
6
Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Thursday, February 5, 2026

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/dbethiopia 

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

#ExchangeRate #DBE #Ethiopia
8
ውድ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾቻችን ተከታዮች በዛሬው የእናስተዋውቅዎ ፕሮግራማችን የባህርዳር ዲስትሪክት የስራ እንቅስቃሴ እናስተዋውቃችኋለን መረጃውን ከዲስትሪክቱ ስራ አስኪያጅ አቶ አንማው ገዳሙ አግኝተናል፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ ባህርዳር ከተማ፣ የሚገኘው ዲስትሪክቱ በስሩ አራት ቅርንጫፎች ማለትም ባህርዳር ቅርንጫፍ፣ ሞጣ ቅርንጫፍ፣ ቻግኒ ቅርንጫፍ እና እንጅባራ ቅርንጫፍ ናቸው፡፡

ዲስትሪክቱ በክልሉ ርዕሰ ከተማ ባህርዳር እንደመገኘቱ ኢንቨስትመንቱን ለመደገፍ ከሚመለከታቸው የክልሉ ባለድረሻ አካላት ጋር ተቀራርቦ በመስራት እና ከክልሉ መንግስት ጋር ጠንካራ የሆነ ግንኙነት ያለው በመሆኑ በደንበኞች የሚጠየቁ ተጨማሪ ድጋፎች ፈጣን ምላሽ እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡

ዲስትሪክቱ በአሁኑ ሰዓት የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ የሚያደርግላቸው ከ144 በላይ የሊዝና የፕሮጀክት ፋይናንስ ፕሮጀክቶች ያሉት ሲሆን በዚህም ለአካባቢው ከፍተኛ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ ለመንግስት የገቢ አቅም በመሆን እንዲሁም የአካባቢውን ምርታማነት ለማሳደግ የሚረዱ ቴክኖሎጂዎችን በማቅረብ ሰፊ ስራ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

የዲስትሪክቱ የብድር ክምችት ስብጥርን በሚመለከት በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ ለተሰማሩ ፕሮጀክቶች እና የሊዝ ፋይናንስ ደንበኞች የቀረበ የብድር አገልግሎት ሲሆን በዋናነት በማምረቻ ዘርፍ፣ በግብርና ዘርፍ፣ በኢንዱስትሪ እና በቱሪዝም ዘርፍ ትኩረቱን አድርጎ በመስራት ለደንበኞች ብሎም ለሀገር ኢኮኖሚ ማደግ የራሱን ድርሻ በመወጣት ላይ እንደሚገኝም ተብራርቷል፡፡

ዲስትሪክቱ ከክልሉና ከዞን ከፍተኛ አመራሮች ጋር በቅንጅት በመስራቱ የባለድርሻ አካላት ድጋፍና መልካም ዕይታ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍተኛ ለውጥ አሳይቷል፡፡ በቅንጅት በመስራት ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ሥራዎች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ በማድረግ ውጤታማ መሆን ችሏል፡፡

ደንበኞች ወደ ዲስትሪክቱ ሲመጡ፡-

- ዲስትሪክቱ የብድር አገልግሎቱን የሚሰጠው በባንኩ የብድር ፖሊሲ መሰረት የብድር/የሊዝ አገልግሎት ለሚጠይቁ ዜጎች የምክር አገልግሎት መስጠትና በቅርንጫፎች በኩል መረጃ/ሰነዶችን እንዲያሟሉ ማብቃት፣ መከታተል፣

- የደንበኛህን ዕወቅ፣ የቴክኒካል ድጋፍ እና የብድር/ሊዝ ጥናት በጥራት እንዲሰራ መከታተል፣ ቅርንጫፎችንና ሁሉም የስራ ክፍሎች ስራዎችን በባንኩ ፖሊሲ፣ፕሮሲጀር እና አሰራር መሰረት እንዲያከናውኑ መከታተልና ማገዝ፣ የብድር ጥናቱን ጥራቱን ጠብቆ እንዲሰራ በማድረግ እና በወቅቱ አጠናቆ ለብድር/ሊዝ አጽዳቂ ቡድን መላክ መከታተልና፣ ማጸደቅ፣

- የደንበኞች መዋጮ አጠቃቀም፣ብድር መልቀቅና፣የፕሮጀክቶች የማቋቋም ስራና የማስፋፋት ሂደት ክትትል ማድረግ፣ለደንበኞች ተገቢውን የምክር አገልግሎት መስጠት፣ መከታታልና ማገዝ፣

- በባንኩ የተቋቋሙ ፕሮጀክቶች ዓላማቸውን እንዲያሳኩ ማለትም የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የሚጠበቅባቸውን ምርት ማምረት እና ከውጭ የሚገቡ ገቢ ምርቶች በሀገር ውስጥ በማረት የውጭ ምንዛሬን ማዳን በተጨማሪም ወደ ውጭ የሚላኩ ምቶችን በማምረት ወይም ኤክስፖርት በማድረግ ለሀገር ኢኮኖሚ የውጭ ምንዛሬ አቅምን ማጠናከር ፤የሚፈለግባቸውን የመንግስት ግብር እንዲከፍሉ እንዲሁም ዓላማቸውን እንዲያሳኩ ክትትል ማድረግና ማበረታታት፣

- በተጨማሪም ዲስትሪክቱ ቸክሊስት በማዘጋጀት የስራ ላይ ግልጸኝነትን ማስፈንና የስነ ምግባር መርሆዎችን ተግባራዊ በማድረግ የደንበኛን እርካታ ማረጋገጥ ላይ ሰፊ ትኩረት ሰጦ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

- ከባለድርሻ አካላት እና ከደንበኞች ጋር የፕሮጀክቶችን ዓላማ ለማሳካት በቅርበትና በትብብር የሚሰራ ሲሆን የዲስትሪክቱ ደንበኞች የቴክኒክ፣የማኔጅመንትና የገበያ ችግር በፕሮጀክቶቻቸው ላይ እንዳያጋጥም ክትትልና የምክር ዕገዛም ይሰጣል፡፡

- የፕሮጀክቶች የክትትል ስራን በሚመለከት በየጊዜው ጠንካራ የክትትል ስራ የሚሰራ ሲሆን ለየፕሮጀክቶች የሚለከታቸውን ባለሙያዎችን በመመደብ በቅርንጫፎች በኩል ወቅታዊ የሆነ የፕሮጀክት ክትትል ይደረጋል፡፡

- ለብድሩ አመላለስ ወሳኝ የሆኑ የብድር ዋስትና ሰነዶች ማለትም ኦርጅናል የዋስትና ሰነዶችን፣ የብድር ውሎችንና የምዝገባ ደብዳቤዎችን በጥንቃቄና በአግባቡ እንዲያዙ ይደርጋል፡፡

- ለተቋቋሙ ፕሮጀክቶች ቋሚ ንብረቶች ወይም በኪራይ ለተሰጡ ማሽነሪዎች ተገቢው ኢንሹራንስ እንዲገባ እንዲሁም ኢንሹራንሱ ወቅቱን ጠብቆ እንዲታደሱ ይደረጋል ተንቀሳቃሽ የፕሮጀክት እና የሊዝ ንብረቶች በብሄራዊ ባንክ የተንቀሳቃሽ ንብረቶች መመዝገቢያ ቋት ላይ እንዲመዘገብ እና በየጊዜው ምዝገባው እንዲታደስ ይደረጋል፡፡

- ደንበኞች በገቡት ውል መሰረት ገቢና ወጪያችውን በአግባቡ እንዲይዙ የማማከር ሥራ በመስራት እንዲሁም ለባንኩ አስፈላጊውን መረጃ በወቅቱ መስጠት ይችሉ ዘንድ የሂሳብና መስል መዝገቦችን እንዲይዙ ዲስትሪክቱ/ቅርንጫፉ ክትትል ያደርጋል፣የምክር አገልግሎትም ይሰጣል፡፡

ዲስትሪክቱ በሚያከናውናቸው ተግባራት በተለይም ፋይናንስ በሚያደርጋቸው ፕሮጀክቶች ዙሪያ የጸጥታ ችግሮች መኖራቸው፣ የመብራት አቅርቦትና ዕጥረት ችግሮች አልፎ አልፎ መከሰት፣ ፕሮጀክቶች ፈጥነው ወደ ስራ እንዳይገቡና ከገቡ በኋላ በሙሉ አቅም እንዳይሰሩ ማድረግ፣ ከዶክመንት ማሟላት ጋር የተያያዙ ችግሮች መኖራቸውና መሰል ችግሮች የሚያጋጥሙት ቢሆንም ችግሮችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር በመፍታ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

በዲስትሪክቱ የሚነሱ ቅሬታዎችን በመፍታት በኩልም በደንበኞች በኩል የሚቀርቡ ጥያቄዎች በዲስትሪክቱና በቅርንጫፎች በኩል በተቻለ ፍጥነትና ደንበኛውን በማነጋገር ምላሽ እንዲሰጥ ስለሚደረግ ቅሬታዎች ሳይከሰቱ ደንበኞችን ለማስተናገድ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ ከዚህ የዘለለ ቅሬታ ሲኖራቸው የባንኩን ቅሬታ አቀራረብ ሂደት ተከትሎ ቅሬታቸውን በዲስትሪክቱ ወይም በቅርንጫፎች አካል ወይም በባንኩ ቅሬታ ማስተናገጃ ነፃ የስልክ መስመር 9878 በመደወል ቅሬታቸውን ያቀርባሉ ቅሬታቸውም በየደረጃው መፍትሄ እንዲያገኝ ተደርጎ መልስ ይሰጣቸዋል፡፡

#DBE #Ethiopia
17👏1
Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Monday, February 9, 2026

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/dbethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

#ExchangeRate #DBE #Ethiopia
5👍1
Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Tuesday, February 10, 2026

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/dbethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

#ExchangeRate #DBE #Ethiopia
3👍3
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2018 በጀት ዓመት ስድስት ወራት በአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር የሊዝ ማሽነሪ ግዥ ፈጽሟል፡፡ የባንኩ ዋነኛ ትኩረትም የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን በማስፋፋት የስራ እድል መፍጠር፣ የኑሮ ውድነትን ማቃለልና ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ነው፡፡

በዚህም ባንኩ ባለፉት ስድስት ወራት 44 አዳዲስ ኢንተርፕራይዞችን ወደ ሥራ ማስገባት ችሏል። ለ39 ኢንተርፕራይዞችም የማሽን ግዥ በመፈጸም ተከላ አከናውኗል፡፡ ባንኩ ባሳለፍነው በጀት ዓመት ለ166 ኢንተርፕራይዞች የማሽን ግዥ መፈጸም የቻለ መሆኑ ይታወሳል፡፡

#DBE #Ethiopia #leasefinancing
6
Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Wednesday, February 11, 2026

🤝21