Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.8K subscribers
2.01K photos
76 videos
4 files
537 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለብድር ገንዘብ ማካካሻነት በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከባቸውንና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የመያዣ ንብረቶች በዝግ ጨረታ እና በድርድር አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

1ኛ.ባንኩ ለኤም ዋይ ሹዝ ኤንድ ሌዜር ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከበውንና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደብረ ብርሃን ከተማ 09 ቀበሌ የሚገኝና በ6.83 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ የጫማ እና የቆዳ ማምረቻ ፋብሪካ. የህንፃ ግንባታዎች፣ ማሽነሪዎች እና የኤልክትሪክ ሥራዎች በጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 397,968,817.12፣ ለመሸጥ ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ዝግ ጨረታ ይካሄዳል፡፡

2ኛ.ባንኩ ለጋቴፕሮ ኃ/የተ/የግል ማህበር በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከበውንና በአቶ ግርማ አፈወርቅ መድምም ስም የተመዘገበ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንፋስ ስ/ላ/ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ውስጥ 1,678 ካሬ ሜትር በሊዝ የተገኘ መሬት ላይ ጋቴፕሮ ቆርቆሮ ፋብሪካ፤ የህንፃ ግንባታዎች፣የኤልክትሪክ ስራዎች፣ ማሽነሪዎች፣ ቁሳቁሶች፣የቢሮ ዕቃዎችና መገልገያዎች፣ የጥሬ ዕቃና የምርት ክምችት በጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 122,600,997.28 ለመሸጥ ህዳር 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ዝግ ጨረታ ይካሄዳል፡፡

በዚሁ መሰረት ንብረቱን ለመግዛት የምትፈልጉ ተጫራቾች በዕለቱ በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልታችሁ ለመጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታው ዝርዝር መረጃ ረቡዕ ጥቅምት 19 ቀን 2018 ዓ/ም የወጣውን አዲስ ዘመን ጋዜጣ አማርኛ ዕትም እንዲሁም እንደ እኤአ ረቡዕ ጥቅምት 29 ቀን 2025 የወጣውን ዘ ኢትዮጵያን ሔራልድ ጋዜጣ ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-524-53-73) ወይም በባንኩ ዌብ ሳይት www.dbe.com.et. ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
❤1
ኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዕለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመን

Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Thursday, November 6, 2025

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://x.com/dbeethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/com.../development-bank-of-ethiopia
ዩቱብ:- https://www.youtube.com/@developmentbankofethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

#ExchangeRate #የኢትዮጵያልማትባንክ
#developmentbankofethiopia
❤3👍1
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ የመስክ ምልከታ አካሄደ፡፡

የምልከታው ዋና ዓላማ 6ኛው ዙር 3ኛ ዓመት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2015/16 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ ልማት ባንክ የማምረቻ (Manufacturing) ዘርፍ የብድር አሰጣጥና አመላለስ ስርዓት ቀልጣፋና ውጤታማ መሆኑን በተመለከተ የተከናወነ ክዋኔ ኦዲት ሪፖርት መነሻ በማድረግ ውይይት ማድረግና ግብረመልሶችን መስጠት መሆኑን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና የመስክ ምልከታው ቡድን መሪ የተከበሩ ዶ/ር የሺመቤት ደምሴ ገልፀዋል፡፡ 

የውይይት መድረኩ የተጀመረው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ባቀረበው የኦዲት ግኝት ክዋኔ ሪፖርት መሰረት ሲሆን በባንኩ የተወሰዱ የማሻሻያ ርምጃዎች ላይ በቀረበው የኦዲት ሪፖርት ማብራሪያዎች በዝርዝር ቀርበዋል፡፡

በሪፖርቱም  የፌዴራል ዋና ኦዲተር ዳይሬክተር  ወ/ሎ ፌሩዛ አብደላ  ግብረ-መልስና ማብራሪያ ለሚያስፈልጋው ጉዳዮች  ጥያቄዎች ያነሱ ሲሆን ለቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች  በባንኩ የስራ ኃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር የሺመቤት ደምሴ በቀረበው የኦዲት ሪፖርት እንዲሁም በባንኩ በኩል በተሰጡ ግብረ-መልሶች መሰረት ሃሳብና አስተያየታቸው የሰጡ ሲሆን በባንኩ ያዩት አሰራር እንዲሁም በፖሊሲ ማሻሻያ ላይ የተደረጉ ለውጦች የሚበረታቱ መሆኑን ጠቅሰው በፌዴራል ኦዲት እና በቋሚ ኮሚቴው ማሻሻያ እንዲደረግባቸው የተነሱት ነጥቦች ላይ ባንኩ በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝደንት ዶ/ር እመቤት መለሰ በበኩላቸው የቋሚ ኮሚቴውና የፌዴራል ዋና ኦዲተር ለባንኩ ስራ ትኩረት ሰጥተው ላደረጉት ሰፊ ውይይት አመስግነው የተደረገው ውይይት ጥሩ ልምድ የተገኘበትና ለቀጣይ ስራ የሚያግዙ የመነሻ ሃሳቦች የቀረቡበት መድረክ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ዶ/ር እመቤት አክለውም በቋሚ ቆሚቴው የተነሱ ነጥቦችና የተሰጡ አስተያየቶችን ባንኩ የሚቀበላቸውና ማስተካከያ የሚያደርግባቸው
❤6