Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.8K subscribers
2.02K photos
76 videos
4 files
538 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ተሳታፊ የሆነበት የቢዝነስ እና ፋይናንስ ፎረም ተካሄደ፡፡

በማደግ ላይ ያሉ የኢትዮጵያ ኩባንያዎች የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማሻሻልና ለማገዝ ያለመ የፋይናንስ ፎረም ህዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም በጋላኒ ሮስተሪና ካፌ ተካሄደ፡፡

በ GIZ Ethiopia እና KFW በተዘጋጀው በዚህ ፎረም ባለድርሻ አካል የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በፎረሙ ተሳታፊ የነበረ ሲሆን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከእነዚህ አለምአቀፍ ተቋማት ጋር በጥምረት እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን ለፎረሙ ተሳታፊዎችና ለኤግዚቢሽኑ ጎብኚዎች አብራርቷል፡፡

#kfw #DBE
1
ኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዕለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመን

Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Wednesday, December 10, 2025

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/dbethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

#ExchangeRate #የኢትዮጵያልማትባንክ
#developmentbankofethiopia
2
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ዘርፉን ዲጂታል ለማድረግ ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር የባንክ ሂሳብን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር የማጣመር ስራ በይፋ ማስጀመሩን አስታውቋል።

#NBE #DBE
6
ኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዕለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመን

Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Thursday, December 11, 2025

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/dbethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

#ExchangeRate #የኢትዮጵያልማትባንክ
#developmentbankofethiopia
4
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየውን ሁለተኛውን ቀጣናዊ የካፒታል ገበያ ጉባኤ ስኬታማ በሆነ መንገድ በማጠናቀቅ አገራዊ የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ያለበትን የለውጥ ምዕራፍ በተጨባጭ ማሳየት ችሏል፡፡

የ2025 ዓለም አቀፍ የካፒታል ማርኬት ጉባኤ በቀጣይ ዓመታት የካፒታል ገበያ ድርሻን የሚያመላክት እና በተለይ ካፒታል ለእድገት ያለውን ፋይዳ የሚያሳይ ነው፡፡

የፋይናንስ ተቋማት ካፒታላቸውን ወደ ታዳጊ አገራት መሰረተ ልማት፣ የፈጠራ ስራዎች እና ሌሎች የልማት ስራዎች ላይ በማዞር ዘላቂ የሆነ እድገት ማምጣት እንዲችሉ አፅንዖት ለመስጠት ጉባኤው ወሳኝ ድርሻ አለው፡፡

ለሶስት ቀናት በዘለቀው ጉባኤ ከተደረጉ የፓናል ውይይቶች መካከል "ካፒታል ለዕድገት" የሚለው አንዱ ሲሆን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር እመቤት መለሰ በፓናሊስትነት ተሳትፈውበታል፡፡

ዶ/ር እመቤት መለስ በውይይቱ የምንከተለው የካፒታል አጠቃቀም ስልት በዓለም ላይ ያለውን የልማት ክፍተት መሙላት የሚችል አለመሆኑን በመግለጽ ይልቁንም እንደ "አረንጓዴ ቦንዶች" (Green Bonds) ያሉ የዘመኑ የፋይናንስ መንገዶችን መጠቀም እንደሚገባ አንስተዋል፡፡ አያይዘውም በአካባቢ ጥበቃ ላይ ያተኮሩ የረዥም ጊዜ ኢንቨስትመንቶችን ወደ አፍሪካና ሌሎች ታዳጊ ከባቢዎች መሳብ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በፓናል ውይይቱ በመንግስት ቁጥጥር ስር የሌለውን የግል ካፒታል ወደ መሰረት ልማት ዘርፎች (መንገዶች፣ ኃይል እና ዲጂታል ቴክኖሎጂ) ማምጣት ወሳኝ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ኢትዮጵያ በቅርብ ዓመታት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት ካስመዘገቡ የአፍሪካ አገራት አንዷ ብትሆንም፣ የፋይናንስ ሥርዓቷ በዋናነት ባንክ-ተኮር ሆኖ መዝለቁ በውይይቱ የተነሳ ሲሆን በአገራችን እየተተገበረ ያለው አገራዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ይህንን ታሪካዊ ክፍተት ለመድፈን እና ዘመናዊና የተደራጀ ካፒታል ገበያ ለመፍጠር ቁልፍ ሚና አለው፡፡

የካፒታል ገበያ (የሰነድ መዋዕለ ንዋይ ገበያ) መመስረት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ቁልፍ ሚናዎች እንደሚጫወት እሙን ነው፡፡
የግሉና የመንግሥት ዘርፍ በትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚያስችለውን የረጅም ጊዜ ፋይናንስ (አክሲዮንና ቦንድ) ከባንኮች ውጭ ለማግኘት ዋና መድረክ ሆኖ ያገለግላል፡፡ በተጨማሪም የግል ሴክተርን በማነቃቃት የአክሲዮን እና የቦንድ ሽያጭ የግል ድርጅቶች ከባንክ ብድር በተጨማሪ ካፒታል እንዲያገኙ ያስችላል።

የፋይናንስ ዘርፍ መረጋጋት አጠቃላይ የፋይናንስ ሥርዓቱ ለድንገተኛ አደጋዎች ተጋላጭነቱንም ይቀንሳል። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ለኢትዮጵያ የፋይናንስ ሥርዓት መሻሻል ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡

ለተከታታይ ሶስት ቀናት በአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ሲካሄድ የቆየው የሁለተኛው ቀጣናዊ የካፒታል ገበያ ጉባኤ በኢትዮጵያ ያለውን የካፒታል ገበያ የፋይናንስ ዕድል ለአፍሪካውያን ማስተዋወቅ ያስቻለ መሆኑን የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሀና ተህልቁ የጉባኤውን መጠናቀቅ አስመልከተው ባስተላለፉት መልዕክት ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አካታች ፋይናንስ ለጋራ ብልጽግና በሚል መርህ የተካሄደው ይህ ጉባኤ የኢትዮጵያ ብልጽግናን እውን ማድረግ የሚያስችሉ ሀሳቦች የተንጸባረቁበት መሆኑንም አንስተዋል፡፡ ሴቶች አካታች የሆነ የካፒታል ገበያ ለመቅረጽ በግንባር ቀደምትነት እየተሳተፉ መሆኑ የተነሳ ሲሆን “ሴቶች በግንባር ቀደምትነት፡ አካታች ካፒታል ገበያዎችን እየቀረጹ ነው” በሚል ርዕስ በተካሄደው የፓናል ውይይት፣ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ እና የካፒታል ገበያ ላይ ሴት መሪዎች ያላቸውን ወሳኝ ሚና የሚያጎላ ጠቃሚ ውይይት የተደረገበት ነው።

በውይይቱ የሥርዓተ-ፆታ ልዩነት በፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ በስፋት ቢታይም የካፒታል ገበያው መጀመር ግን ሴቶችን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ ወርቃማ ዕድል ይዞ መምጣቱ ተነስቷል፡፡ በውይይቱ በፓናሊስትነት የተሳተፉት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር እመቤት መለሰ ሴቶች በካፒታል ገበያ ውስጥ ያላቸውን ሚና ለማሳደግ መወሰድ ስላለባቸው እርምጃዎች እና ስለሚገጥሙ ችግሮች ሃሳባቸውን ሰንዝረዋል፡፡

በፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ፣ በተለይም ወደ ከፍተኛ የአመራር ደረጃዎች ሲታይ የሴቶች ተሳትፎ በቁጥር አነስተኛ መሆኑ ዋናው ችግር መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን ይህም በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ውስጥ የሥርዓተ-ፆታ እኩልነትን ይጎዳል ተብሏል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ለሥርዓተ-ፆታ እኩልነት ያለው ቁርጠኝነት በተለያየ መንገድ እንደሚጠቀስ በውይይቱ የተጠቀሰ ሲሆን የብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች በባንክ ቦርዶች ውስጥ ቢያንስ ሁለት ሴት አባላት እንዲኖሩ ማዘዙ አንዱ መገለጫ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በኩልም ለሕዝብ ሰነድ ለሚያወጡ ኩባንያዎች የቦርድ አባላት ዝቅተኛውን የሴት ተሳትፎ መጠን (ለምሳሌ 30%) እንዲያሟሉ የሚጠይቁ መመሪያዎች እየተዘጋጁ ነው። ይህ ተነሳሽነት በድርጅታዊ አመራር ውስጥ የሴቶችን ተሳትፎ በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የሚመራው በሴት መሪ መሆኑ በራሱ ለሥርዓተ-ፆታ እኩልነት መንግስት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑም በውይይት ተንጸባርቋል፡፡

የሴቶችን ልዩ የኢንቨስትመንት ፍላጎት የሚያሟሉ የፋይናንስ ምርቶችን እና ፖሊሲዎችን መቅረጽ እንደሚገባም በፓናል ውይይቱ የተነሳ ሲሆን "የሥርዓተ-ፆታ ቦንዶችን" (Gender Bonds) የመሰሉ ምርቶችን ማጥናትና መተግበር ሴት ባለሀብቶችን የመሳብ እና በሴቶች በሚመሩ ኢንቨስትመንቶች ላይ ትኩረት የማድረግ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል።
ሴቶች የሙያ መሰናክሎችን እንዲያልፉና ወደፊት እንዲራመዱ የምክር፣ የእርስ በእርስ ትስስር እና የሙያ ዕድገት ስልጠናዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ወሳኝ መሆኑን በፓናል ውይይቱ ተነስቷል፡፡

ጉባኤው የፋይናንስ ዘርፍ መሪዎችን፣ የፖሊሲ አውጪዎችን እና የገበያ ተሳታፊዎችን በማሰባሰብ በሀገሪቱ የፋይናንስ ሥርዓት ላይ ጠንካራ እና አርቆ አሳቢ ውይይቶች የተደረጉበት መድረክ ነበር። የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር እዮብ ተካልኝን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት መድረክ፣ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ለካፒታል ገበያው ዕድገት መሠረት እንደጣለ ተመልክቷል።

#CMS2025
#CAPITALMARKETS
#ADDISABABA
#ETHIOPIA
#ECMA
8👍1
ኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዕለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመን

Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Friday, December 12, 2025

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/dbethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

#ExchangeRate #የኢትዮጵያልማትባንክ
#developmentbankofethiopia
5
መላው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሰራተኞች የባንኩ ፕሬዚዳንት በመሆን ለተሾሙት ዶ/ር ኢሳያስ ካሳ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆን ምኞታችንን እንገልጻለን፡፡ #DBE #Ethiopia #ECMA
26👏9
መላው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሰራተኞች የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ በመሆን ለተሾሙት ዶ/ር ብሩክ ታዬ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆን ምኞታችንን እንገልጻለን፡፡
ባንኩን ለማገልገል በቦርድ አባልነት የተሰየሙትን ክብርት ዶ/ር ሶፍያ ካሳ፣ ክቡር ስዩም መኮንን፣ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ፣ አቶ ሃቢብ መሀመድ፣ ረዳት ፕሮፌሰር ማርታ በለጠ እና ዶ/ር ጥላሁን እስማኤል መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡

#DBE #Ethiopia
30👏8
ኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዕለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመን

Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Monday, December 15, 2025

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/dbethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

#ExchangeRate #የኢትዮጵያልማትባንክ
#developmentbankofethiopia
8
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶክተር ኢሳይያስ ካሣ ከቀድሞዋ የባንኩ ፕሬዝዳንት ዶክተር እመቤት መለሰ ጋር የሥራ ርክክብ አደረጉ፡፡
#Ethiopia #DBE
👏1610
ኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዕለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመን

Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Tuesday, December 16, 2025

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/dbethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

#ExchangeRate #የኢትዮጵያልማትባንክ
#developmentbankofethiopia
7